• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ፎርሙላ

May 2, 2014 12:50 am by Editor Leave a Comment

ፎርሙላ (ቀመር)

አንድ የጎሳ ፖለቲካ ማለት በመጀመርያ ቤተሰብህን የተለዩ ፍጥረት እንደሆኑ መስበክ መጀመር ማለት ነው። እነርሱ የተለዩ መሆናቸውን በደንብ ማሰብ ሲጀምሩልህ ደግሞ በመቀጠል የሰፈርህን እና የወንዝህን ሰዎች ልዩ መሆናቸውን በሚገባ መስበክ ነው። የሰፈርህን ሰዎች ልዩ እና የተለዩ መሆናቸውን ስትነግር ግን የአንተ ቤተሰብ ጋር እንደማይደርሱ ግን ደግሞ ከቤተሰብህ ዝቅ ባለ መልክ የተለዩ መሆናቸውን ወትውታቸው። በመጨረሻ አንተ የቤተሰብህም ሆነ የሰፈርህ ብቸኛ አለቃ መሆንህን ትነግራቸውና ከሰፈርህ ማዶ ያሉ ሰዎች ደግሞ እርኩስ፣ የተለዩ፣ ጥንትም አባቶችን ሲበድሉ እንደነበሩ የሆነ ያልሆነ ተረታ ተረት እየነገርክ ተራራ የሚያህል ጥላቻ እንዲያድርባቸው አድርግ።

ፎርሙላ (ቀመር) ሁለት 

ከእዚህ በኃላ በሰፈርህ ሰዎች እና ማዶ ባሉ ሰፈር ሰዎች መካከል በአንተ የጦር አበጋዝነት ጦርነት እንዲከፈት አድርግ። ጦርነቱን ልትከፍት ስትል ትልቅ ችግር ሊገጥምህ ይችላል። ለምሳሌ ለዘመናት በክፉም  ሆነ በደግ አብረው የኖሩ ሰዎች ናቸው እና ከአንተ ሰፈርም ሆነ ከማዶ ሰፈር ያሉ የበሰሉ ሽማግሌዎች ወይንም አስታራቂዎች ነገሩን እንዳያበርዱብህ ተጠንቀቅ። ”የፍቅር ዘመቻ” ብሎ በሰፈርህ መካከል ዘፈን ልዝፈን፣ ፍቅርን ልዝራ፣ ብሎ የሚነሳ ሀገር የወደደው ዘፋኝ ካለ ቀድመህ በቻልከው ነገር በማማሰያም ሆነ በብረት ምጣድ ደብድበህ አባረው። የስም ማጥፋት ናዳ ልቀቅበት። ዘፋኝ እና የሃይማኖት ሰዎች አንድ ናቸው። ሁለቱም ዓለም አንድ ነው፣ ምናምን እያሉ አላማህን ያደናቅፉብሃል። ‘ቀንድ ቀንዳቸውን’ በላቸው። ከሃይማኖት በፍቅር የተሰበሰቡ ማሕበራት ካሉም እግር ከእግር እየተከታተልክ አድክማቸው። ከቻልክ ዝጋቸው።

የሃይማኖት እና የኪነት ሰዎች ብቻ አይደሉም የዓላማህ ጠላቶች ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ሁሉ ቀድመው የሰፈርህን ሰዎች ከማዶ ሰፈር ሰዎች ጋር አብረው እንዲኖሩ ሊሰብኩ ይችላሉ እና ፈጥነህ ከእየቤታቸው ፖሊስ ልከህ ልቀማቸው! ያዛቸው! ማዕከላዊ ወስደህ አጉራቸው! ነግሬሃለሁ ጉድህን ይዘከዝኩታል። በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር መካከል ልታጋጭ ያሰብከውን ጉድ ሁሉ ለሀገር ይነዙልሃል። ይህ ብቻ አይደለም ቤተሰብህ ከሰፈርህ ሰው የተለየ አለመሆኑን፣ አንተም በቤተሰብህ እና በሰፈርህ ሰዎች ላይ መንገስ እንደማይገባህ፣ ሌላ ‘በሰፈርህ እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል ልዩነት የለም በፍቅር እንኑር’ የሚል ሰው መንገስ አለበት ብለው ለሕዝቡ ይነግሩብሃል። እናም ፍጠን! እሰራቸው!ልክህን አሳያቸው!።

ፎርሙላ (ቀመር) ሶስት 

ይህንን ሁሉ ከጨረስክ በኃላ አንተ እና ቤተሰብህ ጥንቱንም የተለያችሁ ፍጥረቶች መሆናችሁን በተለይ አዲስ ለሚወለዱት ልጆች እየሰበክ በሰፈርህ ሰዎች እና በማዶ ሰፈር ሰዎች መካከል  እረጋ ብለህ ቡናህን  እየጠጣህ ጦርነት እንዲከፈት ማዘዝ ትችላለህ። ተቀናቃኝህን ሁሉ እንደሆነ እስር ቤት ሰደሃቸዋል። የዘፋኙንም ስም ከማዶ ሰፈር ካሉ መሰሎችህ ጋር ሆነህ ስሙን አስጠፍተሃል። ከእዚህ በኃላ ማዶ ያሉ መሰሎችም ሆኑ አንተ አንድ አይነት ጫወታ ላይ ገባችሁ ማለት ነው። መንደር ከመንደር እየቆጠረ ህዝቡ ሲባላ እነርሱ በውስኪ አንተም በኮኛክህ መዝናናት ፈታ! ማለት ነው።

ፎርሙላ (ቀመር) አራት 

ጦርነቱ  ሲደረግ አንተ በሰፈርህ ሰዎች ላይ ንጉስ  ሆነህ ”ካለእርስዎ አመራር የት እንደርሳለን?” ስትባል ጀነን፣ ጎምለል ማለት ነው። አሁን ጥሩ ጊዜ መጣልህ የሀብት መጠንህ ይጨምራል። ምክንያቱም የሰፈርህንም ሆነ የማዶ ሰፈር ሰዎችን ገንዘብ ወደ ኪስህ እየከተትክ አለምህን መቅጨት ትችላለሃ!። በመካከል ታድያ ሥራ አትፍታ እዛኛው ማዶ የራሱ የሰፈሩን ሰዎች የመሰሉ ሰዎች ሰው እየላክ ”የእዝህኛው ሰፈር ሰዎች እናንተን ይጠላሉ ተጠንቀቁ!” ማለት ለእራስህም ሰፈር ሰዎች እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ጣል ማድረግ።ግጭቱ በደንብ አልጋጋልም  ካለህ ቀድሞ ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩ የአንተ ሰፈር ሰዎች ”የሰሩት ኃጢያት አለ” የሚል የሐሰት ታሪክ ማዶ ሰፈር ካለው መሰልህ ጋር በሚስጥር ተነጋግረህ  ”ማስታወሻ” በሚል ስም የቂም ሐውልቶችን በየሰፈሩ መደርደር በተለይ ሴቶች ስሜታቸው የሚነካ የሰውነት ክፍል ለምሳሌ ጡት እና ጣት የመሳሰሉ የሰውነት ክፍሎች ተቆርጠው ነበር ብለህ ሃውልት መስራት። ያኔ ወጪ ወራጁ ”ህም! ድሮ እንዲህ አድርገዋል አሉ” እያለ ከንፈር እንዲነክስ ማገዝ። አዎ ማገዝ።

ፎርሙላ (ቀመር) አምስት 

የሰፈርህ እና የማዶ ሰፈር ሰዎች አንድ መሆናቸውን ሊሰብኩ የሚነሱ ከመከከልህ ከተነሱ ወይንም ደግሞ የእዚህ አይነት አስተሳሰብ አላቸው የምትላቸውን ገልሰቦችም ሆነ የሃይማኖት ሰዎች ማኅበራት በሙሉ ተለጣፊ ስም መስጠት “አጎብዳጆች፣ አሸባሪዎች፣ የሰፈሬን ሰዎች ሰላም የሚያናጉ፣ ዥንጉርጉር አብዮት ሊያስነሱ ያቀዱ” እያልክ ማሰር እና መግደል።

መደምደምያ 

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እና በባህር ማዶ እና በሀገር ቤት በጎሳቸው ላይ እራሳቸውን ያነገሱ እና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጥላሉ ሁሉ ሲጠቀሙበት የሰነበቱት የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ  ይሄው ነው። ኢትዮጵያ በእናንተ ዘመን አልተፈጠረችም እንዴት እንደምትኖር ታውቅበታለች። ግዴላችሁም ይህች ሀገር አምላክ አላት። በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥላቻ ያደረበት ለጥላቻውም አስር ምክንያት ቢደረድር በመንግሥትነትም ሆነ በተቃዋሚነት ቢሰየም፣ የቂም ሐውልቶችን እንደ አሸን ቢያፈላም ሆነ በነፃነት ስም ከመቶ ዓመት በፊት ይህ ትውልድ ላልኖረበት ዘመን እየጠቀሰ ለስልጣን መወጣጫ ሊጠቀም ቢሞክርም  ከህዝብ ፍርድ አያመልጥም። አሁንም ግዴላችሁም ይህች ሀገር ጎሳ እና ብሔር የማያውቁ ለሰው ልጆች በሙሉ የሚፀልዩ ቅዱሳን እና የሚሰማቸው አምላክም አሏት። አሁንም ኢትዮጵያዊነት የጋራ መጠለያችን ነው። የጎሳ ፖለቲካ ፎርሙላ-ቀመራችሁ  ተነቅቶበታል።

ጉዳያችን

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule