• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የተባረኩ እጆች” – በአራት ዓመት 326 ገደማ የልብ ቀዶ ጥገና ያደረጉ ሐኪም

July 20, 2021 09:41 pm by Editor Leave a Comment

ከቶንሲልና ተያያዥ ህመሞች ጋር በተያያዘ የሚመጡ በተለይም ቦርቀው ባልጠገቡ ህጻናት ላይ የሚያጋጥሙ የልብ ህመሞችን በማከም ይታወቃሉ።

መሳቅ፤ መጫወትም ሆነ መቦረቅ አቅቷቸው ነጋቸው የጨለመባቸውን በርካታ ህጻናት ለመታደግ በመቻላቸውም ስማቸው በብዙዎች ይጠቀሳል፤ ኢትዮጵያው ልብ ቀዶ ጠጋኝ ሃኪም ዶ/ር ፈቀደ አግዋር።

ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ታሪክ አዲስ ምዕራፍን ከፍተዋል የሚባልላቸው ዶ/ር ፈቀደ በግላቸው 326 ገደማ ቀዶ ጥገናዎችን ማድረጋቸውን ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ለመገመት ሊያዳግት በሚችል ደረጃ በርካቶችን ረድተናል የሚሉት ዶ/ር ፈቀደ እነዚህን የብዙዎችን ህይወት የታደጉ ቀዶ ጥገናዎች በ4 ዓመታት ውስጥ ነው ያደረጉት።

ከ326ቱ ውስጥ 290 ገደማዎቹ ቀዶ ጥገናዎች ሙሉ በሙሉ የልብና የሳንባን ስራ በማቆም የተሰሩ ናቸው። “27 አካባቢ ብቻ ናቸው ልብም ሳንባም ሳይቆም የሰራኋቸው” ሲሉም ነው የሚያስቀምጡት።

ዶ/ር ፈቀደ እና የስራ ባልደረቦቻቸው በኢትዮጵያ እምብዛም ያልተለመደውን የህክምና ግልጋሎት ነው በመስጠት ላይ ያሉት። በዚህም ብዙዎች በሃገራቸው በቤተሰባቸው መካከል ሆነው በሚያግባባቸው ቋንቋ እየተነጋገሩ ርቀው ሄደው ሳይንገላቱ ህክምናውን ለማግኘት ችለዋል።

ይህ መሆኑ በአገልግሎቱ በቶሎ አለመገኘት ምክንያት ሊጠፋ የሚችለውን ህይወት ከመታደግ፤ እንግልትና ድካምን ከማስቀረትም በላይ እንደ ሃገር ሊታጣ የሚችለውን የምንዛሬ ገንዘብ ያድናል።

በራስ ሰው፣ አቅም እና ሃብት ታክሞ መዳኑም ቀላል አይደለም። ወደ ውጭ ሃገር የሄደው ታማሚ ሁሉ ድኖ ስለመመለሱም ዋስትና የለም።

“እኔ ህንድ በምማርበት ጊዜ ወገኖቻችን የሚያሳልፉትን ይህን መከራ አይቻለሁ” የሚሉት ዶ/ር ፈቀደም “በሃገርህ መሬት በሃገርህ እውቀት ስትሰራ ይሄን ሁሉ ችግር ነው የምታስወግደው” ሲሉ ይናገራሉ።

ዶ/ር ፈቀደ “ዋናው ቁም ነገር የምትሰጠው ግልጋሎት ልብን ቀደህ ስትጠግን የምታስገኘው ውጤት ከዓለም ጋር ተቀራራቢ ነወይ? የሚለው ነው” ይላሉ፤ ሰዎች ወደ ውጭ ሄደው ከሚያገኙት ህክምና ያነሰ ውጤት የሚገኝ ከሆነ ወደ ውጭ ሄደው መታከማቸው ተገቢነት እንዳለው በመጠቆም።

ውጤቴም፤ በፍጹም ከሌላው ዓለም የማይተናነስና ቆንጆ ውጤት ያለው ስራ ሰርተናልም ነው እውቁ ልብ ቀዶ ጠጋኝ ሃኪም የሚሉት። ይሄን ማንኛውም ሰው ስራዎቻቸውን በሚመለከት በዓለም አቀፍ መጽሄቶች (ጆርናልስ) ላይ ጭምር ከጻፏቸው ጽሁፎች አይቶ ለመረዳት እንደሚችል በመግለጽ።

በአዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት ዶ/ር ፈቀደ የሶስት ልጆች አባት ናቸው። በዚሁ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም በህንድ ሃገር ቤንግሎር ተምረዋል።

ዋና ስራዬ ቀዶ በመጠገን የሰዎችን ህይወት መቀየር ነው የሚሉት ዶ/ር ፈቀደ የሰራሁት ብዙ ነው ብዬ አላምንምና አሁንም ቀዶ ጥገናዎችን ማድረግ እፈልጋለሁ ሲሉ ይናገራሉ። (አል ዐይን አማርኛ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Social Tagged With: fekade agwar, gifted hands, heart surgeon

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule