ይኽን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ዐርብ የካቲት 28 ቀን (March 7, 2014) አንድነቶች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” የሚል ህዝባዊ ንቅናቄ (ህዝባዊ ሰላማዊ ዘመቻ) በ14 ከተሞች {አዲስ አበባ፣ ደሴ፣ አዋሳ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ መቀሌ፣ ደብረታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ለገጣፎ፣ እና በተጓዳኝ ከተሞች ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ)} እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ነው። መግለጫቸውን እንዳነበብኩ ዘመቻው ለታሪካችን፣ ለተያያዝነው የነፃነት ትግል እና አይናችን ለተከልነበት የዴሞክራሲ ሽግግር የሚሰጣቸው ጠቀሚታዎች አሉን? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስቼ ጥቂት ከራሴ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ ለዘመቻው ድጋፌን በመስጠት እና አንድነቶችን በማበረታት ተሳትፎዬን እንድገልጽ ህሊናዬ የግድ አለኝ። ስለዚህ የዚህ ጽሑፍ ግብ ዘመቻው የህውሃት/ኢህአዴግን የመሬት ባላቤትነት ፖሊሲ ለማሻሻል ብሎም ዛሬ በኢትዮጵያ የምርጫ ፓርቲዎች የሚያካሂዱትን የነፃነት ትግል እና ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ሊሰጥ የሚችለውን ጥቅም መመርመር ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply