• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ይድረስ ለገራፊዎቻችን – እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!

July 7, 2015 09:38 am by Editor 1 Comment

“በምርመራው ወቅት የነበረው ድብደባ እና ክብረ ነክ ስድብ ወደ ምድር የመጣሁበትን ቀን እንድረግም አደረጉኝ፡፡ በተለይ ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል እየዛቱ የውስጥ እግሬን ክፉኛ ገረፉኝ፡፡ . . . እኔም ልብሴን እንደማላወልቅ ነገርኳቸው፡፡ በዚህም ከአሁን ቀደሙ ለየት ያለ ከባድ ድብደባ አስተናገድኩ፡፡ ድብደባው ከአቅሜ በላይ ሲሆን ግን ከውስጥ ሱሪዬ ውጭ ያለውን ልብሴን ለማውለቅ ተገደድኩ፡፡ የውስጥ ሱሪዬንም እንዳወልቅ አዘዙኝ፡፡. . . “

ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ የክረምት መግቢያ መባቻ፣ ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ደግሞ የፆም ሐዋሪያት መፍቻ ነው፡፡ በዚች እለት እኔም እንደወትሮዬ በአካባቢዬ በምትገኝ አንዲት ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ከስርዓቱ አፈና የተረፉትን ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜናዎችን ማንበብ ተያያዝኩት፡፡ በዕለቱ ከታተሙት ጋዜጦችና መፅሄቶች መካከል ከፍተኛ ሽፋን ተሰጥቶት ይዘገብ የነበረው በዚች ምስኪን ሀገር በስስት የሚታዩ አራት ከፍተኛ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በግፍ ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት መወርወራቸውን የሚያትት ነበር፡፡ ከዛ በፊት ደግሞ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎች ሲዘገብ የነበረው በኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ የሆኑት ጋዜጠኞችና ጦማሪያና በማዕከላዊ እስር ቤት እየደረሰባቸው ያለው ስቃይና የፍርድ ሂደት ነበር፡፡

ማንበቤን አቋርጬ ለጥቂት ደቂቃዎች ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ይህ ነገር የስርዓቱ የተለመደ የስልጣን ማራዘሚያ ዘዴ ቢሆንም ቅሉ እስከ መቼ እንዲህ ይቀጥላል? ይህ ስርዓት በኢትዮጵያውያን ላይ እስከመቼ ነው የሚቀልደው? የኢትዮጵያ ህዝብ የዴሞክራሲ፣ የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲ አየር የሚተነፍሰውስ መቼ ነው? ከዘመናዊ ባርነት ተላቅቆ በነፃነት የሚኖርበት ጊዜስ ምን ያህል ሩቅ ይሆን? ነፃ ተቋማት የምንገነባውስ መቼ ይሆን? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እያሰላሰልኩ በአካባቢው የስርዓቱ ጠባቂ የሆኑት የፌደራል ፖሊሶችና የደህንነት አባላት ከሁለት መኪና ወርደው የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ አስቆሙት፡፡ የነበርኩበት ካፌ ተከበበ፡፡ አንድ የመገናኛ ሬድዮ የያዘ የፌደራል ፖሊስና ሁለት ሳምሶናይት የያዙ ደህንነቶች በቀጥታ ወደ እኔ መጡና የፌደራል ፖሊሱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳየኝ፡፡ በቁጣ “ተነስ! ፖሊስ ጣቢያ ቃልህን ትሰጣለህ!” የሚል ትዕዛዝ አከለበት፡፡ የተጠቀምኩትን ሻይ፣ ያነበብኳቸውን ጋዜጣና መፅሄት ሂሳብ ከፍዬ ከካፌው ወጣን፡፡

ካፌውን ለቀን ከወጣን በኋላ በተዘጋጀው የደህንነት መኪና ውስጥ ገባንና በፖሊስ ታጅቤ ወደ መኖሪያ ቤቴ አቀናን፡፡ ስንደርስ የመኖሪያ አካባቢዬ፣ መውጫ፣ መግቢያው በፌደራል ፖሊስ ተከብቧል፡፡ የደህንነት ሰዎች ካሜራቸውን እስኪያስተካክሉ ድረስ እኔ መኪናው ውስጥ ቆይ ተብያለሁ፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ ደህንነቶችም ካሜራቸውን አስተካከሉና እኔም እየተቀረፅኩ ወደ ቤቴ እንድገባ ተደረገ፡፡ ከነበሩት የደህንነትና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ከታጠቁት መሳሪያ አንፃር አንድ ግለሰብን የሚይዙ ሳይሆን አካባቢው ትልቅ የጦር ቀጠና ይመስል ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየው ስርዓቱ ያጋጠመውን የፍርሃት ደረጃ ነው፡፡ በመኖሪያ ቤቴ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡30 እያንዳንዱ ነገር ተፈተሸ፡፡ ያለምንም ማስረጃ ፍተሻው ተጠናቀቀ፡፡ በፍተሻው ወቅት ፖሊስና ደህንነቶች ያሳዩት የነበረው ብልሹ ስነምግባር የስርዓቱ አንድ አካል ስለሆነ ብዙም አልገረመኝም፡፡ ፍተሻው ከጠናቀቀ በኋላ ጉዞው ገዥዎች ኢትዮጵያውያንን በገዛ ሀገራቸው፣ በግፍ፣ አሰቃቂና ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ የሚያሰቃዩበትና በስውር የሚገድሉበት ማዕከላዊ እስር ቤት ሆነ፡፡ ማዕከላዊ ስንደርስ በተለምዶ ሳይቤሪያ ተብሎ የሚጠራው ጠባብ፣ ጨለማ እና ቀዝቃዛ የእስር ቤት ክፍል ተወረወርኩ፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ አቶ ዳንኤል ሺበሽ እና ከተለያዩ ክልሎች ለቃቅመው ያሰሯቸው ሌሎች ስድስት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡

ከሁለት ቀን በኋላ እኔና በእኔ መዝገብ የተከሰሰው መምህር ተስፋዬ ተፈሪ በአራዳ ምድብ ችሎት ቀረብን፡፡ የእለቱ “ዳኛ” ክሱን “እራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ፀረ ሰላምና ፀረ ህዝብ አሸባሪ ቡድን አባልና አመራር በመሆን፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍሎች አባላትን በመመልመል፣ በማደራጀት፣ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫን ለማደናቀፍ፣ አመፅና ሁከት በመቀስቀስ ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ ሆን ብሎ የሽብር ቡድኑን አመራር በመቀበል . . .” ወዘተ የሚል ነበር ያነበበችው፡፡

ከፍርድ ቤት መልስ ወደ ምርመራ ክፍል ተጠርቼ በሀይል የኢሜል ሚስጥር ቁልፎቼን ተቀበሉኝ፡፡ ማታም ከምሽቱ 2፡30 ወደ ምርመራ ክፍል ተጠራሁ፡፡ በምርመራው ወቅት የነበረው ድብደባ እና ክብረ ነክ ስድብ ወደ ምድር የመጣሁበትን ቀን እንድረግም አደረጉኝ፡፡ በተለይ ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል እየዛቱ የውስጥ እግሬን ክፉኛ ገረፉኝ፡፡ ከምሽቱ 2፡30 የጀመረው ድብደባና “ምርመራ” እስከ ሌሊቱ 8፡00 ድረስ ቆይቶ ወደ ጨለማውና ቀዝቃዛው የማጎሪያ ክፍሌ መለሱኝ፡፡

በማግስቱ ከቀኑ 8፡00 አካባቢ እንደገና ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰድኩ፡፡ አንድ እድሜው በግምት በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኝ የደህንነት አባል “የኋላ ታሪክህን ከስር ከመሰረቱ አስረዳ!” ብሎ በቁጣ ትዕዛዝ አይሉት ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ የህይወት ታሪኬን በዝርዝር አስረዳሁት፡፡ ከአሁን በኋላ የሚመረምረኝ እሱ መሆኑን ከገለጸልኝ በኋላ “የትናንትናው ሌሊት ምርመራ እንዴት ነበር?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም ምርመራው ምን ይመስል እንደነበር ጥያቄውን በጥያቄ ጀመርኩለት፡፡ “የሰው ልጅ፣ ያውም ወገን እንዴት እንዲህ ይደበደባል?”፣ “አልተማራችሁም እንዴ?”፣ “ፎረንሲክ ሰልጣኞቹ የሉም እንዴ?” እና መሰል ጥያቄዎቹን በመጠየቅ የደረሰብኝን ኢ-ሰብአዊና ዘግናኝ ደብደባ እያስረዳሁት እያለ በድንገት “በቃ!” ብሎ ጠረጼዛውን በመደብደብ አስቆመኝ፡፡ እሱም ምርመራው ገና እንዳልተጀመረና በምርመራው ሂደትም አካሌን ብቻ ሳይሆን ህይወቴንም ላጣ እንደምችል የ”መርማሪነቱን” ካስፈራራኝ በኋላ ወደ ክፍሌ መለሰኝ፡፡

በዚህ ቀን ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ የጀመረው አሰቃቂ ድብደባና “ምርመራ” በግምት ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ተጠናቀቀ፡፡ ከአንድ ቀን በፊት ከነበረው የባሰና ጭካኔ የተሞላበት ነበር፡፡ በተለይ ለሁለተኛ ጊዜ የተገረፈው የውስጥ እግሬ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ከዚህ “ምርመራ›› በኋላ እንደተረዳሁት በቀኑ ምርመራ ወቅት “ፎረንሲክ ሰልጣኞች የሉም እንዴ?” ብዬ ያቀረብኩት ጥያቄ የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ ምክንያቱም ማታ “ለመሆኑ የእኛን የትምህርት ደረጃ የት ታውቃለህ?” እያሉ ነበር ያሰቃዩኝ፡፡

ከሶስት ቀን በኋላ ወደተለመደው የ”ምርመራ” ክፍል ተጠርቼ ተመሳሳይ ጥያቄና ዱላ አስተናገድኩ፡፡ ይህኛው ካለፉት ቀናት የሚለየው በእረፍት ቀን መሆኑ ነው፡፡ በጣም የገረመኝ ነገር ቢኖር ክብሩን የሰው ልጅ ለማሰቃየት ሙሉ የእረፍት ጊዜያቸውንም በመግረፍ የሚያሳልፉ መሆናቸው ነው፡፡ ሰኞ እለት በግምት ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰድኩ፡፡ ምርመራው በተለመዱ ጥያቄዎችና ዱላ ተጀመረ፡፡ በድብደባው ወቅት ከመርማሪዎች አፍ በሚወጣው የአልኮል ጠረን መርማሪዎቹ ሞቅ እንዳላቸው ተረድቻለሁ፡፡ የተወሰነ ከደበደቡኝ በኋላ ልብሴን እንዳወልቅ ትዕዛዝ ተሰጠኝ፡፡ እኔም ልብሴን እንደማላወልቅ ነገርኳቸው፡፡ በዚህም ከአሁን ቀደሙ ለየት ያለ ከባድ ድብደባ አስተናገድኩ፡፡ ድብደባው ከአቅሜ በላይ ሲሆን ግን ከውስጥ ሱሪዬ ውጭ ያለውን ልብሴን ለማውለቅ ተገደድኩ፡፡ የውስጥ ሱሪዬንም እንዳወልቅ አዘዙኝ፡፡

“አላወልቅም” አልኩ

“ለምን?” አሉኝ፡፡

“ኃይማኖታችን፣ ባህላችን፣ የአባቶቻችን ስርዓት የሰው ልጅ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እንዲቀጣ አይፈቅድም” አልኳቸው፡፡ አሁንም አልተሳካልኝም፡፡ ከፍተኛ ድብደባ፣ ከዚህም በላይ በጣም ክብረ ነክ የሆኑ ስድቦችን ሰደቡኝ፡፡ ከዚህ የማሰቃያ ክፍል ስመለስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዮሴፍን ታሪክ በማንበብ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ያች ቀን በዚህ መልኩ አለፈች፡፡

አርብ ሐምሌ 18/2006 ዓ.ም የገብርኤል ዋዜማ ከቀጨኔ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አመታዊ ክብረ በዓል በእልልታ ደምቋል፡፡ የዕጣኑ መዓዛ አልደረሰንም እንጅ ዝማሬው በደንብ ይሰማን ነበር፡፡ በዚህ ምሽት ያለ ወትሮው “ምርመራ” የተጀመረው ከሌሊቱ 5፡00 ገደማ ላይ ነበር፡፡ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ የምግብ ፍላጎቴ በጣም ወርዷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየጊዜው የሚፈፀምብኝ ድብደባና ሞራላዊ በደሎች ተጨምረው የዚህን ቀን ድምደባ መቋቋም አቅቶኝ ራሴን ስቼ እንደወደኩ አስታውሳለሁ፡፡

ቅዳሜንና እሁድን ከማዕከላዊ ምርመራ አንጻር በ”ሰላም” አሳልፌ ሰኞ ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰድኩ፡፡ “መርማሪው” ደስታ ይባላል፡፡ ከእሱ በፊት ከፍተኛ አመራርነት ላይ ያሉት የደህንነት አባላት መርምረውኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ለእሱ አሳልፈው የሰጡኝ፡፡ “መርማሪ” ተብዬው ደስታ ማዕከላዊ ከገባሁ ጀምሮ ግቢው ውስጥ አይቼው ከማላውቀው ሌላ የደህንነት አባል ጋር ሆኖ ጠበቀኝ፡፡ ወደ ክፍሉ እንደገባሁ እንግዳው የደህንነት አባል “የሽብር ቡድኑ አላማ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ፡፡ እኔም “እኔኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በኢትዮጵያ ባህልና ወግ ተኮትኩቼ ያደኩ፡፡ እኔ አሸባሪ ከሆንኩ የሚሸበረው የየት ሀገር ዜጋ ነው?” ብዬ ስመልስለት “መርማሪው” ደስታ ንግግሬን በድብደባ አስቆመኝ፡፡ እንግዳው ደህንነት እንደሚገድለኝ ከዛተብኝ በኋላም ወደ ጨለማና ቀዝቃዛው ክፍሌ ተመለስኩ፡፡ ያም ሆኖ እኔ ላይ የደረሰው በደልና ግፍ በዚህ የማሰቃያ ክፍል ስቃይ ከሚደርስባቸው ሌሎች ኢትዮጵያውያን አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ ግን ደግሞ ማዕከላዊ ከሚገኙት ጨካኝ ገራፊዎች መካከል ምን ላርግልህ፣ ምህረት፣ ደስታ፣ … የተባሉና ሌሎችም ስማቸውን የማላውቃቸው በየ ተራ “ጥሩ” ገራፊነታቸውን ሞክረውብኛል፡፡

በማዕከላዊ ቆይታዬ የገረመኝ ነገር ቢኖር መርማሪዎች በሙሉ በትዕዛዝ የተሰፉ እስኪመስሉ ድረስ ተመሳሳይ መሆናቸው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቅምና የብቃት ማነስ ችግር ሁሉንም ያመሳስላቸዋል፡፡ ሁሌም ከአፋቸው የማትጠፋ “ተናገር!” የምትል ቃል አለች፡፡ ምን እንደሚናገር ባያውቀውም በእሱ እጅ የሚገኝ ማንኛውም እስረኛ መናገር አለበት፡፡ ያው በቁጣ “ዝም በል!” የምትል ከመርማሪዎቹ የማትጠፋ ሌላ ቃል እስከሚነገረው ድረስ፡፡ “እንዳያልፉት የለም፣ ያ ሁሉ ታለፈ” እንዳለው ብአዴን ይህ ሁሉ በደልና ግፍ አልፈን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከተዘዋወርን በኋላም ምንም እንኳ የማዕከላዊ ድብደባ ባይኖርም የችሎቱ ድብደባ ከማዕከላዊ ባልተናነሰ መልኩ ሲያሸማቅቀን እና ሲያመላልሰን ይኸው እንደቀልድ ሐምሌ 5/2007 አንድ አመት ሊሆነን ነው፡፡ ዛሬ በቂልንጦ እስር ቤት ሆኜም ብዙ ነገሮች ያሳስቡኛል፡፡ ሀገሬ በአምባገነኖች ስር ሆና፣ ዜጎች በጨካኝና ዘግናኝ ድብደባ እየተሰቃዩ እስከ መቼ እንቀጥላለን? በንፁሃን ዜጎች ላይ “አሸባሪ” የሚል ክስ እየተለጠፈ እስከ መቼ ይሰቃያሉ? በእስር ቤት ከደረሰብኝና እየደረሰብኝ ከሚገኘው ስቃይ ይልቅ ለውጥ! ለውጥ! ለውጥ! ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት! የሚል ድምፅ ይሰማኛል፡፡ እውነት ይህን ድምፅ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምድር እውን ሆኖ እናየው ይሆን?

ገራፊዎቻችና አሰቃዮቻችን ሆይ!

ያደረጋችሁብን ሁሉ ፅናታቸውንና የሀገር ፍቅራችን ይበልጡን አጠናከረው እንጅ ቅንጣት ታክል አልቀነሰብንም፡፡ ግን ለራሳችሁ ስትሉ ግፍና ሰቆቃውን ባታበዙት ይሻላል፡፡ እደግመዋለሁ! ለራሳችሁ ስትሉ ጉድጓዱን አርቃችሁ አትቆፍሩት፡፡ እኛ መከራውንና ግፍን በፅናት የምንቀበለው እናንተን ወደ ትልቅ ጉድጓድ ገፍትረን ነፃ ለመውጣት ሳይሆን በጋራ፣ እኛም፣ እናንተም አብረን ነፃ እንወጣ ዘንድ ነውና! (ፎቶ: ለማሳያ ከኢንተርኔት የተገኘ)

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

(ከባህሩ ደጉ፤ ቂሊንጦ እስር ቤት ለነገረ ኢትዮጵያ የተላከ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Rss Dejen says

    July 8, 2015 08:35 pm at 8:35 pm

    America and its allies are responsible for the horrors of Ethiopia in the post cold war era. Pres. Obama, can you try to make your leadership more human instead of furthering the inhuman rather criminal scheme of your immediate predecessors? You are expected to be the most powerful and just man. And the land of Joseph Kennedy should remain free and just world. You are brilliant person but trapped to operate otherwise to your wills and enthusiasms.
    Sir, why are you becoming a human machine singing/acting the schemes of the Regan/Bush era’s. In the post cold war era, America is simply a set of states where all peoples of the world live in a state of absolute obedience due to illusions of all facets (human, economic, environmental, etc). Why is America the bloodiest country since the 1980s?
    Your plan to visit the land of the authentic sovereigns, Ethiopia, portrays the vivid fact that Ethiopia/Ethiopians have lost their heritages of sovereignty and authenticity. Your visit to ET is a disgrace because you are leader of the bloody neocolonial America.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule