ከቶንሲልና ተያያዥ ህመሞች ጋር በተያያዘ የሚመጡ በተለይም ቦርቀው ባልጠገቡ ህጻናት ላይ የሚያጋጥሙ የልብ ህመሞችን በማከም ይታወቃሉ። መሳቅ፤ መጫወትም ሆነ መቦረቅ አቅቷቸው ነጋቸው የጨለመባቸውን በርካታ ህጻናት ለመታደግ በመቻላቸውም ስማቸው በብዙዎች ይጠቀሳል፤ ኢትዮጵያው ልብ ቀዶ ጠጋኝ ሃኪም ዶ/ር ፈቀደ አግዋር። ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ታሪክ አዲስ ምዕራፍን ከፍተዋል የሚባልላቸው ዶ/ር ፈቀደ በግላቸው 326 ገደማ ቀዶ ጥገናዎችን ማድረጋቸውን ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ለመገመት ሊያዳግት በሚችል ደረጃ በርካቶችን ረድተናል የሚሉት ዶ/ር ፈቀደ እነዚህን የብዙዎችን ህይወት የታደጉ ቀዶ ጥገናዎች በ4 ዓመታት ውስጥ ነው ያደረጉት። ከ326ቱ ውስጥ 290 ገደማዎቹ ቀዶ … [Read more...] about “የተባረኩ እጆች” – በአራት ዓመት 326 ገደማ የልብ ቀዶ ጥገና ያደረጉ ሐኪም