በሰሜን አሜሪካ ለምትኖሩ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አባሎች፣ ደጋፊዎች እና
አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
የስብሰባው ቀን፦እሑድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008 ዓም (Sunday April 24, 2016)፤
ሰዓት፦በኒውዮርክ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9:00 (3፡00 PM) ሰዓት ጀምሮ፤
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባሎቹ እና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የፕሮጀክቱን አላማ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር በቴሌኮንፈረንስ የሚደረግ ስብሰባ ለማካሄድ አቅዷል። የስብሰባው ዓላማ የሞረሽ-ዐማራ ድምፅ የሬድዮ ፕሮጅክትን እውን ለማድረግ የሚያስችል የገንዘብ እና ሌሎች ዓይነት ድጋፎችን ለማሰባሰብ ይሆናል።
ስለሆነም «የዐማራ ጉዳይ የኢትዮጵያም ጉዳይ ነው» የምትሉ ሁሉ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተገኝታችሁ የትውልድ እና የታሪክ አደራችሁን በመወጣት፣ ድምፅ-አልባ ለሆነው ኢትዮጵያዊው ዐማራ እንድትደርሱለት በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በምትኖሩበትአገርከታች የተጠቀሰውን የስልክ ቁጥር በመደወል፣ ከዚያም የመግቢያ ቁልፍ ቁጥሮችን ተራ በተራ በመጫንየስብሰባውን ሂደት መከታተል ትችላላችሁ።
የስልክ ቁጥሮች፦
- ለአሜሪካ፦(712)-775-7035
- ለካናዳ፦(712)-775-7060
የመግቢያ ቁልፍ፦ 272339 #
ዐማራውን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
Leave a Reply