• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!

June 12, 2015 08:40 am by Editor Leave a Comment

* የእናት 9 ዓመት ሰሚ ያጣ ጩኸት

የ4 ዓመት ደልዳላ እያለ ድክ ድክ እያለ ሮጦ ለቀላል ህክምና ከጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አፍንጫ ስር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ገባ። ብዙም ሳይቆይ ከሰመመን መንቃት አልችል አለ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከሰመመን አልነቃም፣ በሃኪሞች ስህተት ብላቴናው መሀመድ ህይዎቱ ተሰናክሎ ላለፉት 9 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነል። ትናንትም ሆነ ከትናንት በስቲያም መሀመድና ቤተሰቦቹ ፍትህ ርትዕ ያገኙ ዘንድ ደጋግሜ ጠይቄያለሁ፣ ዛሬም እጠይቃለሁ! ላለፉት በዘጠኝ አመታት ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጀምሮ ሳይኖር “አለሁ” እስከሚለን  የሴቶች ማህበር ተወካዮች ፍትህን ለመሀመድ ያስገኙ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ ፍትህ ማስገኘት ገዷቸዋል፣ ተበዳዮች ፍትህ  ርቋቸዋል. . .!

ክልትሙ ተንከባሎ ዛሬ ላይ ሲደርስ . . .

ታሪኩን ከመሀመድ እናት ቃል በቃል ስሙት፣ ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ የብላቴናው መሀመድ አብድልአዚዝ ቤተሰቦች ደጋግመው ያደረጉት ውትወታ በቀደም የጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ተቀባይነት አግኝቶ አያውቅም።  ለአዲሱ አምባሳደር የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አገኘና በጉዳዩ ላይ ክትትል መጀመሩን ተመለከትን።

ቆንስል መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በያዘው ማግስት ደግሞ ለ9 ዓመት የዋለለው የፍትህ ጥያቄ መልስ አገኘ! አዎ …  በአሳር በመከራ ለመሃመድ ቤተሰቦች ያለማሰለስ ባደረጉት ጉትጎታ 2.5 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል ካሳ እንደሚሰጥ በሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አንድ አጣሪ ኮሚቴ ውሳኔ ተላለፈ። ውሳኔው ባይከፋም ለሰዓታት ከመተንፈሻ መሳሪያ ውጭ መንቀሳቀስ የማይችለው ብላቴና ቤተሰቦች የተወሰነውን ካሳ ተቀብለው ከሀኪም ቤቱ እንዲለቁ የተላለፈውን ፍርደ ገምድል የወላጅ ቤተሰቦች ተቃወሙት! በውሳኔ አሰጣጡ ሂደት የተገኙት የጅዳ ቆንስል ተወካይም የወላጆችን ውሳኔ በመደገፍ የውሳኔውን ፍትሃዊ አለመሆን ሳይቀበሉ ቀረ! ውሳኔ ያሳለፈው ኮሚቴ በህክምና ስህተት መሀመድ በደል የደረሰበት መሆኑን የሚያረጋግጠው ሰነድና ሙሉ ውሳኔ በአስር ቀናት ውስጥ ለወላጅና ለቆንስል መስሪያ ቤቱ እንደሚሰጥ፣ አስፈላጊ ነው ካሉ  ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ እንደሚቻል  ተገልጾ ጉዳዩ በተያዘው ቀጠሮ ተዘጋ … ይህ የሆነው ከወራት በፊት ነበር!

ህግ አስከባሪ የማጣት እንቆቅልሽ!

ዛሬስ?  ዛሬ የተገባው ቃል የማይጨበጥ፣ የማይዳሰስ ጉም ሆኗል፣ ቆንስል መስሪያ ቤቱ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል አቀርብኩት ያለው አቤቱታ መልስ አላገኘም፣ ወላጆች ላፍታ ከመድሃኒትና ከህክምና ውጭ መቆየት የማይችለውን መሀመድን ይዘው እንዲዎጡ እየተወተወቱ ነው! እናት ልጃቸውን በቅርብ እንዲያስታምሙ ከተሰጣቸው ማደሪያ በኃይል እንዲለቁ ተገደዋል፣ መጠለያውን በጸጥታ አስከባሪዎች እንዲለቁ ሲደረግ ለቆንስል መስሪያ ቤቱ  ቢያመለክቱም መጠለያውን ከመልቀቅ አልታደጓቸውም! የሳውዲ መንግስት የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት አጣሪ ቡድን  ያረጋገጡት ግፍ ተፈጽሞ የመሀመድ ቤተሰቦች በተለይም ብርቱዋ እናት  ዛሬም ድረሱልኝ እያሉ ነው! ቆንስል መስሪያ ቤቱም፣ የተላለፈውን የውሳኔ ሰነድ ተረክቦ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካላት ማቅረብ ተስኖታል! የጎደለባቸው ፍትህ እንዲሰፍን ዛሬም ተገፊዋ ይጮሃሉ … “ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም!” የሆነበት እንቆቅልሽ ግን አልገባን ብሏል!mo

እንኳንስ ይህም መሰል ግፍ ተሰርቶ በአደባባይ ተፈጽሞባቸው፣ በከባድ የሳውዲ መንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች የተፈጸመ የህግ ጥሰት የሚሸፋፍን የህግ ስርአት ሳላለመኖሩ ብዙ መረጃ ማቅረብ ይቻላል።  የቀደመውን ትተን ዛሬ የወጣውን የሳውዲ ጋዜጥ ብንመለከት ያን ሰሞን በሳውዲ አየር መንገድ ተጓዠ የነበሩ ሁለት ታዳጊዎችን ደፍረው የተመሰከረባቸው ሁለት የአየር መንገዱ የጸጥታ ሰራተኞች የአራት አመት እስራትና 1000 ጅራፍ ተፈርዶባቸዋል! የእኛ ብላቴና መሀመድ ስቃይና የወላጆቹ አቤቱታ ጉዳይ ግን ጠያቂ አጧቷልና ህግ ፊት እንኳ የሚያቀርበው ጠፍቷል! ስለሆነም የዜጎች መብት የሚያገባቸው አካላት የት አሉ? ብለን እንጠይቅ ዘንድ እንገደዳለን!

ስለ ጎደለብን ፍትህ መከበር  እንናገር!

ለሰብዕናና ለፍትህ ቀናኢ አይደለንም፣ በሳውዲ አረቢያ የከተመው ነዋሪ ከኮሚኒቲ አባልነት ሸሸቷል፣ የጅዳና የሪያድ ኮሚኒቲዎች የአባላት ድርቅ የመመታታቸው ሚስጥር ተአማኒነት ማጣት እንጅ “ቡዳ” በልቷቸው አይደለም፣ ባሳለፍናቸው በርካታ አመታት ተወካዬዮቻችን ማህበራት ምስረታ አድርተው ትልቁን ኮሚኒቲ  አኮላሸተውታል፣ እናም እላችኋለሁ፣ ለሰው መብት መቆምን ፈነጋግላችሁ የልማት ማህበራት እንደ እንጉይ የመፈልፈሉ የመጠመዳችሁን አደጋ ዛሬም በውል ያልታያችሁ ጉዳይ ፈጻሚ የመንግስት አካልት አካሄዳችሁን ልትገመግሙ ግድ ይላል። ከምንም በላይ ዘንድሮ በተሃድሶ ላይ ነው የምንለው ቆንስል መስሪያ ቤት መመሪያ ወርዶ እያስፈጸመ ቢሆንም መልሶ ከዳጡ ወደ ማጡ እንዳይወድቅ እሰጋለሁ! ለተገፊው መሀመድ ፍትህ ማግኘት ሁላችን ልንተጋ ግድ ይለናል፣ ቢያንስ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካል ይቀርብ ዘንድ ሁላችንም የቻልነውን ከማድረግ ጎን ለጎን መሀመድን በጸሎት እናስበው!

ተወካዮቻችን የግፉአንን እንባ በመጥረጉና መብትታቸውን በማስከበሩ ሰናይ ምግባር ቆመው አለማየታችን የምስኪኗ የመሀመድ አብድልአዚዝ እናት እንባ የሚነግረን እውነታ አይጠፋም! “ስለ እውነት እንመስክርና የመጣው ይምጣ!” ማለትን ለደፈረ ባለፉት በርካታ አመታት በዋነኛነት የዜጎች መብት የቆሙት ተወካዮቻችንም ሆነ የሚያደራጇቸው ማህበራት  ድግስ እየደገሱ በስሙ ገንዘብ ከመሰብሰብ ያለፈ ስራ ሰሩ ቢባል ለህዳሴውን ግድብ አደረጉ የሚባለውን ድጋድ ብቻ ነው የምናገኘው! ለሀገር ግንባታ፣ ለልማትና ድንበሩ ተደፈረ ሲባል ለሀገሩ ቀናኢነት የሚያሳየው ዜጋ ፍትህ እጦት ግን ዛሬም ተዘንግቷል . . .! ይህ በጣሙን የሚያም፣ ሲነገሩት እንኳ መስዋዕትነትን የሚያስለፍል እውነታ ቢሆንም ነግ በኔ ነውና እኔ የምፈራው መከፈል ያለበት መስዋዕትነት የለም!

በእሱ ስራ አንገባም፣ የዘገየው ፍትህ ይሰፍን ዘንድ ለፈጣሪ አቤት እንላለን፣ መልስም እናገኛለን! ምድራዊ ነንና የተወካዮቻችን ጀሮ የጠፊዎችን ድምጽ ይሰማ ዘንድ ከመማለዱ ጎን እንደ ፍጡር የፍትህ ማስከበር ጥሪያችን ትሰሙ ዘንድ እንማለዳችኋለን!

የየራስ ፍርዳችሁን ስጡ፣ እኔ እንዳገባኝ እናንተም ያገባኛል ካላችሁ፣ የማቀርበውን ጭብጥ መረጃ፣ ስለ ሰብአዊ መብት መከበርና ስለ ፍትህ መረጃውን እየተቀባበላችሁ ጩኹት… የተነፈግነውን ፍትህ ማግኘት እስክንችል የእናት ፍቅርን የምታውቁትም ሆነ የማታውቁ፣ የእናት አንጀትን መላወስ ህመም ጠልቆ የሚሰማችሁትም ሆነ ስሜቱን የማይገባችሁ፣ የምትወዱትን ነገር በግፍ ስለመነጠቃችሁ እያሰባችሁ ስለ መሀመድና ስለ ግፉአን ቤተሰቡ ፍትህ ማግኘት አቤት ትሉ ዘንድ አደራ እላችኃለሁ. . .!

በሳውዲ መንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አጣሪ ኮሚቴ በህክምና መሰናከሉ የተረጋገጠው የብላቴናው  ጉዳት ዛሬ ላይ ሲደርስ ፍትህ እጦቱ አንገሽግሾናል፣ ብላቴናውና ቤተሰቦቹ ፍትህ ይሻሉ፣ እኛ የወገናችን ጉዳይ ያገባናልና ፍትህ፣ እንሻለን፣ ፍትህ ናፍቆናል! ጉዳዩን ወደ ፍትህ አቅርቡልን!

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓም

(ሙሉ የመሀመድን እናት ቪዲዮ ከፊስ ቡክ ገጼ ማግኘት ትችላላችሁ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule