• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፣ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ!

January 21, 2017 10:51 pm by Editor 1 Comment

የዛሬ አራት ዓመት ዐማራ ነኝ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ብዙ ማሰብና ማውጠንጠን ይጠይቅ ነበር። ምክንያቱም ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት በዐማራው ነገድ ላይ የተነዛው ፕሮፓጋንዳ በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ዐማራ ነኝ እንዳይሉ ገደብ የጣሉ ነበሩ። የመጀመሪያው ምክንያት ዐማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን በመሆኑ፣ ራሱን ወደ ነገድ ደረጃ ማውረድ ውርደት ወይም ከኢትዮጵያዊነት የሚያፋታው አድርጎ መቁጠሩ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ነው። ሁለተኛው በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ የሩቅና የቅርብ፣ የውጭና የውስጥ ጠላቶች የተራገበው ኢትዮጵያን የማጥፋት የተቀነባበረ ዘመቻ ዋነኛው ዒላማ ዐማራው በመሆኑ፣ የዐማራውን ማንነት ጥላሸት የቀባ፣ መልካም ስሙንና ዝናውን ያጎደፈ፣ «በጡት ቆራጭነት፣ በወራሪነት፣ በገዥ መደብነት፣ በጨቋኝ ብሔርነት፣ በነፍጠኝነትና በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጠሩ ለተባሉ ችግሮች ሁሉ ፈጣሪ» ተደርጎ በመወንጀሉ ምክንያት የዐማራው ልጆች ራሳቸውን ዐማራ ነኝ እንዳይሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ መሆኑ ነው።

በነዚህና በሌሎች ተዛማጅ ምክንያቶች የዐማራው ልጆች፣ በመሰል የሌሎች ነገድ ልጆች ተክደውና ተገድፈው በነገዱ ላይ፣ በተለያዩ ፖለቲካዊ ቡድኖችና ስብስቦች ከስም ማጥፋት እስከ ዘር ማጥፋትና ዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምበት፣ ‘ለምን? እንዴት?’ ያሉት እምብዛም እንደነበሩ በነገዱ ላይ የደረሰው ዕልቂትና የዕልቂቱ አለማቋረጥ ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን የዐማራው ነገድ ልጆች፣ በኢትዮጵያዊነት ራሱን ደብቆ  የወገኑን ዕልቂት እያየ እንዳላየ፣ እየሰማ እንዳልሰማ የሆነውን፣ ወደራሱ ኅሊና ተመልሶ ዘሩን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ እንዲችል፣ ዐማራው በማንነቱ ዙሪያ ተደራጅቶ፣ ማንነቱን አስጠብቆ፣ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ ያቀረቡት ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ እንደነበሩ እናስታውሳለን።

ሆኖም ዐማራው፣ ለቀረበው ኅልውናውን የማስጠበቅ ጥሪ የሰጠው ምላሽ፣ ከተደገሰለት ጥፋት ጋር የተጣጣመ ባለመሆኑ፣ ፕሮፌሰር አሥራት በዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ታስረው እንዲገደሉ መደረጉን የምናስታውሰው በቁጭት ነው።  የአሥራት መገደል በተወሰነ ደረጃ ተነሳስቶ የነበረው የዐማራዊነት ማንነት እንቅስቃሴ ከመዳከም አልፎ፣ እንዲከስም አደረገ። ይህም ዐማራን ለማጥፋት የዘመናት ዝግጅት ያደረገው ወያኔ፣ የዐማራውን ልጆች፣ ያለይሉኝታና እሳ፣ በተገኘበት እንደክፉ አውሬ እያደኑ ጨረሱት። ዐማራውን በገፍና በግፍ እያደኑ ሲጨርሱ፣ ከዐማራው ወገን ኧረ ለምን? የሚል ድምፅ ባለመሰማቱ፣ ወያኔ በመሀል፣ በምሥራቅ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ  ለዘመናት የኖረውን ዐማራ አገርህ አይደለም፣ ካገር ለቀህ ውጣ በማለት ሀብት ንብረቱን ዘርፈው አባረሩት። ዐማራው በአያት እና ባባቶቹ  ሕይዎት፣ አጥንትና ደም ተጠብቃ በኖረችው አገር የመኖር መብቱን ተነጠቀ።

ይህስ በዛ! ያሉ ወገኖች፣ ከተሸፈኑበት ኢትዮጵያዊ ካባ ራሳቸውን ገልጠው፣ ለወገናቸው ድምፅ መሆንን መረጡ። እነዚህ ለወገናቸው ራሳቸውን ቤዛ ለማድረግ የቆረጡ ወገኖች« ዐማራውን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!» በሚል መፈክር  ጥፋት ለታወጀበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ለመሆንና ዐማራው ራሱን አደራጅቶ ኅልውናውን እንዲያስጠብቅ ሲንቀሳቀሱ፣ ከማኅበረሰቡ የተገኘው መልስ ቀና አልነበረም። በማንነት ዙሪያ መደራጀት፣« ወያኔን መሆን ነው»፣« ወያኔ በቀደደው ቦይ ገብቶ መፍሰስ ነው»፣ «ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው» ከማለት አልፎ፣« ዐማራ የሚባል ነገር የለም»፣ «ዐማራ ማነው?» የሚሉ ጭፍን ሀሳቦችን በመርጨት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ለዐማራው ድምፅ የመሆን እንቅስቃሴውን በለጋው ለመቅጨት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

ይሁን እንጂ፣ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፤ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ለድል እንደሚያቃርብ ከልብ የሚያምኑት፣ በቁጥር እጅግ ትንሽ፣ በዓላማ እጅግ ግዙፍ የሆኑት የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መሥራች አባሎች፣ ሳይሰለቹና ሳይታክቱ ባደረጉት የዐማራውን ነገድ የማሳወቅ፣ የማንቃት፣ የማደራጀትና መረጃዎችን የማሰራጨት ትግል፣ ይኸውና ዛሬ እንደ ተርብ የሚናደፉ፣ እለፈ አዕላፍ የዐማራ ልጆች ዝምታቸውን ሰብረው፣ በማንነታቸው ኮርተው ወገናቸውን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግና የኢትዮጵያን አንድነት ዳግም ትንሣዔ ዕውን ለማድረግ ሌት ተቀን ከሳይበር እስከ አካላዊ ጦርነት ገጥመው ወያኔንና አጋሮቹን የተፉትን ምራቅ እንዲልሱ እያስገደዱት ይገኛሉ። ይህ የጽናትና የቁርጠኝነት ውጤት ነው። ያለቁርጠኝነት ለድል መብቃት አይቻልምና፣ ሞረሽ ወገኔ ባለፉት አራት ዓመታት በቁርጠኝነት ያካሄደው ዐማራውን የማንቃትና የማደራጀት ትግል ፣ ትግሉን ወደ ትጥቅ ትግል ያሸጋገረው ስለሆነ፣ ይህንም በድል አድራጊነት ለመወጣት ቁርጠኝነቱን በእጥፍ ድርብ ማሳደግ ይጠበቃል።

ስለሆነም፣ የዐማራው ልጆች፣ የተፋፋመው የዐማራው  የመደራጀትና ማንነትን የማስከበር ትግል ለድል እንዲበቃ፣ ሁሉም የዐማራ ልጅ፣ በሀሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብ፣ በምክር፣ በሰው ኃይል ወዘተ ሊተባበር ይገባል። «ድር ቢያብር  አንበሳ ያስር» ነውና ብሂሉ፣ ሊያጠፋን የዘመተውን አጥፊ ቡድን ጨርሶ ሳያጠፋን፣ አጥፊውን ለማጥፋት ድጋፋችሁን ከምንጊዜውም በበለጠ ዛሬ እንሻለን። ብረትን መቀጥቀጥና ተፈላጊውን ቅርጽ ማስያዝ የሚቻለው ሲግል ሲቀጠቅጡት ነውና፣ ወያኔውም የሚወድቀው ራሱን በፈጠረው ሁለንተናዊ ችግር ተማሮ አደባባይ የወጣው የሕዝብ ቁጣ ሳይበርድ፣ቁጣውን ማጋጋል ለነገ የሚባል ተግባር ሳይሆን አሁኑኑ ልንያያዘው የሚገባን ነው። በመሆኑም በውስጥና በውጭ ለሚደረገው ትግል ገንዘብ ወሳኝ ድርሻ ያለው ስለሆነ፣ ጀግኖቻችን ከእኛ ድጋፍ ማነስ የተነሳ ትግላቸው እንዳይጓተት የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን እያቀረበ ሳይውሉ ሳያድሩ በሚችሉት መጠን የወገናችንን ትግል በገንዘብ ለመርዳት የሞረሽ ወገኔ አማራ ድርጅት ድሕረገጽን (http://www.moreshwegenie.org/) በመጎብኘት፡ የጎፈንድሚ (GoFundMe)፤ የፔይፓል (Paypal)፤ ወይም የባንክ አካውንታችንን  ቁጥር ተጥቅመው የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል በመሆን የማያቋርጥ ድጋፍዎን በአንክሮና በትሀትና ያሳስባል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት              ቅዳሜ  ጥር ፲፫ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.             ቅፅ፭፣ ቁጥር  ፲


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Ali says

    February 6, 2017 12:45 am at 12:45 am

    በሁለት ጉዳዮች ለመርዳት ዝግጁ አይደለሁም፦
    1) የገባንበት አዘቅት ጥልቀት እና ስፋት፤ እንክዋን ተለያይተን አንድ ሆነንም በቻልነው፤
    2) እንደ ሄኖክ ያሉ የሞራል መሰረታቸው የተናጋ፤ ለአማራ ሳይሆን ለቲፔኤል ኤፍ የቆሙ በሚመስል ደረጃ እጅግ የወረደ ሃሳብ የሚያቀርቡ ሰዎችን ይዛችሁ የትም አትደርሱም፤ ለአንድነት ፤ በአንድነት ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ህብረት መፍጠር ያለባችሁ ይመስለኛል፡፡

    አብሲቴ…እያለ የሚጽፍ ሰው ይዝችሁ፡ ከጾታ እኩልነት አንጽር እንክዋን … ኢትዮጵያዊያት እንስት እይታዘብዋችሁም?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule