ቅማንት እና ዐማራ የተባሉት ነገዶች ለዘመናት አብረው ኖረዋል። አብረው በመኖራቸው ብዛትም በረጅሙ የአገራችን የመዋሐድ እና የመቀላቀል ሂደት አንድ ሆነዋል። ስለዚህ እኒህ ሁለት ነገዶች በጊዜ ሂደት የጋራ ኃይማኖቶች ተከታዮች፤ አንድ መግባቢያ የአማርኛ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ አገር እና መልከዐምድራዊ መለያ፣ ከዚህም በላይ አንድ የነፃነት ታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል። በመሆኑም የወል የሆነ ማኅበራዊ ሥነልቦና መስርተዋል። በዛሬው ዘመን የነገዶቹን ተወላጆች ሁለንተናዊ ማንነትን መነሻ አድርጎ ለመለያየት መሞከር፣ ውኃ እና ወተት ከቀላቀሉ በኋላ እንደገና ለመለየት እንደመሞከር ይቆጠራል፥ ውሕድ አካል ሆነዋልና።
ሆኖም የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ዐማራን ለማጥፋት ላለው ረጅም ዕቅድ ብቸኛ ማሳኪያ መንገድ አድርጎ የወሰደው የ«ከፋፍለህ ግዛው» ሥልትን ነው። የዚህ ሥልት ማስፈጸሚያ በሕገ-አራዊቱ ያሠፈረው አንቀፅ ፴፱ መሆኑ ይታወቃል። በተግባርም እንደሚታየው የትግሬ-ወያኔ ነገድን ከነገድ፣ ጎሣን ከጎሣ፣ ኃይማኖትን ከኃይማኖት ማለያየት እና ኢትዮጵያውያን አብረው ስለጋራ አገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮቻቸው እንዳይመክሩ እና በአንድ እንዳይቆሙ አድርጓቸዋል። ለዚህም የዐማራውን ነገድ፣ ጨቋኝ፣ አፋኝ እና ገዥ፣ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎችን ኢትዮጵያዊ ነገዶች ተጨቋኝ፣ ታፋኝ እና ተገዥ በማስመሰል በመካከላቸው መተባበር፣ መተማመን፣ መከባበር፣ መቻቻል እና በአንድ ማሰብ እንዳይችሉ ማድረግ የዘወትር ተግባሩ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን እኩይ ዓላማውን ለማሣካት በየነገዱ እና በየጎሣው ስም ድርጅቶችን ሲቀፈቅፍ፣ ለይስሙላ ያህል የእነዚያ ነገዶች ወይም ጎሣዎች ተወላጆች «የድርጅት መሪዎች» ቢባሉም፣ በተጨባጭ ግን እኒህ ድርጅቶች የሚመሩት በትግሬ-ወያኔዎች መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። ሰሞኑንም ቅማንትን ከዐማራ ለማፋጀት ተብሎ የሚዶለተው ሤራ የዚህ ሥልት አካል ነው።
የትግሬ-ወያኔ ቅማንትን ከዐማራ ለመለየት የሚፍጨረጨረው የራሱን የረዥም ጊዜ ግብ ለማሣካት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። በመሠረቱ ቅማንትን በፀረ-ዐማራነት አደራጅቶ፣ አሰልጥኖ እና መርቶ ከጎንደር ዐማራ ጋር እንዳይኖር እና የራሱን ክልል እንዲመሠርት የተፈለገው ለቅማንት ነገድ በመቆርቆር አይደለም። የመጨረሻው ግብ አዲስ የሚመሠረተውን የቅማት ክልል፣ የትግሬ-ወያኔ በኃይል «የትግራይ አካል ናችሁ» ካላቸው የወልቃይት እና የጠገዴ ወረዳዎች ጋር በማገናኘት ሰሜን ጎንደርን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማጠቃለል መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንን ሤራ እንዲያስፈጽሙ ከቅማንት ነገድ ተወላጆች መካከል ጥቂት የፋሽስት ጣሊያን ባንዳ ልጆች ተመልምለዋል፤ በቀዳሚነት የሚታወቀውም የባንዳው ልጅ እና የዘመናችን ባንዳ ነጋ ጌጤ ነው። ከታሪክ እንደሚታወቀው በፋሽስት ጣሊያን ጊዜ «ደጃዝማች ጣሹ» የተባሉትን የቅማንት አባት እና ጀግና መሪ፣ በፀረ-ዐማራነት ሕዝቡን እንዲያደራጁ እና የራሳቸውን አስተዳደር እንዲመሠርቱ፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው እንዲያጠፉት ላቀረበላቸው የመነጣጠል ጥያቄ፣ «አሻፈረኝ! ቅማንት ዐማራ ነው፣ ዐማራም ቅማንት ነው!» ብለው ለአንድነት በመቆም የፋሽስት ጣሊያንን ሤራ ማክሸፋቸው ይታወቃል። በተቃራኒው ግን «ጌጤ» የተባለው የነጋ አባት ለጣሊያን ፍርፋሪ በመገዛት ቅማንቱን እና ዐማራውን ለመለያየት መሣሪያ እንደነበር ታሪካችን ያስታውሰናል። በተመሣሣይ ሁኔታ የትግሬ-ወያኔ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ፣ የቅማንትን ነገድ አደራጅቶ የራሱን ክልል እንዲመሠርት፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ እንዲያጠፋው፣ የቅማንትን ነገድ በነቂስ በዚህ ዓላማ ዙሪያ እንዲያደራጅ ኃላፊነት የሰጠው ለባንዳው ልጅ ነጋ ጌጤ እንደነበር ይታወሳል። የታላቁ ባንዳ የጌጤ ልጅ፣ የትግሬ-ወያኔ ምልምል የሆነው ባንዳው ነጋ ጌጤ፣ ይህን ኃላፊነት ከጌቶቹ ተቀብሎ ቅማንትን ከዐማራ ለመለያየት ያልማሰው ጉድጓድ፣ ያልቧጠጠው ገደል የለም። ነጋ ጌጤ እንደአበደ ውሻ ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ የሚያደርገውን መክለፍለፍ እንዲያቆም፣ የጎንደር ጌጦች እና ኃውልቶች የሆኑት ዕውነተኛዎቹ የቅማንት አባቶች እና እናቶች፦ እማሆይ አበቅየለሽ ይመር፣ ግራዝማች ካሰኝ ዓለማየሁ እና የመሳሰሉት፣ በወቅቱ መክረው እና ገስጸው ከትግሬ-ወያኔ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዳይወጣ ማድረጋቸውን የጎንደር ሕዝብ ቅማንቱ እና ዐማራው በነቂስ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
ስለሆነም በነጋ ጌጤ አማካይነት ዐማራውን እና ቅማንቱን የመነጣጠሉ እና ለታላቋ ትግራይ መሥፋፋት የሚሆነው ሠፊ መሬት ማግኛ መንገድ በሕዝቡ እንቢተኝነት ሳይሳካ በመቅረቱ፣ ለትግሬ-ወያኔ የእግር እሳት ሆኖበት ቆይቶ ነበር። በዚህም ምክንያት የትግሬ-ወያኔ ዓላማውን ሳያሳካ ከደደቢት በረሃ የነደፈው «የታላቋ ትግራይ» ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል በማመን ሌላ ሥልት ነደፈ። ይኸውም «ቅማንት ተደራጅቶ የራሱን ክልል ካልመሠረተ ነገድ አይደለም፣ ዐማራ ሆኗል» በማለት፣ ምንጊዜም የኢትዮጵያ ነገዶች አንድ ተብለው ሲቆጠሩ፣ ከቁጥር ጎድሎ የማያውቀውን የቅማንትን ነገድ በ1999 ዓ.ም. ባካሄደው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ አስቀድሞ በተጠነሰሰ ሤራ እንዲሰረዝ አደረገው። ይህ በታሪካችን ሆኖ የማያውቅ ድርጊት መፈጸሙን ያዩ የነገዱ አባሎች፣ የትግሬ-ወያኔን ነጣጥሎ የማጥፋት ሤራ ሳይረዱ፣ ላቀደው ዕቅድ መሣካት መሣሪያ ሆነው ቀረቡ። እነዚህ ወገኖች በቅማንቱም ሆነ በዐማራው ዘንድ እጅግ የተከበሩ ሰዎች ነበሩ። አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው የተማሩ እና ያወቁ ከሚባሉት የሚመደቡት እነ አምባሣደር ዘመነኝ ካሰኝ እና ዶክተር ማለደ ማሩ ለትግሬ-ወያኔ የተንኮል ወጥመድ ሰተት ብለው በመግባት፣ የቅማንቱ እና የዐማራው መጠፋፊያ እጄታ ሆነው ቀረቡ። በዚህም ምክንያት እነ ግራዝማች ካሰኝ ዓለማየሁ፤ እማሆይ አበቅየለሽ ይመር እና ሌሎችም ያከሸፉት ቅማንትን እና ዐማራን የመነጣጠል ዓላማ እንደገና ሕይዎት ዘርቶ እንዲያንሰራራ አደረጉት።
የነገሩ ሂደት እንደሚከተለው ነው። በቅድሚያ እኒህ ግለሰቦች «ከሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ለምን እና እንዴት እንፋቃለን?» የሚል ጥያቄ ለመንግሥት ተብየው አቤቱታ አቀረቡ። አቤቱታ የቀረበለት አካልም፣ ያሤረው ወጥመድ ግዳይ እንደጣለለት አውቆ፣ «ለጥያቄአችሁ አጥጋቢ መልስ ከፈለጋችሁ፣ ነገዳችሁን አደራጅታችሁ የማንነት ጥያቄ እንዲያነሳ እና የራሱን ክልል እንዲጠይቅ አድርጉ» የሚል ቀጭን መመሪያ ይሰጣቸዋል። በእነዚህ ሁለት ግለሰቦች አነሳሽነት፣ እንደ ነጋ ጌጤ ባሉ ባንዳዎች ትብብር፣ ለ25 ዓመታት ወያኔ በነዛው የመለያየት ፕሮፓጋንዳ የተሳቡ እና ወንዝ የማያሻግራቸው ቢሆንም «ዕውቀት አለን» የሚሉ የትግሬ-ወያኔ ተላላኪ ካድሬዎችን በማሰባሰብ ቅማንትን ከዐማራው የመነጠል ሤራ በሠፊው እንዲራገብ ተደረገ። በዚህም መሠረት በሰሜን ጎንደር አስተዳደር ውስጥ ከ100 በላይ የቀበሌ ገበሬ ማኅበራትን ያጠቃለለ ግዛት፦ በሰሜን ከወልቃይት እና ጠገዴ ጋር፣ በደቡባዊ ምዕራብ ደግሞ ከአገው-አዊ ዞን ጋር የሚዋሰን፣ ጎንደር ከተማን ያካተተ ግዛት፣ «የቅማንት ክልል» ተብሎ እንዲከለል ተደረገ።
የሁለቱን ነገዶች ተወላጆች አብሮ የመኖር ጤናማ ግንኙነት፦ ከሰላም ወደ ብጥብጥ፣ ከፍቅር ወደ ጠብ፣ ከመከባበር ወደ መናናቅ፣ ከመቻቻል ወደ ሆደባሻነት፣ ከአንድነት ወደ መነጣጠል ያሸጋገረውን የነባር አንድነትን የማጥፋት ድርጊት በዚህ ወቅት እንዲፈጸም የተፈለገበት ዋናው ምክንያት ግልጽ ነው። የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን ለመናድ የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት ዘመን የሱዳን መንግሥት ለዋለለት ውለታ፣ ከምዕራብ ኢትዮጵያ ከሰሜን ወደ ደቡብ 1,600(አንድ ሺ ስድስት መቶ) ኪሎሜትር ርዝመት፣ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ደግሞ ከ50 እስከ 60 ኪሎሜትር ወርድ ያለው ለም እና ድንግል መሬት ለመሥጠት ስምምነት ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ስምምነት ተፈጻሚ ለማድረግ የወሰን መካለያ መሥመር(ችካል) ለመቸከል በሱዳን መንግሥት እና በወያኔ በኩል ዝግጅት እየተደረገ ነው። ይህን ሠፊ የሆነውን የኢትዮጵያ ታሪካዊ መሬት ለማስከበር፣ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ አንገታቸውን ለደርቡሽ የሰጡበት፣ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ከቱርክ ጋር የጦርነት ገና የተጫዎቱበት እና ተደጋጋሚ ድል የተጎናጸፉበት፣ በደማችን የቀላ መሬት ነው። የሁለቱ ነገዶች፣ ማለትም፥ የቅማንት እና የዐማራ ነገዶች ተዋጊዎች፣ ለአገራቸው ነፃነት ቀናዒ፣ ለሠፊ መሬታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ለጭብጥ አፈሯ ጉጉ የሆኑት ካልተለያዩ እና እርስ በራሳቸው መናቆር ካልጀመሩ፣ ወደ ራሳቸው የውስጥ ጉዳይ ካላዩ፣ የድንበር ማካለሉን ተግባር በቀላሉ ማከናወን እንደማይችል ግልጽ ነው። ለዚህም እንዲረዳው የትግሬ-ወያኔ ለቅማንቱ በዚህ ጊዜ መሬት አካልሎ መስጠቱ በሁለት መንገዶች ጥቅም ያስገኝለታል። አንደኛው ከሱዳን መንግሥት ጋር የሚያደርገው የድንበር መካለል ያለብዙ ችግር ይከናወናል ብሎ ያስባል። ሁለተኛው ደግሞ ሁለቱ ነባር እና ውሕድ ነገዶች በመሬቱ መካለል ሳቢያ በመካከላቸው የነበረው አንድነት ላልቶ እና ጠፍቶ ወደ ጦርነት ይገባሉ። ይህ ጦርነት በቅማንቶቹ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት «ቅማንቶቹ ለሰላማቸው ሲሉ ወደ ትግራይ እንጠቃለል ብለው ጥያቄ አቀረቡ» በሚል ስበብ ሰሜን ጎንደርን ወደ ትግራይ የማጠቃለሉ ዓላማቸው የሰመረ እንዲሆን ያስችለናል ብለው ያስባሉ። ለዚህም መደላድል ይሆናቸው ዘንድ በሰሜን ጎንደር አካባቢ፣ በስሜን አውራጃ፣ በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ታላቁን የአገሪቱን ተራራ ራስ ዳሼንን፣ በስድስተኛ ክፍል የትግራይ ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ መጽሐፍ «በኢትዮጵያ ትልቁ ተራራ ራስ ዳሼን የሚገኘው በትግራይ ክልል ነው» ሲሉ ጽፈው ትውልዱ ከወዲሁ ሰሜን ጎንደር ወደ ትግራይ መጠቃለሉ የማይቀር እንደሆነ እንዲያውቅ አድርገዋል።
ይህ የትግሬ-ወያኔ እቅድ «አልሠራም» የሚባል አይደለም። በአሁኑ ሰዓት የቅማንት እና የዐማራ ነገድ ተወላጅ ባንዳዎች፣ ለትግሬ-ወያኔ አሽከር በመሆን ሕዝብን ከሕዝብ የማነጣጠል ሥራ በመሥራት፣ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች መካከል ደም የማቃባት ድርጊት እየተፈጸመ ነው። በጭልጋ፣ በአርማጭሆ፣ በመተማ፣ በቋራ፣ ወዘተርፈ በሕዝቡ መካከል ጠቡ እየሠፋና እየከረረ በመምጣቱ በየጊዜው የሚታየው የሕዝብ መፈናቀል እና ሞት በግልጽ ያሳያል። ይህን ድርጊት የጎንደር ሕዝብ እና በተለይም የሁለቱ ነገድ ተወላጆች በዝምታ ወይም በችልታ ሊመለከቱት አይገባም። ጉዳዩ እጅግ ተባብሶ በርካታ ሰው ከመፈናቀሉ፣ ከመሞቱ እና ከመሰደዱ በፊት የሁለቱ ነገዶች የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች መጠፋፋቱ ሥር ሳይሰድ እና መመለሻው ሳያጥር የወያኔን የመከፋፈል ዓላማ ሊያመክኑ ይገባል። በተለይም የወያኔ እጄታ ሆነው የተሰለፉትን ግለሰቦች እና ቡድኖች በመለየት ከማኅበረሰቡ የማግለል ሥራ ማከናወን ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
የትግሬ-ወያኔ የሚያካሂደውን ሕዝብን ከሕዝብ የማፋጀት እና የትግራይን ግዛት የማሥፋፋት ተግባር እንዲሠምርለት ተግተው በባንዳነት ከሚያገለግሉት የቅማንት ተወላጆች መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፦
(1) አቶ ካሤ መንግሥቴ፦ ይህ ሰው ቀደም ሲል መምህር የነበረ እና በአሁኑ ጊዜ በጡረታ የተገለለ ነው። መኖሪያ ሠፈሩም ጎንደር ከተማ፣ ልዩ ስሙ ቸቸላ አካባቢ እንደሆነ ታውቋል። ቅማንትን እና ዐማራን ለማለያየት ለሚሠራው የማፋጀት ሥራ የትግሬ-ወያኔ በየወሩ 2,500 (ሁለት ሺ አምስት መቶ) ብር እንደሚከፍለው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አረጋግጧል።
(2) አቶ ተስፋሁን ሙላት፦ በቀድሞው መንግሥት ወታደር የነበረ እና ቦርድ የወጣ፣ በአሁኑ ሰዓት ማራኪ ዩኒቨርሲቲ የሚሠራ የወያኔ ካድሬ እንደሆነ ተረጋግጧል።
(3) ዶክተር ይግዛው ከበደ፦ የማራኪ ዩኒቨርሲቲ ሐኪም ሲሆን፣ ሁለቱ ነገዶች በነባር አንድነታቸው እንዳይቀጥሉ ከልቡ ሌት ተቀን የሚሠራ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰብ እንደሆነ የደረሱን መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
(4) አቶ ዐባይነህ ዘውዱ፦ ይህ ሰው በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጋይንት አውራጃ ውስጥ ተመድቦ ይሠራ ነበር። በዚያን ወቅት ጋይንት አውራጃ ውስጥ በትግሬ-ወያኔ ለተገደሉት 3 ሰዎች ሕይዎት ተጠያቂ ነው። በዚህ ተግባሩም ከትግሬ-ወያኔ ባገኘው ታማኝነት ዳኛ እንዲሆን አድርገውት አያሌ ሰዎችን በፍርደ-ገምድልነት ወኅኒ የከተተ እና የአያሌዎች ቤት እንዲፈታ ያደረገ ወንጀለኛ ግለሰብ ነው። የትግሬ-ወያኔ መጥጦ መጣል መለያ ባሕሪው ነውና፣ በአሁኑ ሰዓት ይህ ግለሰብ ከዳኛነቱ ተባርሮ በጥብቅና ሥራ እንደሚተዳደር ታውቋል። ሆኖም ለቅማንት እና ለዐማራ መለያየት ተግተው ከሚሠሩት መካከል አንዱ ነው።
(5) አቶ ከፍያለ ማሞ፦ ይህ ሰው ጭልጋ ውስጥ የሚኖር፣ የከፋፋዩ ቡድን አስኳል ከሆኑት አንዱ ነው።
(6) አቶ መልኬ ዓለም፦ ጎንደር ከተማ የአቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሚሠራ፣ ቅማንትን ከዐማራው ከሚለያዩት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነ።
(7) አቶ ብርሃኑ አቃናው፦ በትምህርት መገናኛ መሥሪያ ቤት የሚሠራ እና የከፋፋዩ ቡድን አባል።
እኒህ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በከብቶች በረት ውስጥ እንደሚያውክ ኮርማ ይመሰላሉ። በአንድ በረት ውስጥ ተዋጊ እና ነሻሪ ኮርማ ካለ የበረቱ ከብት በሙሉ ሰላም እንደማያገኝ ይታወቃል። የበረቱ ሰላም መሆን የሚረጋገጠው ተዋጊው ኮርማ ከበረቱ ሲነጠል ብቻ ነው። የቅማንት እና የዐማራ ነገዶችም ሰላማቸው የተረጋገጠ የሚሆነው በመካከላቸው ያሉ የትግሬ-ወያኔን የጥፋት ዓላማ አራማጆች «አውቀንባችኋል» በማለት ከውስጣቸው ማግለል ሲችሉ ብቻ ነው። እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች እና በውስጣቸው ያደራጇቸውን አገር እና ትውልድ አጥፊ ግብረ-አበሮቻቸውን፣ የጎንደር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ «ጥቁር ውሻ ውለዱ» ብሎ ከማውገዝ አልፎ፣ ከማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሊያገልላቸው ይገባል። በመሆኑም የቅማንቱን እና የዐማራውን ነባር አንድነት በዳበረ መልኩ እንዲቀጥል ማድረግ ለነገ የሚባል ተግባር አይደለም። ስለዚህ ማኅበረሰቡ በግልፅ ከማውገዝ አልፎ፣ ከመጥፎ ከፋፋይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ግዴታ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ግለሰቦቹ መበጥበጣቸውን፣ የሰላማዊ ዜጎችን ሕይዎት እና ንብረት ከማጥፋት አይቆጠቡም። ለዚህም ሰላምን እና አንድነትን ፈላጊው የጎንደር ሕዝብ እነዚህን እና መሰሎቻቸውን ነቅቶ በመጠበቅ፣ በተለመደው ጀግንነቱ አገራዊ ዳርድንበሩን ከቆረሳ እንዲከላከል ጥሪያችን በታላቅ አክብሮት እናቀርባለን።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply