• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ!? ኡክሬይን

March 12, 2014 06:25 am by Editor 1 Comment

ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ አለበለዚያ ድንጋይ ብለው ይጥሉሻል ይባላል! ለራስህ እውቅበት፣ ትርጉም እንዳታጣ ለማለት ነው፣ መቼም ይህን ታውቁታላችሁ!

ነገሩን ወደ ዘመናችን ዓለም አቀፍ ፖለቲካ ስናዞረውና ልንማርበት፣ ተመክሮ ልናገኝበት ከፈለግን እንደሚከተለው ነው።

ሰው  ህዝብ ሀገር ለራሱ ሲል፣ ወዳጅ ረዳትና ነገረፈጅ በዓለም መድረክ ላይ አለኝ በሎ፣ በራሱ ሳይሆን በነርሱ ተማምኖ ነገር ዓለሙን ከተወው፣  ለራሱ ሲል ካላወቀበት የኋላ ኋላ ጉድ ጉድ ተብሎ፣  መቼም ምን ይደረግ ተብሎ ይተዋል፤ ይወድቃል፤ ለወሬውም ይረሳል ማለት ነው።

ጉድ አንድ ሰሞን ነውና ሊቢያ ጉድ ጉድ ሲባል ከርሞ  ዛሬ ተረስቷል! ኢራክማ የት የሌለ፤ ስለ አፍጋኒስታንም ለማለገጫ ከልሆነ  በስተቀር  ብዙም ልብ አይባል! ግብጽም ከሰሞኑ ትንሽ ሰንበት ብሎ ይረሳል፤ የመን ተረስቷል፣ ሲሪያም ጨዎቹ(ፖለቲከኞቹ) ሳያውቁበት ሲቀሩ ትንሽ ቆይተው ከርስ በርስ ፍጅታቸው ጋር መረሳታቸው፣ መለመዳቸው መሰልቸታቸው አይቀርም!

ሁሉም ጋ እሳቱ ተለኩሶ  እስቲግል፥እስቲጋይ ድረስ ሃይ ሃይ ይባልና ወደ አመድ የሚያደርገው ጉዞ ሲረጋገጥ ወደ ሌላው ይታለፋል! በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት ነው!

ዛሬ ደግሞ፣ ኡክሬይን/Ukraine ነው ጉድ ጉድ ተብሎ ወደ ጉድጓድ ሊላክ የተሰናዳው!  ኡክሬይን ውስጥ፣ የማልዳን አምባ ጓሮው/ አብዮት የሚል ስም ያተረፈው/ ከአንድ አራት ወራት በፊት ለዜግነት መብትና ለመልካም አስተዳደር ጸረ መንግሥት ትግል ሲፋፍም ከጎናቸው ያልቆመ ነጻ ሀገርና ሰው አልነበረም። ከአውሮፓ እስተ አሜሪካ ከብራዚል እስከ ጃፓን! ጉድ ጉድ፣ ሃይ ሃይ ሲል የኡክሬይን ጨዎች ደግሞ ከምንጊዜም የላቀ  ለመጣፈጥ  ሲሟገቱ  ያልደገፋቸው አልነበረም። ከአውሮፓ እስተ አሜሪካ ከብራዚል እስከ ጃፓን ሁሉም ጉድጉድ ሲላቸው ግን፣ እዚያ ማዶ ያለውን ጉድጓድ ለመሆኑ አይታችሁታል ብሎ አንድም የጠየቃቸው የለም!   በተለይም አውሮፓና  አሜሪካ ካባለቤቶቹ ያወቁ ቡዳ ሆነው፣ ከማልዳኖቹ በልጠው አብረው የጀግና መዝሙር አዝማች አቀባይ እየሆኑ በየአዳባባዩ  ታዩ እንጂ  – ተዉ አይሆንም፤ እኛም ልንጋፈጥበት የማንችለው ጉድ ጓድ ኣዛ ማዶ አለ – ብሎ  ያስፈራራቸው ያስጠነቀቃቸው ማንም  የለም።

ጨው ለራሷ ሳይሆን ለሌላ ልጣፍጥ ካለች፣ ሌላው ከጣፈጠው ሲጣፍጠው ጣፊጡን ያላምጣል እንጂ፣ ለመሆኑ አንተንስ አንቺንስ ይጠፍጥሻል ብሎ የማይጠይቅበት ዘመን ውስጥ መሆናችን ዛሬ በጉልህ የታየበት አካባቢ በእርግጥም ኡክሬን ነው።

የትላንቱ ዩጎዝላቭያማ ተረስቷል!

ዛሬ የኡክሬይን ጉድጓድ ከተፍ ብሏል። መስኮብ ይገባኛል ያገባኛል የሚለውን አንዱን የኡክሬን ክፍለ ሀገር በጠበንጃ ሀይል ይዞ ህዝቡን ወደ ምርጫ ልኮ፣ ያ አንድ ሆኖ ከፋም ለማ ባንድ መንግሥት ሥር ይተዳደር የነበረውን ኡክሬንን ለመከፋፈል ሀ  ብሎ ጀመሯል። የፖ ለቲካ ጠንቋዮች ሌሎቹ ዘንድ፣ ወደ ምስራቅ ያሉት ከፍለ ሃገሮችም ይህ መከራ ይቀጥል ይሆናል ይላሉ!

ነገሩ  የዛሬ ሃያ ሁለት ዓመት በሀገራችን በኢትዮጵያ  የሆነውን ያስታውሰናል። ባጨሩ፣ ባለጉልበት መሃል ሃገር ገብቶ፣ የተቀረው ሌላው ሃገር ተለያይቶ  ለመኖር፣ አዎ የተለያየ  አስተዳደርና መንግሥት ለማቋቋም ይፈልግ አይፈልግ ሳይጠይቅ፣  ህዝቡን አስመርጠን ኤርትራን ነጻ አወጣን እንደተባለው ጉዳይ ነው። የመገነጣጠል አባዜ የያዛቸው ሰዎች የሚወዱትን ምሳሌ  እንዳው ለማንሳት ያህል፣ ባልና ሚስት እንኳን ሲጣሉ ፍቺውን ትፈልጋላችሁ ተብለው ሁለቱም ነበር የሚጠየቁት! እነርሱስ ቢሆኑ በመስኮብ ጠበል አይደል የተጠመቁት!

የመስኮቡም ፑቲን በኡክሬኑ አምባጓሮ ማግስት የቀድሞውን ፕሬስዴንትን ታቅፎ ከሰሞኑ ክሬምያ የሚባለውን ከፍለሀገራቸውን፣ በብዛት የሩስያ ተወላጆች ላሉበት ክፍለ ሃገራቸው ሀላፊነት አለብኝ ሲል ከሩስያ ጋር „በህዝብ ምርጫ“ ሊቀላቅል ነው።

እንደ  እውነቱ ከሆነ ግን፣ ነግ በእኔ ነውና እዚህ ላይ የሚገርመው  የሩስያው አምባገነን እርምጃ ሳይሆን፣ ለመልካም አስተዳደር ይታገሉ የነበሩት የኡክሬን ጨዎች ወዳጆች ነን የሚሉት ምዕራብ አውሮፓና አሜሪካ ይህ ዓይነቱ ጉድጓድ ሳይገለጽላቸው ሳይታያቸው መቅረቱ ነው! ይህን በውነት ሳያውቁት ይሆን? ለማያውቅሽ ታጠኝ ብለን እንለፈውና ስለ ጨው ጣፋጭነት እናውራ!

የአበው አባባሉ – ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ አለበለዚያ ድንጋይ ብለው ይጥሉሻል – ይባላል።  ትርጉሙን ለየት እናድርገው፤  ድንጋይ ብለው እንዳይጥሉሽ ለነርሱ ብለሽ ጣፍጪ ሳይሆን፣ ለራስሽ፣ አንድም ጨርቅሽን ጥለሽ እንዳትሄጂ/ እንዳታብጂ/ ሌላም ድንጋይ እንዳያደርጉሽ፣ የሌላው ጠጠር እንዳትሆኚ፥ አዎ ለራስሽ  ስትይ ጣፍጪ ብለን እንፍታው።

ነግ በእኔ ነውና እኛም ወደ ሃገራችን መለስ ብለን ስናየው፣ ለመልካም አስተዳደር የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ መሃል ሀገር በምርጫም ሆነ በሰላማዊ ዓመጽ ወይንም በሁለቱ የተሳካ  ለውጥ በማድረጉ ላይ ብቻ ከተጠመደ ፣ የተደገሰልን ጉድጓድ እንደማይጠፋም ለማወቅ መቼም ጠንቋይ መቀለብ አስፈላጊ አይደለም ። እኛም ወዳጅ ያደረግናቸው አውሮፓና አሜሪካ -ከዚያ ማዶ ጉድጓድ አለና ተጠንቀቁ- እንደማይሉን፣ ብዙም ሌላ ታሪክ ሳናገላብጥ ከሰሞኑ ከምናየው የኡክሬኑ የፖለቲካ ትርምስ መማር እንችላለን።  አንዳንዶቹን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናዮችን በድጋፈ፥ነዋይ የአፍዝ አደንግዝ ጨዋታ አደንዝዞ ፣ ነገ የኤርትራው አምባገነን ኢሳይያስም ሆነ እርሱን ለማስወገድ ሌት ተቀን የሚያሴሩትና እርሱን የሚተኩት ሰዎች፣ የሚደክሙለት የመንደር ራዕይ ይህንኑ የመሰለ መሆኑ ግልጽ ነው።

ኦሮሞው ካመረረ፣ አማራው ካኮረፈ፣ ደቡቡም (እንደ ጠቅላይ ሚኒስቴራችን) ከታወረ፡ ምሥራቁም ካከረረ፣ ምእራቡን ሱዳን ከወሰደው፣ ሰሜኑም ከኔ ወዲያ ካለ፣ ያች ኢትዮጵያ የምንላት የሁላችንም የታሪክ ሀገር የሆነችው ምድራችን አየር ላይ ብቻ  ተንሳፋ ብኮከቦች ብች ታጅባ ልትቀር ነው ማለት ነው!!

እግዚአብሄር ግን በቀላል አማርኛ አዳምንና ሄዋንን ያለው፣ ወደ ምድር ውረዱ፣ ብዙ ተባዙ፣ ተባበሩ፣ እርስ በርስ ተነጋገሩ፣ ተደማመጡ፣ ከተደማመጣችሁ፣ ከተነጋገራችሁ ትግባባላችሁ፣ ትተባበራላችሁ፣ ከተባበራችሁ ደግሞ እንኳን የዱር አራዊቱን ቀርቶ ያ የሚያበጣብጣችሁን ከፉ ከይሲንም፣ ክፉ መንፈስንም ታሸንፋላችሁ ነው!!! በሳይንስ የታወቀችው ሉሲና ግብረአበሮቿም ቢሆ ኑ ጉዞዋቸው ከዚህ የተለየ አይደለም። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!

ለራሳችን ስንል ጣፋጭና ጨዋ እንሁን!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Gebre says

    March 24, 2014 02:20 pm at 2:20 pm

    Nice Article….keep it up

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule