• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት – ስዩም ተሾመን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደምትገል ማስጠንቀቂያ ላከች

October 28, 2019 09:31 am by Editor 11 Comments

“ሕዝብ ስዩምን ሊጠብቀው ይገባል”

በጃዋር ትዕዛዝ ንጹሃን መጨፍቸፋቸውን፣ መታረዳቸውን፣ የእምነት ተቋማት መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን ተከትሎ ሴራው እንዴትና በነማን ቅንጅት እንደተቀነባበረ ይፋ በማድረግ ላይ ባለው አምደኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስዩም ተሾመ ላይ የግድያ ዛቻ ተሰነዘረ። የግድያው ዛቻ በቀጥታ የተላከው ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል ጌታቸው ነው።

ህወሓት ፖሊሱን፣ ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ኢኮኖሚውን ከፍተኛውን የአገሪቱን ሥልጣን በተቆጣጠረበት ወቅት በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ጎን ለጎን ትግል ሲያካሂድ የነበረው ስዩም ተሾመ በተደጋጋሚ ታስሯል፣ ቶርቸር ተደርጓል፣ ተሰቃይቷል፣ እንደዜጋ ለምን ጻፍክ በሚል የከፋ ወንጀል ተፈጽሞበታል።

በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ቢያልፍም ግንባሩን ሳያጥፍ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን በብዕሩ ተጋፍጧል። ለውጡ እውን ከሆነ በኋላም ሥራውን አቁሞ “ነጻ ውይይት” በሚል ርዕስ ቃለ መጠይቅ በማቅረብ የህወሓትን ገበና አደባባይ እርቃን አውጥቷል። 

ቀድሞም ጥርስ የተነከሰበት ስዩም እሁድ ይፋ እንዳደረገው አቶ ጌታቸው ረዳ ለወሲብ ሲዳራ የሚያሳይ፣ ከጃዋር መሀመድ ጋር አገሪቱን አተራምሶ መንግሥት ለመገለበጥ ያሴሩትን ሤራ የሚያጋልጥ የኢሜል መልዕክቶችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ማስፈራሪያው በቀጥታ የተላከለት።

ዜጎች ጥበቃ ሊያደርጉለት እንደሚገባ በተደጋጋሚ ቢነገርም ስዩም ግን ግንባሩን እንደማያጥፍና እስከወዲያኛው በጀመረው ሥራ እንደሚቀጥል በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።

ህወሓት ከፍተኛ ኃላፊነት የሰጠችውና የፓርላማ አባል የሆነው ጌታቸው የራያን ህዝብ በመሸጡ ብቻ ሳይሆን በሴሰኛነት፣ በዝሙት፣ ሃብት በማሸሽ፣ ከአገር ውጪ ንብረት በማካበት፣ በሶማሊ ክልል የተሞከረው አገር የመበተን አጀንዳ ከከሸፈ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመሩትን መንግሥት በነውጥ ለመጣል ከድብረጽዮን (ጌታቸው አሰፋ) ውክልና ወስዶ በቅማንት፣ በወላይታ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች ለሚፈጸሙ የማተራመስ ዕቅዶች ዋና አስተባባሪ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚህ የጌታቸው ረዳ ዛቻ “ይድረስ ለጌታቸው ረዳ፤ እኔ ያመንኩበትን ሰርቼ እንጂ አንተን ፈርቼ አልሞትም” ስዩም የሰጠው መልስ የሚከተለው ነበር፤

ይህን የኢሜይል መልዕክት የፃፍከው እኔን በማስፈራራት አንተና ድርጅትህ ህወሓት በሀገር ደህንነትና የዜጎች ህይወት ላይ የምትፈፅሙትን ወንጀል ከማጋለጥ እንድታቀብ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እኔን በማስፈራራት ያመንኩበትን ነገር ከማድረግ ለማስቆም መሞከር ሞኝነት ነው። ምክንያቱም ይህን ፈፅሞ ማድረግ አይቻልም። አንድ የማዕከላዊ መርማሪ ልክ አንደ አንተ በእብሪት ተወጥሮ “ጥጋብህ እዚህ ደርሷል! ጠብቅ ቆይ አሳይሃለሁ!” ብሎ ሲዝትብኝ “ሌሊት ላይ ወደ ማሰቃያ ክፍል ወስጄ ጥፍርህን እየነቀልኩ አሰቃይሃለሁ!” ማለቱ እንደሆነ ገምቼያለሁ። ነገር ግን ክፍሌ ውስጥ ገብቼ በፍርሃት ስንበቀበቅ አታገኘኝም። ከዚያ ይልቅ ከእግሬ ጣቶች የአንዱን ጥፍር በገዛ እጄ ነቅዬ ስቃዩን ተለማምጄ ነው የጠበቅኩት!!! አሁን አንተም ይህን ማስፈራሪያ እዚህ ፌስቡክ ላይ ከለጠፍኩት “እንደ ውሻ በድንጋይ ተወግረህና ተሰቃይተህ ትሞታለህ” ብለሃል አይደል?? ቱፍ!! እኔ ወንድ የአባቴ ልጅ ነኝ። ያመንኩበትን ሰርቼ እንጂ ፈርቼ አልሞትም። ይሄው የአንተን ማስፈራሪያ እዚህ አውጥቼ ለጠፍኩት!!! በል እስኪ እንዳልከው ቅጥረኞችህን ላክና ግደለኝ!

ጎልጉል አስተያየት የጠየቃቸው እንደተናገሩት ከሆነ መንግሥት እንደ ጃዋር ላሉት ጥበቃ የሚያቆም ከሆነ በዚያ ተጻራሪ ለአገርና ለሕዝብ ኅልውና በዚህ መልኩ መስዋዕትነት ለሚከፍሉ ዋስትና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

“ስዩም ያለመታከት ከሚወጣቸው መረጃዎች በእጅጉ እየተጠቀመ ያለው ሕዝብ ወገናዊነቱን ለስዩም ጥበቃ በማድረግ ሊወጣ ይገባዋል” ያሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ “አገር ለመበታተንና ሕዝብን ለማጋደል ቀን ተሌት ለሚሠራው ጃዋር ድጋፍ እየሰጡ ካሉት ቄሮዎች የእውነትና የአገር ፍቅር ስሜት ላቸው ትምህርት ቢወስዱ መልካም ነው፤ እነርሱ ለጥፋት ይህንን ያህል ሲተጉ እኛ ደግሞ አገር ለማዳን ለሚሠሩ ከዚህ እጥፍ ልንሠራና ልንተጋ ይገባል” ብለዋል።

በአጠቃላይ አስተያየት የሰጡ እንደተናገሩት ከሆነ ግን እንደዚህ ባለ መልኩ የግድያ ሙከራና ሤራ ከአንድ የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሰነዘር መንግሥት እየሰማ ዝም ማለት የለበትም፤ ጌታቸው ረዳን በኃላፊነት መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ለስዩም ተሾመም ልዩ ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል ብለዋል።   


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column, seyoum teshome, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Silesh Seyoum says

    October 29, 2019 02:37 pm at 2:37 pm

    እዉነተኛ እና እዉነት አይሞትም ሞት ለዉሸታሞች

    Reply
  2. Babilon Jutass says

    November 1, 2019 12:07 am at 12:07 am

    ድሮም የቁሞ ቀር አስተሳሰብ እና የአምባነን፣ የጠባብ ፣ የሙሰኛ እና የሌባ ድርጅት ከዚህ በላይ ማሰብ የት ያውቅና! መግደል፣ ማሰቃየት፣ መዝረፍ፣ ማሸማቀቅ፣ ወዘተ. ላለፉት 28አመታት ሲሰራው የኖረ የደንቆሮ ስራ ነው! አገር መምራትማ የት ያውቅና! ለነገሩ ችሎታውስ የት ኖሮት!ዛሬም በስብሰውም እየሸተቱ እንኳ መግማታቸውን ማያውቁ ለመታጠብም ሆነ ለመፅዳት ማያስቡ መትላታቸውን መገንዘብ ያቃታቸው እና በተቀመጡበት እራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው መቀመጫ ሚያበላሹ ሰዎች እንዴት ለሌላ ሰው ብሎም ለሀገር ሊያስቡ ይችላሉ! ምክንያቱም ሲጀመር ማርክዝም ሌኒዝም ሚስማር ቀርቅሮ ይዟቸው እንዴት ይለወጡ! በ60ውቹ አሰተሳሰብ እንዴት የዛሬ ሀገር ይመራል! ለዚህ ነው ሰው ሲቀነጭር ሚታየው መግደል ማስገደል ብቻ የሚሆነው! ስለዚህ ወንድሜ ስዩም እራስህን ጠብቀህ ስራህን ስራ ለበሰበሱ በሽተኞች ጆሮህን አትስጥ! የተዘረፈ ገንዘብ ስለያዙ ሁሉን ማድረግ ሚቻል ይመስላቸዋል! ፈጣሪ አንድ ቀን የጃቸውን ይሰጣቸዋል! #ኢትዮጵያ# ድሮም ሆነ ዛሬ ጠባቂዋ በሰበሱ መሪዎች ሳይሆን በፀዱ በነቁ ባስተዋሉ ልጆቿ እና ፈጣሪዋ ነው! እንደ ሰዎች እማ ብሆን………..!!!

    Reply
  3. Yilna says

    November 1, 2019 03:30 pm at 3:30 pm

    ወገቡን የተመታ ጅብ እስኪሞት ማላዘኑ አይቀርም። እዚህም ያለው ልሙስሙስ መንግስ እድላቸውን አስፍቶላቸዋል። አገር እያበጡና የዘር ማጥፋትን ሲፈጽሙ አንገድልም በሚል ልፍስፍስነት በተንሻፈፈ የቀን ቅዘት ፍልስፍና የሚንከዋረረው ጅል መሪ ነው የተጫወተብን። ጥፋተኛና ወንበዴን አንገልም እያለ ንጹሀንን አቅመ የሌላቸውን አዛውንቶች የሚያስገድል።

    Reply
  4. yhenew says

    November 1, 2019 04:18 pm at 4:18 pm

    How it is thought
    No, he scoffs when pure blood cries out.
    I # Ethiopia
    እንዴት ሆኖ ይታሰባል
    አይ የንፁሃን ደም ሲጮህ እንዲህ ያስለፈልፋል።
    አይ #ኢትዮጵያዬ
    ስይሜ ኑርልን
    ገዳዮች ሟቾች ናቸው።

    Reply
  5. ሲራክ says

    November 1, 2019 05:25 pm at 5:25 pm

    እውነትና እውነተኛ አይሞትም::

    Reply
  6. ????? says

    November 1, 2019 05:28 pm at 5:28 pm

    እውነትና እውነተኛ አይሞትም:: ሞት ለገዳይ!!

    Reply
  7. Ashenafi says

    November 1, 2019 09:23 pm at 9:23 pm

    NO coment

    Reply
  8. biniyam says

    November 1, 2019 09:53 pm at 9:53 pm

    መንግስት ሽብር ፈጣሪዎችን አንድ ይበልልን

    Reply
  9. Getachew says

    November 1, 2019 09:56 pm at 9:56 pm

    ቱፍ!! እኔ ወንድ የአባቴ ልጅ ነኝ። ማለቱ ጀግና ነኝ የሚል ሰው ጥበቃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም

    Reply
  10. Kiburjela says

    November 2, 2019 09:38 am at 9:38 am

    Both TPLF and Seyoum are terrorist, but so sadly Seyoum is a beggar on top of that. He soon plans to open a go fund me account to ridicule Amhara and snatch their money through the emotionally charged but false write ups like this one.

    Reply
  11. Kibrom says

    November 13, 2019 03:04 am at 3:04 am

    If source of email is authentic then
    Seyoum should report to Ethiopian
    authorities, international consulates
    in Addis, and human rights groups.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule