• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በነገራችን ላይ “ውይይቱ” የት ደረሰ?

January 29, 2017 12:12 am by Editor Leave a Comment

የሙስናውን የመረጃ እጦት ኩምክና ሰምተን ስቀን ሳንጨርስ ሰሞኑን ደግሞ የውይይት ፉገራ አመጡ። ልክ እንደቀበሌ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን በአዳራሽ ውስጥ አጉረው ሲያበቁ እነሱ ከመድረክ ሆነው ይቀልዱባቸዋል። የNBC ውን፤ የዴቭድ ሌተርማን ‘ሌት ናይት ሾው” (late night show) የሚመስል ነገር በቴሌቭዥን ለቀውብን ነበር። ሁለቱ ባለስልጣኖች፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ መድረክ ላይ ጉብ በለዋል። በአነስተኛና በጥቃቅን የተደራጁ 21 የፓርቲ መሪዎች ደግሞ እንደ ቲያትር ተመልካች አዳራሹ ውስጥ ተሰይመዋል። እነዚያ ከላይ፣ እነዚህ ከታች ተቀምጠዋል።  እነዚያ ይናገራሉ፣ እነዚህ ደግሞ ይሰማሉ።… ሌላ ምን አማራጭ ሊኖራቸው?

ውይይት ብለውታል። ሌላው አይደለም። አቀማመጣቸው ብቻ የውይይቱን አቅም እና ያይል ያሳብቃል።  በሙስናው የመረጃ እጦትት ኩምክና ስቀን ሳናበቃ ነው ይህንን ፉገራ የለቀቁት። ሲት ኮም ክፍል ሁለት።

አይጋ ፎረም ላይ ስለሁኔታው የጸፉት “ባለሙያ” የሃገራችን ችግሮች በውይይት ብቻ እንደሚፈቱ አስምረውበታል። “ይህንን ማን አጣው?” ብሎ ሚጠይቃቸው አልተገኘም እንጂ። በድርድር ሰላምን ለማምጣት መልካም ፈቃዱ ካለ፤ መጀመሪያ በእስር ላይ ያሉትን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በመፍታት ነበር የሚጀመረው። ከቶውንም የህሊና እስረኞች ለመደራደርያ መቅረብ አልነበረባቸውም። አሁን ግን የምናየው የተገላቢጦሹን ነው። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ እንዳስቀመጡት “መጀመርያ የፖለቲካ እስረኞችን ፍቱ!” የምትለው ቅድመ ሁኔታ ለገዥው ፓርቲ የሰጥቶ-መቀበል መደራደርያ ሆና ቀርባለች። ይህ የተቃዋሚዎች የመደራደር አቅም ምን ያህል እንደሆነ የሚለካው አንዱ መስፈርያ ነው።

ድርድር የምትለዋ ርዕስ እነሱ በችግር በተወጠሩ ቁጥር የሚመዟት አንደኛዋ ካርድ ለመሆንዋ ያለፉ ተመክሮዎች ምስክሮች ናቸው። አለም አቀፍ ጫና ሲበዛና የህዝብ ልብ ሲሸፍት ይመዙዋትና አዘናግተው ሲጨርሱ መልሰው እኪሳቸው ይመልሷታል።  እንግሊዞቹ “talks the talk but doesn’t walk the walk.” እንደሚሉት ነው። ወሬውን ያወሩታል –  ስራውን አይሰሩትም። በዚህ መንገድ ከሰባት ግዜ በላይ በህዝብ እና በተቃዋሚዎች ላይ ቀልደዋል።

ድርድር ወይንም ውይይት አንድ ነገር ነው። በድርድሩ ቢቻል የበላይነትን አልያም እኩል ስፍራ መያዝ ሌላ ነገር። በክብ ጠረጴዛ የመቀመጥ እድል ሳይኖራቸው መወያየት ከመሞከር ይልቅ አለማድረጉ ይመረጣል። ጉልበተኛው የጫወታውን ህግ በሚወስንበት ጫወታ መሳተፍ ከማጅራት መች እጅ ጥምዘዛ የተለየ አይሆንም።

አንዳንዶች ተገቢ የሆነ ጥያቄ ያነሳሉ። “የተቃዋሚዎች ጡንቻ ከገዥው ፓርቲ የጠነከረ ባለመሆኑ የሚሰጣቸውን መቀበል ግድ ይላቸዋል።” ይላሉ። ይህ እይታ ትክክል ሊሆን ይችላል። በዚህ መንገድ መሄዱ ግን ፍጹም ስህተትና ሕዝብን መካድ ነው የሚሆነው።

የገዥው ፓርቲ ጸብ ከህዝብ ጋር ነው። ሕዝብ በጅምላ ይገደላል፣ ሕዝብ በፈረቃ ይታሰራል፣ የሕዝብ ሃብት ይዘረፋል። በዚህ ሁኔታ – ከሕዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ለረጅም መዝለቅ ደግሞ አይቻልም። የውይይቱ አጀንዳ የህዝብ ጥይቄ ላይ የሚነሳ ሲሆን ለተቃዋሚዎች የሞራል ብቻ ሳይሆን የሃይልም የበላይነት ይሰጣቸዋል። እዚህ ላይ ተቃዋሚ ስል የተገዙትን ወይንም የተቃውሞ አራራ ያላቸውን እንዳልሆነ ግልጽ ይሁን። እርግጥ ነው። ደፋር እና ትክክለኛ የምንላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በእስር ቤት አልያም በስደት ላይ ናቸው።

የቴሌቭዥን ጋዜጠኛው ታዲያ አፉን ሞልቶ “የፓርቲዎች ውይይት” እየተካሄደ እንደሆነ በዜና አወጀ። ይህን ውይይት ልማቱ ካመጣቸው አዳዲስ ፍላጎቶች ጋር በማያያዝ ለመተንተን ግን አልደፈረም።

በአቶ ይልቃል ጌትነት የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ኢሕአዴግ በጠራው የፓርቲዎች “ውይይት” እንዲቀመጥ የተፈቀደለት እስከ ሻይ እረፍት ድረስ ብቻ ነበር። የሰማያዊ ፓርቲ ባህርይ እስከ ሻይ እረፍት ድረስ ተገምግሞ ሲያበቃ፣ ፓርቲው ጽንፈኛ እና ጸረ-ሰላም በመሆኑ ከምድቡ ተሰርዟል። ሌሎች “ነግ በኔ” ብለው መባነን የነበረባቸው በዚህ ግዜ ነበር። እነ አስመላሽ ወልደሥላሴ የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በውይይት ብቻ ነው ብለው ሳይጨርሱ ተሳታፊውን ማባረር ሲጀምሩ ጉዳዩ እዚያው ያቆማል።

በፖለቲካ ኩምክና የሚታወቀው የእንግሊዙ ሳሻ ቦራት የተወነበት “The Dictator” የሚለው ፊልም ታወሰኝ። የዋዲያ ሪፐብሊክ መሪ የሆነው አድሚራል ጀነራል አላዲን የሩጫ ውድድር አዘጋጅቶ ሲያበቃ ተሳታፊዎችንም ራሱ መረጠ። ዳኛው ራሱ ጀነራል አላዲን ነው። ጀነራል አላዲን ተወዳዳሪም ነው።  ሩጫውን የማስጀመርያ ሽጉጡን አንስቶ ወደሰማይ ተኮሰ። ሩጫ ተጀመረ። ከዚያም ተወዳዳሪዎቹን  በሙሉ እግር-እግራቸውን እያለ ጥሎ በውድድሩ አንደኝነቱን አበሰረ።

በ”ስልጣን ወይም ሞት!” መፈክር የሚሄደው ይህ ድርጅት ያዘጋጀው መድረክ ከጅምሩ የሚሸት ነገር አለው። በቅንነት እና በሙሉ ልብ የሚደረጉ ውይይቶች ከአነሳሳቸው ይታወቃል። “ከአያያዝ ይቀደዳል፣ ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ፣ ይህ በግማሽ ልብ የተጀመረ መድረክ ለሃገር ሰላም ታስቦ እንዳልነበር ግልጽ ነው። ለውይይቱ የተጠሩት “ሰላማዊ መንገድ የመረጡ” ተቃዋሚዎች ብቻ ናቸው ተብሏል። ጉድለቱ የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው።

አንዱን ትክክለኛ ልጅ፣ ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ ብሎ የሚመድበው ማን ነው? አንዱን ጠርቶ እንነጋገር እያለ፣ ሌላውን ደግሞ አንተ “ጽንፈኛ” መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ ከሚል አካል ሰላም ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኝመት ይሆናል። ህወሃት ለውይይት ሲጠራ የራሱ መለኪያ አውጥቶ ለመሆኑ ከአጠራሩ ሂደት እና ከተጋበዙት እድምተኞች ለመረዳት አያዳግትም። በውይይቱ የበላይነትን ይዘው ለመደራደር መስፈርቱን የሚያሟሉትን ከጠራ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደፈረደ ይቆጠራል።

እሳት ከሌለ ጭስ አይታይምና ይህ ሾው ያለ ነገር፣ ያለ ግዜውም አልመጣም። የሰሜኑ ችግር እጅግ እየባሰ መጥቷል። ከወደ ምዕራብም ችግር አለ። የአልባሽር ፍቅር ከደቡብ ሱዳን እያላተማቸው ነው። ደቡብ ሱዳን አሁን ያመረረች ይመስላል። ይህ ደግሞ ለአማጽያን ከኤርትራ የተሻለ አማራጭ ሊሆንላቸው ነው።  ሰሞኑን ግጭቱ ተካርሮ ዲፕሎማት እስከማባረር ተደረሷል። የካይሮ እጅ ኖርበትም አልኖረበት፣ የጁባው ዲፕሎማሲ የስርዓቱን ግባዓተ-ቀብር ማፋጠኑ በግልጽ የሚታይ ነገር ነው።

ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ የከተተበት ምክንያት ገዥው ፓርቲ የሚታመን ስርዓት ባለመሆኑ ብቻ ነው። ለበርካታ ግዜ ህዝብን እና ተቃዋሚዎችን በሃሰት አዘናግቷል። ከመተማመን በፊት ውይይት ሊኖር አይችልም። ይህ ደግሞ የሚሆነው የሰማዕታት ቤተሰቦች ሲካሱ  እስረኞች ሲፈቱ እና ሁሉም ፓርቲዎች ሲጋበዙ ነው። ያለበለዝያ ጠቀሜታው ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ ይሆናል።

ታጋባዥ ተቃዋሚዎቹ ለጥቂት ሰዓታት ከገዥው ፓርቲ ጋር ከተመካከሩ እና በባለስልጣናቱ ከተመከሩ በኋላ እረፍት እንዲወስዱ ተደርገዋል የሚል ዜና ተለቅቋል። ፓርቲዎቹ ከ15 ቀናት እረፍት በኋላ  እንደሚመለሱ አይጋ ፎረም ላይ አነበብኩ። ሳባቲካል እረፍት መሆኑ ነው። ለሰዓታት ውሎ የ15 ቀን እረፍት ከተሰጣቸው፣ ለቀናት ቢወያዩ ደግሞ የአመት እረፍት የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። የዚህ አይነት ውይይት ያልተለመደና እንግዳ ነገር ቢሆንም በገዥው ፓርቲ በኩል ለሚሰሩ ሸፍጦች ግዜ መግዣነት የታሰበም ይመስላል።

የድርድሩ ቀልድ ግን የተበላበት ካርታ ስለሆነ የሚደረደረው ምክንያት ሁሉ ውሃ አያነሳም።

(ክንፉአሰፋ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule