• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

October 10, 2014 08:25 pm by Editor 1 Comment

ከአዘጋጆቹ፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?” በሚል ርዕስ ለጻፉት ሥርዓት ጠብቆ ምላሽ የሚሰጡ ተቀብለን እናትማለን ባልነው መሠረት ኢብኑ ሙነወር “መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” በሚል ርዕስ ጨዋነት በተሞላበት አጻጻፍ የላኩልንን ምላሽ ከዚህ በታች አትመናል፤ ምስጋናችንንም እናቀርብላቸዋለን፡፡ ሌላ አዲስ አጀንዳ እስካልመጣ ድረስ በዚሁ ይህንን ውይይት የቋጨን በመሆኑ ምላሽ ጽሁፎችን የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ ጉዳዩን መቀጠል የሚፈልጉ ከጸሐፊዎቹ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋውና ኢብኑ ሙነወር ጋር በኢሜይል ወይም በፌስቡክ ወይም በሌላ በሚያመቻቸው መንገድ በመገናኘት ሃሳባቸውን መላክ ይችላሉ፡፡


በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መንግስት ለአመራሮቹ በሰጠው ስልጠና ላይ የተንፀባረቀውን ሀላፊነት የጎደለው ፀረ-ሀይማኖት እይታ በማስመልከት “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?” በሚል ርእስ በሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው የተፃፈ ፅሁፍ ዛሬ መስከረም 29/2007 አውጥታችኋል፡፡ በቀረበው ፅሁፍ ላይ “በጨዋነት” መመለስ ለሚፈልጉ ሁሉ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን በመግለፃችሁ “የኔ” የምለውን ሀሳብና ማስተካከያ ስልክላችሁ እንደምታወጡት ተስፋ በማድረግ ነው፡፡

በኔ በኩል እንደ ሙስሊምነቴ “ይመለከቱኛል እርማትም ይሻሉ” ከምላቸው ፀሀፊው ካነሳቸው ነጥቦች የተወሰኑትን እያነሳሁ ጥቂት ማለት እወዳለሁ፡፡

1. “የእስላም ሴቶች በትምህርት ተቋማትና መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ሂጃብና ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን ይበጥስ” ማለታቸው በተነሣ ጊዜ አቶ ሽፈራው “ማተቡም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢሆን መውለቁ አይቀርም” …” እዚህ ጋ ማለት የምፈልገው ሀሳብ አለኝ:-

1.1. “ኢስላም” የሀይማኖቱ መጠሪያ እንጂ የተከታዮቹ መጠሪያ አይደለም፡፡ የተከታዩ መጠሪያ “ሙስሊም” ነው፡፡ በርግጥ ይህን ከባድ ነገር አድርጌው ሳይሆን በስፋት የሚንፀባረቅ ስህተት ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ እርምቱን ማስታወሱ አይከፋም ብየ ነው፡፡

1.2. ወደ ነጥቡ ስገባ እውነት ሙስሊሞቹ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን ይበጥስ” ብለው ከሆነ እኔም ስህተት እንደተሰራ ይሰማኛል፡፡ ምክኒያቱም ሙስሊሞቹን ጂልባብና ኒቃብ እንዲያወልቁ እያስገደደ ያለው የሴኩላሪዝም ጭንብል የለበሰው መንግስት እንጂ ህዝበ-ክርስቲያኑ አይደለምና፡፡ “እኔን የምትገድለኝ ከሆነ እንግዲያው እከሌንም ግደል” አይነት አመክንዮ ጤነኛ አይደለምና፡፡

1.3. ባይሆን አንድ ነገር እሰጋለሁ፡፡ ልክ ፀሀፊው እንዳደረገው ለራሳቸው የእምነት እሴቶች የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ሳለ (ማድረግም መብታቸው ነው) የሙስሊሞችን እምነታዊ እሴቶችና የሚከላከሉባቸውን ‪ምክኒያቶች‬ ዋጋ የሚያሳጡ ወይም ‪‎የሚያቃልሉ‬ ሲመለከቱ ጊዜ ምናልባት ሙስሊሞቹም እንዲህ አይነት ሀሳብ ቢሰነዝሩ ብዙ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ማለት የፈለግኩት ሀሳቡ ትክክል ነው አይደለም ሳይሆን የተናገሩበት አግባብ ሊጤን ይገባዋል ነው- ምናልባት ተናግረው ከሆነ፡፡

1.4. ከዚያ ባለፈ “ማተቡም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢሆን መውለቁ አይቀርም” የሚለው የአቶ ሺፈራው ንግግር (እውነት ከሆነ ደግሞም አይባልም አልልም) አስተዋይ ለሆኑ ክርስቲያኖች ትልቅ መልእክት ነበረው፡፡ መንግስት የሙስሊሞቹን እምነት ሲዳፈር “ኒቃብና ማተብ የተለያዩ ናቸው” እያሉ ለመንግስት ብርታትና ጊዜ ከሚሰጡ “ነግ-በኔ” ብለው ከወዲሁ “ለምን” ቢሉ መልካም ነበር፡፡ ዘመቻው ‪ምናልባትም‬ ሙስሊሙ ላይ ብቻ ላይሆን ይችላልና የተነሳው፡፡

2. ሌላው ፀሀፊው “ለማንኛውም ለሁሉም ሰው ግልጽ ይሆንለት ዘንድ የማተብንና የሂጃብ ሊቃብን ምንነት ማየት ይኖርብናልና” በማለት ያጋደለ ድምዳሜ ሰርቷል፡፡ ልክ ማስተዋል እንዳቃተው መንግስታችን የሙስሊሟ ሴት ልብስ መታገድ እንዳለበትም አምኖ ሊያሳምነን ሞክሯል፡፡ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ነው ነገሩ፡፡ በዚህ ነጥብ ስር የተነሱትን ሃሳቦችና የራሴን ምልከታ ጥቂት ልበል፡፡
ፀሀፊው የሙስሊሟ ልብስ መታገድ እንደሚገባው ሁለት ምክኒያቶችን አቅርቧል፡፡ አንዱ የልብሱን ዋጋ ማቅለል ነው፡፡ “ሂጃብና ኒቃብ ለመከለያነት ለመሸፈኛነት ለመደበቂያነት ለመሸሸጊያነት ከሚያገለግል ልብስነት ‪የዘለለ‬ ትርጉምና አገልግሎት የለውም” በማለት፡፡ ሌላኛው የፀጥታ ስጋት ነው “ለአሸባሪዎች መጠቀሚያነት” ሊውል ይችላል በማለት፡፡

2.1. በቅድሚያ የሙስሊሟም የአለባበስ ስርኣት የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ ፀሀፊው “እኛ ክርስቲያኖች ማተብ የምናስርበት ምክንያት በኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር በሆነ በእግዚአብሔር ልጅ) ማመናችንን ለሌሎች ለሚያዩን ሁሉ ለመመስከር ወይም ክርስቲያን መሆናችንን ለሌሎች ለማረጋገጥና ክርስቲያን በመሆናችንም እንደማናፍርበት ይልቁንም እንደምንኮራበት ለማረጋገጥ ነው” እያለ ስለማተብ ሲሞግት ሙስሊሙም ተመሳሳይ ነገር እንደሚል ባይዘነጋ መልካም ነበር፡፡ ይሄ እኮ ቀላል ሂሳብ ነበር? ደግሞም ከማንነት ባለፈ የሙስሊሟ አለባበስ ሌላ ፋይዳም አለው፡፡ እራሱ ፀሀፊው እንዳለው “በሴትነታቸው ሰው እንዳይፈትኑ ወይም እንዳይፈተንባቸው እንዳያሰናክሉ ወይም እንዳይሰናከሉባቸው” ያገለግላል፡፡ ይሄ ከትልቅ ማህበራዊ ቀውስ የሚታደግ ልዩ ስርኣት ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እምነታዊ ግዴታ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

2.2. የፀጥታ ስጋቱን በተመለከተ በቅድሚያ ስጋቱ የጋራ ስጋት ነውና የመፍተሄ አቅጣጫውም በጋራ ነው መፈለግ ያለበት፡፡ ይልቅ እንዲህ አይነቱ ሚዛን አልባ እይታ እና “እኛ እናውቅልሃለን” ነው የስጋት ምንጭ ለሆኑ አካላት ምክኒያት እየሰጠ ያለው፡፡ በትንሽ በትልቁ ማንነቱ የሚደፈርበት፣ እምነታዊ እሴቶቹ ኢላማ የሚሆኑበት አካል የእምነትና የሞራል ገደብ ሳይገድበው የራሱን ፅንፈኛ አካሄድ በእምነት ስም ሊያራምድ ይችላል፡፡ በተለያዩ የአለማት ክፍል እያየን ያለነውም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከዚህ ጋር ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ይልቁንም መፍተሄው ማግለል ሳይሆን ማሳተፍ ነበር፡፡ ስለሙስሊሟ አለባበስም ብንመጣ በየተቋማቱ ጠባቂዎችና ፈታሾች አሉ፣ ለወንድ ወንድ ለሴት ሴት፡፡ ኒቃብ የለበሰችዋ ሙስሊምም ልክ እንደሌሎቹ ሴቶች የምትፈተሸው በሴቷ ብቻ ነው፡፡ አለቀ፡፡ ለሴቷ ደግሞ ለጉዳዩ የሚያስፈልገውን ያክል ትገለጣለች፡፡ ቀላሉን ነገር አቀበት እያደረግን በሴኩላሪዝም ስም እምነትን ለሚያጠቁ አካላት አጋር ባንሆን መልካም ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ ከኢትዮጵያ በበለጠ አሸባሪዎቹ ጥርሳቸውን የሚነክሱባቸው፣ ከኢትዮጵያ በበለጠም ሽብርን በመዋጋት ስም የሚታወቁ በርካታ የምእራቡ ሀገራት ውስጥም ኒቃብ ይለበሳል፡፡ ኒቃብን ያገደችዋ ፈረንሳይ እራሷ ኒቃብን ለማገድ ‪በቀዳሚነት‬ ስታራግብ የነበረው የሽብር ስጋት ሳይሆን ጭፍን ጥላቻዋን የሚያንፀባርቅ ሌላ ምክኒያት ነበር፡፡

3. የአቀራረብ እርማት፡-
በቅድሚያ የማልደብቀው ነገር ፀሀፊው በእምነት ስም ከሚፅፉ ብዙ ፀሀፊዎች አንፃር ሲታይ ቀላል የማይባል ሚዛናዊነት አይቻለሁ፡፡ ይህን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሚዛናዊ ለመሆን ሲቸገር ብቻ ሳይሆን አላስፈላጊ ቃላት ሲሰነዝርም አስተውያለሁ፡፡ ይሄ ለማንም አይበጅም፡፡ ለምሳሌ እነዚህን ሁለት አ/ነገሮች ያስተውሉ፡- “ሂጃብና ኒቃብ የሚያደርጉ እስላም ሴቶች … በየትኛውም መመዘኛ ሊነጻጸር የማይችል የማይገባ ነገርን ለማነጻጸር በመሞከራቸው ‪አለማወቃቸው ባመጣባቸው‬ ስሕተት ‪ሊያፍሩ‬ ይገባል፡፡” “ስለሆነም ማተብን በሂጃብ ኒቃብ ምንነትና አገልግሎት አንጻር ማየት ፍጹም የተሳሳነና ‪ከድንቁርና‬ የመነጨ ‪ከባድ ድፍረትም‬ ነው፡፡” እንዲህ አይነቱ ያልፀዳና ያጋደለ አቀራረብ ወደ አላስፈላጊ እንካ ስላንትያ ነው የሚያስገባን፡፡ እናም ፀሀፊው በሀሳብ ስላልተጋሩት ብቻ በድንቁርናና በአጉል ድፍረት ለመሸበብ መሞከሩን እርማት ሊወስድባቸው ከሚገቡ ነገሮች ሊያካትተው ይገባል እላለሁ፡፡

4. ፅንፈኛ ሴኩላሪዝም
ሴኩላሪዝም በግርድፉ ሀይማኖት በአስተዳደር ውስጥ አስተዳደሩም በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ የማድረግ ስርኣት እንጂ ግለሰቦችን እምነት አልባ የማድረግ ስርኣት አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው የሴኩላሪዝም አረዳድና አፈፃፀም ግን አጉራ ዘለል ነው፡፡ ከመንገስት ቀርቶ ሀላፊነት ከሚሰማው ግለሰብም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ በተጨባጭ እየታየ ያለው ልክ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ስርኣቶች እንደሚንፀባረቀው በቃላት ባይገለፅም በተግባር ግን በሴኩላሪዝም ጭንብል እምነትን ለይቶ ማጥቃት ወይም በእምነት ውስጥ ገብቶ ማቡካት ነው፡፡ የሚያሳዝነው መሬት ላይ ያለው እውነታ ሌላ በሚዲያ የሚነገረው ሌላ መሆኑ ነው፡፡ ማንን እንደሚዋሹ እራሱ ግራ ያጋባል፡፡ “የምታዩትን ሳይሆን የምንነግራችሁን እመኑ” የሚል ሀይል የክፉ አካሄዱ ዳፋ ለሀገርናMuslim and Christian Girl outside National Museum of Ethiopia - Addis Ababa - Ethiopia ለህዝብ ቀርቶ ለራሱም እንደሚተርፍ በምን ቋንቋ ቢነገረው እንደሚገባው አላውቅም፡፡

የመጨረሻውን ነጥብ እንዲሁ ሀሳቤን ለመግለፅ ያክል እንጂ ከፀሀፊው ጋር አያይዤ አይደለም ያነሳሁት፡፡ ከዚያ በተረፈ ሀሳቤን የመግለፅ እድሉን የሰጠኝን ጎልጉል የድረ-ገፅ ጋዜጣና ‪በአንፃራዊ‬ መልኩ የተሻለ ሚዛናዊነት ያየሁበትን ፀሀፊ ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ “ሰዎችን የማያመሰግን አላህን አያመሰግንም” ይላሉ ነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ውዳሴና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና፡፡)

(የፎቶው ባለቤት Adam Jones ነው:: ፎቶውን ያገኘነው እዚህ ላይ “Muslim and Christian Girl outside National Museum of Ethiopia – Addis Ababa – Ethiopia” በሚል ታትሞ ነው:: የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አዲስ አበባ ህዳር 26 2006ዓም/May 16, 2013 ነው::)

munewor@gmail.com

ibn.munewor@facebook.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. zebiba says

    October 11, 2014 12:04 am at 12:04 am

    ወንድም ኢብን መኑር አላህ ሀይር ጀዛክን ይክፈልክ
    የዲነል ኢስላም ድንጋጌዎች ከሌላ ሀይማኖት ጋር በማመዛዘን የምንሰራው አይደለም በራሱ ምሉ የሆነ ነው ከሌላ ሀይማኖት ይህ ተቀንስዎልና ከዲነል ኢስላም ይህንን ቀንሱ ሲባል የሚቀነስ አይደለምይህ በጣም ትኩረት የሚያስፈልገው ነገር ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule