• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአምባገነኖች ፀሐይ ጠልቃለች!

January 20, 2015 12:27 am by Editor Leave a Comment

በእኛ በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ለ23 ዓመታት ተመዝኖ ቀሎብናል – ይህ የጥቂት ሽፍታዎች ቡድን! የመንግስትነት ስም ሊመጥነው የማይችል የውንብድናና የማፍያ ተግባር በ’መንግስትነት’ ሽፋን ሲራመድም ቆይቷል – ላለፉት ሁለት አስርታት፡፡ ዛሬ፡- ይህን በገሃድ የሚታይ ጥሬ-ሀቅ ያልተገነዘበ አንድም ኢትዮጵያዊ አይገኝ፡፡

ይህንን የጥቂቶች “የምዝበራ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ” ለመሸፈን እና የተለየ ልባስ/ጭንብል ለማልበስ፤ እነዚህ መዝባሪዎች አያሌ ፎቆቻቸውን ከህዝብ በመዘበሩት የህዝብ አንጡራ-ሃብት አማካይነት ህዝብን ባፈናቀሉበትና ከቀዬው-በነቀሉበት በዚያው ስፍራ ላይ ለማቆም ችለዋል፡፡ ፎቆቻቸውን ያነፁት የእነርሱ-ዝርፊያ የሃገር-‘ልማት’ እንዲባልና በዚህም ሰፊው-ህዝብ ተደናግሮ ይህንን በአገር ላይ የሚሠራ “ጥፋት” በበጐ ጐኑ እንዲመለከተው ለማድረግ ነው፡፡

‘ልማት’ እና የዘር-ልዩነት ላይ ያተኰረ “የአፓርታይድ-ፌደራሊዝም” ም በግራና በቀኝ እግር ወደተለያየ አቅጣጫ ለመጓዝ የሚደረግ ዓይነት ከንቱ-መውተርተር መሆኑን በተግባር አይተናል፡፡ “አንቀጽ-39″ም በእኩልነት ላይ ወደተመሠረተ “አንድነት” ሳይሆን፤ በ”አድሎ”ና በተዛባ-መስፈሪያ ከተቃኘው የአሁኑ የብሔሮች-መበላለጥ አስከፊ ሁኔታ መውጫ/መለያያ በር ሆኗል፡፡ የመገንጠል – አሰፍሳፊነትም ከቀድሞው ጊዜ ይልቅ ዛሬ ላይ በርትቷል፡፡ ማንም በማንም መረገጫ – ስር መረገጥ አይፈልግምና!

ይህ “መዝባሪ-ቡድን” በነጋ በጠባ የሚምል የሚገዘትባቸው “ብሔር-ብሔረሰቦች” እኩል የሚሆኑት ህዳር-29 ብቻ ነው፡፡ ከህዳር 29 በስተቀር በቀሩት 364 (1/4ኛ) ቀናት እነዚህ ብሔሮች ወደዘመናዊው – እስር ቤታቸው ይገባሉና! የእስራት ሠንሰለታቸውም ‘አብዮታዊ-ዴሞክራሲ’ የሚባል ስውር የዕዝ-መዋቅር ነው፡፡ ከየብሔሮቹ የተውጣጡ ቱባ የጭቃ-ሹሞች ከሰሜን ጫፍ ወደደቡብ የሚንቆረቆረውን ቀጭን-ትዕዛዝ ተከትለው እንደ እንዝርት ይሾራሉ፡፡ ለቋንቋ ችሎታቸው ብቻ የተመለመሉት እኒህ ተላላኪና ጉዳይ-አስፈፃሚ የየክልል ጭቃ-ሹሞች በምንም ዓይነት መለኪያ የህዝባቸውን-ጥቅም እና ልዕልና ለማስከበር የሚችሉ አለመሆናቸውን ራሱ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ማወቅ ብቻም አይደል ንቋቸዋል፡፡ በህዝባቸው ዓይን ውስጥም ሚዛን የማይደፉ ቀሊል ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ይህን፡- በመሠረቱ የምዝበራ-ጥማት እና “የቁሳቁስ-ሰቀቀን” ያደረበት ገዢ-ቡድን ቅቡልነት /ተቀባይነት ለማላበስ፤ ላለፉት 23 ዓመታት ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም፡፡ “ደርግንና ጭቆናን ገረሰስኩ!” በሚለው ዲስኩር የትግራይን-ህዝብ ከጐኑ ለማሠለፍ በአፍላ-የሥልጣን ዘመኑ ብዙ ደክሟል፡፡ ቆየት አለና ደግሞ፡- ‘የሃይማኖቶች እኩልነትን አረጋገጥኩ!’ ሲል ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎችን የመደላደያ መሠረት ለማድረግ ረጅም ርቀት ተጓዘ፡፡ ከ1997ቱ ክፉኛ አወዳደቅ በኋላ ደግሞ፡- ‘በቃ እኔ የልማት-መንግስት ነኝ፤ ስለ ዴሞክራሲ አትጠይቁኝ’ አለና የልማት-ዝማሬውን ቀጠለ፡፡ በዴሞክራሲ-መድረክ ላይ፡- በብሔሮች እኩልነት፣ በሃይማኖት ነፃነት፣ በአገር ሉዓላዊነት በዜግነት መብት ወሳኝ-ነጥቦች ላይ ተፈትኖ የወደቀው ይህ “መዝባሪ-ቡድን”፤ በልማት መድረክም ላይ በማህበራዊ-ፍትህ፣ በገቢ ክፍፍል፣ በኢኮኖሚ-ብልጽግና፣ በመሠረታዊ-አቅርቦቶች ስርጭት፣ በመሬት ድልድል፣ በምርታማነትና በዜጐች ተጠቃሚነት ዙሪያ ዳግም ታላቅ-አወዳደቅ ወደቀ፡፡

ዛሬም የሞት-ሞቱን በአልሞት ባይ ተጋዳይነት መንቧቸር “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን”፣ “የህዳሴ-ጉዞ”፣ “የህዳሴ-ግድብ”፣ “ቀላል-ባቡር”፣ “ስኳር-ፋብሪካ”፣ “ቤቶች-ግንባታ”፣ “የመሠረተ-ልማት ዝርጋታ”፣ . . . እያለ በህዝብ ልብ ውስጥ ስፍራ ለማግኘት ይታትራል፡፡ ከሚለፍፈው ውስጥ 5%ቱን የተገበረ ሲሆን፤ 95%ቱን ደግሞ በተጣባው “የምዝበራ-ልክፍት” የተነሳ ወደ ወሮበላ-ቡድኑ መሪዎች የግል ኪስ ይሸኛል፡፡

እነዚህ ሁሉ ግዙፍ-ፕሮጀክቶች የግዙፍ-ምዝበራ ማካሄጃ ግንባሮች ናቸው፡፡ እነ ኤፈርት፣ መሰቦ፣ ጉና፣ ሜቴክ (መከላከያ-ኢንጂነሪንግ) እና ሌሎች በግለሰብ-ሎሌዎች ስም ጭምር የሚንቀሳቀሱ ኩባንያና ኢንዶውመንቶች የምዝበራ-መሣሪያዎች ሲሆኑ፤ በሚሊዮናት የሚቆጠሩ ምስኪን ወጣት-ኢትዮጵያውያን ግን በድንጋይ-ጠረባና በጥቃቅን የችርቻሮ ስራዎች ተሰማርተው ከእጅ-ወደ-አፍ ኑሯቸውን በመፃጉዕነት ይገፋሉ፡፡

ታዲያ ዛሬ፡- ከኢህአዴግ ጋር ያለው ማነው? ህዝብን በግዙፍ ተስፋ ለመደለል የሚሞክርበት ግዙፍ ቅጥፈቱና፤ የ”ላም አለኝ በሰማይ. . . ” ግዙፍ ፕሮጀክቶቹ አይደሉምን? ከዚህስ የተረፈው ግዑዝ ጠብ-መንጃ መታቀፍን የዕለት ስራው ያደረገው ምስኪን ወታደር አይደለምን?

እኔም እላለሁ፡- የ‘ስርዓቱ’ ምሰሶዎች በተናጉና ከውስጡ የሚከዱ ሰዎች በተበራከቱ ጊዜ . . . ያኔ ‘የስርዓቱ’ ጀንበር መጥለቋን አስተውሉ!

ስርዓት ያልፋል፤ አገርና ህዝብ ግን ፀንተው ይኖራሉ!

Aduun abbaa hirrootaa dhiitetti.
Galatoomaa!!!

(ምንጭ: ፍኖተ ነጻነት ፌስቡክ ገጽ)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule