የ18 የግል ኮሌጆች ፍቃድ ታገደ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አደረግኩት ባለው ድንገተኛ የቁጥጥር ስራ የፖሊሲ ጥሰት ፈፅመዋል ያላቸውን 18 የግል ኮሌጆች ፍቃድ አግዷል፡፡ ከታገዱት በተጨማሪ መለስተኛ የፖሊሲ ጥሰት በፈፀሙ 26 የግል ኮሌጆች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም ድንገተኛ ቁጥጥር የተደረገባቸው 59 የግል ኮሌጆች ሲሆኑ 18ቱ ታግደዋል፤ 26ቱ ከቀላል እስከ ከባድ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በድምሩ 44 የግል ኮሌጆች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል፡፡ ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍና በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ … [Read more...] about የፖሊሲ ጥሰት በፈጸሙ 44 የግል ኮሌጆች ላይ እርምጃ ተወሰደ