ወያኔ ስልጣንን የሙጥኝ ይዞ ሀገራችንንና ህዝቧን ቁም ስቅል ማሳየት ከጀመረ እነሆ 26 ዓመታት ተቆጠሩ። ከጀሌዎቹና ፍርፋሪ ከሚበትንላቸው አጨብጫቢዎቹ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል የህዝብ ድጋፍ ሳይኖረው ይልቁንም በህዝብ ተጠልቶና ተተፍቶ ከሩብ ምዕተዓመት በላይ ስልጣን ላይ የመቆየቱ ነገር እንቆቅልሽ የሆነባቸው እጅግ በርካታ ናቸው። በአንፃሩ ስርዓቱን ለማስወገድ በተለያየ አቅጣጫ የሚደረገው ትግል ውጤት አልባ መሆን ተስፋ አስቆርጧቸው የወያኔ ከወንበሩ መነሳት የማይታሰብ እንደሆነ የደመደሙም አልጠፉም። ይህ ፅሁፍ የገዢው ቡድን የስልጣን ዕድሜ እንዲህ የተንዘላዘለበትንና እስካሁን የተደረጉ የለውጥ ትግሎች ውጤት ያላመጡባቸውን ምክንያቶች እንዲሁም ወደፊት ወያኔን ለማስወገድ የሚደረጉ ትግሎች ከግንዛቤ ቢወስዷቸው መልካም የሚሆኑ ነጥቦችን ለመዳሰስ ይሞክራል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply