• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3

May 18, 2013 02:51 am by Editor 1 Comment

የአቶ መለስን መሞት መንግስት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። መንግስት ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የመለስ ራዕይ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ በሃዘን መግለጹን የሚያብራራ እና መታሰቢያ ተቋም የሚመሰረት ህግ አወጀ። የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተቋም የገቢ ምንጭ የግል ለጋሾች፣ ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ምንጮች እንደሚሆኑ አዋጁ ጨምሮ አብራራ። መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ ህውሃት ‘የመታሰቢያ ተቋም መስራች ጉባኤ’ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ድራማ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ መለስ ራዕይ ፍቅር መጠመዱን እና ይኽን ፍቅሩን በሃዘን መግለጹን የተለያዩ ተናጋሪዎች በጉባኤው እንዲያብራሩ አደረገ። የመታሰቢያ ተቋሙ ግቦች እና ተዛማጅ ጉዳዮችም ተነገሩ። በድርጅታዊ የሚስጢር አሰራር ቀደም ብሎ የተመረጡ የቦርድ አባላት በጉባኤው ላይ አንደ አዲስ ተመረጡ። ወ/ሮ አዜብም ፕሬዘዳንት ተደርጋ ተመረጠች። ‘መለስ እንደተሰዋ ሁሉ እኛም እስከምንሰዋ ድረስ ለመስራት ቃል እንገባለን‘ የሚል የደርግ አይነት መፈክር በማሰማት ምርጫውን መቀበሏን ገለጸች። ይኽ ድራማ የታየው በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ይሁንና አዜብ መስፍን በጉባኤው ላይ ‘እንደ መለስ እስከምንሰዋ ድረስ እንሰራለን’ ስትል ‘እስክንሞት ድረስ አምባገነናዊ አገዛዛችን ይቀጥላል’ ማለቷ ይመስላል። አምስት ነጥቦች አነሳለሁ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    May 21, 2013 01:45 am at 1:45 am

    ክፍል ፫….(ሀ) መጀመሪያ ስለአቶ መለስ ራዕይ፥
    **በአቶ መለስ አመራር የአንድን ብሔር ወይንም ቡድን(የሀገር ልጅ ዘመድና ጓደኛ ጋብቻ)ያካተተ ሆኖ… የፈዴሬሽን ምክር ቤት የተሞላው በፖለቲከኞች እንጂ ከፖለቲካ ነፃ በሆኑ ሙያተኛ ህግ እና ህገ-መንግስት ተርጓሚ ዳኞች አይደለም። በዚህ ምክር ቤት ውስጥ ያሉት ሰዎች በመለስ የተመረጡ ስለሆኑ የመለስን ራዕይ የሚጋሩ በመሆናቸው ማሰር፣ መግረፍ፣ ማሰደድ፣ማፈናቀል፣የመጀመሪያ ሥራቸውና ዓላማቸው ነው።በዚህም በእየክልሉ በጥቅም የተገዙ ሆድአደር አድርባዮች በአማርኛው ተናጋሪ ሕዝብ ላይ ለሚፈፀም ማናቸውም ወንጀል በታማኝነት የመልስን ራዕይ ለማስፈፀምና የግል ሥልጣንና ሀብታቸውን ለማጋበስ ተግተው ይሠራሉ።”አቶ መለስ አዲሲቷን ኢትዮጵያን የፈጠሩ” ማለት ከዚህ በፊት ብሔር ብሔረሰቦች በዛች ሀገር አባት-አያት-ቅድመ አያት,-የቀደም ቅድም-አያት ያልነበራቸው “በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ወታቦ የተፈለፈሉ ጫጩቶች ናቸው ይለዋል”። ወያኔ አልተሳሳተም፣ ተቃዋሚው ቡድን ተጭበርብሮበት ያጭበረብራል ሕገመንግስቱ ላይ ያለውን ሁሉ ኢህአዴግ እየተገበረ ነው በለው!!በረቀቀና በስብዕና ባሸበረቀ የብሔር ብሔረሰቦችን አልባሳት ለብሰው መሬቱን እየሸጡ ወርቅ የሚሸልሙና ለህዝቦች?መሬትን፣ ወደብን፣ ዜጋን፣ አሳልፈው እየሸጡ የአካባቢውን ሀገራት ሚስጠርና ፖለቲካ ለአሳዳሪዎቻቸው በመሸጥ ፪፩ዓመትን ሥልጣን በልዩ ጥበቃና ድጋፍ የቆዩ… ከሃያላን መንግስት ሲቀበሉት የኖሩትን ጉቦ አሁን “በፋውንዴሽን” ሥም የግለሰቦችና የውጭ መንግስታት ዕርዳታ በሚል የማጭበርበሪያ ራዕይ በውጭ አሽሸውት የነበሩውን ገንዘብ ሁሉ የማስገቢያ ዘዴ… ለፓርቲያቸው የገንዘብ ምንጭ,ለህወሓት የተቋቋመው ‘ኢፈርት’ ገንዘብ የሚደብቅበትና በተዘዋዋሪ ለጦር ሠራዊቱ የገቢ ፈሰስ የሚደረግበት የወሮ በላ ጥልቅና ረቂቅ ውንብድና የሚደረግበት በሀገር ውስጥ የድሃ ልጅ በአጓጉል ልማድ ተለክፎ፣ ቢያልፍለት ሲሸሽ በዱር በጫካ የአውሬ እራት፣በወንበዴ በባሕር ሲጣል፣ ሴት ዜጎቻችን የዓርብ ጎረምሳ የወሲብ የጥም ማርኪያ ሲሆኑ፣ሆድ ዕቃቸው ሲሸጥ፣በመንገድ በእየእሥርቤቱ ሲዋረዱ፣ኪራይ ሰብሳቢዎች ወያኔ በገንዘብ ይረዳሉ። የባለሥልጣን ልጆችና ዘመዶች በውጭ ሀገር የቤት ባለቤት፣ ባለንግድ ቤት ከድሃው አፍ እየነጠቁ አስመጪና ላኪ ሆነው፣ ለድሃው ህዝብ ዓይንና ጆሮ የሆነውን ዜጋ በማስፈራራት የጆሮ ጠቢና አሸባሪነት ትምህርት እየሰለጠኑ የሚኖሩበት አደረጃጀት ፈጥረዋል …..!!

    አማራ መሳዩ ብአዴን(ዘረ ቅይጥ ድንበር ዘለሎች) እና ራዕዩ ሳይከለስ ሳይበረዝ አስቀጥላለሁ ብለው የተነሱት አቶ ኅይለመልስ ከቡድን አመራር ወደ “ኅብረት አመራር” በመለወጥ ሀገሪቱ ምላስ ያለው ብቻ እየቆላ እያንዳንዳዳቸው የፓርላማ አባላት የጠቅላይ ሚ/ኒስትርነት ማዕረግ አላቸው።አቶ ኅይለመልስ በኅብረት ሲመሩ ስለተፈናቀሉ ዜጎችና የህገ መንግስት ጥሰት፣ በክልል አስተዳደርና በወታደሩ ሙሉ ትብብርና በፌደራል በሞቱት ራዕይ የተሠራን ወንጀል… መጀመሪያ የገንዘብ ሚ/ኒ አስተያየት ሰጥቶ፣ የጤና ሚ/ኒስትሩ ማስተባበያ አድርጎበት፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ኒትሩ ተቆጭተውበት፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ ወጥተው፣ በውጭ የሚገኙ ሚዲያዎች ትችት አቅርበውበት፣የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ዘግበውት ከርሞ አሁን ፓርላማ ግባና ቀባጥር ተብሎ በደረሳቸው የራዕይ አስፈፃሚ የህወሓት ሹማምንት ትዕዛዝ ሲቀባጥሩ ዋሉ።

    “እዚህ ቃላቸው ላይ ግን ለብዙዎች ቀና የመሰሉ ግን ብዙ የተቀባዠረ መልዕክት አለው በለው!”

    (፩)ይህ አሁን እየተፈፀመ ያለው የአማራ ተወላጆችን ማፈናቀል ቀጥሎ በኦሮሞው ላይ እንዲፈፀም ተነድፎ እንደነበር ያውቃሉ።
    (፪)የኢህአዴግ ክልል አስተዳደሮች ፀረ-ሕዝብና ፀረ ህገ-መንግስት እንደሆኑ ያውቃሉ፡
    (፫)ኢህአዴግ በኪራይ ሰብሳቢ እንደተሞላ ያውቃሉ
    (፬)በአካባቢው ገንዘብ ያለው አማራና ኦሮሞ እንደማይፈናቀል ያውቃሉ።
    ፭)ይህ ማለት ሀገሪቱ የምትመራው በራዕይ እንጂ በምሁራን ወይም የሕጎች ሁሉ የበላይ ተብሎ በሚነፋለት ህገመንግስት እንዳልሆነ መስክረዋል። ለመሆኑ የህገመንግስቱን ትርጓሜ ያላወቁ የማያከብሩና የማያስከብሩ እንዴት ተሾሙ???? (፮)የንግግራቸው ማጠቃለያ ግን የተፈናቀሉ ይመለሳሉ ወይም ካሳ ያገኛሉ አይልም። የሚለው “ይህንን የማፈናቀል ሥራ በሚስጠር መሥራት ሲገባቸው በገሀድ ሠርተው ለሕዝብ ያጋለጡን ይታሠራሉ፣ ይባረራሉ፣ማድረግ የነበራባቸው ደን አቃጥለው፣ ንብረት አውድመው፣ ተፈናቃዮች አደረጉት ብለው መወንጀልና ማሳመን ነበረባቸው። አሁን ለጊዜው ቢመለሱም በሚስጥራዊ አሠራር እራሳቸው በግዴታ ፍቃደኝነት እንዲፈናቀሉ መሠረታዊ ፍላጎታቸው እንዲጓደል እንዲገለሉና ተማረው እንዲጠፉ ይደረጋሉ ብለው በደንብ አስረድተዋል። ይህንን ባያስፈፅም ኅይሌ አይኖርም በለው!!

    (ለ) የኢትዮጵያ ህዝብ የአቶ መለስ ራዕይ እንዲቀጥል ጠይቋልን?

    (፩) ከሀገር ሉዓላዊነት የብሔር፣የግለሰብና የፖለቲካ ፓርቲ ሉዓላዊነት ይቅደም ጎጠኝነት ዘረኝነት ይቀጥል አላለም!
    (፪) የመናገር፣ የመፃፍ፣ መረጃ የማግኘትና የማዳረስ፣ መብት ይገፈፍ ይቀጥል አላለም!
    (፫)የአንድ ብሔር የበላይነት ሰፍኖ በውጭ ሀገር መማራቸው ይቀጥል ሌላው ምግብና ውሃ ናፍቆት ይሙት አላለም ! (፬)በአንድ የፖለቲካ ጥላ ሥር በአንድ ሰው የመርዝ ፋውንዴሽን መበከሌ ይቀጥል ተውልድ ይፍዘዝ ይደንግዝ አላለም! (፭)የቋንቋ ልዩነት የሃይማኖት ልዩነት አለ ማለት የዜግነት ልዩነት ነው መለያየታችን ይቀጥል አላለም! (፮) አስከፊውን ሥርዓት በኅብርት የጣለ ህዝብ ይከበራል ይደገፋል እንጂ መናቁ መዋረዱ ይቀጥል አላለም! (፯)በቋንቋህ ተናገር ያለው መልስ ቋንቋ ፈጠረልኝ ይርገጠኝ ያዋርደኝ እስትንፋሴ በእርሱ ናት አመልከዋለሁ አላለም! (፰)አማራ መሬትህን ከሚያርስ ህንድ፣ ቻይና፣ ዓረብ፣ ይውረስህ ያለው ትክክል ነው ይቀጥል አላለም! ተበድረንም (፱)የምፅዋት ስንዴ እናበለሃለን በፖለቲካችን በንግድ ዓለም አትግባ የምንሠራውን አትጠይቅ የተባለው ይቀጥል አላለም!(፲)ስኳር ቀምሰህ ጤፍ በልተህ የማታውቅ ሁሉ አክብረኸንና ወደኸን ተቀመጥ አለበለዚያ እናፈርስሃለን የሚለው ይቀጥል አላለም!

    (ሐ) የኢትዮጵያ መንግስት፥
    *መንግስት ህዝብ ነው ሕዝብ ሊመርጥም ሊሽርም መብት አለው መንግስት ህዝብን በቅንነት ሊያገለግል ግዴታ አለበት። በዚህ ጊዜ የሚንቀሳቀሱም የማይንቀሳቀሱም ንበረቶች ሁሉ የመንግስት ናቸው ቁጥጥር ማይጣልበት ሥርዓት ነው ማለት እነዳልሆነ መረዳት አለብን። ለመሆኑ ኢህአዴግ ጥቂቶችን እያበላ ብዙሃኑን እያባላ ቆሞም ሞቶም ያተራምሳል? ?
    “የፓርቲ መሪ መታሰቢያ ተቋም መገንቢያ ገንዘብ ምንጭ ደጋፊ ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆኑ መላው የአገሪቱ ግብር ከፋዮች እንዲሆኑ ያስገድዳል። ለመታሰቢያ ተቋም የሚያስፈልጉ ነገሮች በሙሉ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ ግሙሩክ እና የግሙሩክ ሰራተኞችን ያዛል አዋጁ”። ይቺ ነች ጨዋታ ከወር ደሞዛቸውስ ይቆረጣል አይልም? ከተወሰነ ሀብት በላይ ያላቸው ለዚህ ፋውንዴሽን ያውርሳሉ ይል ይሆን? ?

    (መ) ሰለ አቶ መለስ መታሰቢያ ተቋምና የተመረጡ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት
    ለመሆኑ ሰውዬው ቤተሰብ አልነበራቸውም? ልጆች የላቸውም? ያችኑ ጭንቅላታቸውን ብቻ ይዘው ነው ዓለምን ለማገልገል ወደዚች ምድር የመጡት? አቤት የአምስት ዓመቱ ቀደዳና ቱሪናፋ የራዕይ ትራንሰፎርመር…ይህ ቦርድ የሚመራው የመታሰቢያ ተቋም አቶ መለስ በህይወት ሳለ ያራመዳቸውን ፀረ-ነፃነት፣ ፀረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ነፃ ምርጫ፣ ህግ በፖለቲካ የሚገዛበትን፣ ፍትህ-አልባ እና ህዝብ አፈናቃይ ፖሊሲዎች የሚያስቀጥል እረጃጅም እጅ ያላቸው ሌቦች መሻገገሪያ ድልድይም ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ሸዋ ጠንቀቅ በል በለው!!ለመሆኑ ቀዳማዊ ኅ/ስላሴ ሀውልት እነዲሠራላቸው በተጠየቀ ጊዜ አቶ መለስ ምን ብለው ነበር”አፄው ሲሞቱ ከሥልጣን ወረወደው ነበር አህን መሬት የሌሎች ነው ሀውልት ይቁም ቢባል የሚቆጡ ይኖራሉ መታሰቢያ የሚሆን ነገር ቢሠራ ግን አይፋም ብለው ነበር”ለመሆኑ እሳቸው በዘጠኑም ክልል የተቀበሩት እንዴት ነው?ይህ እነደ ናዚ ቀኝ እጃቸውን ሰቅለው የተሠራው ሀውልት በእርግጥ ማንነታቸውን ይገልፃቸው ይሆን??ለመሆኑ እሳቸው ይህ ሁሉ ራዕይ ሲኖራቸው ሌላው ጀሌ እንዲሁ የኪራይ ሰብሳቢ፤ አድርባይ ሆኖ፣ ቢል ቦርድ ሲሰቅል፣ የውሸት ታሪክ ሲፅፍ፣ግለሰቡ ያልሠሩትን፣ ያልፃፊትን፣ እየቀባጠረ ፀረ ሕዝብ ሴራ ሲሸርብ ንብረት ሲያካብት ሕዝብ ሲያተራምስ ኖሯልን??አሁን የበለጠ የወንጀለኛ መፈልፈያ ወታቦ ፋውንዴሽኑ ጥላ ከለላ ሆኖ እንዲመሠረት ይቀሳፍታልን?ፋውንዴሽኑ አባይን ሊያፈርሰው በለው!!ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule