• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕወሃትና የኢትዮጵያዊነት ገጽታው

March 1, 2014 06:29 am by Editor 2 Comments

ባለፈው የካቲት 11 2006 የህወሃት ምስረታ በአል ሲከበር ጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን ንግግር ሲጀምሩ የትግራይ ሀዝብ ከአስከፊው ብሄራዊ ጭቆናና ፋሽስታዊ ስርአት ጋር ተናንቀው … ብለው ነበር እናም በርግጥ የህወሀት የትግል መስመር እና አለማ ምን ነበር? አሁን እንደሚባለው ኢትዮጵያን ከአስከፊው የደርግ ስርዐት ለመታደግ ወይስ በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ እነደተናገሩት “የድህነት ጠበቃ የነበረውን ደርግ” አሸንፎ ብልጽግና ለማምጣት?

ሕወሐት የተመሰረተበትን አላማ የሚገልጽ የህወሀት ማኒፌስቶ (በ 1968 የታተመ መጸሔት) ለዚህ ጥሩ መልስ አለው ሰነዱ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አጠቃላይ የህወሀት አላማ እና መድረሻ “የጨቋኟ አማራ ብኄርን” ጭቆና ለማስወገድ እና የትግራይ ሪፓብሊክ ማቋቋም ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ እድገትም ሆነ የወደፊት አላማ ያስቀመጠው የልማት እቅድ ሳይሆን  የኢትየጵያን አንድነት በሚያፈራርሱ ዘረኛ አስተሳሰብ የታጨቀ ነው፡፡ ለዚህም ይመሰላል ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ዘወትር በሸገር ራዲዮ የምንሰማውንና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚወደውን አባባል የጎሪጥ የሚመለከቱት ብዙ የነበሩት፡፡ ስለዚህም የህዝቡን ስሜት ከዚህ ለማስለወጥ ብዙ ነገሮቸ ተብለዋል፡፡ ለምሳሌ የዚሁ ስርአት አጫፋሪ በሆነው ኢትዮ ቻናል  በተባለው ጋዜጣ ላይ (እትሙን አላስታውሰውም) ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ክቡር ቃል አጅግ ተራ በሆነ አቀራረብ ምንም ነገር ለዘላለም አይኖርም ስለዚህ ይህ አባባል ስህተት ነው የሚል ትርጉም ሰጥቶ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳውን  ይዞ ብቅ ያለው፡፡ በነራችን ላይ ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት የሚሉንም እነሱው ናቸው አናም ዘላለም የሚለው ቃል ትርጉም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ጠባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ስለሆነ ነው፡፡

አሁን ጠዋት ማታ የሚያደነቁረን የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የሚነግረን የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው ኢህአዴግ ያመጣው  የዘር ፖለቲካ በነሱ አገላላጽ “የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ሲረጋጋጥ” መሆኑን ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ተረጋግጧል በሚሉት በዚህ ዘመን የትግራይ ተወላጅ (የህወሃት አባል) መሆን ብቻ ሁሉም በሮች እንዲከፈቱለት የሚያደርግ ልዩ የይለፍ ካርድ መሆኑን የምናየው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁል ጊዜ የሚያስገርመኝን አንድ ማሳያ ላስቀምጥ፤ ብዙ የትግርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ሰዎች (በተለይም የስርአቱ አጫፋሪዎች)ንግግር ሲኖር ወይም ትንሽ ጭቅጭቅ ሲኖር ልክ የትግራይ ተወላጆች እነደሚሉት ዋእ! ዋእ! ሲሉ እንሰማለን፡፡ ዘወትር ፈገግ ቢያሰኘኝም ለኔ የዚህ ትርጉሙ ብዙ ነው በጣም ብዙ።

እንደምናስታውሰው ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስለ ሀገር ፍቅር የሚናገሩ ነገሮች በሙሉ በመንግስት ሚዲያዎቸ በአዋጅ የተከለከሉ ይመስል አስከ ቅርብ አመታት ድረስ መስማት ብርቅ ነበር፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያዊነትን ከህዝቡ አእምሮ ለመነጠል በስውር አንዳንዴም በግልጽ የሚደረጉ ግፊቶች ነበሩ፡፡ አሁንም በተለይ ለዚህ ዘመን ትውልዶች ሀገራችን የረጀም ግዜ አኩሪ ታሪከ እንዳላት ሳይሆን ተራ የሆነ የዘር ፖለቲካ እንደ አኩሪ ታሪክ ይማራሉ፡፡ የሃገራችን ህፃናት ማንታቸውን ረስተው የፈረንጅ ቋንቋ የሚናገሩ ሆነው እየተቀረጹ ነው፡፡ በሃገራቸው ቋንቋ አንድ ዓረፍተ ነገር ተናግሮ መጨረስ ሲተናነቃቸው እያስተዋልን ነው። አንድ ሰው 12 አመት መሉ ተምሮ እንግሊዝኛ መናገር የዕውቀት ጣሪያ እስኪመስል ድረስ ዛሬ በሀገራችን በተለይም በአዲስ አበባ የልጆች የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንግሊዝኛ መሆን ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በክልሎች አካባቢ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህረተ ከመሰጠቱ ጋር ተያይዞ (በነገራችን ላይ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር በራሱ ችግር የለውም) እነዚህ ተማሪዎች ሌሎች ቋንቋዎችን  በተለይም አማርኛን እንዲጠሉ በመደረጋቸው የሀገራቸውን ብሄራዊ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ዜጎች ማየት ጀምረናል፡፡

ናትናኤል ካብቲመር
ናትናኤል ካብቲመር

ሀገራችን ኢትዮጰያ አንድነቷ ተከብሮ የኖረው በልጆቸዋ ውድ መስዋትነተ እንደሆነ ማወቅ ማንነትን ማወቅ እንጂ የብሄር ጭቆና ማስታወስ አይደለም በነገራችን ላይ ኢትዮጵየዊነትን ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር ማገናኘት አንዱ የህወሃት አስገራሚ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ሁሉም ማወቅ ያለበት ግን ህወሃትም ሆነ እርሱ የሚመራው ኢህአዴግ ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጰያዊያንን በዘር ከመከፋፈል ውጭ ሰለሀራችን ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ሁለንተናዊ አድገት የማይጨነቅ መሆኑን ነው፡፡ስለዚህ እኛ ኢትዮጰያዊያን ፀረ ኢትዮጰያ አቋም ያለውን አስከፊ ስርዐት ማስወገድና ልጆቻችንን ታላቅ ሀገር እንዳላቸው ማስተማር  ለነገ ብለን የማናሳድረው ሀላፊነት ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

natnaelkab@gmail.com

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ephiphi says

    March 11, 2014 08:49 am at 8:49 am

    teru melketa new hewehat Ethiopia wedema rasun manor kechalh yanen new yemefelgew. .ya demo bandanet new

    Reply
  2. Sabakoo says

    March 11, 2014 06:26 pm at 6:26 pm

    The reality is you are using Ethiopianism to manupulate others and to robe its resources. When others say we are Ethiopian you do not accept and grant them the true meaning of nationalism. Why others did not benefit economically, politically and culturally during Emiyye Minilk, HS and Dergue if Ethiopia is for all? Some times you need to know others can equally sense what had been happning. I can agree with you there is still problem: people deserve more rights, but not the same way to used to be. Even thinking that way would destroy that country for ever.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule