• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ውዳሴ መስከረም ወጽዮን

March 19, 2014 08:24 am by Editor Leave a Comment

በብዙ አገሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሴቶችና የወንዶች ቁጥር ብዙም አይለያይም፤ እኩል ለእኩል ይሆናሉ፤ ነገር ግን ይህ የቁጥር እኩልነት በኑሮአችን ላይ አይታይም፤ በ1983 የወያኔ ሠራዊት በየመንገዱ ይታይ በነበረበት ጊዜ አንድ ቀን ወደሂልተን ሆቴል ስገባ አንዲት ልጅ ከቁመትዋ የሚረዝምና ከክብደትዋ የበለጠ ጠመንጃ ይዛ አየሁና ዕድሜዋን ብጠይቃት አሥራ አራት አንደሆነ ነገረችኝ፤ ይቺ ልጅ በዚህ ዕድሜዋ ስንት መከራ እንዳየች እግዚአብሔር ይወቀው፤ በዚያን ጊዜ እንደስዋ ያሉ ብዙ ሴቶች ወያኔዎች አይቻለሁ።

የመጀመሪያው ወያኔ/ኢሕአዴግ ያዘጋጀው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ በጉባኤው ውስጥ አንዲት ሴት ብቻ ነበረች፤ እስዋም ከሠራተኞች ማኅበር የተወከለች ነበረች፤ እነዚያ ጠመንጃ እየተሸከሙ በእግራቸው አዲስ አበባ የገቡትና በየመንገዱና በየመሥሪያ ቤቱ በር ላይ ሲጠብቁ የነበሩ የወያኔ ሴቶች በጉባኤው ላይ በአንድም ሴት አልተወከሉም ነበር፤ ነገሩ በጣም ከንክኖኝ ለመለስ ዜናዊ ነገርሁት፤ ይህንን ጉድለት በማንሣቴ ደስ ባይለውም ስሕተት መሆኑን ተቀብሎ ወደፊት እንደሚታረም ነገረኝ፤ ከዚያም በኋላ ቢሆን ከነጻነት አስፋው ሌላ (የእስዋን አርበኛነት ባላውቅም) በመድረኩ ላይ የምትታይ ሴት አልነበረችም፤ ምናልባት እነዚያ ከጫካ የመጡት እንደ ነጻነት በአውሮፓና በአሜሪካ አልሠለጠኑም ይሆናል፤ እንዲያውም ትንንሾቹን ወያኔዎች ወደትምህርት ቤት ቶሎ ማስገባት ያስፈልጋል ብዬ በመናገሬ ነጻነት አስፋው አንተ ብሎ ለነሱ አሳቢ ብላ ቁጣዋን አውርዳብኛለች፤ ምናልባትም ተማሪዬ በነበረች ጊዜ የደረሰባትን ‹‹ግፍ›› ልትመልስ ይሆናል፤ ዋናው ነጥቤ ግን በወያኔ ዘመን ብዙው ሰው ሲያልፍለት እነዚያ ጠመንጃ ተሸክመው ያየኋቸው እንኳን ሊያልፍላቸው ለዓይንም የጠፉ ይመስላል፤ አሁን በቅርቡ አንዳንድ መደበኛ የትራፊክ ፖሊሶች ሆነው አይቻለሁ፤ በተቀረ ከላይ ተንሳፍፈው የምናያቸው የእንትና ሚስት ወይም የእንትና እኅት ናቸው ይባላል።

ነጻነት አስፋው
ነጻነት አስፋው

እንዴት እንዲህ ሆነ? ይህ እንግዲህ ከአገዛዙ በኩል የጎደለ ነገር መኖሩን ያሳያል፤  ሴቶቹ የተፈለገባቸውን ግዴታ ከወንዶቹ እኩል ከአከናወኑ በኋላ ከመድረኩ የወጡ ይመስላል፤ አገልግሎታቸውን ጨርሰው የወጡም ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወንዶችም ወጥተዋል፤ ግን ይህ ብቻ አይመስለኝም፤ እንዴት እንደገቡ ስለማናውቅ እንዴት እንደወጡ ለመገመት አስቸጋሪ ነው፤ ስለዚህ ወደሌላ አቅጣጫ ብናተኩር ኢሰመጉ (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ) ሲቋቋም ከመሥራቾቹ ቢያንስ ግማሹ ሴት እንዲሆን ያላደረግሁት ጥረት አልነበረም፤ ቢሮአቸው ወይም ቤታቸው ድረስ እየሄድሁ የለመንኋቸው ነበሩ፤ በመጨረሻም የኢሰመጉ አባሎች ውስጥ ሴቶች አሥር ከመቶም አልደረሱም፤ በኋላ ለኢሰመጉ አቤቱታውንና ኡኡታውን የሚያቀልጡት አብዛኛዎቹ ሴቶች ነበሩ፤ ቆይቶም ለቅንጅት እንቅስቃሴ ብዙዎቻችን በተቻለን መጠን የሴቶችን ቁጥር ለማበርከት ከፍተኛ ጥረት አድርገን ነበር፤ ውጤቱ ግን የማያረካ ነበር፤ ዛሬም ቢሆን በየፓርቲዎቹ የሚታዩት አብዛኛዎቹ ወንዶች ናቸው፤ ሴቶች ከአሥር በመቶ እንዳያልፉ የወሰኑ ይመስላል፤ ግን የትና እንዴት ተሰብስበው ወሰኑት!

በጋዜጦችና በመጽሔቶች ላይ የሚጽፉም ቢሆን በእኔ ግምት ከአሥር በመቶ አያልፉም፤ በቃሊቲ እስር ቤት ከርእዮት ሌላ ሴት ጋዜጠኛ ያለ አይመስለኝም፤ እዚያም ቢሆን ያው ከአሥር አንድ ግድም ሊሆን ነው፤ እየፈሩና እያፈሩ ነው እንዳንል ይህንን የሚያስተባብሉ ሌሎች ምክንያቶች አሉ፤ የኢትዮጵያ ሴቶች በማዝናኛው መስክ ያላቸው ድርሻ በጣም የላቀ ነው፤ በዘፈንም በጭፈራም ቢሆን ከወንዶቹ ጋር የማይተናነስ ቁጥር ያላቸው ይመስለኛል፤ በስፖርትም በወንዶችና በሴቶች መሀከል ያለውን ርቀት በጣም እያጠበቡት ነው፤ ሌላም ድርጅት ሴቶች በብዛት የሚገኙበት አለ፤ እድር፤ ታድያ ለሌሎቹ ማኅበራት ሲሆን፣ ለፖሊቲካና ሀሳብን ለመግለጹ ሲሆን ወደኋላ የሚይዛቸው ወይም እንዳይገቡበት ወደውጭ የሚገፋቸው ምን ዓይነት ኃይል ነው? ሌላ ትዝ ያለኝና የሚያስደስተኝ በሥጋ ቤት በላተኛነትም ሴቶቻችን የሚያሳዩት የነጻነትና የእኩልነት መንፈስ ነው፤ ይህንን የኢትዮጵያ ሴቶች በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሳትፎ እንደትንሽ ነገር ሳንመለከተው ጥልቅና ትክክለኛ ጥናት ሊደረግበት የሚገባ ይመስለኛል፤ ይህንን ረጅም መንደርደርያ (እኔ አስተማሪ ሆኜ ይህንን ያህል መንደርደሪያ የሚጽፍ ተማሪ ፍሬ ነገሩ ጥሩ ቢሆንም ከD በላይ አያገኝም ነበር!) መንደርደሪያው ያነጣጠረው ዕድልና ጊዜው ያለው ሰው ይህንን ጉዳይ እንዲያጠና/አንደታጠና ለመቀስቀስ ነው፤ የጽሑፌ ዓላማ ውዳሴ መስከረም ወጽዮን ነው። Olympics Day 7 - Athletics

እንዳመጣጣቸው ቅደም-ተከተል ወይዘሮ መስከረምና ወይዘሮ ጽዮን ለፋክት መጽሔት ብርቅ ጽሑፍ አቅራቢዎች ናቸው፤ ብድግ ብዬ እጅ እየነሣሁ እንኳን ደህና መጣችሁ! ያበርታችሁ! እላለሁ፤ በሀሳብ ማሰራጫው ዓለም ለወጉም ቢሆን ከወይዘሮ መዓዛ ሌላ የለም፤ በማናቸውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለየብቻቸውም ሆነ በቡድን የሚሠሩ ሰዎች የኢትዮጵያን ወንዶች ይወክላሉ አልልም፤ በተጨማሪም ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሆኑትን ሴቶች አይወከሉም፤ ሁሉንምና ማናቸውንም የኢትዮጵያ ጉዳይ ወንዶች ብቻ ያውም ማንንም በትክክል የማይወክሉ ወንዶች (ወንዶች የምለው ሰዎች እንዳልል ነው፤)  ገርድፈው እያቀረቡት ሲወሰን አንድ አገርና ሕዝብ የሚሄድበትን አቅጣጫ ለመገመት አያስቸግርም፤ በምንም ተአምር ወደላይ ሊሆን አይችልም።

በበኩሌ ወይዘሮ መስከረምንና ወይዘሮ ጽዮንን የማደንቃቸው በአእምሮአቸው ለምነትና ንቃት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳቸውም ጥንካሬ ነው፤ የቁልቁለቱ ኃይል በሚያስደነግጥ ሁኔታ እያደገ በመጣበት ዘመን ድምጽን ማሰማትና ለየት ያለ ሀሳብን ይዞ ወደአደባባይ መውጣት አስቸጋሪም አደገኛም በሆነበት ጊዜ የወይዘሮ መስከረምና የወይዘሮ ጽዮን ብቅ ማለት የወደፊቱን አመልካች የሆነ ልዩ ብርሃን ስለሚመስለኝ ደስ ይለኛል፤ የኤፍሬም ሥዩም የቅኔ ችሎታ ቢኖረኝ ለነዚህ ለፋክት አዳዲስ ብርሃናት መወድስ እቀኝላቸው ነበር፤ ወይም አላሙዲንን ብሆን ጠቀም አድርጌ እሸልማቸው ነበር፤ አግረ-መንገዴን አላሙዲን ስለሽልማት ማሰብ እንዲጀምር ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

የህንድን፣ የቻይናን፣ የታይላንድን፣ የመሀከለኛው ምሥራቅን ሴቶች ጠንካራ ተሳትፎ ስመለከት እቀናለሁ፤ የእኛዎቹን ምን ነካቸው እያልሁም ራሴን እጠይቃለሁ፤ በአፍሪካም ሴቶች ፕሬዚደንቶች ሲሆኑም እቀናለሁ፤ ለዚህ ነው መስከረምንና ጽዮንን ብርቅ ናቸውና ብርቅ አድርጌ የማያቸው።

የሴቶችን ተሳትፎ እኔ በቀላሉ አላየውም፤ ትግሉን በስሜት ስለሚገጥሙ የሚያይ ሁሉ ለመሳተፍ ያምረዋል፤ አባቶቻችን ትልቁን ቁም-ነገር አበላሽተው ሴት የላከው ሞት አይፈራም ያሉት በዚህ ምክንያት ነው፤ ፈረንጆች መለስ አድርገው በእያንዳንዱ ትልቅ ሰው በስተጀርባ አንዲት ሴት አለች ይላሉ፤ እንደየቴዎድሮስ ምንትዋብ፣ የምኒልክ ጣይቱ ማለት ነው፤ የምፈራው በዚህም በኩል ሳኡዲ አረብያና የመን እንዳይቀድሙን ነው፤ ሴቻችን ካልተነሣሱ ቆመን መቅረታችን ነው።

ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule