• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለመላው የዐማራ ልጅ የተሰጠ ማሳሰቢያ

September 5, 2016 11:33 pm by Editor Leave a Comment

ጉዳዩ፦ የመጭውን ዘመን መለወጫ (መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም.) በፈንጠዝያ ሳይሆን፤ ዕለቱን በመሪር ሐዘንና በቁጭት አስቦ ስለመዋል።

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ በዐማራው ወገናችን ላይ ከፋሽስት ጣሊያን በከፋ መልኩ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ሲፈጽም እነሆ 41ኛ ዓመቱን አገባድዶ በ42ኛው ላይ ይገኛል። በተለይም ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የጅምላ የጥፋት ዘመቻ አውጇል። የአገዛዙ የኅልውና መሠረት የሆነው ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት ዕድሜና ፆታ ሳይለይ፥  ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ አዛውንትን፣ ጎልማሶችን፣ ወንዶችና ሴቶችን ቤት ለቤት እያደነ እጅግ መርዘኛ በሆነ ጥይት እየደበደበ የዘር ፍጅት እያደረሰ ነው።

የትግሬ-ወያኔ በከፈተው በዚህ ዐማራን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ እህት ወንድሞቻችን ተገድለዋል፤ አያሌዎች ቆስለዋል፤ በርካታዎች ታስረዋል፤  ተጫውተው ያልጠገቡ፣ ክፉ ደጉን ያልለዩ ሕፃናት በአረመኔዎቹ ወያኔዎች ተቀጥፈዋል። ልጆቻችን አድገው ከበስቋላው ሕይዎታችን ይታደጉናል ብለው ተስፋ የሰነቁ ወለጆች፣ ተስፋቸውን አጥተዋል፤ ቤተሰብ ፈርሷል። እነዚህ ወንድም እህቶቻችን ሕይዎታቸውን፣ አጥንታቸውን፣ ደማቸውን የሰጡት እና መስዋዕት የሆኑት፣ ለዐማራ የማንነት ጥያቄ ተገቢ መልስ ለማስገኘት ነው። እነርሱ ለእኛ ነፃነት ሲሉ ሞቱ፣ ተሰቃዩ። እኛስ እነርሱ የሞቱለትንና እየተሰቃዩ ላሉበት ክቡር ዓላማ፣ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ብለን ራሳችን በመጠየቅ፣ ከትውልድና ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድን ተግባር ልንፈጽም ይገባል። ስለሆነም ጀግኖቹ ሰማዕታት እህት ወንድሞቻችን የሞቱለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ፣ ዓርማቸውን አንግበን፣ በአንድነት የድሉን ቀን ለማቃረብ በጽናት ወያኔን ልንዋጋው ይገባናል።

ከሁሉም በላይ ትግሉ የሚጠየቀውን ማናቸውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ ራሱን በሁለንተናዊ መልኩ ማዘጋጀትና ትግሉን በቆራጥነት መቀላቀል ነገ ዛሬ የምንለው ጉዳይ አይሆንም። ማድረግ ካሉብን ድርጊቶች  መካከል በጣም በትንሹ በኑሮአችንም ሆነ በሕይዎታችን ምንም ዓይነት ኪሣራ በማያስከትሉት መጀመር ይቻላል። ስለዚህ የሚከተሉትን ተግባሮች በማከናዎን ከዚህ በታች ስማቸው በተዘረዘሩት ሰማዕታት ስም ጥሪያችን እናቀርባለን።

አንደኛ፦   በሚመጣው የዘመን መለወጫ ቀን በዓሉ ከሚጠይቀው ፈንጠዝያ፣ ሣቅና ጨዋታ ተቆጥበን፣ ዕለቱን የሐዘንና የቁጭት መግለጫ የሆነውን ጥቁር ልብስ ለብሰን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ እያውለበለን እንድንውል፤ ስንበላና ስንጠጣ ሰማዕታቱን በጸሎታችን እንድናስባቸው።

ሁለተኛ፦  ከኢትዮጵያ የሚመጣ እንጀራ እስከ ወዲያኛው ላለመግዛት እንወስን።

ሦስተኛ፦   በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለመጓጓዝ እንወስን።

አራተኛ፦   ከወያኔና ከወያኔ ጋር ንክኪነት ካለቸው ድርጅቶች፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች፣ ወዘተርፈ አንጠቀም።

አምስተኛ፦      የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ከሆኑ ሰዎች ጋር የነበረንን ግንኙነት እናቋርጥ።

ስድስተኛ፦      ዐማራው መከበር የሚችለውና ወያኔን እስከ ወዲያኛው ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ሥልጣን አሽንቀጥሮ መጣል የሚችለው በማንነቱ ሲደራጅ ነውና፣ በዐማራ ስም የተደራጁ ድርጅቶችን እንደግፍ፤ እንርዳ።

ሰባተኛ፦  በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመውን ዕልቂት ለዓለም ማኅበረሰብ በስፋት ለማሣወቅ፣ በየአለንበት አካባቢ በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ትዕይንቶች እንሣተፍ፣ የተማጽኖ ደብዳቤዎችን እና መልዕክቶችን ለየአገሩ ፖለቲከኞች፣ መንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እናድርስ።

ሠንጠረዥ፦ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በትግሬ-ወያኔ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችን ስም ዝርዝር

ተራ ቁጥር የተገዳይ ሙሉ ስም ዕድሜ የመኖሪያ አድራሻ
1. ዕድሜዓለም ዘውዱ 27 ባሕር ዳር
2. ገረመው አበባው 25 ባሕር ዳር
3. ተፈሪ ባዩ 16 ባሕር ዳር
4. ሰሎሞን አስቻለ 25 ባሕር ዳር
5. ሙሉቀን ተፈራ 27 ባሕር ዳር
6. አደራጀው ኃይሉ 19 ባሕር ዳር
7. አስማማው በየነ 22 ባሕር ዳር
8. ታዘበው ጫኔ 21 ባሕር ዳር
9. አሥራት ካሣሁን 24 ባሕር ዳር
10. የሽዋስ ወርቁ 20 ባሕር ዳር
11. ብርሃን አቡሃይ 29 ባሕር ዳር
12. ሽመልስ ታዬ 22 ባሕር ዳር
13. አዛናው ማሙ 20 ባሕር ዳር
14. ሢሣይ አማረ 24 ባሕር ዳር
15. ሞላልኝ አታላይ 21 ባሕር ዳር
16. እንግዳው ዘሩ 20 ባሕር ዳር
17. ዝናው ተሰማ 19 ባሕር ዳር
18. ዋለልኝ ታደሰ 24 ባሕር ዳር
19. ይታያል ካሤ 25 ባሕር ዳር
20. እሸቴ ብርቁ 37 ባሕር ዳር
21. ሞገስ 40 ባሕር ዳር
22. አደራጀው ደሣለኝ 30 ባሕር ዳር
23. ማኅሌት 23 ባሕር ዳር
24. ተስፋዬ ብርሃኑ 58 ባሕር ዳር
25. ፈንታሁን 30 ባሕር ዳር
26. ሰጠኝ ካሤ 28 ባሕር ዳር
27. ባበይ ግርማ 26 ባሕር ዳር
28. አብዮት ዘሪሁን 20 ባሕር ዳር
29. ሀብታሙ ታምራት 27 ባሕር ዳር
30. ሞገስ ሞላ 23 ባሕር ዳር
31. ታደሰ ዘመኑ 26 አዴት
32. እስቲበል አስረስ 19 አዴት
33. አበበ ገረመው 27 ጢስ ዐባይ
34. ይበልጣል ዕውነቱ 24 ጢስ ዐባይ
35. ሰሎሞን ጥበቡ 30 ቻግኒ
36. በረከት ዓለማየሁ 28 ዳንግላ
37. ያየህ በላቸው 30 ዳንግላ
38. ዓለማየሁ ይበልጣል 27 ዳንግላ
39. ሽመልስ ወንድሙ 28 ቡሬ
40. አለበል ዓይናለም 28 ደብረማርቆስ
41. ስሙ ገና የሚጣራ ደካማ እናት ያሉት   ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03
42. ዓይንአዲስ ለዓለም 24 ደብረወርቅ
43. አበጀ ተዘራ 28 ወረታ
44. ደመቀ ዘለቀ 22 ወረታ
45. አለበል ሃይማኖት 24 ወረታ
46. መሣፍንት አማራ 22 እስቴ
47. በለጠ ካሤ 32 ደብረታቦር
48. ይህነው ሽመልስ 30 ደብረታቦር
49.  ማዕረግ ብርሃን   ደብረታቦር ቀበሌ 01
50. መምህር ተስፋዬ ብርሃን   ደብረታቦር ቀበሌ 01
51. ባየሁ   ጎንደር
52. የቻፖራ ወንድም   ጎንደር
53. በለጡ መሐመድ   አዘዞ
54. እንጀራ ባዬ   አዘዞ
55. ግርማቸው ከተማ   ላይ አርማጭሆ
56. አዛናው ደሴ   አርማጭሆ
57. አራጋው መለሰ   አርማጭሆ
58. ሲሣይ ታከለ   አርማጭሆ
59. ሊሻን ከበደ   አይምባ
60. መሌ   አይምባ
61. ሰጠኝ አድማሱ   ደልጊ
62. ታረቀኝ ተሾመ   ደልጊ
63. ኖኖክ አታሎ   ደልጊ
64. ደሴ ደረሰ 53 ሻውራ
65. ግርማቸው ሞገስ   ሻውራ
66. ወርቁ   ሻውራ
67. ማማየ አራጋው   ዳንሻ
68. ፈንታ አህመድ   ዳንሻ
69. ክንፈ ቸኮል   በአከር
70. ፍሥሃ ጥላሁን 25 አዲስ አበባ
71. ቅዱስ ሀብታሙ 16 አዲስ አበባ
72. ይበልጣል ደሴ    

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል-ኪዳን ነው!

ዐማራው ኅልውናውንና መብቱን በትግሉ ያስከብራል!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት!

ሰኞ ነሐሴ ፴ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.                

ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፯

 

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule