ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው እውነተኛ “ትራንስፎርሜሽን” ከሁከት ይልቅ ውይይት፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፣ ከብቀላ ይልቅ ይቅርታ መሆኑን በማስገንዘብ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በግል ደብዳቤ መላኩን አስታወቀ፡፡
ንቅናቄው በደብዳቤው መልካም ተግባር በመፈጸም በትውልድ ሁሉ “ታላቁና ደጉ መሪ” እንዲባሉ ምኞቱን ገልጿል። ንቅናቄው ለጻፈላቸው ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ይሰጣሉ የሚል ሙሉ እምነት እንዳለው ለጎልጉል በእርግጠኝነት ተናግሯል።
ኢትዮጵያ የሁሉም አገር እንደሆነች በማስታወቅ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር ፊርማ የተላከው ደብዳቤ አቶ መለስ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥሪ ሲቀርብላቸው ባለመቀበል ለህዝብ መንገድ ንቀት ሲያሳዩ ማለፋቸውን ያስታውሳል። የአንድ ጎሣ፣ ብሔር፣ ቡድን፣ ሃይማኖት፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ብቻውን መግነን እንደሌለበት የተቆመው አኢጋን “ኢትዮጵያውያን ከፈጣሪ የተሰጣቸውን መብት እንደገና ይጎናጸፉና ይለማመዱ ዘንድ እርስዎ የሚወስዷቸው ደፋር እርምጃዎችና ቀልጣፋ አመራሮች ወሳኝነት አላቸው” ሲል አቶ ሃይለማርያምን አደራ ይላቸዋል።
“በአሁኑ ጊዜ እርስዎ የአገር መሪ ሆነዋል፤ ይህም ማለት እርስዎ መሪ የሆኑት ለወከልዎት ፓርቲ/ግንባር (ኢህአዴግ/ደኢህዴን/ህወሓት…) ወይም ከእርስዎ ጋር ለሚስማሙት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ከእርስዎም ሆነ ከድርጅትዎ ጋር ለማይስማሙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ …” መሆኑን በማስገንዘብ አቶ ሃይለማርያም ሁሉንም ያካተተ እርቅ እንዲወርድ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረበው አኢጋን፤ ቀናነት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አስምሮበታል።
“አዲሲቷ ኢትዮጵያ” እንድትመሰረት የቀደመችው ኢትዮጵያ መታደስ እንደሚኖርባት፣ ይህም ተሃድሶ እኩልነትን፣ ሰላምን፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ዕርቅን መሠረት በማድረግ “ከጎሣ ይልቅ ሰብዓዊነትን በማስቀደም” እንደሚገባው፣ የገለጸው ደብዳቤ ሲቀጥል “ሰብአዊነትን ማስቀደም በቀደመውም ይሁን በአሁኑ እርሳቸው በሚመሩት የኢህአዴግ አገዛዝ ሥር ለሚገኙት መብታቸው ለተነፈገ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም እርስዎንም ጨምሮ ለእያንዳንዱ የደኢህዴን፣ የኦህዴድ፣ የህወሓት፣ የብአዴን … ኢህአዴግ አባላትም ጭምር የሚጠቅምና ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣ የኢትዮጵያ ፈውስ ነው። በዚህ መንፈስ የምትመሰረተው አዲሲቷ ኢትዮጵያ ዘረኝነት የመከነባትና ከፈጣሪ የተሰጡ መብቶች የተከበሩባት እንደምትሆን እንደ አቶ ሃይለማርያም አይነት መንፈሳዊ ሰው በቀላሉ የሚረዳው እውነት” እንደሆነ አመልክቷል።
“በልጅነቱ ሐኪም የመሆን ሕልም የነበረውና ከወንድሙ ጋር ወደ ትምህርት ቤት በኪሎሜትሮች የሚቆጠር ርቀት በመጓዝ ትምህርቱን የተከታተለው የቦሎሶሬው ወጣት ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ብሎ ያሰበና የገመተ ማን ይሆን?” ሲል የጠየቀው ደብዳቤ፤ ከፈጣሪ ዕቅድ ውጪ ይህንን ሊያስብ የሚችል አንዳችም ፍጡር እንደሌለ ይጠቅሳል። በማያያዝም “በእንደዚህ ዓይነት ወቅት ባማረ የአበባ ስፍራ በምትመሰለውና እያንዳንዳችንም አንድ ውብ አበባ በመሆን ትልቁን የኢትዮጵያን እርሻ የምናሳምርባት አገራችን መሪ መሆንዎ እንደ ንግሥት አስቴር ፈጣሪ ለዚህ ጊዜ ለምክንያት ያደረገው ይሆን?” በማለት ፍትህና ርትዕ ለተጠሙ ህዝቦች አቶ ሃይለማርያም መልስ እንዲሆኑ ተማጽኗል።
እስረኞችን በመፍታት፣ የተለየ ሃሳብ ካላቸው ጋር ሁሉ በግንባር በመነጋገር ለኢትዮጵያና ህዝቧ ባለውለታ እንዲሆኑ ጥሪውን አስተላልፏል። “አገር በሰውነት ክፍል ይመሰላል፤ ከሰውነት ክፍል አንዱ ሲጎዳ ሁሉም ይታመማል፤ ሁሉም ይጎዳል፡፡ ይህ በሰውነት ክፍል የመሰልነው የሁላችንም መኖርያና መመኪያ የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዚህች አገራችን ውስጥ የታመሙ የሰውነት ክፍሎች አሉ፡፡ እነዚህን ክፍሎች በጥቅሉ “አሸባሪ፣ ለሕግ የማይገዙ፣ ባለ ሁለት ባርኔጣ ለባሾች፣ …” ከማለት በፊት ህመማቸው ምን እንደሆነና ለዚህም ህመማቸው ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ተገቢው መንገድ ነው፡፡ ይህንን ሲያደርጉ ፈጣሪ ከእርስዎ ጋር ይሆናል፤ ሕዝብም ከጎንዎ ይቆማል፡፡ እምቢ በማለት ግን የታመመውን ክፍል ከማከም ይልቅ “ማስወገድ ነው፤ እርምጃ መውሰድ ነው” የሚል ግትረኛ መንገድ የሚከተሉ ከሆነ በጥቂቱ የተጎዳው የሰውነት ክፍል አመርቅዞ መላውን ሰውነት ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል፤ እርስዎም ለብቻዎ የሚቆሙ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ወቅት የደቡብ ክልል ወይም የድርጅትዎ ተወካይ ብቻ ሳይሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ መሪ እንደመሆንዎ ሕዝብን ለማዳመጥ ጊዜ መስጠት” እንደሚሻላቸው የመከረው ደብዳቤ በቀጥታ የተጻፈው በአድራሻ ለራሳቸው እንደሆነ ንቅናቄው አስታውቋል። ንቅናቄው አዲሱ ጠ/ሚኒስትር እንደ አቶ መለስ የእርቅና የሰላምን መንገድ ወደ ጎን ይተዋሉ የሚል እምነት እንደሌለውም ለጎልጉል አስታውቋል። የደብዳቤውን ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Ta says
what a wonderful message in deed! I love it and if PM HMD read this article, he will definitely respond to the letter.
keep on doing good always!
Sergute Selassie says
የእንጀራ እናት።
የእንጀራ እናት የሚለው ቃል በተለምዶው — እንደ እኔ ቃሉ እራሱ እንጀራ ከመሰለ ዘንከታ፤ ለረሃብ ደራሽ ከሆነው የባህል ማእከል ጋር ተገናኝቶ ድርጊቱ ግን በአመዛኙ የሳጥናኤል መሆኑ ሁልጊዜም የማዝንበት ነው። እኔ እንኳን ዛሬ እንጀራ እናት የሚለውን ያነሳሁት ያቺ ለልጆች ጡት ፍለጋ ማስታገሻ የምተሰጠውን በባዶ አዬር ብቻ የተሞላችውን ጡጦ ማለቴ ነው። ሰው ሰራሿን ፕላስቲክ …። አዎን የጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ራዕይም ይህው ነው። አንድ ሰዓሊ እሷን ከአፋቸው አስገብቶ ቢስልልኝ እንዴት የልቤን ባደረሰ … ሄሮድስ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ልባቸውን አስገብተውላቸው ከሄዱት ተዋናዮች አንዱ አዲሱ ጠ/ሚር አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ናቸው። አማኝነታቸውማ ትናንትም ነበር ደምን እያዬ … አሁንም በእግር ብረት የታሰረውን ሰባዕዊ መብት እዬተሳለቀ …
ሟቹ ጠ/ሚር በጡረታ የመገለልን ህግ ሲያጸድቁ የደረደሩት ያ … ሁላ ጥቅማጥቅም እራሳቸውን አስበው ነበር። እንደ ታመሙ ስለሚያውቁ። ይህም ብቻ አይደለም እሳቸው ከሥልጣን ሲለቁም ልባቸውን ያሰገቡላቸው ወ/ ሮ አዜብን አስበው ነበር። በጡሩታ እሳቸው ሲገለሉ ከሙሉ ጥቅም ጋር፤ ባለቤታቸውን ደግሞ በቀጣይ ጠ/ሚርነት ድርብ ተጠቃሚ ለመሆን ነበር ህልሙ። እንጂ … ለአቶ ኃይለማርያም አስበው ፤ ዕምነትም ኑሯቸው አይደለም። ያው … ከተጠቀሙ በኋላ እንደ ሌሎቹ … ነበር የታሰበው። ባይሆን ሞት ቀደማቸው እንጂ …
ለማንኛውም ሰው ያልደረሰበት የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ፍልስፍና በሸፍጥ የተቀመመ ነበር። ማንነትን ከውስጥ በስደት መሰንጠቅ። የሚያሰጠጓቸው ሰዎች ሁሉ ማንነታቸው መንታ መንገድ ላይ የተገተሩትን ብቻ ናቸው። ለዚህ ሁለት ናሙና ልስጥ ..
ካህዲዋ – እትብትን ለማጫነት ለታላቋ ትግራይ ራዕይ የሸለሙት ወ/ሮ አዜብ የትግሬ ዝርያ ፈጽሞ የለባቸውም። ዘረ መሰረታቸው ጎንደር ወልቃይት ልዩ ስሙ የቃብቲያ ተወላጅ ናቸው። ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራን ጨምሮ የሥራ፤ የትምህርት የለቅሶ፤ የማህበራዊ ቋንቋው አማርኛ ነው። ትግረኛ ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ነው። እንዲያውም አማርኛ ቋንቋ ልጆች ተኮላፍተው ሲናገሩት እንኳን የአማርኛ ክብሩ ተናካ ዬልጆች መጫወቻ ሆነ ብለው ይቆጡ ከነበሩት ውስጥ … ጎንደሬ በጋሻው ላይ ታሪካቸው የተጻፈው ጀግና አባ ሻንቆ መለሰ ኃይሉ ይገኙበታል። ለአማረነቱና ትውፊቱ የቀደሙት የተለዬ አክብሮትን ትህትና የነበረው ትውልድ ነበር።
በሌላ በኩል አሁንም አንድም የወልቃይትና የጠገዴ ሰው ወደ ከተማ ለመኖር ቢያስብ ጎንደር እንጂ ትግራይን ፈጽሞ በህልሙ እንኳን አያስበውም። አብዳችኋል እንደሚሉ ነው የሚደመጡት። ምን ለማለት ነው … የአቶ መለስ ዜናዊ ፍልስፍና ማንነት ያለውን ውስጥ አውጥተው አርቲፊሻል መለስ የሆነ ሰው ሰራሽ ማንነት አስገብተው ይገጥማሉ። ጥሩ የጋራጅ ሰው ነበሩና … ፍልስፍናቸውም ያለ ተቀናቃኝ አቆይቷቸዋል። ይገርማል ሞተው እንኳን እዬጠቡት ነው በደመነፍስ … አገሮቻቸው ….
ስለዚህ ወ/ሮ አዜብ እንደ ትግሬ መሆን አይችሉም። ልሁን ቢሉም አያምርባቸውም። እነሱም አይቀበሏቸውም፤ አያስጠጓቸውም፤ ተቆርቋሪ ነኝ ለማለት ቢሞክሩ ያድጣቸዋል … ላጥ ያለ ገደል ይጠብቃቸዋል። እንደ አማራ ነኝ ማለትም አይችሉም በሰላም ያረፉትን አጽሞች ሁሉ ትግሬ ነበራችሁ በማለት ያሳወጁ፤ የመቃብር አጽምን የረገጡ፤ በዘር ማጥፍት ወንጀል በክልሉ እዬተፈጸማ አጋፋሪ የነበሩ …ናቸው። ስለምን ማንነታው አልነበርም ተስዷል … ሁለት ያጣ ጎመን። መጠጊያ ግን ነበር የሄሮድስ ኢትዮጵያን የማጥፍትና የታላቋ ትግራይ ራዕይ … እሱም አፈር ቅሟል። ሃፍረት – ውርዴት – መሸማቀቅ፤ ጥግ አልባነት – ከታሪክ መሰረዝ የወ/ሮዋ ዕጣ ፈንታ ነው … ዘመን ይቅር የማይለው … ስርዛትን ተከናንበው … እንደ አጎነበሱ ይኖራሉ። ቀና ማለት ፈጽሞ አይችሉም። የተሰበረ ቅስም።
ሁለተኛው አቶ በረከት ስሞኦን ጎንደር ከተማ ሰፈረ አንባጅኔ ከአቶ ገ/ሕይውትና ከወ/ ሮ ብሬ የተፈጠሩ ኤርትራዊ መሆናቸው አደባባይ የዋለ ጉዳይ ነው።። አባታቸው አባ ገ/ሕይወት የህንጻ ሥራ ባለሙያ ነበሩ። እማም ብሬ ደግሞ ሱቅ ነበራቸው። ሁለቱም በሰላም ተስማምተው፤ ተጎራብተው፤ አበልጅነት ተናስተው ይነሩ ነበር። በልጅነት ትውስታዬ ውጪያቸውን በዚህ መልክ አውቀዋለሁ። ውስጣቸውን ግን እንኳንስ እኔ በዛ ዕድሜዬ ወላጆቼም ዬሚያውቁት አይመስለኝም። ሱቃቸው ግን ደንበኛ ነበርኩ። ስላክ ከጨዋ ሰፍር አንባጅኔ እራቅ ቢልም እሄዳለሁ። ስለምን የእማማ ብሬ ምርቃት ከረሚላ ስለ ነበር። ዘይትም ተገዛ ሱካር ያው ድንቡልቡሏ ነጭ የአረቂ ከረሚላ አይቀሬ ነበረች። ለጉንፋንም ትረዳ ነበረች። …
አሁን ይህን ነጥብ ያነሳሁት ወ/ሮ አዜብ ጎንደሬ ግን የትግሬነት ሰብዕና ተገጠመላቸውና ተገቡ። ጎንደርን ለመጠቅለል የታላቋ ትግራይን ራዕይ ለማሳከት፤ በተሟላ ዕቅድ የተከናወነ ጋብቻ ነበር። አቶ በረከተም ኤርትራዊ ለዛውም የአማራ ሰብዕና ተገጠመላቸው። ሁለቱም የራሳቸው ሰብዕና የሌላቸው ናቸው። አሁን እስኪ እሰቡት በዛ የሥልጣን ቦታ ያን ያህል ውሸት … የአቶ መለስ ዜናዊ ህመም እስከ ህልፍት የሰጡት መግላጫ ውጥንቅጥ አስቡት። የኔ የሚሉት የውስጥ ማንነት ሆነ በራስ የመቆም አቅም የላቸውምና። ተብልቷል፤ ተመልምሏል። ዝም ብለው ቀፏቸውን አቁመው ነበር እኮ ሲጫወቱባቸው የኖሩት። እንዳይደፍሩ ኤርትራዊ ተብለው ይጠረጣራሉ። እንዳይዘልቁ ደግሞ የተነደለና የተንጠለጠለ መሬት ያልያዘ ማንነትን አግብተዋል።
አቶ መለስ በሥልጣን በነበሩባቸው ዘመናት ሁሉ በዙሪያቸው የነበሩት ሁሉ ስታሥሱት ሃቁ ቁልጭ ብሎ ይታያችኋል። ትክክለኛ ኦሮሞ ያለሆኑትን በቃ የኦሮማ መሪ ያደርጓቸዋል። ማህል ላይ የሚገትር ሰው ሰራሽ ሰብእና ይገጥሙላቸዋል። አቶ አዲሱ ለገሰንም በሚመለከት እጅግ በሚገርም ሁኔታ ነው ውልቅልቃቸውን አውጥተው አማረነትን የገጠሙላቸው። እንጂ አቶ አዲሱ እማ …
ስለሆነም በረቀቀ ስልትና ዘዴ ማንነቱን ያጣ፤ መንፈሱ የተሰረቀ – ሽብሽብ፤ ያዳጠው – ህሊና ፤ ለመወሰን የተሳነው -ጥገኛና አቅመ ቢስ ማንነት ፤ አገጣጠመውና ልብስ አልበሰው በፕሮቶኮል ቀፎውን ኮፈሰው አኖራቸው። ስለሆነም — ወኔው ሁሉ መቅኖ ቢስ፤ በራስ የመተማመን መንፈሱ ሁሉ ስደተኛ ሆነ። በዚህ ስልት ነው ሞት አስኪወስዳቸው ድረስ በሰብዕና ላይ ልክ እንደ ጥንቸል ሙከራ ሲያድረጉ የቆዩት … . የአቶ መለስ ታሪክ ለእኔ የጨላማ ድርሰት ነው።
ይህም ማለት አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ የራሳቸው ማንንት ፍርፋሪ የላቸውም። በፍጹም። ያን የእንጀራ እናት የፕላስቲክ ጡጦ እዬጠቡ ሰብእና ያለው ራዕይን ጨርሶ አላሰቡትም። ታውሬያለሁ ። ዓይን የለኝም። ከፊትም ከኋላ ምሩኝ ነው ያሉት። እንደ ሰው እንኳን ለመቆም ከአሁኑ ደክሟቸዋል። መቅኗቸው ከድቷቸዋል። አላዝንም። አቅመ ቢስ ከሆኑ አልችልም በማለት ወያኔንን ማፈረጥ ሲቻል … ይተበሰባሳሉ። … ይሄ ወንድነት የሚሉት ሰብዕናም እኔ እንጃ …
ያው አቶ መለስ ነው ማንታቸውን ቀብረውት የሄዱት። እርግጠኛ ሆነው፤ ወሳኝ አቋም ይዞ ለመውጣ በእሳቸው ዙሪያ ያለው የማንነት ጉዳይ ፍለስት ይታይበታል። የቲ.ፒ.ኤል.ኤፍ መስራች አባል አለመሆናቸው፤ ይህ በእራሱ ትልቅ ተራራ ነው። ትግሬነትም – የክትንት ነው፤ የጫካ ተመክሮ ሌላው መስፈርት ነው፤ ሁሉም በዬፍርጃቸው ወጥረው፤ መተንፈሻ ነስተው እያፋጠጧቸው ነበር እስካሁን የቆዩት … ለዛውም እየተወዛወዙ … ልዝዝ ብለው ወይን አይነዱ ወይ አያነዱ ዕዳ ነው። ይህም ይቀጥላል።
አሁን ወደ መነሻዬ … አዎን እኔ ዶ/ ኦባንግ ኢትዮጵያ ነው አምለው አቶ ኦባንግ ሜቶን … የላከው የመልካም ምኞት መልእከት እና ተማእጽኖም ደግግሜ አንብቤዋለሁ። አቶ ኦባንግ ከሚመራው ንቅናቄ የምጠብቀው ስለነበር አልደነቀኝም። ውስጡን ማዬት ይቻላል። የአዲስቱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ፖለቲካዊ አቋም – ፍጹም ለስላሳ ነው። የሚመቻቸውም ወገኖች ግን ይኖራሉ።
የሆነ ሆኖ መጠዬቁም ቢሆን ንቅናቄው መብቱ ነው። መልስ መጠበቁም መብቱ ነው። እነዚህን እርምጃዎች እኛ ባለን ጽኑዑ አቋም ላይ ሊለውጥ የሚችለው ምንም ነገር የለም። ለአቶ ኃይለማርያም ግን ቢያንስ ለህሊናቸው ይህን መሰሉ ለስላሳ አቀራረብ እረፍት የሚሰጣቸው አይመስለኝም። በተለይ የቃለ ወንጌል ተገዢ ናቸው እንደሚባሉት ከሆኑ። ህሊናቸው ደግሞ ያው መሪና ምርኩዝ ካልተዋሰ ወይንም የፕላስቲኳን ጡጦ ካልተማጠነ። ሌላው ደግሞ ለወያኔ ውጪ ላሉ ደጋፊዎቻቸው ብድርንና እረዳታ ሲያጎርፉላቸው ለኖሩትም ሀገሮችም ከተቃዋሚው ጎራ አንድ ለእናቱ ዬአዲስቱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መገኘቱ ለዓለም ዓቀፉ ሚዲያ ፍጆታ መልካም ነው።
አሁን ማንይሙት አማራ ሆኖ ኦሮሞ ነህና ምራ ቢባል … ይሆናል። አይቻልም። አለማቻል የሚለው ቃሉ እራሱ አይገለጽልኝም። እንደ ኦረሞ ደፍሮ አቋም ይዞ መታገል ፤ ለኦረሞ ህዝብ አይችልም። ብዙ ነገር የማያውቃቸው ረቂቅ ተፈጥሮዎች አሉና። በሌላ በኩል አማራ ሲጓዳ ሲዳፋ፣ ሲንግለታ፣ ሲታሰር ደግሞ ሁለመናው በመሆኑ ቢወቀውም አማራ ነኝ ብሎ የውስጥ ስቃዬን ይፋ አድርጎ አይታገልም። ስለምን የእሱ የሆነውን ማንነት ተቀምቶ የእሱ የሆነ መለያ ተነጥቆ ሌላ አርቲፊሻል ሰብዕና ተስክቶለታል። ኢትዮጵያዊነትንማ እርሱት …. የአቶ መለስ የግልቢያ ጨዋታ … ለዘመናት ውስጥን ህምም ላይ ይጥላል። ዕዳው መጠነ ሰፊ ነው … ቁስለት! የህሊና ቁስለት ታውቃለችሁ ለዛውም የመረቀዘ …?
ለዚህ ሁሉ መካራ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙት፤ ዓይን እያላቸው የማያዩት፤ ህሊና እያላቸው የማያስተውሉት የወያኔ ባለስልጣኖች ዬችግር መንስኤ ይህው ነው። ሀገር ለባእድ ከመቸብቸብ ወዲያ ምን ረመጥ ጉድ አለ … ትናንትን የረገጠ፤ ዛሬን የጨፈለቀ፤ ነገ ሳይመጣ ገና … አድረቆ – ያሳረረ … ያኮማተረ … ይህንን በጸጋ ተቀብለው ሲያስተናግዱ ከነበሩ የዳመና ተዋናዩች መፍትሄ – እእ!
እንደ ማጠቃለያ …….
የአቶ ኦባንግን ኢትዮጵያ መልእክት በመብት፤ በነፃነት ደረጃ የድርጅቱና የሚሰማውን በመጻፉ ሆነ በመላኩ አልረበሸኝም። እንዲያውም ሰሞኑን በኢሰአት ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ ከአቶ ኤፍሬም ማንዴቦና ከአቶ ፈቃደ ጋር ባደረገው ውይይት አባይን አስመልክቶ አቶ ፈቃደ ላላቸው አዎንታዊ ዕይታ ሳይጨርሱት ሲያቋርጣቸውና የእራሱን አቋም ሲገልጽ ድብን ነው ያልኩት።
ስለምን ማስጨረስ ያስፈልጋል። ሌላው የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልዩነት አውቆ ወጥ ዕይታ ለመፍጠር ምቹ ነበር። ጋሼ ሙሉጌታ ሳያቋርጥ አቶ ፈቃደን አስጨረሶ እሱ እንደ አወያይነቱ እንደ ተክሌ ጫር አድርጎ ወይንም ምንም ሳይተነፍስ ዕድሉን ለአቶ አፍሬም ሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ ….ኖሮ … ፤ አቶ ኤፍሬም የብዙኃኑን ዕይታ የሚወክል ሃሳብ ያመነጩ ነበር ። ባያመነጩ እንኳን ማጠቃለያ ላይ እሱ እልባት ቢሰጥበት መልካም ሆኖ ሳላ — ? አሁን ለምሳሌ የህንድን ግሪን ሪቮሌሽን አቶ ኤፍሬም ያለነሱትና አቶ ፈቃደ ጣልቃ ገብተው በጥልቀት አንስተው ያላሰተዋልናቸውን ነገሮች ሁሉ እንድንፈትሽ የቤት ሥራ ሰጡን …
ምን ለማለት ነው — ዴሞክራሲ ፅንሰ-ሓሰቡና ተግባሩን መለማመድ አለብን። መማር አለብን። አንድ የጎንደር አባባል አለች „ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ ዴሞክራሲን እንወደዋለን። ስንወደው ግን እስከ ንፍጥ ልጋጉ መሆን አለበት። ሁሉንም መሆን ይኖርበታልና። የማይመቹነንም በአክበሮትና በትእግስት ተከታትሎ ሃስብን በሃስብ፤ ተግባርና በተግባር አታግሎ የነጠረውን መውሰድ። አባዛሁት መስል …. ስለ ትእግስታችሁ አመሰግናለሁ።