• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!

October 14, 2014 09:51 pm by Editor Leave a Comment

ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል የቱን ያህል የከበደ እንደሆነ የሚያውቀው የግፉ እና የመከራው ተሸካሚ የሆነው ዐማራው መሆኑኑን ማንም አይስተውም። ያም ሆኖ ግን፣ ሰብአዊነት የሚሰማው ማናቸውም ሰው፣ በሰዎች ላይ የሚፈጸምን ግፍ እና በደል በራሱ ላይ እንደተፈጸመ በመቁጠር፣ ድርጊቱን ለማስቆም የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። ለተራቡት የርሃብ ማስታገሻ ያጎርሳል፤ ለታረዙት የእርቃን መሸፈኛ ከፈን ይለግሣል፤ ለተጠሙት የውኃ ጠብታ ያስጎነጫል፤ አልፎ ተርፎም ግፍ ፈጻሚዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል።

በዓለም ዙሪያ በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በወገኖቹ ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ ከማጋለጥ በተጨማሪ ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ላጡ ወገኖቹ የሚችለውን ያህል እጁን ከመዘርጋት የታቀበበት ወቅት የለም። ይህ ተግባሩ በሕይዎት ሳለ የመንፈስ ልዕልናን ሲያጎናጽፈው፣ በመጨረሻ የሕይዎት ዘመኑም «ስራብ አብልታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል? እንግዳ ስሆን አስተናግዳችሁኛል? ስታሰር አስፈትታችሁኛል?» ተብለው ከፈጣሪያቸው ለሚጠየቁት ጥያቄ አዎንታዊ መልስ እንዲኖራቸው የሚያስችል በመሆኑ የጽድቅን ጎዳና መከተሉን ያሳያል። ይህ ተግባር ለረጅውም ሆነ ለተረጅው ሥጋዊ እና መንፈሣዊ ጉዳዮችን አጣምሮ በቀና ጎዳና መጓዝን የሚያመለክት በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ለማድረግ የሚሞክረው ይህንኑ ተግባር ነው። ስለሆነም «ለወገን ችግር ደራሹ ወገን መሆኑን» በማጉላት፣ በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጡ ወገኖቻችን የችግር ማቃለያ፣ የቀን መግፊያ የሚሆን ዕርዳታ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

ሰሞኑን ደግሞ በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን እንዲሁም በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጅ ዞን፣ በጉራፈርዳ ወረዳ ካለፈው የ2004 ዓም ዕልቂት በተአምር ተርፈው የነበሩትን በርካታዎቹን ዐማራዎች ገድለው የቀሩትን በማፈናቀላቸው፣ ለዕለት ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ የሰው እጅ እንዲመለከቱ አድርገዋቸዋል። ለነዚህ ወገኖች ካለእኛ ካለወገኖቻቸው ሌላ ሊታደጋቸው የሚችል ባለመኖሩ፣ ሞረሽ-ወገኔ ለእነዚህ ወገኖች ሕይዎት ማቆያ የሚሆን ዕርዳታ ለማሰባሰብ ተዘጋጅቷል።

ስለሆነም ሰብአዊነት የሚሰማን ሁሉ፣ በጭፍን የዘር ጥላቻ ላይ ተመሥርቶ ከጥይት አልፎ በርሃብ አሰቃይቶ ለመግደል የተወሰነባቸውን ወገኖቻችንን ሕይዎት ለመታደግ በሚከተለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የምትችሉትን ዕርዳታ እንድትለግሱ በተፈናቃይ ችግረኞች ስም ይጠይቃል።

Bank of America

Account Number: 435030804511

Router Number: 051000017

SWIFT Number: BOFAUS3N

ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት!


በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አጥብቀን እናወግዛለን

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን 

አንድ ሕዝብ ከዚህ ዘር የተወለድህ ነህ ተብሎ ስልጣን በጨበጡ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምበት፣ በአዶልፍ ሒትለር የሚመራው የጀርመን ናዚዎች መንግስት አይሁዶችንና ጂፕሲዎችን እንዳጠፋ አንብበናል፣ ሰምተናል፣ ተንቀሳቃሽ ዶኩሜንታሪ ፊልሞችን አይተናል። አዶልፍ ሒትለር አይሁዳውያንን ሲያጠፋ “አርመኖችን ማን ያስታውሳል” ነበር ያለው። አርመኖች በቱርኮች አልቀዋልና። ዛሬም የትግራይ ብሔረተኞችና የነሱም መንታ ወንድሞች ከሆኑ ብሔረተኞች አልፎ በተቃዋሚነት ተሰልፈናል የሚሉት ሳይቀሩ ትላንት፦ በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በወልቃይት፣ በጸገዴ፣ በወለጋ፣ ወዘተርፈ እና ዛሬ በጉራፈርዳ፣ ከሳምንት በፊት በጋምቤላና አካባቢው፣ እንዲሁም ከ2 ወር በፊት በግምቢና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል “ማን ያስታውሳል” ከማለት አልፈው “ማን ደንታ ይሰጠዋል” ያሉ ይመስላል።

more sh“ኢሳት” በኦክቶበር 10/2014 በጉራፈርዳ በሚኖሩ አማሮች ላይ ጥቃት ተከፍቶ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውንና ብዙ ሰው መሰደዱን፣ እንዲሁም በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሕፃናት፣ እናቶችና ጎልማሶች ፎቶ እንደደረሰው፤ በጉራፈረዳ የተነሳው ግጭት አስከፊ በሆነ ሁኔታ እንደቀጠለ ገልጿል። “ሐራ-ኢትዮጵያ” ደግሞ በቤንቺ ማጅ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ወያኔ አሰልጥኖ ባሰማራቸው የአካባቢ ታጣቂዎች የተጀመረው የአማራው እልቂት ተባብሶ ቀጥሏል ይላል። በተጨማሪም “ዘ-ሐበሻ” የተባለው ድረ-ገጽ፣ 25 አማሮች ተገድለዋል ይባል እንጂ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ ብሏል። ይህ እንግዲህ ሳምንት ባልሆነው ጊዜ ውስጥ የተፈፀመ ሲሆን፣ ከዚህ ዓመት የመስከረም ወር የመጀመሪያ ሣምንት (Mid-September 2014) ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ የተገደሉ አማሮች ቁጥር ደግሞ 521 ደርሷል። ይህ ቁጥርም እየጨመረ መሄዱ አያጠያይቅም። ሜጢ አካባቢ ልዩ ስሙ የሪ ቀበሌ አራት አማሮች ተቃጥለው ሬሳቸው ተገኝቷል። በሜጢ ከተማና አካባቢው ከአንድ ሺ በላይ ቤቶችና አንድ ቤተክርስቲያን እንደተቃጠለ መኢአድ በ16/01/2007 ዓም ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ከወራት በፊት በሰኔ 13/2006 ዓም (June 20/2014) ከወለጋ በተለይ ከግምቢና ከቄለም የግንፍሌ ወረዳ እስከ 8000 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን አማሮች በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ከሞት የተረፉት ከአካባቢው እንዲወጡ ተደርገዋል። ከግምቢ ብቻ እስከ 3000 የሚደርሱት ተፈናቅለዋል። ብዙዎቹ ተገድለው፣ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፏል፣ ቤታቸው ተቃጥሏል። ከሞት ተርፈው ባህርዳር የገቡ በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ በሰኔ 13/2006 ዓም (June 20/2014) በቀረበው የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ዝግጅት ከተፈናቃዩ ከአቶ ጋሻው ፈቃደ፣ ከአፈናቃዮች መካከል ደግሞ፣ የኦህዲድ የድርጅት ሀላፊ ከሆኑት ከአቶ አወቀ እና ከኦህዲድ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ከወይዘሮ ራዲያ ኢሳን ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ግልጽ አድርጓል።

አማራውን በማፈናቀል በአገዛዙ የ«ኦሮሚያ» ክልል ባለሥልጣኖች፣ “አድማ በታኝ” የሚባሉ ፖሊሶች፣ የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ክፍል፣ የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ፣ በአጠቃላይ የአካባቢው ባለስልጣኖች ቀጥተኛ ተሣታፊዎች ነበሩ። እኒህ የአገዛዙ አካሎች በየከተማው ያለውን የኦሮሞ ነገድ ተወላጅ ሕዝብ በአጠቃላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ተባብሮ እንዲነሳ በመቀስቀስ በንብረት ዘረፋው ተባባሪ እንዲሆን በማድረግ፣ እንዲሁም በአካባቢው ታጣቂዎችን አሰልጥኖ በማሰማራት፣ ወዘተርፈ የሚሳተፉበት ለመሆኑ የድምጽ፣ የተንቀሳቃሽ ምስልና የጽሁፍ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።

በጉራፈርዳ አካባቢ ያሉ የአገዛዙ ወታደሮች የመዠንገርና የሸኮ ተወላጆችን አዳዲስ የጦር መሣሪያ አስታጥቀው በዐማራ ተወላጆች ላይ እንዲነሱ ማድረጋቸውን የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትና ከሞት የተረፉት አረጋግጠዋል።

በሰኔ 2006 ዓም በግምቢ በነበረው ማፈናቀል፣ መግደልና መዝረፍ ላይ “አድማ በታኝ” የሚባሉ ፖሊሶች ተሳታፊዎች እንደነበሩ በቪኦኤ የቀረበው ቃለመጠይቅ ግልጽ አድርጓል። በዚህ ዓመት ከመስከረም ወር የመጀመሪያ ሣምንት ጀምሮ በጋምቤላ አካባቢ በተጀመረው የአማራን ዘር በማጥፋቱ ዘመቻ፣ የአገዛዙ የቀይ መስቀል አንቡላንሶች ግጭቱ ወደተከሰተበት ጋምቤላ አካባቢ መሣሪያ አቅራቢዎች እንደነበሩ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። እንዲሁም በዚህ ሳምንት የወያኔን ሠራዊት የጫኑ መኪናዎች ወደ ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ አካባቢ ተንቀሳቅሰው ግጭት ከተከሰተበት አካባቢ የሚሸሹትን አማሮች አንድ ጫካ ውስጥ አግደው ይዘዋል።

“እንዳያማህ ጥራው …” እንደሚባለው በ“ኢትዮጵያዊነት ስም” በወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ቆመናል የሚሉት ደግሞ፣ ለአማራው ህዝብ “ፍትኅ” ብለው ሲጠይቁ የሚሰማው “ወደ ነበሩበት ቀያቸው እንዲመለሱ” የሚል ነው። ሀብት ንብረታቸው ለተዘረፈባቸው፣ ቤታቸው ለተቃጠለባቸው፣ በጉልበት የደከሙ፣ እንዲሁም ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ለሞተባቸው፣ በፍትኅ ጥያቄ የወያኔ አገዛዝ ከሚያሰማው “ወደ ቀየህ ተመለስ” የተለዬ፣ ለአማራው ህዝብ ፍትህ ጠይቄአለሁ ብሎ ደፍሮ ሊናገር የሚችል ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ወዘተርፈ አለ ለማለት ይቸግራል።

ሆኖም በግምቢና አካባቢው “ሁኔታው ተረጋግቷል” በሚል ተፈናቃዮችን ወደ መጡበት ቀያቸው ተመልሰው ሀብት ንብረታቸውን እንዲረከቡ ተብሎ በወያኔ ባለስልጣኖችን አባባል፣ “ከክልል አስተዳዳሪዎች ጋር ተናበው” ከተመለሱ አማሮች መካከል ምን ያህሉ በህይወት እንዳሉ፣  ለጊዜው የሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን መረጃ ባይኖረውም፣ በ“ተረጋግቷል” ስም “ወደ ቀያችሁ ተመልሳችሁ ሀብትና ንብረታችሁን ተረከቡ” ተብለው ወደ ሜጢ ከተማ ከተመለሱ 42 ሰዎች መካከል 40ዎቹ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መኢአድ በ16/01/2007 ዓም ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። እንዲሁም ዛሬ በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ አካባቢ በወያኔ ሠራዊት ጫካ ውስጥ ተከብበው ስላሉት አማሮች የሚደርሰንን ዘግናኝ እልቂት፣ መረጃ ለሚያቀብሉን ሰዎች ደህንነት ስንል ለማለፍ ተገድደናል።

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ አጥብቆ ያወግዛል። አቅሙ በሚፈቅደው መጠንም በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያጋልጣል። በዚህ አጋጣሚም፣ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን፣ የወንጀል ፈጻሚዎችን ስም፤ የነበራቸውን ወይም ያላቸውን ሀላፊነት፣ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ፣ ወንጀል የተፈጸመባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር፣ ወዘተርፈ የመሳሰሉ መረጃዎችን በማድረስ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነት በጸኑ ልጇቿ ለዘለአለም ተከብራ ትኑር!!!

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

moweswe@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule