ሁላችንም ተወልደን ባደግንባት ሃገራችን ውስጥ እየሆነ ያለው የመግደልና የመገደል ትርምስ፣ እንኳን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ይቅርና ለዓለም አቀፉ ኅብረተ ሰብ ሳይቀር አስገራሚ የመነጋገሪያ ዋና አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፤ ፖለቲከኞቻችንና ‘መንግሥትም’ ለተፈጠረው ችግር ያልሆነ ምክንያት በመስጠት የመወነጃጀሉን ሥራ ተግተው ቢቀጥሉበትም መገዳደሉ ግንከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጠ ልዩ ትእዛዝ መሰረት የበለጠ ተባብሷል።
የክርስቲያን ደሴት እየተባለች ለበርካታ ዘመናት የተዘመረላት ሃገራችንም፣ መገለጫ ባህሪው ፍቅር የሆነውና ሰይፍ ማንሳት የማያውቀው የመጽሐፍ ቅዱሱ እውነተኛውየክርስትናሕይወት ምልክት እንዳልነበረንተግባራችን እየመሰከረብን ነው፤ በሰው ልጆች የታሪክ ሂደት ውስጥ ክርስቲያን ሲገደል እንጂ ሲገድል ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅምና፤ ይህን ስል ግን በክርስትና ስም የሚነግድ አስማሳይ የለም እያልኩ አይደለም፤ የማወራው ለሌሎች ሰዎች በረከትና ጥቅም ጭምር እንድንኖር ስለሚያደርገው ስለ እውነተኛውና ተግባራዊ ስለሆነውየክርስትና ሕይወት ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply