በኦታዋ ካናዳ በተካሄደው ጉባኤ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2012 የተመሠረተውና የኢትዮጵያ የአንድነት ኃይሎች ትልቁ ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ (ሸንጎ) በዛሬው ዕለት ባካሄደው የምክር ቤት ስብሰባ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ድርጅቱን የሚመሩ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
በዚህም መሰረት ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴው አባላት ውስጥ ዶክተር ታዬ ዘገዬን፣ ሊቀመንበር ወይዘሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግደይ ዘርአጽዮንን ዋና ጸሀፊ እና አቶ መሐመድ ጀሚልን ምክትል ዋና ጸሀፊ አድርጎ መርጧል፡፡ የተቀሩት የኮሚቴው አባላት ደግሞ የተለያዩ የተግባር ኮሚቴወችን በኃላፊነት ይመራሉ።
ሸንጎው በቅርቡ አጠቃላይ ጉባዔ በማካሄድ ኢትዮጵያችንና ሕዝቧ የሚገኙበትን ሁኔታ በጥልቅ ከመረመረ በኋላ ሀገራችን ከምትገኝበት አስከፊና አደገኛ የግፍ ሥርዓት ተላቃ አንድነቷ ተጠብቆ እኩልነት፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም የህግ የበላይነት ወደ ተከበረበት ለሁሉም ዜጎቿ የሚሆን ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚያስችለውን ለውጥ እውን ለማድረግ መደረግ በሚገባቸው መሠረታዊ ጎዳዮች ላይ የትግል አቅጣጫ ነድፏል።
ይሀ አሁን የተመረጠው የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ ብቻ ሳይሆን በአንድነት ኃይሎችም ላይ የተነጣጠረውን ጥቃት በመመከትና የአንድነት ኃይሎችን በማጠናከር የሕዝባችን የነፃነት ራዕይ እውን እንዲሆን ለማስቻል ከፍተኛ አደራን ተቀብሏል።
ይህን ለማድረግም ከባዕዳን ተጽእኖ ነፃ ሆኖ ራሱ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ ያማከለና መሠረት ያደረገ ትግልን አጠናክሮ ይቀጥላል።
የሸንጎው የጋራ አቋሞች
- በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት በሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትና ሉዓላዊነት ላይ የማያወላውል እምነት
- ፍትህ የሰፈነበትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ጸንቶ መታገል
- ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ መከበር አለባቸው ብሎ ማመን
- በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ምንም ዓይነት አድሏዊነት እንዳይኖርና ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሕግ ፊትና በሶሻልና የፖለቲካ ነፃነታቸው እኩል ዜጎች መሆናቸውን በተግባር ማረጋገጥ
- የህወሀት/ኢህአዴግ መንግስትና አገዛዝ ሥርዓት የአፈናና የጭቆና ሥርዓት በመሆኑ መለወጥና በህገ-መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ የአስተዳደር ሥርዓት መተካት እንዳለበት መቀበል
የሚሉት ሲሆኑ እነዚህን መሠረታዊ መተክሎች የሚቀበል ማንኛውም ግለሰብ፤ ስብስብ ወይም ድርጅት ሸንጎውን በመቀላቀል ወይም በጋራ በመሥራት ሕዝባችንንና ሀገራችንን በጋራ እንድንታደግ ጥሪያችንን በድጋሜ እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ጥቅምት 13፣ 2008 (ኦክቶበር 24፣ 2015)
koster says
I donot see the difference between your goals and that of AG7 so would you please elaborate. I thought your group is just “alen lemalet” and in preparation for another London conference just to have parliamentary sits or power. If you really care for Ethiopia and Ethiopians right to choose their leaders narrow your differences with AG7 and fight together to shorten the suffering of our people and the disintegration of Ethiopia.