• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል

September 6, 2017 02:15 am by Editor Leave a Comment

የህወሃት አገዛዝ 2010 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ለማክበር የጀመረውን ከባህሪው የወጣ ድርጊት ተመልክተው አንዳንዶች ስርዓቱ እውነተኛ የመንግስትነት ባህርይን እየያዘ ነው ሲሉ ይደመጣል። እነዚህ የዋሆች  ሰሞኑን ከነሀሴ 26 ቀን ጀምሮ የፍቅር ቀን፣ የእናቶችና ህፃናት ቀን፣ የአረጋውያን ቀን፣ የሰላም ቀን፣ የንባብ ቀን፣ የአረንጓዴ ልማት ቀን፣ የመከባበር ቀን፣ የሀገር ፍቅር ቀን፣ የአንድነት ቀን እና የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ መለያዎች አዲሱን ኣመት ለመቀበል ህወሀት የያዘውን ፕሮግራም እንደ አንድ ማስረጃነት ሲጠቅሱ ይታያል። ታርሟል በሚል። መሬት ላይ የምናያቸው የስርኣቱ ባህርያት በምክንያት ለገመገመ ሰው ግን ስርዓቱ ለመሻሻል ፍላጎት እንደሌለው ይገነዘባል። በእኔ ምልከታ ችግሩ ከድርጅቱ ፍጥረታዊ ባህርይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ።

በመጀመሪያ ደረጃ ህወሀት ከምስረታው ጀምሮ በጠላትነት የሚያሳድደው አመለካከት ፍቅር፣ አንድነት እና ኢትዮጵያ የሚለውን ሀይል አይደለም እንዴ? እስከዚህ ሰዓት ድረስ  የተበዳይና የበዳይ ድርሰት እየደረሰ በህዝቦች መካከል ቁርሾ የሚዘራው ማነው? በሌላ በኩል የዘር ብሄርተኝነትን ከሚገባው በላይ በማራገብ ኢትዮጳዊነትን ያኮሰመነ  መንግስትስ ማን ነው? የህወሃት አገዛዝ አይደለምን? ታዲያ አሁን ምን ተገኘ የሚለው በደንብ መታየት ያለበት ይመስለኛል። በእኔ ምልከታ ይህ እርምጃ  ህወሀት በአሁኑ ወቅት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በአንድነት የተነሳበትን ተቃውሞ ለማቀዝቀዣነት የዘረጋው ስልት ነው። የአንድነት ሀይል ነው ተብሎ የሚታሰበውን የአማራ ሀይል ጉርሻ ነገር በመስጠት ማስታገስ ላይ ያነጣጠረ ስልት። በዚህም በቅርቡ በአማራ ክልል በክልል ደረጃ  ለመተግበት ህዝቡ በእቅድ የያዘውን በቤት ውስጥ የመቀመጥ ህዝባዊ አድማ ማለዘብ የስልቱ ዋና አላማ ነው። ይህም ህወሀት ሙሉ ሀይሉኝ በኦሮሚያውና ሌሎች ክልሎች  ላይ እንዲያተኩር ይረዳዋል። ህወሀት እንደዚህ እይነት ብልጣ ብልጥ እርምጃዎች  ይዞ ሲመጣ ይበልጥ ጠንቃቃ መሆን እንዳለብን ልምዳችን አስተምሮናል። ከትንፋሽ በኋላ ይበልጥ አሳሪ ህግና አሰራሮችን ይዞ በበቀል የመጣባቸው ብዙ ልምዶች ስላሉን። ከ1997 ምርጫ ተከትሎ የአንድነት ህይሉን፣ ነጻ ፕሬስ እና ማህበራትን ለማጥፋት የወሰዳቸው እርምጃዎቹን ማስታወስ ይገባል። ድርጅቱ ግለሰብና ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ከተማዎችንም በቂ በቀል የሚቀጣ መሆኑን ማስታወስ ይገባል።

የህወሀት እታደሳለሁ የሚሉ ለቁጥር አታካች መሀላዎች ያመጡልን ነገር ቢኖር በተደራጀ መንገድ የሚያካሂደው የሀገር ሀብት ዘረፋ መባባስ ነው። የባርነት ሰንሰለቱ ይበልጥ መጥበቅ ነው። የህዝቦች እርስ በርስ ጥላቻ መበራከት ሌላው ህወሀት እድሜው በጨመረ ቁጥር አብረው የጨመሩ ክስተቶች ናቸው። ስለዚህ “ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል” ብለናል። ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ሀገራችን ያላት መንገዱ አንድ ብቻ ነው። ህዝቦች መሪዎቻቸውን በምርጫ ካርድ ወደ ስልጣን የሚያመጡበት የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መዘርጋት ብቻ። ለዚህም ከተጽህኖ ነጻ የመከላከያና ፖሊስ ሰራዊቶች፣ ነጻ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም እንደ ኬንያው  ነጻ ፍርድ ቤቶች በህዝቦች ንቁ ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት በአጭር ወቅት መገንባት ይኖርባቸዋል።

ያሬድ አውግቸው (yaredawgichew@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule