• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ምን ነካው?

September 4, 2017 08:02 pm by Editor Leave a Comment

ከአጭር ግዜ እረፍት በኋላ፣ EBC ላይ ብቅ ያለው “ቤቶች” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በክፍል185 እጅግ አስደምሞናል። ተመልካቹ ህዝብ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥላሁን ጉግሳ ላይ እየወረደበት ያለው “አሽቃባጭ፣ የወያኔ አቃጣሪ…” ወዘተ ውግዘቶችና ስድቦችን ባልጋራም፣ ይህ አንጋፋ አርቲስት ጥበብን የፖለቲካ መደለያ ስለማድረጉ ግን ምስክር አያሻም። በአንድ ወቅት እጅግ ተወዳጅ የነበረ ይህ ድራማ በመጠነኛ የህወሃት ልማታዊ ቅኝት እየተቃኘ መጥቶ አሁን ላይ ወገን የለየ ይመስላል። ዶፍ ሲጥል ገሚሱ ይበሰብሳል፤ ሌላው ተጠልሎ ይመለከታል፣ ጥቂቱ  ደግሞ ይቀልዳል። ቀልደው ሞተዋል!

ይህንን ድራማ ስመለከት፣ ገሃዱን አለም ከምናቡ አለም በቅጡ ሳይለዩ፣  ሃያልነትዋን ያልተረዱ አርቲስቶች ጥበብን ለተልካሻ ጉዳይ ሲመነዝሩዋት አስተዋልኩ። ወዶ ይሁን ተገድዶ ብቻ፣ በህዝብ ላይ የተከፈተ ጦርነት ላይ ተሰልፎ ፣ በተለይ ለጥበብ ጥብቅና ቆሞ ሲገዘትላት ከኖረ ስው ማየቱ ደግሞ የበለጠ ያምማል።

“…ምን ፍትህ አለ እያልን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን። ይህ ትክክል አይደለም።… “ይለናል አንጋፋው ጥላሁን ጉግሳ። ይህንን የስክሪፕት ረቂቅ ልቦናው ይንገረው ወይንም ደግሞ ህወሃት እንጃ። ነጋዴዎች ቅሬታቸውን በአግባቡ ለሚመለከተው ክፍል እንዲያቀርቡ የሚመክረው የጥበብ ሰው የመንግስት አካላትም ሲያጠፉ እንደሚከሰሱ በዚሁ ትወና አስረግጦልናል። ግና እነዚህ ባለስልጣናት መች እና የት እንደተከሰሱ ጨምሮ ቢነግረን ኖሮ ከውግዘቱ ይድን ነበር። “(የግብሩ) ትመና ፍትሃዊ ነው።” በሚለው ላይ ጸንቶ ሲያበቃ፣  “አንዳንድ” ያላቸው ነጋዴዎች በማጭበርበር ላይ እንደተሰማሩም ይጠቁማል።

ከሕዝብ የምንሰማው ግን ሌላ ነው። ነጋዴዎች በመገኛኛ ብዙሃን እየቀረቡ፣ የተጣለብን ግብር አግባብ አይደለም ቅሬታችንን የሚሰማ አካል አጣን ነው የሚሉን። ጥበብ የገሃዱ አለም ነጸብራቅ እንጂ ተቃራኒ የሚለውን አስተምሮት ጥላሁን በዚህ ተውኔቱ አሳየን።

ለመሆኑ ለፍቶ አዳሪውን ነጋዴውን “አጭበርባሪ” እያሉ በአደባባይ መሳደብ ጥበብ ነውን?

“መረጃ  ደብቀውናል። ያለመረጃ ነው ውሳኔ የምሰጠው” እያሉ የሚያላዝኑት ሃይለማርያም ደሳለኝ እንኳን ደፍረው “በሃገሪቱ ፍትህ አለ” ብለው አይናገሩም።

“ወጣ ወጣና እንደሸምበቆ…” አለ ያገሬ ሰው። ቀጣዩ ስንኝ አያድርስ ነው። ከአጀማመሩ አምሮ ዝናው ሲገንን፣ ነገር አለሙን ወዲያ ሲል የሚወርድ ዱብዳ ነገር። አያድርስ ነው። ሕዝብ “ስራህን ወደድነው።” ሲለው ድራማው የእስትንፋስ ያህል ያስፈልገው እየመሰለው የሚሳሳት ጥቂት አይደለም።

ወትሮውን በየመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ “ሃብታችን ሕዝብ ነው፣ …!” ሲሉ የሚደመጡ አርቲስቶቻችን ከግዚያዊ የግል ችግራቸው በዚህ መንገድ ያመልጡና፣  አንዳች ማዕበል ሲነሳ ደግሞ ከሕዝብ ሲላተሙ ማየት ሳያስተዛዝብ አልቀረም።

ወገን  በኢ-ፍትሃዊ የግብር ተመን ተወጥሮ እያለቀሰ ባለበት በዚህች ቀውጢ ወቅት፣ እንደ ሙሴ “ህዝቤን ልቀቅ!” ማለት እንኳን ባይገድደው ብሶቱን በዚያች ትንሽ ቀዳዳ ማሰማት ያባት ነበር። ነገሩ ተገበጠና ጭራሽ በዱብዳ የግብር አዋጅ እየተሰቃየ ያለውን ነጋዴ አብሮ መውጋት ጀመረ።

የቤቶች ድራማ ከጥበባዊ ይዘቱ ወደ ልማታዊ ይዘቱ ማጋደል የጀመረው መሃል መንገድ ላይ እንደነበር አስታውሳለሁ። ባልጠፋ የሙያ ሰው፣ ባልጠፋ የጥበብ አፍቃሪ፣ ጥላሁን ጉግሳ  እነ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጠርቶ በአደባባይ ስራውን ሲያስገመግመው ነው ቤቶች የህወሃትን ጠረን ያያዘው። ከዚያን ግዜ ጀምሮ ኩምክናውና ጥበቡ ለዛውን አጥቶ፣ ልማት ተኮር ሆነ።

የጥበብ ሰው ለህብረተሰቡ ፍትህ የሚቆም።  ከፊትም ተስልፎ መስዋዕት የሚሆን እንጂ ሕዝብ አቤት ብሎ የሚተነፍስበት ቀዳዳ ባጣበት ግዜ፣ ይልቁንም በቁስሉ ላይ እንጨት የሚሰድድ አይደለም። የቤቶች ድራማም ቢሆን ከነጋዴው ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ ነጋዴውን መልሶ እንደ አጭበርባሪ አድርጎ ማቅረብ የጤና ነው?

በንግዱ ማህበረሰብ ላይ በመረጃ ሳይሆን በግምት የተቆለለው የገቢ ግብር ተገቢ አይደለም። ይህ  ደግሞ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል መወገዝ ያለበት ጉዳይ ነው።

“ህዝቡ አጎብዳጆች ይለናል።” ብላ ነበር አርቲስት አስቴር በዳኔ በአንድ ወቅት። ለጥበብ ሰው ከዚህ በላይ ሞት የለም። ከምንወድዳቸው የጥበብ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ስናይ ደግሞ ያምማል!

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule