የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
ጥር 5 ቀን ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ሌንጮ “ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ሲሉ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን ግልጽ አድርገዋል። “ይሳካል?” በማለት ጠያቂው ላቀረበው “ይሳካል አይሳካም ተብሎ ወደ ትግል አይገባም” በማለት አቶ ሌንጮ ማምረራቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
ህወሃት የዘረጋውን የፌዴራል ሲስተም እንደሚቀበሉትና የኦሮሞ ህዝቦች ጥያቄም በዚያው ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ “በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የተመሰረተ ሳይሆን በህግና በህገመንግሥት በተደነገገ የህዝቦች አንድነት እናምናለን” ብለዋል። የግለሰብ መብት ከብሔር መብት መቅደም አለበት፣ የብሔር መብት አስቀድሞ ሊከበር ይገባዋል በሚል ሁለት አቋም ከሚያራምዱት የተለየ ፕሮግራም እንዳላቸውም አቶ ሌንጮ አስታውቀዋል። የግለሰብም ሆነ የቡድን መብት መከበር አለበት የሚል ፕሮግራም ያለው አዲሱ ድርጅታቸው በዚህ አቋሙ ከሌሎች እንደሚለይ አመልክተዋል።
በምርጫ የመሳተፍን ጉዳይ አስመልክቶ የእሳቸው ድርጅት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ምርጫ ቢገቡ ፍላጎታቸው መሆኑንን አቶ ሌንጮ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከምርጫ በፊት ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፈት ምርጫ ብቻውን መፍትሔ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ህዝብን አገር ቤት ገብቶ ማስተማር፣ መቀስቀስና ማብቃት በዋናነት አስፈላጊ እንደሆነም አስምረውበታል።
ከኢህአዴግ ጋር ድርድር ስለማድረጋቸው ለተጠየቁት፣ እስካሁን የተደረገ ድርድር እንደሌለ አቶ ሌንጮ ጠቁመዋል። አያይዘውም ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋርም የመደራደር እቅድ እንዳላቸው አመልክተዋል። አቶ ሌንጮ በተደጋጋሚ አገር ቤት መሄዳቸው መገለጹንም በማንሳት አስተባብለውታል። አቶ ሌንጮ ድርድር ስለመደረጉ ባያምኑም በተለያዩ ጊዜያት በኖርዌይና በተለያዩ አገራት ከኢህአዴግ መልዕክተኞች ጋር አሁን ይፋ ባደረጉት ጉዳይ ዙሪያ መነጋገራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣም በቅርቡ ኢህአዴግ ብሔር ተኮር ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑንና ከሌሎች ማናቸውም ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ሃሳብ እንደሌለው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
አቶ ሌንጮ የሚመሩት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት መወሰኑን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ “መረጃ የለኝም፤ የድርጅት ሰዎች ብትጠይቅ የተሻለ ነው” በማለት ዜናውን ይፋ ላደረገው የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል። የሚመለከታቸውን አካላት ለማግኘትና በሪፖርቱ ለማካተት እንዳልተቻለ ከሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል። አብዛኛው የኦነግ ደጋፊዎች የነበሩ በድርጅቱ የትግል ጉዞና ውጤታማ አለመሆን መማረራቸውን የተለያዩ ድረገጾች በስፋት ይዘግቡ ነበር።
ለአቶ መለስ ቅርብ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ “አገር ቤት ገብተው ይሳካላቸው ይሆን?” የሚለውን ለመናገር “ህገ መንግሥቱንና ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ተቀብዬ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተስማምቼና ወድጄ ወደ አገር ቤት ለመግባት ችያለሁ” በማለት ኢቲቪ ዜናውን ይፋ ሲያደርገውና “ያሳዘነውን መንግስትና ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲሉ ከተደመጠ በኋላ እንጂ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት እንደሚቸግራቸው አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው ተናግረዋል። “ውሳኔውን ተፈጥሯዊ ጫና” ነው ያሉም አሉ።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በለው! says
>>>>”የብሔር ብሔረሰቦችን ጥያቄ ማስተናገድ ያልቻለ….ተኝቶ ነበረ ሕዝብ ከእንቅልፉ ሲባን እና ሲነቃ…” የኬንያ ኦሮሞ አለ የኢትዮጵያ ጨዋ ኦሮሞ መሆን ይቻላል!… ሕገመንግስቱ የጋራ ተላትን የሸዋ አማራን የበላይነት አጥፍቶ ለሁሉም እና ለእያንዳንዱ የራስ ገዝ መሬት መለያ ባንደራ ሰጥቷል። ሻቢያህወአት ማኒፌስቶ ባለ ራዕዩ የብሄር ብሄረሰቦች አባት እኛ የሞቱ ጠ/ሚ ከተናገሩት>>>
አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል። “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። አቶ ሌንጮ “ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን”
____አቶ ሌንጮ ለታና ጃዋር መሐመድ አንድ የኦሮሞ ባንዲራ ይዘው አንዱ “ኢትዮጵያ እገባለሁ እታገላላሁ” ሲል ሌላው “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ” እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አደለንም! ኢትዮጵያዊነት የአማራ ባህልና ሀገር በግድ የተጫነብን ነን ! ይለውና ቆይቶ ለብሔር ፌደራሊዝም ታላቅ ክብር አላኝ ይህም በእና ትግል የተጎናፀፍነው ፀጋ ነው ይለዋል…ቆይቶ ኦሮሞ መገንጠል አለበት! ፷፭ ከመቶ የሀገር ገቢ ከኦሮሞ ክልል ነው ይለዋል! ከ፴፬ሚሊየን ኦሮሞ ፹ከመቶ ሙስሊም ነውና የሙስሊም ድምፅ የለም! የሙስሊም ኦሮሞ ነፃነት ድምፅ ይሰማ ! ከዚያ በኋላ በአክሱምና በፋሲለደስ ግንብ ጎን መጅሊስ ይቆማል ይለዋል። ቀጥሎም ፖለቲካል ኢኮኖሚውንና መከላከያውን በመቆጣጠር ሀገር መምራት ያለበት ኦሮሞ ነው ይለዋል።
___አቶ ሌንጮ ለታ “ሀገር ውስጥ ገብቼ እታገላላሁ” ሲሉ….ከማን ጋር? ለምን? ይታገላላዩ ብሎ ማሰብም መልካም ነው።
**ትግሉ ከተስፋዬ ግብረእባብ ጀዋሪያን ? ከአቶ መለስ ራዕይ ? ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሀሳብ “በአንድነት ፓርቲ ያሉ የፊውዳሉ ቤተሰብ የልጅ ልጆች አማራዎች ናቸው ስላሉ ለወደፊቱ የአማራ መንግስት መመሥረት ሠግተው ይሆን? ታዲያ..ህወሃት የዘረጋውን የፌዴራል ሲስተም እንደሚቀበሉትና የኦሮሞ ህዝቦች ጥያቄም በዚያው ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ “በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የተመሰረተ ሳይሆን በህግና በህገመንግሥት በተደነገገ የህዝቦች አንድነት እናምናለን” ብለዋል። የሻቢያህወአት ኦነግና ኦብነግ የጋራ ማኒፌስቶ የፀደቀው ነሐሴ ፲፭/፲፱፹፯ ዓ.ም አደለምን ለምን እስከዛሬ ሳይቀበሉት ቀሩ? ምንአልባት አሁን ካርታውን ሲያዩ እንደጃዋር ቋምጠው ይሆን!?
____ለመሆኑ ኦሮሞ ምን ጎደለበትና ነው አቶ ሌንጮ ዘራፍ እታገላላሁ ያሉት? የፈረደበት ኦሮሞ ከማን ሲቧደን ሊኖር ነው?
Oromia Creates 900,000 Jobs not babies!
Close to 900,000 jobs were created in Oromia Regional State during the concluded budget year. While evaluating the 2012/13 performance report, Oromia Industry & Urban Development Bureau head, Abdulkader Hussein said the performance exceeds the target by 100,000. He said the plan was to create jobs for 800,000 people during the reported period. Animal fattening, agriculture, services, tourism, manufacturing, trade, and construction as well as wood and metal works are among the areas the jobs were created.
Publication: The Ethiopian Herald, Thursday, August 29, 2013.
State Creates 212,000 Jobs
Tigray Regional State has created jobs for 212,000 people over the concluded budget year. , the State micro and small scale enterprises agency said. Speaking in a relevant meeting held in Melekele Town to evaluate the 2012/13 fiscal year performance, development and planning head with the Micro & Small Scale Enterprises Agency, Asefa Tegegn said 83,450 of the beneficiaries are women. He said that the jobs were created in construction, metal work and agriculture areas.
Publication: The Ethiopian Herald, Wednesday, August 28, 2013. .. read more (sours Ethiopian review)
(ለመሆኑ ጃዋር መሐመድ፣ ተስፈዬ ግብረእባብ፣ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ኦሮሞ ገድሎ የሰፈረበትን መሬት ሁሉ በሻቢያህወአት ተሰጥቶት እየዘረፈ እገደለ እየኖረ ለምን የአዞ እንባ የቁራ ጩኸት ያሰማሉ? ለአቶ መለስ ቅርብ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ “አገር ቤት ገብተው ይሳካላቸው ይሆን? ምኑ (ኦፌዴን፣ኦሕዴድ…ኦ..ኦ..)ሊጋቡ ነው ሊዋጉ? አቶ ሌንጮና ጃዋር ምንም የሚጠይቁት አይኖርም ቋንቋችን፣ መሬታችን፣ ሰውነታችን፣ ክልላችን፣ ዕድገታችን በሕገመንግስቱና በብሄርና ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ተከብሯል ብለዋል። ተጠይቀው የሚመልሱት ግን ብዙ ነገር ይጠብቃቸዋል።
**“ህገ መንግሥቱንና ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ተቀብዬ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተስማምቼና ወድጄ ወደ አገር ቤት ለመግባት ችያለሁ” በማለት ኢቲቪ ዜናውን ይፋ ሲያደርገውና “ያሳዘነውን መንግስትና ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን” ፅንፈኛውን አሸባሪውን ነፍሰገዳዮችን ጨምረው በማጋለጥ እራሳቸውን ንፅሕ መሪ መሆናቸውን ሲያስመሰክሩ ዴሞክራሲ የሚያምኑ ለተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲነት ብቁ መሆን በእሳቸውና በአንጃዎቻቸው ተጀመረ ይባላል። አለበለዚያ መለስን አስቀድመው ከኋላ ሀገር ሲሸረሽሩ የኖሩ ገድለው ከፊት ቀድመው ማልቀሳቸው የተለመደ የጫካ አብዮት እንጂ ዴሞክራሲዊ የሰለጠነ ፖለቲካ ተብሎ መቦልተክ የለበትም በለው!!ታላቋ ኢትዮጳያ ከመላው ሕዝቧ ጋር በሰላም ለዘለዓለም ትኑር ፅንፈኞች አመፀኞች ሜንጫ አብዮተኖች ከኋላ የቀረውን ሳይሆን ወደፊት የቀደመውን በማየት ይማሩ! ኢህአዴግ ፭ዓመት ለሽግግርና መጥፎን ከደግ ለመለየት፣ ፲ዓመት ለሽግግርና አብሮ መሥራት፣ በ፳ ዓመት በግልፅ ተወዳድሮ ተሸንፎ በሌላው ላይ ትችት የማቅረቢያ ግዜ ነበረው አልተጠቀመበትም። ወደፊትም ያደርገዋል ለማለት ይስቸግራል አዋጪው የሚበላበት የተሳሳተ መንገድ.. ማሸበር፣ ዳርድንበር መቀነስ፣ ከውስጥ ማፍረስ፣ ከዳር መሽረፍ፣ከመሐል መሸጥ ብቻ “ቀለም አልባ ልማታዊ ብቸኛ ከራሱ ተወዳድሮ እራሱን የሚያሸንፍ መንግስት ሆኖ ይዘልቃል። እንግዲህ በ፶ዓመት ያልተማሩ፣ በ፵ዓመት ያልነቁ፣ በ፳፪ዓመት ያልተጠነቀቁ እየው በእየተራ እየሳቁ አለቁ! በለው!!ሰላም ለሁሉም ይሁን በቸር ይግጠመን።
Bariisoo says
Ato Belew,
when the Wests are keeping the Africans at least for 500-700 years behind you are dreaming and sing the same song day and night. the song of my way was/ is the high way. when you beat the drum to sing my way the high way; kingship has gone once for all, Eritrea has gone once for all,do you want repeat the same? I think you are not serious, think positively and do your part and come up with solutions.look the Americans since 1788 they made some amendments but not change their constitution.when you come to poor Ethiopia the Ethiopian constitution and laws are changed with the leaders.Teferi came his constitution and laws gone with him. Mengistu came and his constitution and laws gone with him. no one can tell with certainty what will follow after WEYANE.Therefore it is not a matter of teasing or painting some one or others what they are actually not. it is a matter of people concern. when you and your likes still dreaming about the past glory and nonsense pride the people are suffering with untold humility and debasement around the globe.your acidulous comments and negative approach will not deter well seasoned politician of the horn to do what he planned to do for the people. Habeshans are stones in river that cannot learn to swim no matter how long they stayed in the water.When he tried to convince us to democratize Ethiopia bare handed Oromo told him that because of habeshans nature democracy and justice will not prevail in that cursed land.H e is going to reap what he sow,already you started to make him confess and ask pardon from you habeshans.Dont worry I think he is determined to face everything but one thing you don’t know is that the Bigs are behind him.take care!!
በለው ! says
ክቡር ባርሊሶ…አቺኑ አመመችኦወን ክፍል አደግማታለሁ። ለማንም ማንም ብሔርና የፖለቲካ ፖለቲካ ተንታኝ ሰብሳቢና በታኝ አጋፋሪ አደለሁም!!።
____አቶ ሌንጮ ለታና ጃዋር መሐመድ አንድ የኦሮሞ ባንዲራ ይዘው አንዱ “ኢትዮጵያ እገባለሁ እታገላላሁ” ሲል ሌላው “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ” እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አደለንም! ኢትዮጵያዊነት የአማራ ባህልና ሀገር በግድ የተጫነብን ነን ! ይለውና ቆይቶ ለብሔር ፌደራሊዝም ታላቅ ክብር አለኝ ይህም በእኛ ትግል አማራን አጥፍተን የተጎናፀፍነው ፀጋ ነው ይለዋል…ቆይቶ ኦሮሞ መገንጠል አለበት! ፷፭ ከመቶ የሀገር ገቢ ከኦሮሞ ክልል ነው ይለዋል! ከ፴፬ሚሊየን ኦሮሞ ፹ከመቶ ሙስሊም ነውና የሙስሊም ድምፅ የለም! የሙስሊም ኦሮሞ ነፃነት ድምፅ ይሰማ ! ከዚያ በኋላ በአክሱምና በፋሲለደስ ግንብ ጎን መጅሊስ ይቆማል ይለዋል። ቀጥሎም ፖለቲካል ኢኮኖሚውንና መከላከያውን በመቆጣጠር ሀገር መምራት ያለበት ሙስሊም ኦሮሞ ነው ይለዋል።
“___ለአቶ መለስ ቅርብ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ አቶ ሌንጮ ለታ “ሀገር ውስጥ ገብቼ እታገላላሁ” ሲሉ….ከማን ጋር? ለምን? ይታገላሉ? ከ(ኦፌዴን፣ ኦሕዴድ…ኦ..፬ ኦ… ፭ )ሊጋቡ ነው ሊዋጉ? አቶ ሌንጮና ጃዋር ምንም የሚጠይቁት አይኖርም ቋንቋችን፣ መሬታችን፣ ሰውነታችን፣ ክልላችን፣ ዕድገታችን በሕገመንግስቱና በብሄርና ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ተከብሯል ብለዋል። ተጠይቀው የሚመልሱት ግን ብዙ ነገር ይጠብቃቸዋል።” “He is going to reap what he sow,already you started to make him confess and ask pardon from you habeshas.Don’t worry I think he is determined to face everything but one thing you don’t know is that the Bigs are behind him.take care!! ይህ ሀቅ ነው መሰከርክልኝ ። (ጌታዋን የታመነች በግ ላቷ ውጭ ያድራል ይባል ለምን!?) ሠላምን እሻለሁ የሰዎች እኩልነት ሰብዓዊ መብት፣ አንዲከበር መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ፅንፈኛ፣ ዘረኛ፣ ኋላቀር፣ ጎጠኛ ከፋፋይ አሸባሪ፤ የሜንጫ አብዮተኛ አይመቸኝም ይጠፋል። ተጨማሪውን ከአቶ እዝራ አስተያየት አንብቡና ይማሩ! በቸር ይግጠመን<<<
ezra says
ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ። ዮሃንስ ለታ ታዲያ ምን ያሰባል ? ከትንንሽ ጭንቅላቶች የሚታሰበው ትንንሽ ነገር ነው። ዮሃንስ ለታ ትናንት በ1993 የሻቢአያ ጫማ ጠራጊ ነበር …ቆይቶ ደግሞ ለሌላው ጌታ በጉዲፈቻ ተሰጥቶ ለለገሠ ዜናዊ ጎንበስ ቀና ሲል ቆይቶ 17.000 ጦሩን በካምፕ ዉሰጥ አስረክቦ በአለቃው ፓስፖርት ተዘጋጅቶለት ስራ እንዲሠራ ወደ ኖርዌይ ተላከ። አሁን ግዳጁን ፈፅሞ ወደ ጙዲፈቻ አሳዳጊው አባቱ ወደ ኢሕአዴግ እሄዳለሁ እና ሰንቅ ሰንቁልኝ ቢል ምን ያስገርማል?
Bariisoo says
Ato below
thank you , you teased me a little with “kubur”. First you didn’t get my message second you try to interpret on the basis of your interest consumption.Really are you serious to call those active Oromo activists as extremists,racists, backwards,,etc?,well it is up to you, if you continue like this, one thing is clear the more you hate or eliminate those bright minds the stronger and determined they are for their cause.Hate is not politics.because of your big mouth or get all and lose all thinking you deteriorate things.when you have no the chance to kill people as you did in the past you are engaged in character assassinations.For some one who observes such behaviors, it is simply a replica of Fascistic or Nazis characters.The main characteristics of fascist are they worship State, leaders, their ethnic supremacy more over they are emotional,irrational,subjective. just look yourself in this Fascist and Nazis mirror.such tendencies cannot be categorized under right or left but mixed up orientations that confuses itself and others.when you are sick for past glory nostalgia we are fresh to restore our lost freedom.you can hate and covet but it makes you more sick and sick.you ordered Ezra to respond and he did it. what a shame of you to do that.
በለው! says
“ልጅ ባርሊሱ….Bariisoo says:
January 16, 2014 04:07 am at 4:07 am
Ato getachew bekele,
well it is very interesting to be clear and concerned to promote ones’ interest.you tried to challenge the challenges but it is not fair to promote hidden agendas by painting others what they are not or trying to worry about non existant challenges.when Africans are fighting each other for none existant wars the civilized nations keep us behind for atleast 500-700 years.you come up with two options.both options are dangerous to current scenario.Those who claim their own history ,culture and religion are not ready to accept what imposed by others as common history,culture and religion.Always where there is civilization conflicts there is opposing parties;ideas and continues frictions and wars.Two sharpend blades can only damge each other. The only better way is to think positively and win _win scenario.Again we are at the turning point of history:In the firstturing point kingship was gone once for all. in the second turing point Eriterea was gone once for all. Now no body can exactly tell what is in pregnancy again in this turning point.I think all sides should make cautions before proposing something as solutions.
ይህ ሙሉ ቃል እኛ ከሞቱ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የተወሰደና በሁሉም ድረገፀች ለሁሉም የሚመለስ መርዝ ነው። ለዚህ ነው ብዙዎች ገና የሚያስቡት ያለፈውን ፶ዓመት በፊት የነበረን ወሬ እነጂ ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም፣ ለድሃው ኦሮሞ…ንጽሕ ውሃ፣ ለወገቡ አልጋ፣ ለእግሩ መጫሚያ፣ ለልጆቹ ዳቦና ትምህርት፣ ለእናቶች ከኩበት ጭስ…ካቲካላ እሳት ከመጠበስ አያስጥላቸውም።..ቋንቋቸውን መናገር ልዩ አያደርጋቸውም ቁምነገሩ ዳቦ ሲሉ ማዳመት ነው። ሆድዳርና ባንዳ ልጆቻቸውም የሚያስተምሯቸው መሻሻል ሰላምን ይቅር ባይነትን ሳይሆን “የሜንጫ አብዮት አንስተው ማጫረስ፣ የጡት ሐውልት፣ የቆለጥ ማስታወሻ፣ እያሉ ኮፒተር ላይ ቂጣቸውን እያለፉ..በፓል ቶክ እነዳህኦቻቸው እያናፉ፣ በመሸታ ቤት ኮረዳ እያሹ..ሆድና ቂታቸው ባበጠ ቁጥር ህዝብ የሰለጠኑና ጨረቃን የነኩ የሚመስላቸው ጨለምተኞች የሚሽነሪስት ሹምባሾች እንዲሁ ለማፍረስና ደም ለማፋሰስ እንደተቅበዘበዙ ይኖራሉ ብልጦቹ እአባሉ ይበላሉ ድሮስ በሻቢያ ተገርፎ ቂጡን ተገርፎ በሚሽነሪስት በፋፋና በወተት ዱቄት ያደገ ምን ይማራል…ይደነቁራል እንጂ! ጥሩ ሰው ትሆናለህ ግን ስሜን ጠርተህ ከጠየከኝ መን ስምህንና ቋንቃህን ብትቀያይር በቀላሉ ማ..ምን አለ? ማ የተፋውን ልሶ ነው የሚተፋው አውቀዋለሁ። አትሳሳት መናጆም አትሁን ህዝብን አስተምር ፈውዳልም ጉልተናም ሄዷል አኔና እናንተም በተራችን ግን አጥፍቶ መጥፋት ከአሸባሪነትም በላይ የሀገርና ህዝብ ክህደት ነው። …Really are you serious to call those active Oromo activists? well it is up to you!
Bariisoo says
Ezra, you are the scum of the society.when you are civilized enough to think as human being then you worth response.no more response to shit like you.
dulby says
Sorry to say this, but it makes me wonder if threr if is a BRAIN left in this Lechod skull?
jarso says
Lencho is a dead beat whose one feet is almost in grave yard as he almost in his last gasp after he laboured and advancing, in vain ,c l ue les and worst rancid ethnic poltics for almost a decade .Now he fall from grace after he surrendered to woyane and declared that he has decided to move to Ethiopia to fight along with the Oromo people . Infact it is a smart move in terms of securing a place where he could enjoy the rest of his life in retirment with tranquility by winning a seat in Woyane ‘s manipulated Parliament .What else can he achieve for the Oromo’s other than subdue and set a stage for woyane to crack fun and making a laughing stock of the oromo people and its struggle. That is it .
ezra says
Dear Bariisoo
pls Do Not Talk bila bila okay. we know very well who is Lencho (Yohanes Leta ) and all OLf’s Gangster too
tolossa says
አቶ ሌንጮ አሁን ቱጃር ሆነዋል፡፡ ስለዚህም ሀገር ይገባሉ፡፡ ‹‹..የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል።..›› የሚል ዜና አይቼ አዘንኩ፡፡ የአንድ ጎልማሳ እድሜ ቅርጥፍ አድርጎ የበላው ኦነግን ሲመሩ ነበሩት አቶ ሊንጮ ይህን ካሉ ሌሎቹስ? አሁንም ኦነግ በማንም አፍራሽ መልዕክተኛ መፍረስ የለበትም ባይ ነኝ፡፡ መልዕክተኞች መሀላችን እየተሰገሰጉ ሊከፋፍሉን አይገባም፡፡ ስንት አመት በጦርነት ያልሆነ ነገር በሰላም ትግልስ የሚሆን ይመስላል?
ዛሬ የኦሮሞ ልጅ ነጻ ወጣ እንዴ ቀንበሩ ተነሳለት? ያኔ ምን አይተው ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ትግል ብለው ተነሱ ዛሬ ምን ተገኝቶ ጓዛቸውን ሸከፉና ወደ ሀገር ለመግባት ተነሱ? ከህዝቡ መዋጮ ሰበሰቡ ሀብት አካበቱ በቃ….! ዛሬ ጁዋርም ገና ማስተርሱን ሳይሰራ በአለቆቹ የፖለቲካ ተንታኝ የሚል ታፔላ ተለጠፈለትና ጩኸቱን በሰፊው ያቀልጠው ጀመረ፡፡ ጁዋር ኬሳ ኬሳ…ክፍል አንድ ላይ ለጠየኩት አራት ጥያቄ አንዱንም መመለስ እንደማይችል አውቃለሁ፡፡ አውርቶ ጀብደኛ መሆን እንጂ ሰርቶ ለኦሮሞ ህዝብ ለውጥ ማምጣትን አያስበውም፡፡ መሰሎችም እያስቡትም፡፡ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው የሚለው ነገር ሲሰማ አንድ ወዳጄ ታዲያ ምን ችግር አለው ፖለቲካ እንዲህ ነው ያለኝ ከልብ አስቆኛል፡፡ አናዶኛልም፡፡ በቃ! የኢትዮጵያ ፖለቲከኛም ሆነ ፖለቲካ አወኩ የሚለው ሁሉ ፖለቲካን ዋሽቶ ማለፍ ጊዜያዊ ድለላ አድርገን እያየን እስከመቼ እንጓዛለን፡፡