ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል በመደረግ ላይ ባለው ማንኛዉም አይነት ትግል ውስጥ ተሰማርቶ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ!!!
አንዳንድ ግዜ እራሴንም ሆነ የሀገሬን ልጆች ክፉኛ እታዘባለሁ፣ ያለንበትም ዝብርቅርቅ ህይወት እራሳችን የፈጠርነው በመሆኑ በጣም አፍራለሁ። ለዚህም ነበር የስው ልጅ ማንነት መለኪያ ስለሆኑት ሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች እውቀት፣ እምነትና ብልህነት ለመፃፍ የተነሳሳሁት። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ የሆንን ኢትዮጵያውያኖች እምነትና ብልህነት እንደ ቁምጣ ያጥረናል ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ምክንያቱም ማንነቱንና የሚሰራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ትውልድ ሁሉ በቀላሉ ወደ ነፈሰበት አብሮ አይነፍስምና።
ሰሞኑን ለንደን ላይ የኦሮሞ ልጆች ተሰባስበው ወጥና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲመክሩ እንደ ሰነበቱ ሁላችንም የምናውቀው ነው። በዚሁ ስብሰባ ላይ ብዙዎቹ ያነሱት ነጥብ ጥንካሬ ያለው ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦች የስነዘሯቸው ሃሳቦች ደግሞ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖችን ሲያስቆጣ በተቃራኒው ትግሬዎችን አስፈድቋል። ይህንን የሚያስቆጣ ሀሳብ ከሰነዘሩት ውስጥ አንዱ ሊበን ዋቆ ይባላል። ይህ ሰው ማን እንደሆነና አላማውስ ምን እንደሆነ ከነባር የኦነግ አመራሮችና ወያኔዎች ውስጥ ሆነው መረጃ በሚስጥር ከሚያቀብሉን አባሎቻችን በደረሰኝ መረጃ ላይ በመመስረት የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃቁ ምን እንደነበር ለማስጨበጥ እሞክራለሁ።
ሊበን ዋቆ የተወለደው ነጌሌ ቦረና ከተማ ውስጥ ነው። ይህ ሰው እድሜውን በሙሉ በህብረተሰቡ አመለካከት እንደ ወራዳነት በሚቆጠሩ ተግባሮች (ስካር፣ ሌብነት) የታወቀ ሲሆን የኦሮሞ ልጆችን ለእርድ አሳልፎ መስጠትን ደግሞ ልዩ ስጦታው በማድረግ እስከ ዛሬ ይዞት ዘልቋል። አሁን ደግሞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የመኖር ህልውናውን ባጣበትና ከወያኔ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቅ በመውደቅ ላይ ባለበት በዚህች አጣብቂኝ ወቅት ዩኒፎርሙን ቀይሮ በአዲስ መልክ ብቅ ለማለት ችሏል።
ሊበን ዋቆ በ1963 አስመራ ከሚገኘው የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም (TTI) ተመርቆ በመምህርነት በጋምቤላና በአርሲ አገልግሏል። አርሲ ውስጥ በመስራት ላይ እያለ የኢህአፓ አባል በመሆን ለደርግ በሰላይነት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህን ወቅት ከእሱ ጋር የታሰሩት የኢህአፓ አባላት በሙሉ ሲረሸኑ እሱ ግን በነፃ ተለቆ በወቅቱ ያበረከተው የተሳካ የስለላ ስራ እንደ ውለታ ተቆጥሮለት ስኮላርሽፕ ተሰጠውና ወደ ቺኮዝሎቫኪያ ተላከ። ከቺኮዝሎቫኪያ ሲመለስ ወለጋ ተመድቦ አብዲሳ አጋ ትምህርት ቤት ውስጥ በመምህርነት እንዲሰራ ነጆ ተላከ።
ነጆ በገባ ማግስት ስለትምህርት ቤቱና ስለ ሰራተኛው ምንም አይነት ግንዛቤ ሳይኖረው ሰራተኛውን ማመስ ጀመረ። በነጆ ከተማ ተማሪዎችን ለሰላማዊ ሰልፍ ይዞ መስከረም ሁለት ለሚደረገው ስልፍ ድጋፍ ለመስጠትና የደርግን ትኩረት ለመሳብ ከዚህ በፊት ማንም ሰው ሞክሮት በማያውቀው ሁኔታ ተማሪዎችን ድጋፍ ሰልፍ ከትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ይዞ በመውጣት ድጋፍ የሰጠ ቀንደኛ የደርግ ካድሬ የነበረና ብዙ ሰው ለእስርና ለሞት አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው።
በዚሁ ትምህርት ቤት ውስጥ ለደርግ ሊሰሩ የሚችሉ ካድሬዎችን በመመልመል ሥራ ላይ ተጠመደ። በሳምንት አንድ ቀን የርእዮተ አለም ትምህርት የሚሰጥበትን የውይይት ክበብ አቋቋመ። ከዚያም ሰዎችን ሁሉ ማንነታቸዉን በመምሰል (ለምሳሌ የደርግ ካድሬ ሲያይ ካድሬ በመሆን፣ ተቃዋሚዎችን ሲያገኝ ተቃዋሚ በመሆን) መቅረብን አጠናክሮ ቀጠለ። በዚያ ጊዜ በምእራብ በኩል የሚደረገው የኦነግ እንቅስቃሴ ገና ለጋ ሰለነበር በተገኘው አጋጣሚ እነሱ ውስጥ ሰርጎ በመግባት በእንጭጩ ለማስቀረት ብዙ ጥረት አድርጎ ነበር።
እድሜው ከ35 ዓመት በላይ መሆኑ እየታወቀ የነጆ ወጣቶች ማህበር ፀሐፊ ሆኖ ተመረጠ። ብዙም ሳይቆይ ደርግ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ሲያቋቁም ከመጀመሪያዎቹ ሶስት የነጆ ተመራጮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመረጠ። የነጆ አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ደበሌን እንኳን በመቅደም የደርግ ፓርቲ አባል ሆነ። ከዚያም አሁን ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩትን ሁለት ጓደኞቹን ሀብታሙ ብርሃኑንና ዶ/ር መዝገቡ ኢፋን ወትውቶና ቃል ገብቶ በማሳመን የፓርቲ አባል ካደረጋቸው በኋላ ከኋላ ሆኖ ማስወጋቱን ተያያዘዉ።
ከዚያም ሀብታሙ ብርሃኑ ፀረ ፓርቲና ፀረ የኢትዮጵያ አንድነት ተብሎ ተፈረጀና በድብቅ እንዲገደል ተወሰነበት። አንድ ቀን ማታ በርይሁን ደበሌ የተባለ ሰው ሀብታሙን በሽጉጥ አፈሙዝ እራሱ ላይ መትቶት ተኩሶ ሊገድለው ሲሞክር ለጥቂት አምልጦ ነጆ ፓሊስ ጣብያ ገባ። ከዚያም በርይሁን ደበሌ ሌላ አባተ ይገዙ የተባለ ሰው ጨምሮ ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሔድ ሀብታሙን አስወጥተው ሊገሉት ሲሉ በወቅቱ የፓሊስ ጣብያው አዛዥ የነበረ አወል የሚባል ስው መሀል በመግባት ነፍሱን ሊያተርፈው ችሏል። ኋላም ሀብታሙ ህይውቱን ለማትረፍ ነጆን በአስቸኳይ ለቆ በመውጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ገባ።
በሌላ በኩል ደግሞ ክትትሉ በመዝገቡ ላይ ተጠናክሮ ቀጠለ። በኦነግ አባልነት ፈርጀውት መግቢያ መውጫ አሳጡት። በድሉ ገ/ሚካኤል የሚባል የደርግ ባለስልጣን መዝገቡን በደንብ ስለሚያውቀውና ስለሚወደው ከመገደል እንዳተረፈው መረጃ ሲደርሰው መዝገቡ የሥራ ዝውውር ወደ አዲስ አበባ በመጠየቅ ነጆን ለቆ ለመወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ስለደረሱበት እምሩ የተባለ የነጆ አስተዳዳሪ መዝገቡ እንዲታሰር ትእዛዝ ሰጠ። አወል ተብሎ የሚጠራ የነጆ ፓሊስ ጣብያ አዛዥ መዝገቡን ለረጅም ጊዜ ስለሚያውቀው በሚስጥር አስጠርቶ ስላለው ጉዳይ ካስረዳው በኋላ በአስቸኳይ ነጆን ለቆ እንዲወጣ ነገረው። ከዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ጀርባ ሆኖ ነገሮችን ሲያሽከርክር የነበረው ሊበን ዋቆ እንደነበር ኋላ በማስረጃ ተረጋግጧል።
ሊበን ዋቆ ፍላቴ በተለያየ ጊዜ ሊቀርባቸው ከሞከረው የነጆ ነዋሪዎች ውስጥ ማርቆስ አብርሃም፣ የቦጂው ተወላጁ መምህር ንፍታለም፣ የነጆ አስተዳደር የነበረ ጂፋር ደበሌ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ኋላም ማርቆስ አብርሃም ለአጭር ጊዜ ወደ ቤጂ በመሄድ ከኦነግ አባሎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና አብሮ ለመስራት ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ተመለሰ። ማርቆስ ወደ ነጆ እንደተመለሰ ከላይ ስማቸው ከተጠቀሰው ማለትም ከመምህር ንፍታለም፣ ከጂፋር ደበሌና ሌሎችም ጋር በመሆን ከሊበን ዋቆ ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ፈጥረው የኦነግን እንቅስቃሴ ለማጠናከር መስራትን ቀጠሉ።
ብዙም ሳይቆይ ከሊበን ዋቆ በስተቀር ሁሉንም ግለሰቦች ይዞ ለማሰር ደርግ ወደ ነጆ ሰራዊት አሰማራ። ማርቆስ እጄን አልሰጥም በማለት ሲታኮስ ቆይቶ ሲገደል የተቀሩትን ደግሞ ደርጎች ሰብስበው አሰሯቸዉ። ሊበን ዋቆ በምእራቡ በኩል የሚንቀሳቀሰውን የኦነግ ሰራዊት ለማስመታት በደርግ ስልጠና የተሰጠው ሲሆን ግዳጁንም በአግባቡ ስለፈፀመ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ተደርጎ በመሾም ወደ ንጉሴ ፋንታ ነቀምት ተላከ።
ከዚያም ኦነግን ለመምታት በደንቢ ዶሎ፣ በቤጂ፣ በጊዳሚ፣ በአንፊሎ፣ በመንዲና ናጆራ የደርግ ሰራዊት እያሰማራ የኦነግ አባልና ደጋፊ የሆኑ የኦሮሞ ወጣቶችን ይዞ ማሰርንና መግደልን አጠናክሮ ቀጠለ። ብዙ ሳይቆይ የሻምቡ አውራጃ አስተዳዳሪ ተደርጎ ተሾመ። ሻምቡ ለጥቂት ጊሴ በአውራጃው አስተዳዳሪነት ከሰራ በኋላ የቦረና አውራጃ አስተዳዳሪ ተደርጎ ወደ ደቡብ ተዛወረ።
በ1987 ዓ.ም. ደርግ በመውደቅ ላይ መሆኑን ሲረዳ ከነትጥቁ ደርግን ከድቶ ለኬንያ መንግስት እጁን በመስጠት ቲካ የስድተኞች ካምፕ ተቀላቀለ። ኬንያ ውስጥ ሚስት አግብቶ ሶርሳ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ወለደ። በ1991 ዓ. ም. ሚስትና ልጁን ኬንያ ውስጥ በመተው ወደ አሜሪካ ተጓዘና ኑሮውን ሜሪ ላንድ ውስጥ ታኮማ ፓርክ መሰረተ (Liben Wako Filate; 7777 Maple Avenue #904; Takoma Park, MD.20912)። በ1993 ዓ. ም. የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ፓርቲ አቋቋመ። ልጁ በኖርዌጂያኖች እርዳታ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ሊቀላቀው ሲፈልግ አባትነቱን ቢክድም በ DNA ምርመራ አባትነቱ በመረጋገጡ ምክንያት አሜሪካ ከመጣ በኋላ የመሰረተው ትዳር ፈረሰ።
በ2013 ዓ.ም. ወደ ኬንያ በመሔድ ሀይማኖቱን ከክርስትና ወደ እስልምና ከቀየረ በኋላ የ22 አመት ልጅ አግብቶ ወደ አሜሪካ ተመለሠ። በኋለኛው የህይወት ዘመኑ በወዳጅነት የቀረባቸው ትግሬዎች ዲግሪ መግዛት ወይም በፎቶ ኮፒ ማሽን አባዝቶ ለአባሎቻቸው ማደል ባህላቸው ሰለሆነ እንደዚህ አይነቱ ዲግሪ ትግሬዎች ሲያድሉ ካልደረሰው በስተቀር ከየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የphd ዲግሪ እንዳላገኘ ማረጋገጥ ችለናል። መለሰ ዜናዊ እንደሞተ ለቅሶ ላይ ከእኔ በስተቀር ሌላ ሰው ላሳር ሲል እንደሰነበተ የአይን ምስክሮችና ፎተግራፍ አረጋግጠውበታል። ኑኑ ተብላ የምትጠራው ልጁም ለወያኔው EBS አገልግሎትና በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ኤምባሲ ውስጥ እንደምትስራ አረጋግጠናል። ወንድ ልጁም እንደዚሁ።
በዚህ የህይወት ወጣ ውረድ ውስጥ ሲዋዥቅ ነበር ትግሬዎች ሊበን ዋቆን አግኝተው የራሳቸውን አስተሳሰብ በማጥመቅ ተልእኮውን በብቃት እንዲወጣ ወደ ለንድኑ ኮንፍረንስ የላኩት። መቸም ትግሬዎች ስልጣን ላይ ለመቆየት ርካሽ ግለሰቦችን ፈልጎ የራሳቸው ማድረግንና ለሚያጠፉት የገንዘብ መጠን ደንታ እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ አያቅም ማለት አልደፍርም።
ግለሰቦች በህዝቡ እስካልተመረጡ ድረስ የህዝብ ውክልና ሊኖራቸው አይችለም። ማራመድም የሚችሉት የራሳቸውን እምነት ብቻ ነው! የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን የመሰረተ ትልቅ ህዝብ ሰለሆነ የመገንጠል መንፈስ የለውም። የመገንጠልን ፕሮፓጋንዳ ማራመድ ደግሞ የሚጠቅመው ትግሬዎችን እንጂ ሌላውን ህብረተሰብ አይደለም። ኦሮሞ ለመገንጠልም ከፈለገ ጊዜ ሊፈጅ ይችላል እንጂ ምንም አይነት ኃይል አያቆመውም። ትግላችንም ከትግሬዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከምእራባውያን ጋርም ነው። ለዚህም ነው ወደ ነፈሰበት መንፈሱን በማቆም በአቋም፣ በእምነትንና በብልህነትን ታንፀን በትእግስት ትግሬዎችን ከትከሻችን ላይ አውርደን ለመጣል ኢትዮጵያዊ የሆን ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንታገል የምንለው። መቸም መጠኑ ይለያይ እንጅ በሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ ሆዳምና ባንዳ መኖሩንም አንርሳ!
(ምንጭ፡ ኪያ ቲላ ፌስቡክ ገጽ በማለት Ethiomedia ላይ የታተመ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply