
በቅድሚያ ለህወሃት/ኢህአዴግ “የአንድን አገር (ኅልውና በማስጠበቅ) አንድ አድርጎ ማቆየት የሚችለው መሪው (ወይም በኢህአዴግኛ ፓርቲው ወይም ግምባሩ) እርሱ ብቻ እንደሆነ የሚናገር ከሆነ ያ መሪ (ፓርቲ ወይም ግምባር) አገሩን ከመገንባት ከሽፏል ማለት ነው … ማንም ሰው (ፓርቲ/ግምባር) ዕድሜልኩን መሪ/ፕሬዚዳንት መሆን የለበትም፤ አዲስ ሃሳብና ትኩስ ኃይል ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያቺ አገር ከቀድሞው እየተሻለች ትሄዳለች፡፡”
ቀጠሉ – “ሰዎች ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ለምን መቆየት እንደሚፈልጉ እኔ አይገባኝም፤ በተለይ ብዙ ገንዘብ እያላቸው …” ልማታዊ አምባገነኖቹን የሚመለከት ነበር፡፡
ለሕገመንግሥት ቀያሪዎችና ሕግ አሻሻዮች “አንድ መሪ በሥልጣን ለመቆየት በጨዋታው መሃል ሕግ ለመቀየር ሲሞክር (በዚያች አገር) ያለመረጋጋትና የነውጥ አደጋ ያስከትላል፡፡”
ራሳቸውን ከአፍሪካ “ዘላለማዊና ልማታዊ” መሪዎች ጋር በማነጻጸር “እኔ በጥሩ ዕድሜ ላይ ነው ያለሁት (ወጣት ነኝ) ሆኖም ለአገሬ ትኩስ ኃይልና አዲስ ሃሳብ የሚያመጣ የተሻለ ነው፤ ይህ ዓይነቱ በአንዳንድ ሁኔታዎች ለእናንተም መልካም ነው”
የማይገባቸው ነገር – “እውነቱን ልንገራችሁ – (ይህ በሥልጣን የመቆየት ሁኔታ) በጭራሽ አይገባኝም፤ አሁን በሁለተኛው ዙር የሥልጣን ዘመኔ ላይ እገኛለሁ፤ በሕገመንግሥታችን መሠረት እንደገና ለምርጫ መወዳደር አልችልም፤ አሜሪካንን ወደፊት ለማራመድ ገና ብዙ የምሰራው አለ፤ ነገር ግን ሕግ – ሕግ ነው! ማንም ከሕግ በላይ መሆን የለበትም፤ ፕሬዚዳንቶችም እንኳን ቢሆኑ”
የሚገባቸው ከሆነ በሚል ለሩብ፤ ለግማሽ፣ ቢቻል ከዚያም በላይ ወይም ገና ከማኅጸን ጀምሮ መግዛት ለሚፈልጉ የአፍሪካ አምባገነኖች ኦባማ ይህንን አሉ፤ “በግልጽ ለመናገር ከፕሬዚዳንትነት በኋላ ያለውን ሕይወት በተስፋ እየጠበኩት ነው፤ ይህ ማለት ከቤተሰቤ ጋር በርከት ያለ ሰዓት የማሳልፍበት፣ በአዲስ መልኩ የማገለግልበት እና አፍሪካን በተደጋጋሚ የምጎበኝበት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” (ተዛማጅ ትርጉም በጎልጉል)
ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ፤ አስተዋይም ልቦና ያለው ያድምጥ!
ኦባማ ለአፍሪካ መሪዎች በፊዝና ብበዋዛ የተሞላ በህዝቦቻቸው ላይ መሰረታዊ ጥያቄ በማፊዝ አጋጣሚ በተከሰተው ሽብር ብተባለ ይምእራባውያን የጥቅም ግጭት ጠንከር ብለው ያስተዳደር ሰብዓዊ ጥሰት በብእር ለሚጽፊ በፕለቲካ መድረክ በግልጽ ተቃውሞ የህዝቡን ሶቆቃ ብሶት ላሰሙ ያለተግባራቸው የራሳቸውን አሸባሪ ስርዓት ለመሸፈን ከዛብጥያ በመጣል ሲመጻደቁ የነበሩት ያሉት በአሜሪካ ፕረዘደንት ተግሳጽ ምክር ሲቸራቸው በህዝብ የቀለዱት ሲቀለድባቸው የመስማት ሆነ የማስተዋል አቅማቸው የዳዠቀ መሆኑን ህዝቦችም ማንነታቸውን በምስወቅ የነጻነት የምብት ትግላቸው የሚያበረታታ ሲሆን በሌላ በኩል ዲክቲተሮችን የሌላቸውን የቸሩት ኦባማ የራሳቸውን የሃገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉብኝታቸውም እቅዱ የቻይናን ዘርግታ ያለችው በአፍሪካ ብልጽግና ቅርምት ለመጋራት የተለመ በመሆኑ ኦባማ በጥቂት ወጭ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህይወት አልሸባብን ለመዋጋት በጥቅም ተጋዥነት ላገልግሎት ተመራጩ ወያኔ በመሆኑ ለጥቅማቸው ሲሉ ምላሳቸውን ነክስዋል ይህም ፕለቲክ ውሸት መሆኑን ለሁሉም በርቶለታል