• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፌዝ ችሎት

August 4, 2015 02:05 am by Editor Leave a Comment

በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የታሰሩበትን ፖለቲካዊ ጉዳይ ህጋዊ ለማስመሰል የተሰየመው የፊዝ ችሎት ለአመታት የከረመበትን ተውኔት ከ 7 አመት እስከ 22 አመት እስር በመፍረድ አጠናቋል፡፡ የፍርዱን ዜና ተከትሎ የሚሰማው የሚነበበው ስሜት ከዚህ በተቃራኒ ፍትሀዊ የሆነ ፍርድ የጠበቁ ሰዎች እንደነበሩ የሚያመለክት ነው፡፡ ከወያኔ የፌዝ ችሎት ይህን ማሰብ ወያኔን አለማወቅ ወይንም ትናንትን መርሳት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ ትግሉ በሚጠይቀው ጽናትና ቁርጠኝት እንዳይካሄድ የሚያደርግ ነው፡፡

ወያኔ በፍትህ ሲያላግጥ በህግ ሽፋን ወንጀል ሲፈጽም እውነትን በጠመንጃው ሲረግጥ ወዘተ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በሀሰት ወንጅሎ፣ በትእዛዝ የሚፈርዱ ዳኞች ሰይሞ፣ የፌዝ ችሎት አቋቁሞ፣ ኣቃቤ ህግ ሳይሆን አቃቤ ወያኔ አቁሞ ፣ በፍትህ ላይ ትያትር ሲሰራ እኛ በተለያየ ምክንያት በተዋናይነት ወይ በተመልካችነት እናስተፍና ተውኔቱን እናደምቅለታለን፡፡ አለም አቀፉ ማህበረሰብም የወያኔን ማንነትና ምንነት የማያውቅ ይመስል የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ ፍትሀዊ ፍርድ አንዲያገኙ እንጠይቃለን በማለት ለወያኔው ትያትር እውቅና ይሰጣል፡፡

የሙስሊሙ ማህረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ወንድሞቻችን ፍትህ የተዛባባቸውና ሕገ ወጥ ተግባር የተፈጸመባቸው የታሰሩ ግዜ ነው፡፡ የሙስሊሙ ተወካይነታቸውን ተቀብሎ መፍትሄ አፈላላጊነታቸውን አምኖ ከእነርሱ ጋር ለወራት የተወያየውና የተደራደረው መንግሥት መከራከሪያ ምክንያት አጥሮት፤ ማሰመኛ ሀቅ ቸግሮት በውይይት ያልቻለውን በጉልበት ለመፈጸም የተነሳ እለት ነው የእነርሱ ጉዳይ በህግ ሳይሆን በፖለቲካ፤ በዳኞች ሳይሆን በጠመንጃ እንደሚወሰን የታወቀው፡፡ ለነገሩ ፍትህ በጠመንጃ መዳፍ ስር ወድቃ አቅመ ቢስ ከሆነች አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ፖለቲከኞቹ ሥልጣን እያቃዣቸው አንባገነንት እያወራቸው ነው ፍትህን የሚረማመዱባት፡፡ ለአመታት ተምረው ጥቁሩን ካባ ለብሰው ቀኝ እጃቸውን ሰቅለው በእውነት ለማገልገል ቃል የገቡት ዳኞች በስልክ እየታዘዙ የሚወስኑበት ከባለስልጣኖች ተጽፎ የተሰጣቸው ፍርድ ግርጌ ፊርማቸውን አኑረው የራሳቸው አስመስለው በችሎት የሚያሰሙበት ህሊና አንዲኖራቸው ያደረጋቸው ምክንያት ምን ይሆን፡፡ ጥቅም፣ የፓርቲ አባልነት፣ ፍርሀት ምንቸገረኝ ባይነት ሕዝብን መናቅ ህሊና ቢስነት፤ ወዘተ የቱ ይሆን!

እነዚህ ወንድሞች ከታሰሩበት ግዜ ጀምሮ ድምጻችን ይሰማ በሚል ትግል የጀመሩ ወገኖች መሪዎቻችን ናቸው ፣ ጥፋት የለባቸውም የታሰሩት በህገ ወጥ መንገድ ነው ወዘተ ይፈቱ በማለት ያካሄዱት ትግል ትክክልና ተገቢ ነበር፡፡ በአንጻሩ ፍርድ ቤቱ ሀቅ እንዲፈርድ ይቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች የወያኔን ማንነት የዘነጉ በየግዜው በፍትህ ስም የተሰሩ ትያትሮችን ያላስታወሱ እንደውም ለፌዝ ችሎት እውቅና የሰጡ ናቸው፡፡

ወያኔ እያንዳንዷን መሰሪ ተግባር በማን አለብኝነትና በስልት የሚያካሂድ ሲሆን ለዚህ እኩይ ተግባሩ ስኬት ደግሞ የእኛ ትናንትን እየረሱ ከአዲስ ነገር ጋር አዲስ መሆን በእጅጉ ጠቅሞታል፡፡ ወያኔ መሰሪ ተግባሩን ለመፈጸም ሲወጥን መጀመሪያ አሸባሪ ተላላኪ ጽንፈኛ ወዘተ በማለት ይፈርጃል፡፡ቀጥሎ የሀሰት የወንጀል ትያትር ያዘጋጅና መንገዴን ያደናቅፋሉ ለስልጣኔም ያሰጋሉ የሚላቸውን ስም አየሰጠ ባልዋሉበት እየፈረጀ በጅምላ ያስርና ፖለቲካዊውን ስራውን የህግ ጉዳይ ለማስመሰል የማይዛመዱ የህግ አንቀጾችን ሁሉ ጠቅሶ የወንጀል መአት ቆልሎ ክስ ይመሰርታል፡፡ በክስ መዝገቡ ላይ ካሰፈረው የውሸት ክስ ጋር ሳይቀር የማይዛመዱ ወረቀቶችን ይሰበስብና ይህን ያህል ገጽ ማስረጃ አቅርበናል ይህን ያህል የሰው ምስክር አለን አንደም ሰው ያለ ማስረጃ አላሰርን በማለት ይደነፋል፡፡ (ቅንጅቶች በዘር ማጥፋትና በሀገር ክህደት ተከሰው እንደነበር መዘንጋት ወያኔን በቅጡ አለማወቅን ያስከትላል)

ወያኔዎች ቂመኛና በቀለኛ ናቸውና ለስልጣኔ ያሰጋሉ ያሏቸውን ሰዎች በመንፈስም ሆነ በአካል ሽባ ካላደረጉ አንቅልፍ ስለማይወስዳቸው በመጀመሪያ ፖሊስ የግዜ ቀጠሮ እየጠየቀ ኋላም ፍርድ ቤቱ በሆነ ባልሆነው ቀጠሮ እየሰጠ መደበኛው ክስ መታየት ሳይጀምር ሰዎችን ለአመታት በማሰር ይቀጣሉ፡፤ በዚህ ወቅት በምርመራ ስም የሚፈጸመውን ከደረሰባቸው ሰዎች ምስክርነት የሰማነው ነው፡፡ በመቀጠል ሂደቱን እውነተኛ የፍርድ ቤት አሰራር ለማስመሰል የተወሰኑ ሰዎች እንዲለቀቁ ይደረግና ክርክሩ ይቀጥላል፡፡ በዚህ ወቅት ሰዎቹ የተፈቱት ለማስመሰያነት በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን በመዘንጋት ታሳሪዎቹ ተከራክረው ነጻ ሊባሉ ይችሉ ይሆናል የሚል ስሜት በብዙዎች ዘንድ ያድርና ችሎቱን በጉጉት መከታተልና ነጻ ናቸው የሚል ፍርድ መሰማት ይቀጥላል፡፡ ይህም ለፌዙ ችሎት እውቅና ያስገኝለታል፡፡ክርክሩ ቀጥሎ የአቃቤ ወያኔ የሀሰት ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ደግሞ አሁንም ማስመሰያውን ይበልጥ ለማጠናከር ጥቂቶቹን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በማለት ፍርድ ቤቱ በነጻ ያሰናብታል፡፡ ይህም ተከላከሉ የተባሉት በቂ መከላከያ አቅርበው የአቃቤ ወያኔን ምስክሮች ምስክርነት ማፍረስ ከቻሉ ነጻ ይባላሉ የሚለውን ስሜት ይበልጥ ያንረውና የወያኔ ተውኔት አድማቂም አጃቢም ተመልካችም እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ በዋናነት ለሚፈሩት ሰዎች የሚሰጠው ፍርድ ግን ሰሙኑን ያየነው አይነት ይሆንና አዲስ ጩኸት አዲስ ውግዘት እናሰማለን፡፡ ወያኔ ከጨዋታ ውጪ ሊያደርጋቸው የፈለጋቸው ሰዎች ተመሰከረባቸው አልተመሰከረባቸው፤ በበቂ ተከላከሉ አልተከላከሉ፤ተከራከሩ አልተከራከሩ ለውጥ የለውም፡፡ለዚህም ወደ ኋላ ሄዶ ሌሎች ፍርዶችን ማስታወስ ሳያስፈልግ ተከላካይ ጠበቃ የነበሩት አቶ ተማም ስለዚህኛው ፍርድ የተናገሩትን መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡

የወያኔ ትያትር ግን በዚህም አይበቃ ይግባኝ ተብሎ ጉዳዩ ለቀጣዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ከአንዳንዶቹ የእስር ቅጣት አመት ላይ የተወሰነ በመቀነስ ጉዳዩ በህግና በህግ ብቻ እየተስተናገደ እንደሆነ ለማሳየት ይሞከራል፡፡ ይህን ያዩ የሰሙ በራሳቸው በታሳሪዎቹም ይሁን ወይንም በቤተሰብ አለያም በጠበቃቸው ፍላጎትና ግፊት ጉዳያቸው በይግባኝ ለሚመለከተው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እዛም ፍትህ ሳይሆን ፖለቲካ ነውና የሚዳኘው የሚታየውም ማስመሳያ አንጂ በህግ የበላይነት የተሰራ አይደለምና ውሳኔው ጸንቶ ይመለሳሉ፡፡

ይህ ሁሉ ሂደት አንደም ለፖለቲካው የፌዝ ችሎት እውቅና ያስገኝለታል ሁለትም በፍርድ ቤት ውሳኔ ለሚለው የወያኔ ስብከት አጋዥ ይሆናል ሶስተኛ የፍድ ቤት ውሳኔ በመጠበቅ ሊደረግ የሚገባው ትግል በወቅቱ እንዳይካሄድ ቢኖርም የተጠናከረ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወያኔ የፈራቸውንና ቅስማቸውን ለመስበር ያሰራቸው ሰዎች ላይ በእስር ቤት የተለያዩ አረመኔያዊ ድርጊቶች እንደሚፈጽም በተጨባጭ ማስረጃ የቀረበ አይተናል ሰምተናል፡፡ ይህም በመሆኑ በተለያየ ግዜ በወያኔ እስር ቤት ቆይተው ከወጡ በኋላ በቀደመ ተግባራቸው (ፖለቲከኛም ሆነ ጋዜጠኛ ብሎም የመብት ተከራካሪ) የቀጠሉ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡

ለወያኔ የፌዝ ችሎት እውቅና ባለመስጠት ረገድ የተሻለ ነገር የሰሩት የቅንጅት አመራሮች ናቸው፡፡ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ስለሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው የሚያስፈልገው፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመገናኛ ብዙሀን ወንጀለኞች ብለውናል፤ርሳቸው ወንጀለኛ ያሉትን ይህ ፍርድ ቤት ነጻ ለማለት አቅሙም ነጻነቱም የለውም፤ ስለሆነም አንከራከርም ፤ፍርድ ቤት መመላለስ ሳያስፈልገን የጠቅላይ ምኒስትሩን ውሳኔ በፍርድ ቤቱ ስም አድርጋችሁ አለንበት ድረስ ላኩልን በማለት አልተከራከሩም፡፡ ቢከራከሩም የሚለውጡት ነገር እንዳልነበረ ከመጨረሻው አፈጻጸም ተረጋግጧል፡፡ ለማስመሰል የተወሰኑ ሰዎችን ነጻ ብሎ አሰናብቶ የተወሰኑ ሰዎችን በተለያየ አመት የቀጣው በፍርድ ቤት ስም የቀረበው የፖለቲካ ፍርድ ይህን አደረጉ ማለት ቀርቶ አንዲህ ብለው ተናገሩ ተብሎ አንኳን በክሱ ውስጥ ያልተጠቀሱ ሰዎችን የቅንጅት ምክር ቤት አባል ስለሆናችሁ በሚል ነው በጅምላ የእድሜ ልክ እስራት የፈረደባቸው፡፡

ስለሆነም ነጻ ፍርድ ቤት በሌለበት ፍትህ እንደማይገኝ በተግባር የታየ በመሆኑ፤ወያኔ ሥልጣን ላይ እያለ ደግሞ ነጻ ፍርድ ቤት የማይታሰብ ስለሆነ ሰዎች ሲታሰሩ የማይገኝ ፍትህ ከመጠየቅና መጨረሻ ላይ እንዲህ አንደ ሰሞኑ ከማዘን ከመናደድና ከመጮኸ በህግ አምኖና በህግ ተከብሮ ለመኖር የሚያስችል ሥርአት ለመፍጠር በአንድነትና በጽናት መታገል ይበጃል፡፡ ተለያይቶ ቆሞ ተራ በተራ ሲጠቁና በደል ከቤት ሲገባ ብቻ መጮህ የሚያመጣው ፋይዳ አንደሌለ ታይቷልና በጎሳ በኃይማኖት በቋንቋም ሆነ በሌላ ምክንያት ሳንለያይ በሀሰት የማንወነጀልበት፤እውነት በጠመንጃ ስር የማትውልበት፤ማንም ሰው (ጠቅላይ ምኒስትሩም ቢሆን) ከህግ በላይ የማይሆንበት ሰው በሰውነቱ የሚከበርባት ዴሞክራሲዊት ሀገር አንድትኖረን በአንድነትና በጽናት መታገል ነው መፍትሄው፡፡

ያለበለዚያ ትናንት የሆነውን እየረሳን ከአዲሱ የወያኔ ድርጊት ጋር አዲስ እየሆንን፤በፍትህ ለሚቀልደው የፌዝ ችሎት በአንድ ወይንም በሌላ መልክ እውቅና እየሰጠን በእኔ ካልደረሰ እያልን አንዱ የሌላውን ጩኸት መስማትና ማገዝ እያቀተው የደረሰበት ብቻ ተራ በተራ ለየብቻው መጮኹን ከቀጠለ፡ወያኔም በህግ መቀለዱን በፍህ ትያትር መስራትን ዜጎችን በሀሰት እየወነጀለ ማሰሩን ይቀጥላል፡፡

ይገረም አለሙ

abutam2006@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በዚህ ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይዘገባሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም አይደለም፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule