• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህዝባዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ እና የተቃዋሚዎች የቤት ስራ

May 21, 2014 10:11 pm by Editor Leave a Comment

ከሰሞኑ ወያኔ መራሹ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያወጣው አዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሚያ ዞን ያካተተ ማስተር ፕላን እና የእዝ አስተዳደር ተግባራዊነትን በመቃወም በብዙዎች የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች ሰፊ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ ተቀስቅሶ በመንግስት ቅጥ ያጣ ግድያና እስር ለጊዜው ጋብ ቢልም አሁንም ቢሆን በህዝቡ ውስጥ ሞልቶ ሊገነፍል የደረሰ ቁጣ አለ፡፡ በሌላ በኩል በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ ሲደረግ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ አሁንም ቢሆን የቀጠለ ቢሆንም እስካሁን ድረስም ቢሆን በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ በሚፈለገው መልኩ ሊስፋፋ አልቻለም፡፡

ለዚህ ዋናው ምክንያት ሁለት ሲሆኑ አንደኛው የመንግስት ህዝባዊ ተቃውሞን አቅጣጫ በማሳት እና በህዝቦች መካከል የተነሳ የዘረኝነት ወይም የሀይማኖት የበላይነት የተፈጠረ በማስመሰል በህዝቡ ውስጥ መከፋፈልን በመፍጠር “የእብድ ገላጋይ” እንደሚባለው እንዳስታራቂ መጥቶ በህዝቦችና በሀይማኖት መሀከል ለረጀም ግዜ የቆውን መዋደድ (ልብ አርጉ መቻቻል አላልኩም) እንዳልነበር አድርጎ የኢትዮጵያ ህዝቦች የተባበረ አንድነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ሲሆን ሁለተኛወ ደግሞ የተቃዋሚዎች ሀዝባዊ ንቅናቄውን በማጠናከርና የጋራ አጀንዳ የሆነውን የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት መገርሰስ የተለየ አትኩሮት በመስጠት እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄው ሰፊ ሽፋን አንዲኖረው እምብዛም የጠነከረና የተቀናጀ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ አጠናክረው ባለማስቀጠላቸው ነው፡፡

በአብዛኛው ህዝባዊ ተቃውሞዎች ውስጥ የሚሳተፉ የወያኔ ካድሬዎች (Under Cover) እንደሚባለው በማዘጋጀት ዋና ተልዕኮዋቸው በህዝቦች መሀከል መቃቃር ሊፈጥሩ የሚችሉ አጀንዳዎችን በሰፊው እንዲሰራጩ  እና በህዝባዊ ጥያቄዎች ውስጥ እንደ አንድ አጀንዳ እንዲካተቱ በማድረግ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በማክሸፍ እንዲሁም ተቃውሞዎችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በመጠምዘዝ ውጤታማ እንዳይሆኑ በማድረግ ከጅምሩ የህዝብ ንቅናቄን ፈር ማሳት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የተቃዋሚወች በአቋም መግለጫ ብቻ መወሰን የተቃውሞ ንቅናቄዎቹ ስኬታማ እንደዳይሆኑ አስተዋጽዎ አድርጓል፡፡  ለዚህ በማሳያነት በቅርቡ የተደረጉት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ምን አይነት ሙከራ እንደተደረገበት እንመልከት፡፡

የመጀመሪያው የሙስሊሞች ህዝባዊ ጥያቄ ሲሆን በመሰረቱ እስካሁን ከታዩት ህዝባዊ ንቅናቄዎች በተሻለ መልኩ የተደራጀ ቢሆንም በሚፈለገው መልኩ ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል አላካተተም (የሀይማኖት ነጻነት ሁሉንም ዜጋ የሚመለከት ቢሆንም) እንደውም ተደጋግመው በሚቀርቡ የመንግስተ መሰረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳዎች (እስላማዊ መንግስት ማቋቋም በሚል ውሸት የታጨቀ) የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ሁኔታውን በጥርጣሬ የሚመለከቱበትና መንግስት የሚወስደውን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ በዝምታ ያለፉበት ሁኔታ የተፈጠረው፡፡ ለዚያውም ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በየአጋጣሚው ትክክለኛውን ጥያቄዎቻቸውን ለማስረዳት ጥረት እያደረጉ፡፡ በዚህ ረገድ ተቃዋሚዎች የመረጡት አካሄድ የጥያቄውን ትክክለኛነትና የገዠው ወያኔ መንግስት እርምጃ ትክክል አለመሆኑን አስመልክቶ መግለጫ መስጠት ብቻ ነው፡፡ጥያቄው የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ በማስረዳት በቂ የሆነ ቅስቀሳ ማድረግ እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ሲገባቸው የተለሳለሰ አካሄድን በመምረጣቸው ተቃውሞው ሰፊ ህዝባዊ ተሳትፎ ሳይኖረው ቀርቷል፡፡ አሁንም ቢሆን ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እድሉ ስላለ ተቃዋሚዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ቅርጽ በማስያዝ የጋራ አጀንዳ ወደሆነው የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት ገርስሶ ወደመጣል ሊመሩት ይገባል፡፡

በሁለተኛነት ማየት የፈለኩት የአሁኑ በኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና ንቅናቄ ሲሆን፡ ህዝባዊ ተቃውሞውን እንደተለመደው ዋነኛው ጥያቄ የኦሮሚያ ክልል ህዝብን ብቻ የሚመለከት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር ችግሩ የጨቋኙ ስርዐት ያመጣው ሆኖ ሳለ እንደተለመደው የጥቂት ሀገወጦች እንደሆነና ችግሩም ከሌሎች ብሄረ ተወላጆች ጋር የተፈጠረ ግጭት ተደርጎ ቀርቧል፡፡

እውነታው ግን ዛሬ በኦሮሚያ ላይ እየተወሰደ ያለው ህገ ወጥ አፈና እና ጭፍጨፋ በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ክልል (መሬት ተቀርሶ ለሱዳን ሲሰጥ)፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች በተለያየ ግዜ ሲወሰድ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ እኔ የምለው ግን የብሄር ግጭት በኢትየጵያ ውስጥ ሆነ ተብሎ የሚጫር ነው ወይስ የብሔሮች አንድ ላይ ተከባበብሮ መኖር አለመቻል? የብሄር ግጭት የሚነሳው ወያኔ የመብት ማስከበር ጥያቄ ሲነሳበት ብቻ ነው እንዴ? በነገራችን ላይ የትኛው ብሄር ነው የእከሌ ብሄር ከክልሌ ይውጣልኝ ብሎ ሰልፍ የወጣው? ወያኔ ግን ሖነ ተብሎ አንዱን ብሄር ከሌላው የሚያጋጩ ነገሮችን በመቆስቆስና የተባበረ አጀንዳ እንዳይኖር በማድረግ  የተባበረ ህዝባዊ ተቃውሞን ማጨናገፊያ ሁነኛ መንገድ አድርጎ ቀጥሎበታል፡፡

ናትናኤል ካብቲመር
ናትናኤል ካብቲመር

ስለዚህ የተቃዋሚዎች የቤት ስራም ማተኮር ያለበት ይህንን የወያኔ ሰይጣናዊ አካሄድ ማክሸፍን ዋና አጀንዳ አድርጎ መሆን አለበት ባይ ነኝ፡፡ የሁሉም ህዝባዊ ጥያቄዎች መነሻቸውም መድረሻቸውም የወያኔ ጨቋኝ ስርዐት መሆኑ በገሀድ እየታወቀ እውነታው እየተድበሰበሰ ሌላ ቅርጽና ይዘት ሲሰጠው በቸልታ መመልከት ለወያኔ አገዛዝ መራዘም ዋነኛ ስትራቴጂ ከመመቻቸት ባሻገር ለወያኔ ህዝብን የመከፋፈል አጀንዳ ስር እንዲሰድ መፍቀድም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በአንድነት ጨቋኙን የወያኔን መንገስት ማስወገድ ዋና ዐጀንዳ አድርገን እንንቀሳቀስ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚነሱት ሁሉም ተቃውሞዎች የጋራ አጀንዳ የጭቆናው ስርአት መወገድ ነው ስለዚህ አዚህ አጀነዳ ላይ አናተኩር ያኔ የሁሉም ጭቆና ማብቂያና መቀበሪያ ይሆናል ተባብረን ወያኔን ከነአስከፊ ጭቆናው ጋር እናስወግደው!!!

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule