• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“HILLARY WINS” መስፍን በዙ

November 10, 2016 10:23 pm by Editor 2 Comments

* የጅብ ችኩል …

መቸም ይህ የአሜሪካ ምርጫ ከቅስቀሳው እስከ ትራምፕ ምርጫ ትዝታው ብዙ ነው፣ በመጨረሻው ቀንና በምርጫው ውጤት ቀን የሆንነው ግን በጣም ያጓጓና ልዩ ትዝታ ይዞ ያለፈ አጋጣሚ ነው፣ ለብዙዎቻችን … የማልረሳውን የእኔን ትዝታ ከትዝብት ጋር ላጋራችሁ …

“እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!” የሚል መርህን ይዘው ከሚንቀሳቀሱት የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ “HILLARY WINS” “ሄለሪ አሸነፈች!” የሚል አንድ አስገራሚ ሰበር መረጃ ከሌሊት 3:34 Am ተሰራጭቶ ደረሰኝ።

HILLARY WINS ከሚለው መረጃ ስር “ቲጂ ቴሌቪዥን ጠዋት ላይ የምርጫ ጣቢያዎቹን ጎብኝቶ ባገኘው መረጃ መሰረት ሄለሪ የአሜሪካ 45ኛ ፕሬዚደንት ሆነው ተመርጠዋል” በሚል የሚያትተው መረጃ አስገራሚ ነበር፣ መረጃው ለሄለሪ ደጋፊ ደስታ፣ ለትራምፕ ደጋፊ ሀዘንም ነበር … መልዕክቱ እንደወረደ እንዲህ ነበር የሚለው:

TG Ethiopian Television did visit some polling stations this morning. Based on what the voters said, TG Ethiopian Television declares that Hillary Clinton will be the 45th President of the United States …  ከጉጉቴ የተነሳ ደስታዬ ወሰን አጣና በሰፊው በመገናኛ ብዙሃን ማልጀ እስክሰማው የአቶ መስፍን መረጃ ነፍስ ዘርቶብኝ እረፍት ማድረጉን መረጥኩ …!

እረፍት አይሉት እረፍት አድርጌ የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ ወደ ስራ ልሰማራ ረዥሙን መንገድ ስጀምር ግን “እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!” የሚል መርህን ይዞ ከሚንቀሳቀሰው የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ “HILLARY WINS”  “ሄለሪ አሸነፈች” መረጃ “በሬ ወለደ” መሆኑን ተረዳሁ! አዘንኩ፣ ቢያንስ ጭብጥ ሳይያዝ ለምን መረጃ ይሰራጫል? ችኮላው ባላስፈለገ ብዬ ጋዜጠኛውን ሳማርራቸው አጅሬ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ ከወደ ምሽት ላይ ማስተባበያ አሰራጭተዋል፣ በተሰራጨው ማስተባበያም “የተሰራጨውን መረጃ እኔ በማላውቀው መንገድ፣ ከፍቃዴ ውጭ የተሰራጨ ነው!” ብለው ይቅርታ ጠይቀዋል …

It is true that when we talked to the voters in Virginia, most of them said that they voted for Hillary Clinton. Since we only talked to Virginia voters, please disregard the previous email. It was sent without my approval.

Thank you
Mesfin Bezu

ያለጭብጥ መረጃ የጅብ ችኩል እየተኮነ “እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!” ቢሉት ፋይዳ የለውም! ከመረጃ ቅበላው እሽቅድድም ለመረጃው ተአማኒነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የአቶ መስፍን በዙ ስህተት ካስተማረን መልካም ይመስለኛል!

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 1 ቀን 2009 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. tesfai habte says

    November 11, 2016 02:41 pm at 2:41 pm

    ወያኔዎች ምን ሃሳብ ነበራቸው ይመስላል መሰለኝ!—-ሄለሪ ክሊንተን ወደ ስልጣን ከመጣ፡ የኢትዮጵያ ሰው የማሰር፡ የመጨፍጨፍ፡ ብሱማል እና ሱዳን ጦርነቶች ሽብር ፈጥረህ ዶላር ለማግኘት፡ ግደል፡ እሰር፡ ሽብር ከፈጠርክህ የግሪን ካርድ ስጦጣ ከአመሪካ ለመቀበል ተስፋቸው ሰማይ ላይ ደርሶ ነበር። ግን ሁሉ ነገር እንደ ታሰበ ሳይሆን እንዳለው ነው። በተስፋ ሁሉ ግዜ ኣይኖርም። አምላክ ሰርተህ ብላ እንጂ ዋሽተህ፡ ገድለ፡ ሰርቀህ፡ ብላ ያለው ሰው የለም። ኲናት ናፋቂው ወያኔ እና አንዳ አንድ ብዶላር የተገዙ የኢትዮጵያ ሰዎች ግን ዛሬ በትራምፕ መድሃኒት ሕመሙ ይዘልቃ መስሎ ይተየኛል!—-ትራምፕ ስራ እንጂ የመግደል አዝማምየ ያለው አይመስልም!—ለመሆኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስንት ግዜ ሰውን እየገደሉ፡ እያጋደሉ ለመኖር ይፈልጋሉ?—-ሰዎች እንደ ትራምፕ ዓይነት ይበቃናል የማለት ፍሎጎታቸው በመለጽ ናቸው። ጦርነት የክፉ ሰው ውጤት ነው።

    Reply
  2. Ethiopian says

    November 20, 2016 06:33 am at 6:33 am

    The sad part of this story is that the writer’s choice to tune to TG TV for reliable information.Really are you actually living on this planet ? TG TV for reliable source of news.. You got to be kidding

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule