• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ

March 27, 2015 10:01 am by Editor Leave a Comment

ኦነግ ሲከተል የነበረው መንገድ ስህተት እንደነበር በይፋ በመናገር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የተሰኘውን አዲስ ድርጅትና ወኪሎች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት አቶ ሌንጮ ለታ ተቀባይ በማጣታቸው ወደመጡበት የተመለሱት ኦህዴድ ባቀረበው ተቃውሞ መሆኑ ታወቀ። የኢህአዴግ አፈ ቀላጤ የስላቅ መልስ ሰጡ። ኦዴግ (ኦዲኤፍ) በ2012 ምርጫ ሊጋበዝ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታል።

የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በመነጠል ከኢትዮጵያ (“አቢሲኒያ አገዛዝ”) መገንጠልን አማራጭ አድርጎ ለግማሽ ምዕተ አመት ሲወድቅ ሲነሳ የኖረውን ኦነግ ሲመሩ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ተቃውሞ ደርሶባቸው ነበር። የቀድሞው የትግል ጉዞ ስህተት እንደነበር በይፋ አስታውቀው ለድርድር ኢህአዴግ ደጅ የዘለቁት አቶ ሌንጮ ከጉዟቸው በፊት የተነሳባቸውን ተቃውሞ አስመልክቶ በሰጡት ማስተባበያ ከውሳኔያቸው ንቅንቅ እንደማይሉና በመጪው ምርጫ እንደሚሳተፉ አረጋግጠው ነበር።

ባለፈው ሳምንት ይፋ በወጣ መረጃ አቶ ሌንጮና ባልደረቦቻቸው የሚያናግራቸው በማጣታቸው አዲስ አበባን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። የጎልጉል የዜና አቀባዮች ምንጮቻችውን ጠቅሰው ከስፍራው እንዳሉት ከሆነ እነ አቶ ሌንጮ ቀደም ሲል ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ኢህአዴግ እነ ሌንጮ አገር ቤት እንዲገቡ ማስተማመኛ ከመስጠቱም በላይ ሊደራደራቸው ፈቃዱ ነበር። በዋናነት ግን እነ ሌንጮን ኦህዴድ ብብት ውስጥ ማስገባት ነበር ዓላማው።

ኦህዴድ በጉዳዩ ላይ ቁርጥ ያለ አቋም በመያዙና እነ ሌንጮ ድርጅቱ ደጅ እንዲጠጉ ባለመፍቀዱ፣ ኢህአዴግ ለጠቅላይ በሚጫወትበት የምርጫ ወቅት ላይ ኦህዴድን ማስቀየም ከመለስ ሞት ጋር ተያይዞ ተነስቶ የነበረውን ችግር እንዲያገረሽ ያደርገዋል ከሚል ስጋት ህወሃት እንደቀድሞው ኦህዴድ ላይ ጫና ማድረግ አልቻለም። በዚህም የተነሳ  የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ ወይም በእንግሊዝኛው ኦዲኤፍ) የሚያስተናግደው ሳያገኝ ሊመለስ ችሏል።

እነ ሌንጮ ወደ አዲስ አበባ እንዲያቀኑ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ዲማ ነገዎ ሚና ተጫውተው ነበር። በተለይም ፕሮፌሰሩ ኦስሎ በተደጋጋሚ በመምጣት ምክክር ማካሄዳቸውን እንደሚያውቁ የሚገልጹ ወገኖች፣ አቶ ሌንጮ እንዲህ ባጭር ጊዜ ዕቅዳቸው ከሽፎ ይመለሳሉ ብለው እንዳልገመቱ ይናገራሉ።

sebhat abayየጎልጉል የኦህዴድ ምንጭ “አረና እና ህወሃት መካከል ማንም ጣልቃ እንደማይገባ ሁሉ ኦዴግ እና ኦህዴድ መካከልም ይህ ሊከበር ይገባል” በሚል መቃወሚያ መቅረቡ ተናግረዋል። ምንጮቹ አያይዝውም እነ አቶ ሌንጮ በግል አቶ ስብሃትን ማግኘታቸውንና ከዛሬ አምስት አመት በኋላ በ2012 በሚካሄደው ምርጫ እንዲሳተፉ ድጋፍ እንደሚስጣቸው ማረጋገጫ እንዳገኙ አመልክተዋል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የጀመረውን መንገድ እንደሚገፋበት ገልጾዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት የኢህአዴግ አፈቀላጤ ሽመልስ ከማል፣ “አቶ ሌንጮና የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ እንደነበሩ አላውቅም ብለዋል” ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule