“በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው “Who is in Charge?” የሚለው ጥያቄ ያሳሰባቸው ቧልተኞች የፈጠሩትን ቀልድ ላልሰማችሁ ላሰማችሁ፡፡ (ኮፒራይቱ የሰፊው ህዝብ እንደሆነ ይታወቅልኝ!)
አንዱ ኤፍኤም ሬዲዮ ይደውላል – ዘፈን ለመምረጥ።
ደዋይ – ዘፈን ለመምረጥ ነበረ፤ የእገሌን …
ኤፍ ኤም- ማን እንበል? ከየት ነው?
ደዋይ- የገዢው መደብ አባል ነኝ—- ከደቡብ!
ኤፍ ኤም- (ደንገጥ ብሎ) ከደቡብ … እሺ ዘፈኑ ይቀጥላል …
(የኤፍኤሙ ጋዜጠኛ ከድብልቅልቅ ስሜት ሳይወጣ ሌላ ዘፈን መራጭ ይደውላል)
ኤፍ ኤም- ሄሎ … ማን እንበል? ከየት ነው?
ደዋይ – ዘፈን ለመምረጥ ነበር
ኤፍኤም- ራስህን አስተዋውቀን?
ደዋይ – የገዢው መደብ አባል ነኝ – ከትግራይ!
ኤፍኤም – እንዴትነው ነገሩ? አሁን ከደቡብ ደውሎ የገዢው መደብ አባል ነኝ ብሎኛል እኮ?
ደዋይ- ዝም ብሎ ነው ባክህ … እነሱ ቀፎ፤ እኛ ሲም ካርድ ነን! …”
(ምንጭ: አዲስ አድማስ “ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም እየመሩን መሆናቸውን ለምን ተጠራጠርን?” ከሚለው መጣጥፍ የተወሰደ)
በለው! says
“ባዶ ቀፎ ከፊት ሲም ካርድ ከኋላ
ከፊት ያፋሽካል ከኋላ እየበላ
ተጣርቶ አይመልስ መልሶም አይጠራ
“Who is in Charge?”አለ ሰሚ አጥቶ ቢጣራ።
በለው!