• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሬየን አልሸጥም – አጭር ወግ

May 8, 2014 08:24 am by Editor Leave a Comment

አዲሱን (የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን) የ”ኦሮሞ ወጣቶች” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው? ማለት ስለማንፈልግ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል (ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል።

ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ  ተከትሎ ወዳጆች “ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ “ጠላቶች ደሞ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ”የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ “ጦማሪዎች ሆይ ምልእክታችሁ  ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ — “

በነገራችን ላይ አማራ ስለመሆኔ እኔ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ቢያንስ እርግጠኛ እስክሆን ብትታገሱኝ ምን ነበረበት ( ስለ-ኔ ከኔ በተሻለ መልኩ የምታውቀው እናቴ እንኩዋ እንዲህ በሙሉ አፍዋ “አንተ አማራ!”  ብላኝ  አታውቅም። ታዲያ የምታውቀው ነገር ቢኖራትም አይደል ? አለበለዚያ ማኛና ሰርገኛ በሚል ማህበረስብ ውስጥ አድጋ እኔን በደም ስሜ መጥራት ባልዳገታት ” እስኪ ለናቴ ጊዜ እንደሰጠሁዋት እናንተም ለኔ ጊዜ ስጡኝ ” ደሞ ለዘር ፣ እድሜ ለወያኔ እንኩዋን የሰው  የንብ ሰፈር እንኩዋ በታወቀበት ዘመን የምን መንገብገብ ነው!)።  አቦ እናት ለዘላለም ትኑር ! ቀጣዩን ሃሳብ በሚቀጥለው መስመር ላይ ያንብቡት።

መልስ አንድ:  ለሞቱት ስንገጥም

ሲረግጡን ታግሰን

ሲሰድቡን ታግሰን

ይሄን ሁሉ ዘመን ብሶት ተንተርሰን

ሃዘን አኮራምቶን

መላ ቅጡ ጠፍቶን

ሁሉም ግራ ሆኖ

በሃሳብ ተውጠን

ከሥጋ ስማችን

ያፈሩ ከበደን።

እና አይሆንም አልን

ሕጉ ይስተካከል

ይሞረድ ይቦረሽ ባለ ጥርሱ መድብል

ድንበሬን መልሱ ክብሬን እንዳሻችሁ

ነጻነቴን ቀሙኝ ስሜን እባካችሁ።

አልጻፍ አልናገር

አልሰለፍ ይቅር

ባልበላም ግድ የለም ዘመን ጾሜን ባድር

አይከፋኝም ከቶ ብሰደድ በገፋ

ሃገሬ ቢቆረጥ ታሪኬ ቢጠፋ

አይሞቅ አይበርደንም እኛ ግድ የለንም

ሰው ቢፈናቀል ቢራቆት ቢራብም

ወደብ አልባ ብሆን ወይም ወኔ አልባ

እሱ አይደልም ለኔ ከቁብ የሚገባ

 እያልኩ ልቀጥል አሰብኩና ተውኩት።  እውነት እውነት እላችሁዋለሁ ሰው እንዳይከፋው እያሰቡ ለመጻፍ ከማሰብ የበለጠ  የሚከብድ ነገር ዕኔ በበኩሌ አላጋጠመኝም። ስለ መፈናቀል ጽፈ ሳልጨርስ ስለ አፈናቃዮች መጻፍ በጣም ይከብዳል፣ ስለ ዘረኛ ስርዓት ጽፈ ሳልጨርስ ስለ ዘረኛ ተጨቁዋኝ መጻፍ አሁንም ይከብዳል። ስለ ኢትዮጵያ ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ መንዝ ወይም ስለ ኦሮሚያ መጻፍ ይደብታል። ስለ ትግሬ አምባገነን ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ አማራ ወይም እሮሞ ታዳጊ አምባገነን ወግኖ መናገር ይከብዳል ።  የነገሩን ውስብስብነት ተረዱልኝ። በደላቸው፣  ስቃያቸው፣ መታሰር መገደላቸው፣ ሁሉም እውነትነት አለው። ግን   ሀሳባቸው ከደረሰባቸው በደል ያንሳል ፣ ስሜታቸው ካሳለፉት መከራ አንጻር ኢምንት ( ታልኢት) ነው፣ ጉልበታቸውን የማያውቁ በትንሽ ነገር የተጠመዱ ታጋዮች ሆኑብኝ፣ ወንድሞቻቸውን የሰዉለትና የምሰዉለት አላማ ከማንነታቸው ይደቃል፣ ጉዋዶች የተሻል ጥያቄ አለ ( ፍንጭ ልስጣችሁ አይደልም ኦሮሚያ  ኢትዮጵያ የኔ ነች የሚል )።   እስኪ አንድ ወደ ሁዋላ እንመለስና እናስብ። ስናስብ ደሞ በርጋታ እናስብ።

አንድ ወደ ሁ-ዋላ

በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት እንዴት ይካለሉ እንደነበር እናስብ (ስለ ደርግ ጠቅላይ ግዛት አሰያየም ብዙ ማውራት አልፈልግም፣ ማወቅ የፈለገ ያንብብ)  ፣ ከዚያ “የዘመናት ብሶት የወረሰው ጀግናው የ ትግራይ ሰራዊት (ስሙን ቀይሮ የ ኢህአዲግ የተባለው ) አዲስ አበባ ገባና ዔርትራን ለማስገንጠል የሚመች ሕግ አወጣ፣  በዚህም ሕጉ ኤርትራን  ብ ቻ ሳትሆን የልጅነት (የእቃቃ ፍቅረኛዬም) ከነ ኮካ ኮላ ኮርክያችን (ጥሪታችን) ጋ አብራ ተገነጠለች (የሚገርመው ኮርኪ ሰለሆነ ነው መሰለኝ ይዘሽ መወጣት አትችይም አልተባለችም)። በመቀጠልም 70 ምናምን ሺ ሰው የጨረሰውና ያስጨረሰውን ጦርነት አካሄአዱ (በቴዲ አፍሮ ቁዋንቁዋ ” ሁለቱ ዝሆኖች”) በኔ ቁዋንቁዋ ዘ-ለቱ  እባብስ።

ያ ጦርነት አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ለሰራው ሥራ የማህተም ማድረቂያ ካሳ ነበር።  ከዛ የመሃል ሀገር ሰው ጨዋተው የተጀመረ መስሎት በደስታ ፓርላማ ውስጥ ጨፈረ (አንዳንዱ ኮፍያውና ሽርጡ እስከሚወልቅ ድረስ) እና በየቤቱ የዘሩን ቆዳ የስል ጀመር። ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ግን ልጅነት ደጎሰ ጨዋታ ፈረሰ አለ ። ድሮስ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚሀብሄር ነሳ እንዳለው እዮብ ወያኔ ሰጠ ወያኔ ነሳ ሆነ  (ስለዚህም ይህ የዘመን ብሶተኛ  ለኤርትራ በደም ለተቀረው ሕዝብ ደሞ በቾክ  ያሰመረውን ሕግ መርገጥ ጀመረ) እና ከተሜ እንዴት ተደርጎ አለ። እኛ ስንት ነገር ስናስብ የምን ዘሎ መቀላቀል አይነት ነገርም አንዳንዶች ሲናገሩ ሰማናቸው። አንዳንዶቹ ልጆቻቸው በበሽታና በድንቁርና ከማለቃቸው የበለጠ የልጆቻቸው አማርኛ መማር አሳሰባቸው፣ በ 2006 መሬታቸውን ከቀማቸው ይልቅ ከመቶ ዓመት በፊት ቸፍጭፎናል የሚሉትን ሚኒልክን  መውቀስ ቀለላችው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል በሚለው ይጠደሰጡት ፣ የአንድን ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ተቃወሙ እና በታንክ እና በ መትረይስ ከሚደበድባቸው ወያኔ ይበልጥ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አመማቸው እና በጠራራ ጸሓይ እየተገደሉ  ወያኔ ይሙት ይላሉ ስል ” ቴዲ አፍሮ ይታሰርልን አሉ” ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ። ለዚያ ነው እየከፈሉት ያለው መስዋትነት ከያዙት ሃሳብ ይበልጣል ያልኩት ።  ነብሳቸውን አይማረውና የጎሳ ማይክሮ ባይሎጅስቱ (መለስ) ይህንን ቆመው ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን? እንደኔ እንደኔ “አዋ ይሄኛው ባክቴሪያ ልክ እንደታሰበው ነው ሪ-አክት እያደረገ ያለው፣ ያኛው አሁንም ቢሆን ትንሽ ራይቦሶማል ትራይባል ሴንስ ኢንሰርት ሊደረግበት ያስፈልገዋል” የሚሉ አይመስላችሁም? አይ እሳቸው ! አይ እኛ !

አንድ ወደ-ፊት

የትግል ስያሜ ያላማ ግብር ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ለምሳሌ ( የትግራይ ነጻ አውጪን እንመልከት)። በመጀመሪያ ትግራይ ማለት ከየት እስከየት ነው ? የመሃል ሃገሩን ትግራይ ይጨምር ነበር ? እንደዚያ ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ሳይሆን የትግራይ ኑዋሪዎች ነጻ አውጪ ነበር መባል የነበረበት። ምክናይቱም ትግሬ ትግራይ ውስጥ ብቻ አይደልምና  የሚኖረው። ለምሳሌ የኛ ጎረቤት የነበሩት እማማ ሐዳስ ( እድሜ ለ ወያኔ የተንጣለለ ቤት ሰርተው ወደ ሳር ቤት ገቡ እንጂ ትግሬ ነበሩ። ግን ነጻ ስለመውጣታቸው እርግጠኛ አይደለሁም።

አሁንም ወደ ነገሬ ልመለስ ( ማንሽ አንቺ በዛሁ የጠፋሁ እንደሁ መልሽን )። ይሄ በተያያዘ ሃሳብ የመጥፋት ችግር አለብኝ”

አሁንም የስያሜ ጦርነትን የሚቀድም ነገር ያለ ይመስለኛል (እንዲሁ ሳስበው ፣ አያርገውና የኦሮሞ ሕዝብ ምናምን የሚባል ድርጅት አዲስ አበባን “ፍንፍኔን በሸዋኛ ” ወይም ” ፊንፍኔ በኦሮምኛ” እዚህ ጋ ቶሎሳ እና ተሎሳ ብለው ሲጣሉ ስላየሁ ጥንቃቄ ቀድሜ ባረግ ብዬ ነው፣ ለማስመልስ ባደረጉት ጥረት ወያኔን ሳያስቡት ገለበጡት እንበል (ልክ ወያኔ ሳያስበው አዲስ አበባ እንደደረሰ ) ከዛ ምን የሚሆን ይመስላችሁዋል ? እናንተ ለመመለስ ትፈሩ ይሆናል ሌኔ ግን የሞተው መለስ በኦሮሞ ልጆች ስም; በኦሮሞ ልጆች ደም፣ በኦሮሞ ልጆች አፈር ብቅ የሚል ይመስለኛል። ከስያሜ ማንነት ይቀድማል። ማንነታችንን ሳናስከብር ስለ ምንነታችን መናገር አንችልም ( “መ ስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት)።  መቼ ነው የነሱን ጨዋታ መጫወት የምናቆመው? መቼ?

ወግ

አንድ ገበሬ እጅግ የሚወደው በሬውን ሊሸጥ ገበያ ይዞ ይወጣና ሳይሸጥ  ይዞ ይመለሳል።

ዘመድ “ምነው ጃል በሬህን የሚገዛ ሰው አጣህ?”

ገበሬ “አይ በሬዬን  ሊገዙ ከመጡት ሰዎች መሃል አንዳቸውም  ለበሬው የሚሆን ድርቆሽ (መኖ ወይም ሳር) አልነበራቸውም፣ ስለዚህ በሬየን ሽጬ በረሀብ ከምገልው ብዬ ነው ሳልሽጥ  ይዤው የተመለስኩ “

እኔም እንዲህ ነው የሚታየኝ።  ወያኔ መውደቅ ስላለበት ተብሎ በሬዬን በርሃብ ለሚገል ገበያተኛ ነጻነቴን አልሸጥም። እንሱም (ወያኔዎችም) ቢሆን  ሲጠነሰሱ እርሾዋቸው ዘረኝነት ነበረና። በሬዬን ልትገዛ ከፈለክ መጀመሪያ ሳር ይኑርህ ፣ መጀመሪያ የሚገዛ ሃሳብ ይኑርህ፣ መጀመሪያ ስለ በሬ እወቅ።  አስራ ስምንት ሚሊዮን ጭቁን፣  አስራ ስድስት ሚሊዮን ጭቁን ቢጠላ ጥላቻው  ወተት አይወጣውም እሱንም የሚጠላውንም  ይዞ ይጠፋል እንጂ።  ብሬ መግዛቱ አይደልም ቁም ነገሩ ፣ ቁም ነገሩ እስክታርደው ድረስም በሬነቱን መገንዘብ ነው።

ገበያ ወጥቶ ሸማች መሆን አይደለም ቁም ነገሩ፣ ቀም ነገሩ ቢያንስ የሸማች ባህሪ ይዞ መገኘት ነው።

በአንድነት ለመቆም አንድ አይነት አመለካከት የግድ ሊኖር ይገባል በሚለው ሃሳብ ብስማማም በይበልጥ የሚያስማማኝ አንድ አይነት አላማ ሊኖር ይገባል የሚለው ነው።

እስከሚገባኝ የታጋይ ሃሳብ የጨቆኑትን ከማሸነፍ፣ የገደሉትን ከማንበርከክ፣ የበደሉትን ከመበደልም የራቀና የላቀ መሆንhenok-yeshitla አለበት ብዬ አስባለው። በታጋይና በበቀልተኛ መሃከል ያለው ልዩነት ይሄም ይመስለኛል። ታጋይ አንድን ስርዓት ሲቃወም ወይም ሲታገል፣ ስርዓቱ ማድረግ የነበረበት ግን ያላደረገውን ነገር ለመለወጥ ይመስለኛል፣ አንድ ታጋይ አንድን ስርዓት ለመለወጥ ሲነሳ ፣ ኢ-ፍትሃውነትንም ሆነ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እውቀቱና ብቃቱ እንዳለው አምኖ ያ እውቀቱና ብቃቱ ስልጣን ላይ ባለው ስራዓት (ስርዓቱ በሚፈቅደው መንገድ ታግሎ) እውቅናን ሲነፈግ ፣ ያ የሚያልመውን ለውጥ ለማምጣት እምቢ ያለ አካል ነው ብዬም አስባለሁ። በቀልተኛ ግን የድሮ ቁስሉንና ብሶቱን ከማሰብ እና ብድሩን እንዴት እንደሚመልስ ከማውተንተን ያለፈ ሕልም የለውም፣ ለሱ የሥርዓት ለውጥ ማለት የበደሉትን (ወይም በድለውኛል በሎ የሚያምነውን) ማህበረሰብ መበደል ነው፣ ለሱ ትግል ቂሙን የሚወጣበት፣ እልሁንና ቁጭቱን የሚገልጽበት አጋጣሚ መፈለግ ነው። ወያኔ የተፈጠረው በዚህ መንገድ ነው፣ ሌላውም በዚህ መንገድ መሄድ ይፈልጋል፣ እንደ ዜጋ የተሻለ ሃሳብ ከሌለህ፣ ከቂመኛነት ወደ ታጋይነት፣ ከባለ አረርንት ወደ ባለ ር-አይነት መለወጥ ካልቻልክ በሬየን አልሸጥም።

ቸር ይግጠመን

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule