• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ” ላይ የተቃጣው ሴራ ከሸፈ

August 5, 2015 12:05 am by Editor 3 Comments

ሳውዲ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የትግል አንድነት ላይ የተቃጣው የህወሃት/ኢህአዴግ ሴራ መክሸፉ ተሰማ! ከዕርዳታ አሰባሰብ ጋርም በተያያዘ የተፈጸመው ተግባር ለሕዝብ ይፋ ሆኗል፡፡

የህወሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች መቀመጫቸውን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ካደረጉ ወዲህ የህዝበ ሙስሊም እንቅስቃሴ ለማፈን የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ከአካባቢው የመንግስት ሹማምንቶች  ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር ይታወቃል። እነዚህ ምስለኔዎች ለአገዛዙ ባላቸው ታማኝነት ከጅዳ እስከ ሪያድ  በዘለቀ የስለላ መረባቸው በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በሚያደርገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉ ሙስሊም ወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር ለኢህአዴግ በማቅረብ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ከነፍሳቸው ይልቅ ለጥቅም ያደሩ መሆናቸውን አያሌ የእምነቱ ተከታዮች ይገልጻሉ፡፡

በተለይ እነዚህ ተላላኪዎች ባላቸው መጠነኛ ሃይማኖታዊ እውቀት ጥቂት የእምነቱን ተከታይ የሆኑ ወንድምና እህቶቻቸውን በማሳሳት ለዚሁ መንግስታዊ ሴራ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ግብዓት አድገዋቸዋል፡፡ ከህወሃት/ኢህአዴግ ስርዓት በሚወርድላቸው በጀት ጡንቻቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየፈረጠመ የመጣው ምስለኔዎች የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በመበታተን በሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትግል አንድነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር መቻላቸው በጌቶቻቸው ዘንድ ምስጋና ሲቸራቸው በአንጻሩ በህዝብ እየተተፉ የመምጣታቸው ምስጢር የነዚህ ተላላኪዎች ማንነት እርቃኑን አስቀርቶታል።

በተለይ እነዚህ ወገኖች  በኃይማኖት ሽፋን ዘረፋ ላይ መሰማራታቸውን የሚገልጹ ምንጮች ጅድና ሪያድ ጨምሮ በተለያዩ የሳውዲ ግዛቶች ውስጥ “ጽናት” ብለው ባደራጁት ስብስብ በመታገዝ የአባላት መዋጮ፤ ልዩ መዋጮ፤ ለታሰሩ የትግል አጋሮቻችን ቤተሰብ ድጎማ ወዘተ በሚል ምክንያት እስከ 300.000 ሪያል ወይም ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ያለደረሰኝ ከህዝበ ሙስሊሙ ኪስ በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም በግፈኞች ወህኒ እየማቀቁ የሚገኙ  ዑስቷዝ ያሲን ኑር ዒሳ፤ አህመዲን ጀበል በቅርቡ ከወህኒ ቤት “ፈርዖን የአምባገነኖች ተምሳሌት፤ የህይወት ግብህን ቅረጽ” በሚል ርዕስ የጻፉትን ጽሁፍ ዘርፈው በማሳተም ከመጽሀፉ ሽያጭ የተገኘውን በሚሊዮን የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸውና ለዚሁ ኢህአዴጋዊ ድብቅ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ማዋላቸው በአብዛኛው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ዘንድ ቁጣን አስነስቷል።

ከዚህ ባሻገር ይህ በኃይማኖት ሽፋን ዜጎቻችን ላይየሚፈጸመው ምዝበራ በተለይ ሳውዲ በሚኖሩ ሙስሊም ሴት እህቶቻችን ላይ ያነጣጠር መሆኑን የሚናገሩ ምንጮች ለዚህ ተግባር ማስፈጸሚያ ጅዳ፤ ጣይፍ እና መካ ከተሞች ውስጥ እስከ 150 የሚሆኑ የተለያዩ  የዎትሳፕ “whatsApp” ግሩፕ እንዳሏቸውና እያንዳንዱ ቡድን ወርሃዊ  መዋጮ የሚከፍሉ ከ50 በላይ ሴት እህቶቻችንን በአባልነት ማቀፉን ያስረዳሉ። ይህ እራሱን “ጽናት” እያለ የሚጠራው የካድሬዎች ስብስብ ሪያድ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ከ70 በላይ የዎትሳፕ “whatsApp” ግሩፕ እንዳሉት ቢነገርም ሪያድ የሚገኙት “የጽናት” ኃላፊዎች  ከእህቶቻችን ቦርሳ  ህገወጥ በሆነ መንገድ ለወራት ሲሰበስቡ የከረሙትን  ከ80.000 ሺህ ሪያል አሊያም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ጥሬ ገንዘብ ጅዳ ለሚገኙት የአገዛዙ ታማኞች ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በተፈጠረ አለመግባባት በተከሰተ ግጭት እስካሁን  ከሁለቱም ወገን የተጎዳ ባይኖርም የህወሃት/ኢህአዴግ ስርአት ስውር ደባ መክሸፉን የሚናገሩ ምንጮች  በሳውዲ አረቢያ “ድምጻችን ይሰማ” የነጻነት ትግል እንቅስቃሴ ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ መሰንበቱን አልሸሸጉም።

ይህን ተከትሎ በሙስሊሙ የትግል አንድነት ላይ የተቃጣውን ስውር ደባ ሕዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን ጠብቆ ህወሃት/ኢህአዴግ ላይ የጀመረውን ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄ  አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ “ድምጻችን ይሰማ” ሪያድ ከተማ ላይ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱን ፍትሕ ራዲዮ ካሰራጨው ዘገባ መረዳት ተችሏል። በዚህ ዙሪያ ጅዳ የሚገኘውን “የጽናት” ሃላፊ ሼክ መሃመድ ዘይን ዘህረዲን የዝግጅት ክፍላችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። (ለጎልጉል፡- ኢንጅነር መሃመድ አባስ ሪያድ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. ሃጂ ኢብራሂም ሙሃመድ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ says

    August 6, 2015 11:31 am at 11:31 am

    በቅድሚያ የማክበር ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ከዚህ በላይ ያስቀመጣችሁት መረጃ ትክክለኛና በአሁኑ ሰዓት በአካባቢያችን እይተፈፀመና እየሆነ ነገር ነው ። ይህን እውነታ እዚህ ለዚህ ገጽ በማብቃታችሁ አሏህ ጀዛችሁን « ምንዳውን » ይክፈላችሁ አዎ ህዝብ የማወቅ መብት አለው ! የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያውቀው የትግላችን መሪዎች ከሚያውቁት « ድምጻችን ይሰማ » ባሻገር በየአካባቢው በዚህ ሰላማዊ ትግል ሽፋን የሚፈፀመው ዘረፋና በትግላችን አንድነት ላይ እያሳደረ የመጣው ተጽኖ ከወዲሁ ፈር ለማስያዝ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም አባቶቻችን ላለፉት 9 ወራት ጉዳዩ አደባባይ እንዳይወጣ ተብሎ ምናላባት የዚህ ድርጀት መስራቾችን « ጽናት» ለመምከር ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የህዘበ ሙስሊሙ የትግል አንድነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ሲገስጹ እንደነበር አውቃለሁ ። ይህ ምከርና ለማጋባት የተደረገው ጥረት ከድርጀቱ « ጽናት » ከግዜ ወደ ግዜ እይተደራጀ አቅም እያገኘ መምጣት ጋር ተዳምሮ ይህ ድርጀት በገንዘብ የሚያሳስተውን አሳስቶ በሰው ሃይል ከጠነከረ በኃላ በውጭ የሚገኙ አንዳንድ የሙስሊም ሚዲያዎችን ዓላም መጠምዘዝ እስከመቻል ርቆ የሄደብት ድርጊት ሳውዲ አረቢያ በምንገኝ የእምነቱ ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። በዚህ ብቻ ያልተገደበው ይህ እራሱን ጽናት እያለ የሚጠራው ቡድን ጸሃፊው በመረጃ አስደግፈው ለዝግጀት ክፍላችሁ እንዳቀረቡት በዋትሰብ ሴት እህቶቻችንን በማደራጀት አሉ የተባሉትን የአካባቢያችን የሃይማኖት አባቶች ሃይማኖታዊ ትምህረት በመልቀቅ በማሰማት እህቶቻችን ለኃይማኖታቸው ያላቸውን ቁርጠኝ ነት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ወራሃዊ የገንዘብ መዋጮ እንደሚሰበስቡ ከባለቤቴ እህቶች አረጋግጫለሁ ። እኔም የወትሰብ አባል እንደመሆኔ መጠን ይህ አካሄድ የህዝበ ሙስሊሙን ትግል እንደ ሚጓዳ ጠንከር ያለ ሃሳብ በመስጠቴ ከጉሩፑ እንድወጣ ብደረግም ጉዳዩን በባበለቤቴ እህቶች በኩል ስለሚደርሰኝ ከማዳመጥ ውጭ ምንም አቅም አለነበረኝም። አዎ ከእህቶቻችን ኪስ ያለደረሰኝ የሚሰበሰበው ሪያል በሚልዮን ይቆጠራል ። እንዚህ ግለሰቦች እየሰሩ ያለው ድርጊት በኢትዮጵያውያን በህዘብ ሙስሊም የነጻነት ትግል ላይ አደጋ ጋርጧል። ይህ ብቻ አይደለም በተለይ ሪያድ ውስጥ ያለው ጽናት እያለ እራሱን የሚጠራው ድርጀት በገንዘብ የተነሳ ለሁለት ተከፍሎ እርስ እንካ ሰልንቲያ የጀመሩበት አጋጣሚ እነዛ ጉዳዩን ላለፉት 9 ወር ሲያስታምሙ ለነበሩ የህዝበ ሙስሊሙ አባቶች እራስ ምታት ሆኖባቸዋል። በሃይማኖት ሽፋን ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተጀመረው ዘረፋ በአሁኑ ሰዓት ቅጣ አጥቷል። ለዚህም ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ የሆነባቸው የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች ተግስታቸው በማለቁ እንዚህን ወገኖች ህይ ሊሉ የሚችሉበት አቅም ስለሌላቸው ቀኑን በትክክል አላስታውሰም ህዝብን ሰብስበው በነዚህ ወገኖች « ጽናቶች »ዘረፋና ክፍፍል ህዝብ ሰለባ እንዳይሆን አስጥንቅቀዋል። አዎ ነገሩ የአዞውን ምስሌ እንዳመጣ ግድ አለኝ « አዞ በተፈጥሮ ያገኘውን ነገር ሲበላ ያነባል ወይም ያለቅሳል » አሁን ጽናቶች የኛን መፈከር እያጮሁ እኛ የምንለውን እያሉ በታሰሩ የህዝበ ሙስሊሙ ተወካዩች እየማሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እታገልለታለሁ ከሚለው ሃይማኖታዊ ነጻነት ያፈነገጠ ስራ እየሰሩ እኛ ትክክል ነን ማለታቸው ያሳዝናል ። ካፈርኩ አይነት ነውረኛ አስተሳሰባቸውን ፊስ ቡክ ላይ በለጠፎቸው ደሃ ወገኖቻችን ስም ለመንገድ መሞከራቸው በህግ ብቻ ሳይሆን በአሏህ ዘንድ ያስጠይቃል። ጎልጉሎች የናንተ ማንነት መለኬያ ጥቀም ሳይሆን ህዝብ ነው ። ለጥቂቶች ማስፈራሪያ ስተሽበረኩ « ህዝብ የማወቅ መብት አለው የሚለውን ሰበአዊ መብት » በመተግበራችሁ በትክክለም ነጻ ሚዲያዎች ናችሁ ። እንንተ ውሸትሞች እያሉ የሚናገሩት እራሳቸው ህዝበ ሙስሊሙን « ጽናት » በሚል ድርጀት መከፋፈላቸውን ከዚህም በላይ በዚህ ድርጀት ስም ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸውን በራሳቸው አንደበት መረጃ እየሆኑ ናቸው ። ታዲያ ውሸታሙ ማነው ? ጎልጉል ወይስ ሃፍረታችን አደባባይ ወጣ ብለው በአንድ ሰው ስም 50 የፌስ ቡክ ገጽ ከፍተው እሳላምዊ ደንብና ስረአት በራቀው አንደበታቸው የሚሳደቡ የጽናት ሃላፊዎች ከልብ አዝናለሁ ። ሙስሊም ጨዋ ነው አይሳደብም ይህ ጨዋነታችን በትግስት አንዲት ጠጠር እንኳን ሳንወረውር ምንም አይነት ህይወትና ንብረት ሳይጠፋ እየሞትን ለኢ.አ.ዴ.ግ ስረዓት ሰላማዊ ታጋይነታችንን አስይተነዋል። ይህ ባህላችን ዛሬ ከኛ አፈንግጠው በሃይማኖት ሽፋን ሊከፋፍሉን ከሚሞከሩና ሃብትንብረታችንን ሰብስበው በአቋራጭ ለመክበር እየተራወጡ ካሉ የጽናት መሪዎች ባሻገር ድምጻችን ይሰማን የምንከተል እውነተና የትግሉ አጋሮች እስላማዊ ባህሪያችን አንደበታችን ህያው ነው ። ጎልጉሎች ከኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም ጎን ቆማችሁ እየከፈላችሁ ላለው ማናቸውም መስወአትነት ሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ ስም ክልብ አመሰግናለሁ ። ከዚህ ባሻገር መረጃው በህዝብ ዘንድ ታአማኒነት አጊቶ በመነበበ ላይ በመሆኑ ሊንክ ካደረጉት ወገኖች ብዛት ማረጋገጥ ችያለሁ ታዲያ ፀሃፊው እንዳለው ለጥቂት ጡንጫቸው በግንዘብ በፈረጠመ ከፋፍዮች ሳትሸበሩ የጋዜጥኝነት ጻናትችሁን ማሳየት ይጠበቅባችኃል። ድል ለናነትና ለእውነተኛ ሚዲያ ወገኖች ሃጂ ኢብራሂም ሙሃመድ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

    Reply
    • Mohammed seicko says

      August 8, 2015 06:08 pm at 6:08 pm

      @haji ibrahim mohammed,Ye ehadig abalma ante neh,bemn endawekubh tawqaleh were abezah,weregna ,wushetam, mgnotachuh mechem aysakam

      Reply
  2. ህሉፍ says

    August 8, 2015 04:46 pm at 4:46 pm

    የዚህ ተዋናይ ወያኔዎች ናቸው በሀይማኖት ጣልቃ ገብተው የሚፈተፍቱት

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule