• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስንቱን አጣን!

October 15, 2013 09:11 pm by Editor 1 Comment

እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።

ከአሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ ተገናኘንና ወደቀድሞ ሥራው ወደወንጂ ተመልሶ እንደሆነ ስጠይቀው ‹‹እንዴት ብዬ! ዕድሜ ልኬን የፈረንጅ አሽከር ሆኜ መኖር አልፈልግም፤ አሁን ደግሞ ያስተማረኝን ሕዝብ ላገልግል እንጂ!›› ነበር ያለኝ፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በወንጂ ባሉት ደመወዞች መሀከል ከፍተኛ ልዩነት ነበረ፤ ቁም-ነገረኛነቱን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ታማኝነት፣ የግል ጥቅሙን ቀንሶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ባሳየው ተግባራዊ አርአያነት የማደንቀው የወታደር ልጅ ነው።

ይህ ሰው በደርግ ጊዜም አልሸሸም፤ በአንድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሥልጣን ቦታ ላይ ነበር፤ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወንበሩን ሲይዝ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የማይፈለጉ መሆናቸው ሲታወቅ አገሩን ጥሎ ተሰደደ፤ በትልቅ ዓለም-አቀፍ መሥሪያ ቤት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ዕድሜው ለጡረታ እስቲደርስ ቆየ፤ ወደሚወዳት አገሩ ለመመለስ አልቻለም፤ ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር ግንኙነት እንዳለው አውቃለሁ፤ አንድ ቀን ስለዚሁ የጋራ ጓደኛችን ስናወራ ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ጠየቅሁ።

የዚህ ወጣት አጎት በወታደርነት ኢትዮጵያን ለረጅም ጊዜ በክብር ያገላገለ ነው፤ ይህ ሰው ወያኔና ሻቢያ በተጣሉ ጊዜ ዜግነታቸው በጉልበት እየተገፈፈ ከአገራቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ሰዎች አንዱ ነው፤ በዚያን ጊዜ በሌላ የኤርትራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ራሱ ሰውዬው በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ሲናገር የሰማሁት የሚከተለውን ነው፤– ‹‹ለኢትዮጵያ በአለኝ ሁሉ አገልግያለሁ፤ ኢትዮጵያን ሳገለግል አንድ እግሬን አጥቻለሁ፤  አንድ ሰው ለአገሩ ከዚህ የበለጠ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ሲናገር አስለቅሶኛል።

የኔ የቀድሞ ተማሪና ወዳጅም ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ሲጠየቅ ‹‹ለጋሼ (ማለት ለአጎቱ) ያልሆነች ኢትዮጵያ ለእኔ አንዴት ትሆነኛለች?  በማለት በጥያቄ መለሰ አሉ፤ አባቱ ያገለገላትን፣ አጎቱ የለፋላትን፣ አያት ቅድመ-አያቶች የሞቱላትንና የደሙላትን አገር እንዲህ በቀላሉ ማጣት ነፍስን ያቆስላል፤ የነዚያን ሰዎች ሁሉ መስዋእት ያከሽፋል፤ ያረክሰዋል፤ ይህንን የተገነዘቡና ያዘኑ፣ ያለቀሱ ሰዎች ናቸው –

እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Truly says

    October 25, 2013 01:42 am at 1:42 am

    Prof. Mesfen Thanks a lot. The cause of all these distraction is the narrow minded, looter tigrean woyane regime who has a huge inferiority complex on Eritrean as well as the Amaharian and Oromo people. Even in the cyber space, those pimps of Woyane are the one who try to create a havoc between we Eritreans and the Ethiopians. Woyane expelled so many Eritrean origin Ethiopian heros, famous politicians, athletes, teachers, pilots, business men,…etc who worked the whole life for Ethiopia. Although the children of the looters regime dig day & night to create & expand the difference among the Eritreans & Ethiopian ( i.e except Adwa -axum pimps ), we have a greater respect for Ethiopia & Ethiopians. I pray for the demis of woyane before everything. Only then the people of both countries enjoy the peace & love. Woyane is the first enemy of Eritrean people, and then Isias.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule