በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ምእራፍ እንዲኖር መፍትኤው ምንድነው? ያልተሞከረው ብቸኛ መፍትኤ እርቅና መግባባት ነው። ለመሆኑ እርቅና መግባባትን እምቢ ባዩ ማን ይሆን? መንግስት ወይስ ተቃዋሚ? ወይስ ዝምተኛው አብዛኛው ሕዝብ? ወይስ ሁላችንም? ሁሉም ክሱን ትቶ ራሱን ይመርምር። ራሳችንን እንድንመረምርበት የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች እንደ መንደርደሪያ አሳብ አድርገን እንውሰድ። ታዲያ በነዚህ ሚዛን ተመዝነን ቀለን እንዳንገኝ አምላክ የእሽታን መንፈስ ለሁላችንም ይስጠን።
መንግስትን በተመለከተ
1ኛ/ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት ኢዮቤሊዩ (“Jubilee”) ማብሰር
2ኛ/ በፊታችን ያለውን ምርጫ ፍታዊ ማድረግ(በራስ መተማመንን ያሳያል)
3ኛ/ ተቃዋሚ የሚያቀርበውን መጥፎ አሳብ እያጋለጡ መልካም የሆነውን ግን በስራ ላይ ማዋል
ተቃዋሚን በተመለከተ
4ኛ/ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን እንዲፈጥሩ (አንድነት ሃይል ነውና)
5ኛ/ የሰላም ትግሉ ከጦርነትና ከአብዮት አመፅ የፀዳ መሆኑን ከልብ ማስመር
6ኛ/ መንግስት የሚሰራውን ስህተት እያጋለጡ መልካም ስራውን አለመካድ
መንግስትና ተቃዋሚ (ሁለቱንም) በተመለከተ
7ኛ/ የንግግር ቃላት በፀጋና በቅንነት የተሞላ ይሁን (ሰውዬውን ወዶ አሳቡን መጥላት እንማር)
ገለልተኛው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተመለከተ
8ኛ/ ዝምታውን አቁሞ ለእርቅና መግባባት ድምፁን እያሰማ መሟገት ይጀምር
ሁሉንም ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በተመለከተ
9ኛ/ ለኢትዮጵያ የጋራ በሆኑት ነገር ላይ አንድነትን መግለፅ (ኢትዮጵያ ከፖለቲካችን በላይ ናት)
10ኛ/ አምላክ ኢትዮጵያን እንዲባርካት እጆቻችንን ወደ ፈጣሪ መዘርጋት
ከሁሉም ወገን ልሰማ እወዳለሁና አሳባችሁን ፃፉልኝ: Z@myEthiopia.com
belachew dagne says
በእውነት ያቀረብከው የእርቅና የሰላም አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦች በጣም ተመችቶኛል ሁሉም ለህገሪትዋና ለህዝብዋ ሰላም ሲል ያለብንን የኢኮኖሚ ችግር ሳንቀርፍ ሌላ ተጨማሪ ችግር ከምንፈጥር ወደ መፍትሄው ብንሄድ በጣም ጥሩ ነው እላለው። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያስባት !!!
tariku says
ሀሳቡ ጥሩ ነው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ካገኘ። በተለይ ከመንግስት ይህ ሁሳኔ ቢመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፉን ለመስጠት አደባባዩን ያጥለቀልቃል። ይህ ሀሳብ ተቀባይነት ቢያገኝ ሀገራችን ትድናለች። ታድጋለች።
ኢግዚያብሄር ለሁሉም ልቦና ይስጥ።
Sholla Gebya says
I don’t know why you guys have kept writing about peace and reconciliation. weyane has never hinted or talked about the subject. Are you trying to detract and buy time for weyane ? You have an iota of evidence to back this assertion, or support your analysis from the government side if this is indeed the direction weyane wants to pursue. We Ethiopians in the Diaspora, have almost reached a conclusion that you are one of those weyane media outlets to detract people from the struggle .
Editor says
Sholla Gebya
እዚህ ላይ ብዙ ጊዜ ለአስተያየት ምላሽ አንሰጥም ሆኖም ግን የጻፉት ነገሮች ባብዛኛው ከመስመር የወጣ ስህተት የያዘ በመሆኑ እርማት ስለሚያሻው ከዚያም ባሻገር እርስዎም መማርና መታረም ስላለብዎት እንዲሁም የማያውቁትን ነገር እኛ ማስተማር ስላለብን ይህንን ለማለት ወደድን:: ለሌሎችም ትምህርት ይሆናል ብለን እናምናለን::
ሲጀመር “… you guys have kept writing about peace and reconciliation” የሚለው ስህተት ነው:: ምክንያቱም ጽሁፉን የጻፍነው እኛ አይደለንም – ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር ናቸው:: እርሳቸው ደግሞ ሰሜን አሜሪካ ተቀምጠው ለምሳሌ “Sholla Gebya” በሚልና በመሳሰለው ዓይነት ስም ራሳቸውን ደብቀው ሳይሆን የጻፉት ፍጹም ግልጽነት ባለው መልኩ ማንነታቸውን አስረድተው ነው:: ስለዚህ Sholla Gebya ይህንን ስህተትዎን ማረም አለብዎ::
ከዚህ ጋር ተያይዞ “Are you trying to detract and buy time for weyane?” ምናምን የሚለው አላስፈላጊ ዝባዝንኬ ብዙም የማይመጥነን ስለሆነ ምላሽ የማንሰጥበት ነው:: ስለወያኔም ሆነ ኢህአዴግ ያለን አቁዋም በምናትማቸው ዜና እና ከሌሎች ሚዲያዎች ለየት ባለ መልኩ በምናወጣቸው ርዕሰ አንቀጾች በግል ያስቀመጥን በመሆኑ ራስዎን ለማስተማር ይችሉ ዘንድ ወደዚያ ሄደው ቢያነቡ ብዙ ትምህርቶች ያገኛሉ::
ከዚህ ሌላ “You [don’t] have an iota of evidence to back this assertion, or support your analysis from the government side” በሚለው ላይ ብዙ ማለት የሚቻል ነበር:: ግን አሁንም ያለመመጣጠን ችግር ይታያል:: እርስዎ ወያኔ እያሉ የሚጠሩት “government” እንደማይባል እንኩዋን አያውቁም:: ማን ተብሎ እንደሚጠራ በተደጋጋሚ ያልንበት ጉዳይ ስለሆነ እዚህ ላይ የቤት ስራ እንሰጥዎታለን:: ሆኖም ይህ ትልቅ የዕውቀት ችግር ወይም ዕጥረት እንዳለብዎት የሚያሳይ በመሆኑ መጀመሪያ የተወሰኑ የፖለቲካ ሀሁ … መቁጠር የሚያስፈልግዎ ስለሆነ ቅድሚያ በዚያ ላይ ትኩረት ቢሰጡ መልካም ነው::
የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር ከዚህ በፊትም ቢሆን ተመሳሳይ ጽሁፎችን አቅርበዋል:: ወደፊትም ይቀጥላሉ ብለን እናምናለን:: እንደ አንድ ዜጋ ልባቸው ያመነበትን በተለይ ሰሜን አሜሪካ “ፖለቲካውን እኛ ካልዘወርነው” የሚሉ “ሁሉን” በተቆጣጠሩበትና አየሩን በሞሉበት መገለል ሳይፈሩ ስማቸው ሳይደብቁ በግልጽ ጽፈዋል – ይህንን ያልተለመደ የብቸኝነት መንገድ በመምረጣቸው ብቻ ሊደነቁ ይገባቸዋል:: ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ በሰላምና ዕርቅ ያምናል:: ይህ ደግሞ ማንም የማይወስድብን ማንም የማይሰጠን መብታችን ነው:: ዓላማችን በምናወጣቸው ኤዲቶሪያሎች በማያሻማ መልኩ አሳይተናል:: ማንም አያስቆመንም ያላንዳች ገደብ እንቀጥልበታለን:: ይህንን ደግፈው የሚጽፉ ወገኖችንም እናስተናግዳለን:: የዕርቅ ሃሳብ አይሰራም የሚሉ ሃሳባቸውን በአመክንዮታዊ መልኩ በማስረጃ በመጻፍ በስማቸው እስከገለጹ ድረስ እናስተናግዳለን::
በመጨረሻም “We Ethiopians in the Diaspora, have almost reached a conclusion that you are one of those weyane media outlets to detract people from the struggle.” የሚለው አገላለጽ “ለኢትዮጵያ የማውቅላት እኔ ነኝ” ከሚለው ወያኔያዊ አስተሳሰብ የሚለየው ይህኛው በእንግሊዝኛ ከሰሜን አሜሪካ መጻፉ ብቻ ነው:: ይዘገንናል! መንፈስ ይረብሻል! ለከት የሌለውን ድንቁርና ያሳያል:: ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን እንዳለው ደግሞ “ድንቁርና ያስፈራል”::
ስለዚህ Sholla Gebya አስተያየትዎ በእኛ ዘንድ “ገበያ” የለውም:: የሚገዙ ካሉ “We Ethiopians in the Diaspora” ያሉዋቸው ጋር መሞከሩ ምናልባት “ገበያ” ያስገኝ ከሆነ ይሞክሩት::
ለዚህ አስተያየታችን ምላሽ አንፈልግም – አንጠብቅም:: ይህና መሰል የዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ጽሁፎች እንዲሁም ሌሎች የዕርቅና ሰላም ሃሳቦች እርስዎ ካለዎት የዕውቀት መጠን የላቁ እና ለማስተዋል የሚከብድዎ ከሆነብዎ በዚህ editor@goolgule.com ይጻፉልን:: ለማቅለልና እንዲገባዎት ለማድረግ የሚቻለንን እንሞክራለን::
ከሰላምታ ጋር
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
base says
I support the idea of the national consensus and reconciliation…That is feasible if the regime is willing to apply it…
በለው ! says
>>>ይህ መልካም ሐሳብ ነው ጥረቱ በአንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑ ያሳዝናል…እንግዲህ በዚህ የማይሳተፉ የግራም፣ የቀኝም፣ የመሐልም የበላይም የታችም አካላት(ዜጎች) ነን በሠላም በአንድነት በእኩልንት በነፃነት እናምናለን (ዲሞክራሲ የተባለው በምትሃት ከሰማይ ይወርዳል) ካሉ የችንቅላት ችግር(ድርቅ) ገብቷል።አራት ነጥብ። ከዚህ ውጭ ሆነው በሌላ ዓለም ውስጥ ኖረው ምድር የሚናፍቃቸው ብቻ ይሆናሉ። ግለሰቡ በተከታታይ ባወጧቸው ፅሑፎችና መመዘኛ ጥያቄዎች ጭራሽም ያልተጠበቁም አዳዲስ ሀሳቦች ፈልቀዋል። ባሕልና ወግ ሆነው የቀጠሉም መጯጯያ መፈክሮች ወሽቃጣ ድግምግም አደናቓሪ ሀሳቦችም እንዳሉ ናቸው ። እኔ “የተጣላው ማነው? የሚታረቀው ማን ከማነው? ለሚለው ምላሹ እያንዳንዱ ከራሱ ተጣልቷል ባይ ነኝ… በጋራ ይጮሃል! በጋራ ይቃወማል! በጋራ ይደግፋል! በጋራ ይገረፋል! በተናጠል ያለቅሳል!..በግሉ ማሰብ ተስኖታል ባይ ነኝ ይህ ሲሆን ጩኽት በሰማበት ሁሉ አደግድጎ ከተነሳ በሠርግ ላይም ከል መልበሱ አይቀርም! ሠርና ምላሽ ሳይሆን ለቅሶና ሠርግ ልዩነቱን ሳያውቅ ሌሎች እየመሩት እየተማረረ ይዘልቃል።
፩) መንግስት የፖለቲካ አስረኞችን መፍታት ብቻ ሳይሆን ማሰር የለበትም። ተፎካካሪውን የሚሾመውም የሚደግፈው የሚያበረውም ሕዝብ ነው። ሕዝብ ፊት ያልቀረበን ተፎካካሪ መንግስት ካሰረ ፀቡ ሀገራዊ ፖለቲካዊ ሳይሆን ግለሰባዊ ቁርሾ ቡድናዊ የጥቅም ሆኖ ይቀጥላል።
፪) የህዘብ አመኔታ ያለው በሥራው የሚታመን ፺፱ በመቶ የፓርላማ ወንበር ላይ የተንሰራፈፈ አውራው ገዢ ፓርቲ በጦማሪያን ትችት..በጋዜጣ ላይ በተፃፈ ጥቅስ ..በአዳራሽ ውስጥና በመንገድ ላይ በተሰማ መፈክር…ሊበረግግና መሪዎችና ደጋፊዎቼ አስተሳሰባቸው ተናወጠ ብሎ ሊፈራ አይገባም!
፫) ተፎካካሪው ለመደገፍና ለመቃወም በአግሩ የመቆም ዕድል ሊኖረው ይገባል..ፓርላማ ያልተሳካለት ተፎካካሪ ህዝብን የሚደረስበት ሚዲያ ሊያገኝ ሀሳቡን ለህዝብ ሊያደርስና ሊደመጥ የግድ ነው። የሚናገረው፣ የሚናገርለትና የሚናገርበት ቦታ ተለክቶና ተከልሎ ከተሰጠው ከመከልከል ምን አነሰ?
፬) እንግዲህ ጨለምተኝነት እልህ ሳይኖር የግድም የማዳነቅ ልክፍትም ሳይኖር….በአሳማኝ ነትብ በመተቸት…በተገቢው ሁኔታ በማድነቅ..የሚጎድለውን በማመላከት ሀገር ለዘለቄታው ሠላማዊ..ሕዝብ ወገናዊ…የፓለቲካው ምህዳር የፉክክር..እንጂ ለግድያ የሚያካርር እንዳይሆን መጠንቀቅ!!
፭) ሠላም በመከባበር በእውነት በግልፅና በተጠያቂነት በአሳታፊነት ይመጣል…አብዮት የተፈጠረውም የሚፈጠረው አስገዳጅ ብሶት ሲጠራቀም ነው። ዘገየ ማለት አይኖርም ማለት አደለም…እንዳይኖር የሚገታው መባሰር በማሰደድና በማሳደድ ሳይሆን በመደማመጥ ሁሉም ለሀገሩ ያገባዋል ሲባል ነው።
፮) ይህ መንግስት የሚሰራውን ሕዝብ ያየዋል..የሚሰራ መንግስት የሚሰረሥር የለውም ማለት አይቻልም። “አሁን ሁላችንም ተነካክተናል እያየን እንዳላየን እንተላላፍ ለወደፊቱ ግን ጣታችሁን አንቆርጣለን “ማለትም በቂ አልነበረም። ያም የሆነው በሚዲያው ክፍተትና በተፎካካሪው ህዝብ ጥቆማና ጩኽት የተጠቆመ ነው። ታዲያ..መንግስት ጥፋቱን ያያል..ሕዝብ ይደሰታል… ሀገር ይጠበቃል…ይህ እንዳይሆን ተፎካካሪን አጥፋልኝ መግባባት አያስፈልግም ማን ከእኔ በላይ ለኢትዮጵያ አሸባሪዎች የሚሉት ቧልት የሚመነጨው ከሌባው ከሙሰኛው ከአድርባይና ጥቅማጥቅመኛው ነው ማለት ነው።
፯) አሁን ከእርስ በእርስ የድምፅ አልባ የመሳሪያ በተጓዳኝ …ክልላዊና የፓርቲ ሰንደቅና መታወቂያ ይዞ የቃላት ጦርነቱ ብሷል ግን ለማነው? ትርፉ? ውጤቱ ማንን ለማስደሰት? የትኛውን ትውልድ አጥግቦ ለማሳደር ይሆን? እንደሞቁ መቅረት የለም መቀዝቀዝም አለ. ከደርግ ብዙ መማር ይቻል ነበር።
፰) ዝምታው ከምን የመጣ ነው? ፈርቶ? ጥቅም የለበኝም ብሎ? ምን አገባኝ ብሎ? ለማን ብዬ ለአንዲት ነፍሴ ብሎ? ሰው እንደሆነ እሆናለሁ ብሎ? አቅመ ቢስ ነኝ ብሎ? እስክሞት ልብላ ብሎ? የጩኽት አድማቂነቱ አዋጪ ሆኖ ስላገኘው? ግራ ተጋብቶ? ከሄደው-የመጣው.. ካለው- የሚመጣውም.. ያው ነው ብሎ ይሆን? ግን ሲመሽ ሲነጋ በተስፋ አንድ ቀን እያለ በፀሎት ላይ ይሆን? ሲጠፋም ይበራል ብሎ ይሆን? አብሮ መታደግ ካልተቻለ አደጋ ነው፤
፱) አባይ ይገደባል ሲባል..የነበረው ጥያቄ የት? እንዴት? በማን? ለማን?ባለሙያ ይሳትፍ? ነበር። የትርጓሜ ማጣመም ካድሬና የጥቅማጥቅመኛ ከህሎት…!ከእኛ በላይ ማን አለ? ደፈርነው! ዋጥነው! ይህንን የጠየቀ ሁሉ አሸባሪ1 ፅንፈኛ! አድረባይ! ሲሉ ወደ ውች ሀገር የመጣውን ቡድን ተልዕኮውን እንዲስት አድረገው የእርሰ በእርስ ሰድብ ድብድብ ኤምባሲዎችን እንደግል ቤት አድረጎ ሌሎችን ማግለል ማመነህ ኸየት ክልል ነሽ ተጀመረ። ሀገራዊ አንድነት በግለሰቦች ማንነት ላይ ልዩነትን ፈጠረ ፡አሁን ውሻ በቀደደው ጅብ ገባ ይህንን ጥያቄ ሌሎች ደግሞ ሲጮህ ሰምተው በማስተጋባት የቀወጡትም ነበሩ..ሲባል ሰምተው እንጂ ምን እንደሆነ እራሳቸውን አልጠየቁም በራሳቸው አልተማመኑም! የጅምላ ጩኽት አደጋው ይህ ነው።
፲) እንገዲህ አምላክ/አላህ ኢትዮጵያን እንደባረከ ሁሉ ሕዝቦቿንም ባርኮ ቅን ልቦና ይስጣቸው። ይህ የዋህ ግን ድሃ ሕዝብ ከበሬታ ሊሰጠው የግድ ነው። ሀገሩ በላቤት ነውና ነፃነት! እኩልነት! ፍትህ!በግለሰቦችና በፓርቲ ልዩ ፍቃድ በችሮታ የሚሰጥ መሆን የለበትም። ይህንንም የዜግነት የማይገሰስ የማይደፈር ግን የሚከበር መብት ከጠያቂነት ወደ አስገዳጅነት መለወጥ ማናወጥ ሳይሆን ለተሰሚነት የሚደረግ ጥረት ነው። ሀገራዊ ዕርቅ ሥንል ችሮታ እንዲደረግ ሳይሆን ችሎታን የተጎናፀፈ መልካም አስተዳዳር የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ነው። ሠላም ለሁሉም ይሁን በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ!