
“ርኢኩ ታህተ ምስዋዕ ነፍሶሙ ለእለ ተቀትሉ በእንተ ቃለ እግዚአብሔር ወበእንተ ዘአቀቡ ህጎ። ወጸርሁ በቃል ዓቢይ ወይቤሉ እስከ ማእዜኑ እግዚኦ ቅድስ ወጻድቅ፤ ኢትትቤቀሎሙኑ ወኢትኴንኖሙኑ በእንተ ደምነ እምእለ ይነብሩ ዲበ ምድር”
“ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” እያሉ ከመሰዊያ በታች ሆነው የታረዱት ነፍሳት በታላቅ ድምጽ ሲጮኹ አየኌቸው (ራዕ 6፡9-10)።
ዓለም በግልጽ ያያቸው በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በየደረሱበት የታረዱትን ብቻ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በውስጥም የተገደሉትን ሁሉ የኢትዮጵዮውያ ነፍሳት ሲጮሁ ማየት አለብን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን(ገአረ ኢየሱስ በህማሙ። ወጸርሀ ኀበ አቡሁ. . . ወእንዘ ሀሎ ህየ ጸርሀ ሀበ አዳም ገብሩ፤ ወሀበ ኩሎሙ ደቂቁ(ሰለስቱ ምእት ገጽ 205፡97-99)የሚለውን አንድም ብላ እንዳስተማረችን፤ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሳለ ጮኸ። በአምላክነቱ ለባህርይ አባቱ፤ በሰባዊነቱ ደግሞ ለባህርይ አባቱ ለአዳምና ለወገኖቹ ለደቂቀ አዳም አሰማ። ይህ ድምጽ ለሚድኑት ምልጃና ድህነት ሲሆን፤ ጩኸቱን ሰምተው ለማይድኑት ግን መፈራረጃ ነው። በማይድኑት ላይ የተነጣጠረው ይህ የክርስቶስ ጩኸት መፈራረጃ እንደሆነ፤ የታረዱትን የነዚህን ነፍሳት ጩኸት በመስማት፣ በመንቃት፤ ነቅተንም እንዲጮሁ ያደረጋቸውን ምክንያት ተረድተን፤ ተገቢውን ኃላፊነት በማንወስድ ሰዎች ላይ የሚመጣብንን ክስና ፍርድ ያሳያል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply