• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቴድሮስ አድሃኖም “ኢህአዴግ ቂመኛ አይደለም” አሉ

August 3, 2015 12:26 pm by Editor 1 Comment

የኢህአዴግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም “ኢህአዴግ ቂመኛ አይደለም” ሲሉ ከቪኦኤ አማርኛው ክፍል ባልደረባ ትዝታ በላቸው ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስታወቁ። ሚኒስትሩ ድርጅታቸውን ከደርግ ጋር በማነጻጸር ከቂም የጸዳ እንደሆነ ሲያስረዱ ጋዜጠኛዋ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ በቂም በቀል ስለተፈጸመውና እየተፈጸመ ስላለው ግፍ ጥያቄ አላቀረበችም። ሚኒስትሩ ኢህአዴግ በህግ የበላይነት ስለማመኑ በመረጃ አልተሞገቱም።

በዘር፣ በብሄርና በጎሳ ላይ ተንጠልጥሎ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው ኢህአዴግ፣ በ፩፱፰፫ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በገሃድ አማርኛ ተናጋሪዎችን ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር በማናከስ፣ ቂም በማቋጠር፣ የስርአተ ማህበሮችን ችግሮች ከነፍጥ ጋር በማያያዝ እያላከከባቸው፣ “ነፍጠኛ” የሚል ስም በመስጠት የህዝብ ንብረት በሆነው መገናኛ የጥላቻ ዘመቻ በማራገብ የደረሰው ጥፋት ሰፊ ነው። የኢህአዴግ የቀድሞ አመራሮች በተለያዩ አጋጣሚዎቸ ይፋ እንዳደረጉት ይህንኑ አማርኛ ተናጋሪ የህብረተሰብ ክፍል ለይቶ የማጥፋትና የማጥቃት እቅድ በፕሮግራም ደረጃ የተቀመጠ ነው።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ለኅልፈት የተዳረጉት “አማራው ተሟጋች አጣ” በሚል ስለ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። በቂም ተወልዶ፣ በቂም እዚህ የደረሰው ኢህአዴግ ከዚህ ከማይደበቀው ታሪኩ ፊት ለፊት ቆሞ “እንዴት ቂመኛ አይደለሁም ሊል ይቻለዋል” የሚሉ ወገኖች ቴድሮስ አድሃኖምን ለመታዘብ ጊዜ አልወሰዱም።

“ደርግ ያለ ርህራሄ ፷ ሚንስትሮችን ረሸነ፣ የውሻ ያህል እንኳን ክብር አልሰጣቸውም” እያሉ የሰው ልጅ ክቡርነትን በመጥቀስ ቂም ኢህአዴግ ቤት እንደሌለ ለትዝታ በላቸው ያስረዱት የኢህአዴግ ሹመኛ፣ “ኢህአዴግ በመሆኔ ደስ የሚልኝ ቂመኛ ድርጅት ባለመሆኑ ነው” ሲሉ ተመጻድቀዋል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከተማ ሽርሽር እንደሚወጡና የአዳማን ልማት ተመልክተው መደሰታቸውን የጠቆሙት ቴድሮስ ይህ ሁሉ ኢህአዴግ ቂመኛ ድርጅት ላለመሆኑ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ አንዳርጋቸው ላብቶፕ ተሰጥቷቸው መጽሃፍ ጽፈው ወደማጠናቀቁ መዳረሳቸውን እግረመንገዳቸውን ጠቁመው ያለፉት ቴድሮስ፣ ይህ ሁሉ የፓርቲያቸውን ርኅሩኅነት የሚያሳይ መሆኑን አመላክተዋል። በሌሉበት የሞት ፍርድ የተበየነባቸው አቶ አንዳርጋቸው ይቅርታ የመጠየቅ መብት አላቸው፣ ግን ምን ሊሆን እንደሚችል አላውቀም ብለዋል። በቤተሰብና በጠበቃ ለመጎብኘት ፈቃድ መከልከሉን አስመልክቶ “ትንሽ የሚጠየቃቸው ጥያቄዎች ሰለነበሩ ነው” ሲሉ አቃልለው መልስ ሰጥተዋል። አሁን ወደ መደበኛ ማረሚያ ቤት በመዘዋወራቸው ሁሉም ነገር እንደሚመቻች ገልጸዋል።

ከሰኔ፩፮ ቀን ፳፩፮ ጀምሮ ባልታወቀ ስፍራ ታስረው የቆዩት አቶ አንዳርጋችው ጽፈውታል የተባለውና በቅርቡ ለንባብ ይበቃል የተባለው መጽሃፍ “ስልጣን ላይ ያለው አካል በአቶ አንዳርጋቸው ስም ያዘጋጀው ነው” ሲል ኢሳት ይፋ ያላደረጋቸውን ምንጮች ጠቅሶ አመልክቷል። ኢሳት እንዳለው በመጽሃፉ ዝግጅት ላይ ህላዊ ዮሴፍ፣ በረከት ስምዖን፣ አባይ ጸሃዬ እንደተሳተፉበት አመላክቷል። የመጽሃፉ ይዘት በኤርትራ ያለውን ትግል የማንኳሰስና የግንቦት ሰባት አመራሮች ስብእና ላይ ያተኮር መሆኑንም አስታውቋል።

እሳቸው ብቻ ተናጋሪ በሆኑበት ቃለ ምልልስ ሚኒስትሩ አስቂኝ ትንተና በመስጠት የቅዳሜውን የቪኦኤ ዝግጅት መዝናኛ አድርገውት ነበር። “እኛ” አሉ አቶ ቴድሮስ፣ “እኛ መቶ በመቶ ምርጫ አላሸነፍንም። ይህ መስተካከል አለበት። ያሸነፍነው በተወዳደርንበት ቦታ ብቻ ነው” ትዝታ ታዳምጣለች ቴድሮስ ቀጠሉ። ኢህአዴግ የአራት ድርጅቶች ጥምረት መሆኑን አስረዱ። የተቀሩት “አጋር” እንኳን ሲሉ ያልጠሯቸውን የጎሳ ድርጅቶች “ተቃዋሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ” አሏቸውና አረፉት።

የጋምቤላ፣ የቤኒሻነጉል፣ የአፋር፣ የሶማሌ ከልል ኢህአዴግ ሰራሽ /እንደራሴ/ ወይም ድቃይ ድርጅቶች “እንደ ሌሎች ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን አውጥተው አይቃወሙንም እንጂ የማንግባባቸው ጉዳዮች አሉ” በማለት እነሱ በሚያስተዳደሩት ከልልሎች ውስጥ ኢህአዴግ አለመወዳድሩን በማሰረዳትና በመተንተን ኢህአዴግ መቶ ከመቶ ምርጫውን አሸነፈ ሊባል እንደማይቻል አመላክተዋል።

አዲስ አበባን አስመልክቶ ኢህአዴግ ትንሽ ከስልሳ በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘቱን፣ ተቃዋሚዎች አርባ በመቶ የሚጠጋ ድምጽ አግኝተው እንደነበር፣ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተቃዋሚዎች ያገኙት ድምጽ ሲደመር ኢህአዴግ ካገኘው በላይ ቢሆንም አንድ ባለመሆናችው ሊያሸንፉ አለመቻላቸውን፣ ያመለከቱት የህወሃቱ አባል ቴድሮስ፣ “ተቃዋሚዎች የተበጣጠሱ ናቸው፤ እኛ አንድ ልናደርጋቸው አንችልም። አንድ ቢሆኑ በርግጠኛነት ከሰላሳ በመቶ በላይ መቀመጫ ማግኘት ይችላሉ” ሲሉ የቀጣዩን ምርጫ ውጤት ተንብየዋል።

ሚኒስትሩ ባልተለመደ መልኩ በመቻቻል፣ በመፋቀር፣ በመረዳዳት፣ በህብረት አገር ለማሳደግ ሁሉም ወገኖች ሊሰሩ እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል። “አዲስ የዴሞክራሲ ግንባታ በመሆኑ ብዙ እናበላሻለን” ሲሉ ችግሮች ስለመኖራቸው ያልሸሸጉት አቶ ቴድሮስ፣ ስለመተባበር ጥሪ ቢያቀርቡም የአርበኞች ግንቦት ፯ ሃይል ታጋይና ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋን በስም በመጥራት ወደ ኤርትራ ማቅናታቸውን ጠቁመው “የሚያመጣው ነገር የለም። እርግጠኛ ነኝ የሚፈይደው ነገር የለም። ዜሮ፣ ፕሮፓጋንዳ ከመሆን ውጪ የሚያመጣው ነገር የለም” ሲሉ አጣጥለዋቸዋል። እሳቸው ይህንን ቢሉም ኤርትራ የመሸገው የአርበኞ ግንቦት ፯ ሃይል በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘሩን፣ ጉዳት ማድረሱን፣ ቁጥራቸው ከአርባ በላይ የሚሆኑ የአየር ሃይል አባላት ከዱ ስለመባሉ ኢህአዴግ በይፋ ሲያስተባብል አልተደመጠም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. rasdejen says

    August 3, 2015 01:42 pm at 1:42 pm

    TPLF is a bunch of traitor (banda) descendants. As descendants of traotors, they planned to revange to what happened to their banda parents. Banda’s were hated and isolated by all the peoples of Ethiopia. the TPLF bunch together with its Shabiya masters designed a fictitious stories that the Amahara’s did all the evil and they should be removed along with their languages. Even Tewahido is associated with these great people, hence should be dimolished according to the rubish TPLF BUNCHES. These fiction was further developed and designed as a political agenda. The whole Tigrigna speaking Ethiopians were brainwashed and nearly all are convicted. I realized these very recently.

    What TPLF did/is doing is exactly what it preached while it was in the bush. We need to look at what they did, NEVER HEAR WHAT A TPLF SAYS. THEY ARE CHRONIC LIERS. THEY ARE BORN OF LIERS. THEY GIVE BIRTH TO LIERS.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule