• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!

February 5, 2014 10:06 pm by Editor Leave a Comment

የመምህራን ማስጠንቀቂያ …

ሰሞነኛው የጅዳዎች ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድን በማስተካከል ዙሪያ ቢሆንም ከ 3000 (ከሶስት ሽህ) በላይ ታዳጊዎችን የሚያስተናግደው የጅዳው አለም አቀፍ ት/ቤት አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን እየሰማን ዝም ብለናል!  ከሳምንታት በፊት መምህራን አመጽ አድርገው ነበር። ከቀናት በፊትም  25 መምህራን ስብሰባ ተቀምጠው፣ በአንድ አቋም ጸንተው ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ላለፉት 8 ወራት በትምህርት ቤቱ ባለቤት በኮሚኒቲው ጉዳያቸው ቢያዝም እስካሁን ከወሬ ያላለፈ አርምጃ አለማየታቸውን ገልጸዋል።  25 ቱ school letterመምህራን ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ለኮሚኒቲው፣ ለጅዳ ቆንስልና ለወላጅ መምህራን ህብረት ባስገቡት ደብዳቤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት የሁለተኛው የትምህት አጋማሽ መጀመሪያ የመኖሪያና የስራ ፈቃዳቸው ተስተካክሎ ካልተሰጣቸው  በማስተማር መደበኛ ስራቸው እንደማይገኙ በላኩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስጠንቀቃቸውን በእጀ የገባው ሰነድ ያመላክታል!

የወላጅ መምህራን ህብረት ስብሰባ ጥሪ …

“ወላጅና መምህራን ህብረት” በሚል ካች አምና በመንግስት ትዕዛዝ የወላጅ ኮሚቴን የተካው ኮሚቴ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ለመምከር ለወላጅ ስብሰባ ጠርቷል። ኮሚቴው የሳውዲን የምህረት አዋጅ ማለቅ ተከትሎ የጅዳ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ለሳምንት ሲዘጋ የሚወክለውን ወላጅም ሆነ መምህራኑን ብሎ ድምጹን አላሰማም። ትምህርት ቤቱ ካንድም ሁለት ሶስቴ በመምህራን ስራ ማቆም አድማ ሲናጥ፣ ከፍተኛ የማህበረሰቡ መዋዕለ ንዋይ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚደረጉ የመምህራን እና ሰራተኛ ዝውውር መባከኑ ሲሰማ የዝሆን ጀሮ ስጠኝ ማለቱ አይደንቅ ይሆናል። የመንግስት ሃላፊዎች ትኩረትና ጥበቃ የማይደረግለትን  የትምህርት ማዕከል ህልውና ለማስጠበቅ ስብሰባ መጥራትና ወላጁን ባለማማከሩ ተወቃሽ ከመሆን ግን አላመለጠም። ለሚታየው እንግዳ፣ ለሚሰማው ባዳ መሆናቸው ያስከፋው ወላጅ ከትናንትም ዛሬ ተስፋ ቆርጧል።

ዛሬ የወላጅ መምህራን ህብረት ተብየውን ምን እንዳሰናከለው፣ ምን እንዳሽመደመደው መስማት ባያጓጓም የወደፊት የወላጁን፣ የመምህራንንና የታዳጊዎችን ትምህርት ቤት አደጋ ላይ መውደቅ  እያየ ስለያዘው አቋም መስማት ጓጉተናል። ማስታወቂያ ባወጣ በሳምንቱ፣ ስብሰባውን ሊያደርግ ቀናት ሲቀሩት ደግሞ ዛሬ ምሽት የህብረቱ አመራሮች በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተዋል። አሁንም ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ምን በል ሊባልም ሆነ ከወላጅ መምህራን ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዳይነካ የሚፈለገውን ቦታና  እንዳይታለፍ የሚፈለገው የቀይ መስመር ገደብ ምን ሊሆን እንደሚችል አንገምትም።  ብቻ ሁነኛ ባለቤት አጥቶ አንደ ስደተኛው ተገፊ ወገን ለሚከላተመው የ3000 ታዳጊዎች ትምህርት ቤት መጻኢ ህይዎት ወላጁ በስብሰባው በመሳተፍ መምከር ይኖርበታል።sch letter

በመግስት ሊደራጅ ያታቀደው ኮሚኒቲ …

ዛሬ ያለው ኮሚኒቲ በአዲስ የመተኪያው የምርጫ ጊዜ በቆንስል መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ተላልፏል። የሚተካው ኮሚቴ ደግሞ የሚደራጀው በመንግስት እንደሆነ እየተነገረን ነው። የምርጫው መዘግየትም ዋናው ምክንያት ይህ እውነት መሆኑ ቆንስል መስሪያ ቤቱ ከመካከለኛው ምስራቅ አገኘሁ ያለውን ሞዴል የኮሚኒቲ ህግና ደንብ ረቂቅ ጊዜውን ለጨረሰው ኮሚኒቲ ይፋ አድርጎታል። ቅንነት በሌለበት መንደር በወረቀት ላይ በሰፈረ ህግና መመሪያ ለወጥ ያመጣ ይመስል የማይገባ ስራ መሰራት ተጀመሯል። የሚጠፋውን ጊዜና የሚባክነውን የማህበረሰብ ንብረት ብክነት ነዋሪው ህብረት ፈጥሮና ማህበሩን ከፖለቲካና ከድርጅት አደረጃጀት ጣለቃ ገብ ሂደት በማስቆም ነጻ ካላወጣው አደጋው የከፋ እንደሚሆን ጥርጣሬው ያየለብኝ ለእኔ ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ። ግን አይደለም። ብዙ ነዋሪ አዲሱን አካሄድ አልወደደውም!

ኮሚኒቲውን በአንድ ባንዴራ ስር ከማደራጀት ተወጥቶ በብሔር ብሔረሰብ ስብጥርና የፖለቲካ ድርጅት ሰወች በኮሚኒቲው በማሰግሰግ የሰራነው ስራ እንዳላዋጣን እናስተውለው። ወላጁም ሆነ አብዛኛው የጅዳና አካባቢው ነዋሪ ለአመታት የራቀው ኮሚኒቲ የጥቂቶች መፈንጫ ከሆነ ወዲህ የሆነውን ቆም ብለን እናስብ! እናም ቢያንስ በልጆቻችን ትምህርት ቤትን ህልውና ለማስጠበቅ ኮሚኒቲውን ሊውጠው ከተዘጋጀ ክፉ አውሬ አፍ ለማዳን እንረባረብ!  በኮሚኒቲውና በትምህርት ቤቱ ዙሪያ በሚደረጉ ስብሰባዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የልጆቻችን ትምህርት ቤት ለመታደግና ለህልናው ወሳኝ የሆነውን ኮሚኒቲ ከወደቀበት አዘቅት አውጥተን ለብሩህ ተስፋ ሂደቱ እንታደገው፣ እናጎልብተው!  ወላጅና መምህራን ህብረት በጠሩት ስብሰባ ተሳታፊ እንሁን፣ በነጻነት ሃሳባችን እናንሸራሽር! የልጆቻችን ትምህር ቤተችን ከአደጋ እንታደገው!  ይህ ማንም የማይገሰው መብታችን ነውና!

ጀሮ ያለው ይስማ!

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule