እንደ የቋንቋና የታሪክ አጥኚዎች እምነት የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት ከካዕብ እስከ ሳብዕ እና እንደአስፈላጊነቱ ከዚያም በላይ ሆሄያት የተቀረጹት ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ነው ብለው ለማሳመን ይጣጣራሉ፡፡ በማስረጃነትም በዐፄ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ከ፫፻፳ወ፬-፫፻፴ወ፮ ዓ.ም. የነበረ ንጉሥ የመገበያያ የወርቅ ሳንቲም ላይ “ኢዛና ንጉሠ አክሱም” ተብሎ ለመጻፍ ተፈልጐ “አዘነ ነገሠ አከሰመ” ተብሎ የተጻፈበት ሳንቲም አግኝተናል ይላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ነገርግን ካሉት ነባራዊ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መረጃዎች አንፃር ሲታይ ሊታመን የማይችል ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ተጨባጭ ምክንያቶች በእነዚህ አጥኚዎች ዘንድም የሆነ አንዳች ደባ እንዳለም የሚጠቁም ሆኖ ይገኛል፡፡
፩. እንደሚታወቀው የግዕዝ ሆሄያት አደራደር ከአሌፋቱ ወይም ከአበገደው ሥርዓት ወደ ሀ ለ ሐ መው ለአጠናን እንዲያመች በሚል ምክንያት የለወጡት አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መሆናቸው ይታወቃል፡፡ አቡነ ሰላማ ደግሞ ይህንን ሥራ የሠሩት ኢዛና ብቻውን ከነገሠበት ጊዜ በፊት ማለትም ከወንድሙ ከሳይዛና ጋር በአንድነት ለ፳፮ ዓመታት ይገዛ በነበረበት ዘመን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ደግሞ ምንን ይጠቁማል አበገደው ወይም አሌፋቱ ከዚያ በፊት ይሠራበት የነበረ እንደሆነ ያሳያል ያለው ሐቅ እንዲህ ዓይነት በሆነበት ሁኔታ ዐፄ ኢዛና ፊደል ሳይቸግራቸው ኢዛና ንጉሠ አክሱም ብለው መጻፍ እየቻሉ አዘነ ነገሠ አከሰመ ብለው የሚጽፉበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልምና፡፡
፪. እነሱ የሚሉትን የግዕዝ ፊደላት ተፈጠሩ የሚሉበትን ዘመን እንኳ ብንወስድ ከክርስቶል ልደት በፊት ፰ እና ፱መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ እስከ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ድረስ ከ ፲ወ፫፻ ወይም 1300 ዘመናት በላይ ለሚያህል ጊዜ ፊደሎቹ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳዩ እንደተፈጠሩ ቆይተዋል ብሎ ማመን ሞኝነት በመሆኑና ከባዱ ነገር መሠረታዊ ፊደላቱን መፍጠር እንጂ ከተፈጠሩ በኋላ የእዝልና ቅጽል አውጥቶ የተለያየ ድምፅ እንዲያወጡ ማድረጉ አይደለምና፡፡ የቋንቋው ባሕርይም የሚያረጋግጠው ይሄንን አይደለም ማለትም መሠረታዊያን ፊደላት የሚባሉትን ወይም በግዕዝ ቤት ተርታ ያሉ ፊደላትን ስናይ ለምሳሌ በ ፊደልን ሲፈጥሩ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦን ሊተው የሚችሉበት ወይም በ በ ላይ የተለያዩ እዝልና ቅጽል በማድረግ ሙሉውን የ በን ድምፅ ቤት ሳይቀርጹ ሊያልፉ ወይም ሊተው የሚችሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ የሚያረጋግጠው ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ወይም ከካዕብ እስከ ሳብዕ በመደበኛነት ሳምን እና ከዚያ በላይ በልዩ ሁኔታ ያሉ ድምፆች ከፊደላቱ መፈጠር በፊት በመኖራቸውና በንግግር ውስጥ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ መሆናቸው ነው፡፡
በመሆኑ ከሰባቱ ድምፆች የአንዷን ወይም የግዕዝ ቤቷን ወይም የመጀመሪያ የመጀመሪያ ፊደላቸውን ብቻ ፈጥረው ከአንድ ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በላይ ዝም ሊሉ አይችሉም፡፡ በን ሲፈጥሩ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ድምፆችን ልክ እንደ በ ሁሉ በንግግሮቻቸው ውስጥ ያሉና የሚያገለግሉ መሆናቸው ስለሚታወቅ በን በፈጠሩበት ወቅት የሰባቱም ድምፆች እንደመመሳሰላቸውና የአንድ ቤት ድምፅ እንደመሆናቸው መጠን በበ ላይ እዝልና ቅጽል በማድረግ እንደ ድምፃቸው ሁሉ ተመሳሳይ ፊደሎችን እንደሚቀርጹላቸው የድምፆቹ ተፈጥሮ ግድ ይላል፡፡ ያደረጉትም ይህንኑ ነው በዚህም ምክንያት መሠረታዊያን ወይም የግዕዝ ቤት ፊደላት ለአንድ ሺህ ሦስት መቶ ዘመናት ከቆዩ በኋላ ነው ከካዕብ እስከ ሳብዕ ያሉት ፊደላት የተቀረጹት የሚለው የባዕዳን ሐሰተኛ ስብከት ሌላውን ነገር ሁሉ ትተን ከቋንቋችን ባሕርይ አንፃር አመክንዮአዊ(ሎጂካል) እንዳልሆነ በቀደመው ተጨባጭ ማብራሪያ መሠረት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
፫. የአክሱም መንግሥታት ጡንቻ፣ ሥነጥበባዊ እውቀቶችና አጠቃላይ ከድንበር ማዶም ሆነ ውስጥ የጦፈ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የነበረበት ዘመን ቀርቶ የአክሱም መንግሥታት በአንፃራዊ መልኩ እየደከመ በመጣበት ዘመን ይህ ፈጠራ ተሟላ ማለትም ፊደላቱ እዝልና ቅጽል ወጣላቸው መባሉ ተአማኒነትን እንዲያጣ ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ፖለቲካዊ (እምነተ-አስተዳደራዊ) እና ኢኮኖሚያዊ (ጥሪታዊ) እንቅስቃሴው የጦፈ የሆነበት ዘመን የደከመ ከሆነበት ዘመን ይልቅ ፊደላቱ አስፈላጊ እንደመሆናቸው መጠን የእንቅስቃሴው መጦፍ የሚፈጥረው ሁለንተናዊ መነቃቃት ለፊደላቱ መፈልሰፍ የሚፈጥረው አስገዳጅ ሁኔታ እያለ እንቅስቃሴው በአንፃራዊ መልኩ በደከመበት ዘመን ይህ ይሆናል ብሎ ማለቱ አሁንም አመክንዮአዊ ባለመሆኑ፡፡
፬. በግልጽ እንደሚታየው የግዕዝ ፊደላት ለላቲን እና ለመሳሰሉት ፊደላት መሠረት በመሆኑ የዚህ ድንቅ የፈጠራ ውጤት አመንጪ ማንነትና ዋጋ (credit) ለመውሰድ ምሁራኑን አግባብነት ለሌለውና ለደነቆረ ሽኩቻ ወይም ሽሚያ ስለዳረጋቸው እውነተኛ መረጃዎችን መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ በመቆነጻጸል ሌሎች መረጃዎችን በማጥፋት በመበረዝ በማድበስበስ የፈጠራና ሐሰተኛዎችን ደግሞ በመፈልሰፍ ሥራ ውስጥ የተጠመዱ ከመሆናቸው አንፃር ይህ ጉዳይ ደግሞ በተለይ በእኛ ላይ ሲሆን ነገሩ የተለየ እና የመረረ መልክ የሚይዝና የድርሰቱ ቅመራ አስደናቂ መሆኑ በተደጋጋሚ የተስተዋለ ከመሆኑ የተነሣ፡፡
፭. ከዚህ ከተጠቀሰው ከኢዛና ዘመነ መንግሥት ብዙ በራቀ ዘመን ሳይቀር በፊት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዓለም ታሪክ ዘንድ የኢትዮጵያ ነገሥታት በክፉም ይሁን በደግ ከሌሎች መንግሥታት ጋር የጽሑፍ መልዕክት የተለዋወጡበት አጋጣሚዎች ስላሉ፡፡ በእርግጥ እነኚህ የጽሑፍ መልእክታት በምን ቋንቋ እንደሆኑ አልተገለጹም፡፡ ግዕዝ ናቸው ካላሉም ሌላ መሆናቸው አልተገለጸም፡፡ ለምሳሌ የሐ.ሥ.፰፣፳፮-፵ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደኢየሩሳሌም ሔዶ በነበረበት ወቅት መጽሐፈ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡፡ ይህ መጽሐፍ በግዕዝ ይሁን በዕብራይስጥ አልተገለጠም፡፡ በዕብራይስጥ ነው ካልን በወቅቱ በሀገራችን ሰፊ የሆነ የሃይማኖት ትምህርት በዕብራይስጥ ይሰጥ ነበር ወይም የቤተክህነት ቋንቋ ዕብራይስጥ ነበር ልንል ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ቅ.ል.ክ በኦሪቱ ሥርዓተ አምልኮ ወይም በብሉይ ኪዳን በኢትዮጵያ ሕዝብ ይመለክ እንደነበር የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ይናገራሉና፡፡ ነገር ግን ትምህርቱ በዕብራይስጥ ይሰጥ ነበር ብሎ ለማመን የሚያስችሉ መረጃዎች ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የሉም፡፡ ትምህርቱ በዕብራይስጥ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ደግሞ ዕራይስጥ የቤተክህነት ቋንቋ የመሆን ዕድል ያገኝ ነበር እውነታው ግን ይሄ አይደለም እንደሚታወቀው የቤተክህነት ቋንቋ ግዕዝ ነው፡፡ ሌላ ቋንቋ የነበረበት ዘመን መኖሩ አይታወቅም ይህም ደግሞ ምንን ይጠቁማል የሃይማኖት ትምህርቱ ከመጀመሪያውም በግዕዝ ቋንቋ ይሰጥ እንደነበረ ነው፡፡ በመሆኑም ጃንደረባው ያነበው የነበረው የኢሳይያስ መጽሐፍ በግዕዝ ነበር ብንል ነገሩ የሚያስኬድና አሳማኝ ይሆናል፡፡ በግዕዝ ከሆነ ሐዋርያው ፊልጶስ እንዴት ሊረዳው ቻለ የሚል ጥያቄ ቢነሣ
፩ኛ/ በሐዋ.ሥራ ም. 2.1-3 ላይ ተጽፎ እንደሚገኘው ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የዓለም ቋንቋዎችን ወይም ልሳናትን ገልጾላቸው ስለነበረ በቀላሉ ሊግባቡ የሚችሉበት ዕድል ስለነበር፡፡
፪ኛ/ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወቅቱ በአካባቢው በነበራት አቅምና ተደማጭነት የተነሣ ግዕዝ ቋንቋ በመካከለኛው ምሥራቅ ታዋቂ ቋንቋ የነበረ ነጋድያንና የመሳሰሉት የኅብረተሰብ ክፍሎችም በደንብ ያወሩበት እንደነበር ይታወቃልና፡፡ ከሁለቱ በአንደኛው ምክንያት ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ያነበው የነበረው የኢሳይያስ መጽሐፍ ግዕዝ ነው ብንል ከሐዋርያው ፊልጶስ ጋርም የመግባባት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን መገመት ይቻላል፡፡ በተለይም ደግሞ እንደ ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ ገድለ ፊቅጦር ያሉ የቤተክርስቲያን መረጃዎች መጻሕፍተ ብሉያት በጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ዘመን 900ዓመታት ቅ.ል.ክ. ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ እንደተተረጎሙ ይናገራልና፡፡ ከዚያም በኋላ በዐፄ በአይዞር ቀዳማዊ ዘመን 500 ዓመታት ቅ.ል.ክ. እንደገና ከግእዝ ወደ ዕብራይስጥ እንደተመለሱ እንደተተረጎሙ ይናገራልና፡፡
በአጠቃላይ በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች እስከ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ድረስ ፊደሎቹ አናባቢ አልነበራቸውም ወይም እዝል እና ቅጽል አልወጣላቸውም የሚለው መላምት ሐሰተኛ ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያ ጥቅሞች ላይ የሚሠሩ ደባዎች የቱን ያህን የረቀቁና ምን ያህል ትኩረት የተሰጠው መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ የሚያሳዝነው የእኞቹ የዋሀን ምሁራን ይህንን እና የመሳሰሉትን የባዕዳን ምሁራን ሐሰተኛና የፈጠራ መረጃዎችን ሳይጠራጠሩ መቀበላቸው ነው፡፡ እነኚህ ምሁራንም ፊደላቱ ከደቡብ ዓረቢያ እንደገቡ ሲናገሩ እንደዜጋ ጥቂትም እንኳ ስቅጥጥ አይላቸውም፡፡ ሁልጊዜ የመረጃ ምንጮቻቸው እና ማጣቀሻዎቻቸው የራሳቸው የምርምር ግኝቶች ሳይሆኑ እነዚያው ተንኮለኞች የባዕዳን ምሁራን ናቸው፡፡ አንዳንዴማ እንዲያውም በሚያሳፍር ሁኔታ ከባዕዳኑም በባሰ መልኩ ከሀገራችን ጥቅሞች በተፃራሪ ሲቆሙ ይስተዋላሉ፡፡
እውነቱ ይሔ ከሆነ ማለትም የዘርፉ ምሁራን ለፊደሎቻችን እዝልና ቅጽል ወጣላቸው ከሚሉት ዘመን 1300 ዓመታት በፊት ፊደላቱ እዝልና ቅጽል ኖሯቸው በተሟላ መልኩ አገልግሎት ይሰጡ ከነበረ እስከ አራተኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ በሀገራችንና በደቡብ ዓረቢያ በሳንቲም ላይ እና በአለቶች ላይ እዝልና ቅጽል ባልወጣላቸው መሠረታዊያን ፊደሎች የተጻፉ ጽሑፎች እንዴት ሊገኙ ቻሉ የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡ እውነት ነው እነኝህ መረጃዎች አሉ፡፡ ከጥናቴ እንደተረዳሁት ይሄ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ሁለት የተለያዩ ቡድኖች በሀገራችን ስለነበሩ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት እግዚአብሔር አምላክ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊደላትን የሰጠው ለአዳም የልጅ ልጅ ለሔኖስ ነው እግዚአብሔር 22 የግእዝና 22 የዕብራይስጥ ፊደሎችን በጸፍጸፈ ሰማይ (በሰማይ ሰሌዳ) ላይ ቀርጾ ሥሎ አሳይቶታል፡፡
በዚህ ምክንያትም በሀገራችን አንደኛው ቡድን እግዚአብሔር ለሔኖስ ከሰጠው ፊዳላት ውስጥ በፍጹም መጨመርም መቀነስም የለበትም መጨመርም መቀነስም ክህደት ነው በማለት እነዚያን ፊደላት ብቻ ይዞ ሲጠቀም የኖረ ክፍል ነበረ፡፡ ሌላኛው ክፍል ደግሞ ለፊደላቱ እዝልና ቅጽል አውጥቶ ለእያንዳንዱ ድምፅ አንዳንድ ፊደል እንዲኖራቸው በማድረግ (phonetic) ማለት የተፈለገን ነገር በትክክል እንበል ብሎ ሲጠቀም የነበረው ደግሞ ሌላኛው ቡድን ነው፡፡ በመሆኑም ሁለቱም ዓይነት አገልግሎቶች እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ሊኖር ቻለ፡፡ በአራተኛው መቶ ክ/ዘመን ግን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (አቡነ ፍሬምናጦስ) በማቴ. ወንጌልን 25፤14-30 ያለውን በመስበካቸውና ፊደላቱን ማበርከት መክሊትን ማትረፍ እንጅ ክህደት አለመሆኑን በመስበካቸው ስምምነቱ ተፈጥሮ ከዚያ በኋላ እዝልና ቅጽል በወጣላቸው ፊደላት መጠቀም ተጀመረ፡፡ በዚህ ምክንያት ነው እዝልና ቅጽል ያልወጣላቸው ፊደላት እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቆዩ የቻሉት እንጅ ፊደላቱ ከዚያ በፊት እዝልና ቅጽል ስላልወጣላቸው አልነበረም፡፡
ባዕዳኑ ይህን ሊሉ ከቻሉበት ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ደግሞ የላቲኑ ወይም የጥንት ሮማውያን ፊደላት የተወሰዱት ከግሪክ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፡፡ እንግዲህ ጉዳዩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ የጥንት ግሪክ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት የጠበቀ ከመሆኑ የተነሣ እንዲያውም ጭራሽ እነሱ ለእኛ ያላቸው ፍቅርና አክብሮት እጅግ በጣም የበዛ ከመሆኑ የተነሣ ወደ አምልኮ ሁሉ የተቀየረበት ሁኔታ እንደነበረ እና እኛን ኢትዮጵያውያኑን ኃጢአት አበሳ ፈጽሞ የሌለባቸው፣ ጠቢባን እና ኃያላን፣ በወቅቱ ያመልኩባቸው የነበሩት አማልክቶቻቸው ጓደኞችና አቻዎች ወይም ባልንጀሮች አድርገው እኛን የሣሉበት ዘመን እንደነበረ የራሳቸው የታሪክ ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡ በዚያ የግንኙነት ወቅት ፊደላቶቻቸውን ከእኛ ፊደላት እንደቀዱ ይገመታል፡፡ ሌሎች ሀገራትም በሚስዮኖቻቸው እና በነጋድያኖቻቸው አማካኝነት ፊደሎቻችንን በቀጥታ እንዳሉ አንዳችም የቅርጽ ለውጥ ሳያደርጉ ወስደው የሚጠቀሙ ብዙ ሀገራት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእኛ እንደወሰዱ የሚያረጋግጠው የሥነ-ጽሑፍ ታሪካቸው ከእኛ እጅግ የዘገየ እና አጭር መሆኑ ዋነኛው ነው፡፡
ምክንያቱም ልጅ አባቱን አይወልድምና፡፡ ግሪካውያኑ እኛን ፍጹማን አድርገው እንዲገምቱን ያደረጋቸው አንዱም ይህ በወቅቱ እጅግ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ሆኖ የታያቸው ፊደላቶቻችን እንደሆነም ይገመታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሌሎች አውሮፓ ሀገሮች ጸሐፍትም በተመሳሳይ ለእኛ የነበራቸው አመለካከት በጣም ቀናና ክብር የተሞላበት ነበረ፡፡ በየሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጉዳዮች እና ሌጀንዶች ወይም አፈታሪኮች ይነሣሉ፡፡ የሕክምናና የመድኃኒት ቅመማ መድኃኒቶችም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን እነኝህና የመሳሰሉት ነገሮች ከኢትዮጵያ ወደ ሀገራቸው ይገቡ እንደነበር የሚነገሩ ታሪኮች በየሀገራቸው አሉ፡፡ ይህንን ነገር ተአማኒ የሚያደርገው የሀገራችን በሥነ ሕይወት ሀብቷ ወይም በ(bio diversity) ሀብቷ በዓለም ካሉ ሀገሮች ዋነኛዋ መሆኗ ነው አሁንም ቢሆን እንኳን የደን ሀብቷ እንዲህ ተመናምኖ ባለበት ጊዜም እንኳን መሥነ ሕይወት ሀብቷ በዓለም የታወቀች ነች፡፡ ይህ ሀብት ደግሞ ለመድኃኒቶች ቅመማ ዋነኛው ግብአት ነው፡፡ በዘመኑ እነኚህ ውለታዎቿ በምዕራባዊያኑ ዘንድ ተገቢ ቦታ ነበረው፡፡ እንደዛሬው የዘረኝነት በሽታ ወረርሽኛቸው ሳይመጣባቸውና ሳያንኳስሱን በፊት፡፡ የእኛን የግዕዝ ፊደላት የተፈጠሩበትን ዘመን እንደምንም ብለው ለማሳጠር ከሚፈልጉበት ምክንያቶችም አንዱ ይህ ነው፡፡ ፊደላቶቻቸውን ከእኛ እንደወሰዱ እንዳይታወቅ ለማድረግና ከእናንተ በፊት ነው ፊደላቶቻችንን የቀረጽነው ለማለት ነው፡፡
የላቲን ፊደላቶችን ስንመለከት ከ፳፮ቱ ፊደላቶቻቸው ከካፒታል ሌተሮቹ ፳፩ዶቹ ከስሞል ሌተሮቹ ደግሞ ፳፫ቱ የተወሰዱት ከእኛው የግዕዝ ፊደላት ነው፡፡ ሦስቱማ እንዲያውም ከነድምፃቸው እንደተወሰዱ ማየት ይቻላል፡፡ ከካፒታል ሌተሮቹ ስንጀምር B የቀድሞዋን መ በማቃናት፣ C ከ ር፣ E እና Mን ከ ጠ፣ H ከ ዘ፣ I ን ከ ፰ ቁጥር፣ Lን ከ ረ፣ Nን ከ ጊ ተንጋላ፣ O እና Qን ከ ዐ፣ Pን ከ የ፣ Rን ከድሮዋ መ የተወሰደችውን Bን በመሽረፍ፣ Sን ከ ፴ ቁጥር ተቃንታ፣ Tን ከ ተ፣ Uን ከ ሀ፣ Wን ከ ሠ፣ Vን ከ ሠ የተወሰደችውን W በመቁረጥ፣ Aን ከ ሠ የተወሰደችውን እና ከ W የተቆረጠችውን Vን ገልብጦ ጭረት በማድረግ፣ Xን ተን በማዛመም፣ Yን ከሀሌታው ሀ ራብዑ ሃ፣ Zን ከ ጊ፡፡ በዚህም መሠረት ከ፳፮ቱ ፳፩ዱ ከእኛ መወሰዳቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ወደስሞል ሌተሮቹ ስንሄድ a ከዓይኑ ዐ፣ bን ከሐምስ ድምፅ ምልክት፣ cን ከ ር፣ dን ከሐምስ ድምፅ ምልክት የተወሰደችው b ዞራ፣ eን ከ ሮ፣ gን ከ የ ዞራ፣ hን ከ ለ ዞራ፣ iን l እና jን ከ፲ ቁጥር፣ mን ከ ጠ፣ nን ከ በ፣ oን ከዓይኑ ዐ፣ pን ከ የ፣ qን ከ የ የተወሰደችው p ዞራ፣ sን ከ ፴ ቁጥር ተንጋላ፣ tን ከ ተ፣ uን ከ ሀ፣ vን ከ ሠ የተወሰደችው w ተገንጥላ፣ wን ከ ሠ፣ xን ተን በማዛመም ፣ yን ከሀሌታው ሀ ራብዑ ሃ፣ zን ከ ጊ፡፡ በዚህም መሠረት ከ፳፮ቱ ፳፫ቱ ከእኛ መወሰዳቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከነድምፆቻቸው የተወሰዱትም ስሞል ሌተሩ a እና o ከዓይኑ ዐ ስሞል ሌተሩ t ከ ተ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ቁጥሮቻቸውንም ቢሆን የወሰዱት ከእኛ ነው፡፡ እነሱ ግን ከዘረኝነት በሽታቸው የተነሣ ከሚንቁት ከጥቁር ወሰድን ላለማለት ከዓረብ ወሰድነው በማለት ከእኛ እጅግ በጣም ዘግይተው ከእስልምና መመሥረት ጥቂት ቀደም ብሎ ከተፈጠሩት ከዓረብኛ ቋንቋ ፊደላትና ቁጥሮች ወሰድነው ይላሉ፡፡ የእኛን የግዕዝ ፊደላት ዓረባዊ ለማድረግ የሚጥሩበት ዋነኛው ምክንያትም ይህ ነው፡፡ ከወሰድንም ከጥቁር ሳይሆን ከዓረብ ወሰድን ለማለት፡፡ ወደ ቁጥሮቻቸው ስንሔድ 0ን ከ ፬ ቁጥር፣ 1ን ከ ፲ ቁጥር፣ 2ን ፯ ቁጥር፣ 3ን ከ ጠ ተንጋላ፣ 5ን Üን በማቆም ፣6ን የሐምስ ድምፅ ምልክታችን፣ 7ን ከገ ወይም ከ ፫ ቁጥርን በማዞር ፣ 8ን 0ን ላይና ታች በማጋጠም፣ 9ን ከሐምስ ምልክት የተወሰደችውን 6 ቁጥርን በመገልበጥ ወይም ዐ ላይና ታች ቅጽል በማድረግ 6 እና 9 ተገኙ፡፡ በዚህ መሠረት ከ10ሩ 9ኙ ከእኛ እንደተወሰዱ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ የተቀሩት ፊደሎቻቸውና ቁጥሮቻቸውም ቢሆኑ በቀጥታ አይደለም ማለቴ እንጂ ከኛ ያልሆኑ ሆነው አይደለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተክርስቲያን ቀንደኛ ጠላት የነበሩት መናፍቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የአማርኛ መዝገበ ቃላታቸውን ሲጽፉ፤ በጥቅሞቻችን ላይ በመቅናት ዐይናቸው ቀልቶ በምቀኝነት እውነትን በማጣመምና ሀብቶቻችንን ለመንጠቅ ሳይደክሙ ያለ ዕረፍት እንደሚያሴሩት ልክ እንደ ምዕራባዊያኑ እኩያን የዘርፉ ምሁራን ሁሉ መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት ፊደሎቻችንን የዐረቦች፣ ቁጥሮቻችንን ደግሞ የጽርአዊያን (ግሪካዊያን) እና የቅብጣዊያን (የግብጻውያን) ነው በማለት ጽፈዋል፡፡ እኒህ ከሀዲና ባንዳ እርጉም ተኩላ በነበረባቸው ኑፋቄ ምክንያት በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ተወግዘው የተለዩ የነበሩና በዚህም ምክንያት በ20 ዓመታቸው ተሰደው ከሀገር ወጥተው ለ30 ዓመታት ያህል በአውሮፓና በመካከለኛው ምሥራቅ እየተዘዋወሩ ምዕራባዊያኑን በሚያስገርም ታማኝነት (በባንዳነት) ሲያገለግሉ ቆይነው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ቃል ሊገልጻቸው የማይችል እጅግ እኩይ የጥፋት ልጅ ናቸው፡፡ አንብባቹህ ትታዘቡት ዘንድ የጽርአዊያን እና የቅብጣዊያን ፊደሎች ናቸው ስላሏቸው ቁጥሮቻችን የጻፉትን ቃል ለቃል ልጥቀስ፡፡
ከቁጥሮቻችን ከ ቁጥር በስተቀር ሁሉም የጽርአዊያን እና የቅብጣዊያን ፊደል ነው፡፡ ይሄንን ያደረጉት ከፍሬምናጦስ (አቡነ ሰላማ) ጋር የነበሩት ጽርአዊያን እና የቅብጣዊያን ናቸው ይባላል፡፡ እንዲህ ያደረጉበት ምክንያት የግእዝን ፊደል ከአኃዝነት አውጥተው የእርሳቸውን ፊደል በግእዝ ፊደል ላይ አኃዝ አድርጎ ለማስገባት ነው፡፡
ይኸውም ሮ ዖ ሚክሮን ከሚሉት ከታናሹ ዖ ስም የመጣ ነው፡፡ êና Ëም የጽርእ ሮ ነው መልኩ የግእዝን የ ይመስላል፡፡ ¤ እና ¦ም የጽርእ ዜታ (ዜድ) ነው፡፡ መልኩ የ ገን ኃምስና ሣልስ ይመስላል፡፡ Ü እና Ý Þ ተዘዋውረውና ተዘቅዝቀው አለቦታቸው አለመልካቸው ተጥፈዋል፡፡ እኒህም በጽርእና ቅብጥ ኒ ሚ ላምዳ በሮማይስጥ ኤን ኤም ኤል የሚባሉት ናቸው፡፡ áም የነሱው አኃዝ ነው መልኩ ተለውጦ እንደ ን ሁኗል፡፡ በወዲያ ግን ራሱ ግጥም ነው እግሩም ቀጥያለ ነው፡፡ ብለዋል
አይገርማቹህን? ከà በስተቀር ሁሉም የባዕዳኑ ናቸው ካሉ እያንዳንዱን እየጠቀሱ ከየትኛው ፊደላቸው እንደተወሰደ መግለጽ ነበረባቸው፡፡ የጠቀሷቸው ግን እነኙህን ብቻ ከመሆኑም በላይ እንደታዘባቹሀቸው ከባዕዳኑ ፊደላት ጋር ባይመሳሰሉም በግድ ለማመሳሰል ምን ያህል እንደደከሙና እንዳልመሰለላቸው ማየት ይቻላል፡፡ ቁጥሮቻችን ከላይና ከታች ያሏቸው ሰረዞች ሲነሡ ፊደሎቻችን መሆናቸውን በግልጽ ማየት እየተቻለ ከባንዳነታቸው የተነሣ ጨርሰው ወደ ማይመስሉት ወስደው ሀብታችንን አሳልፈው ለባዕድ ለመስጠት ደከሙ፡፡ እኒህ እኩይ ሰው ምን እንደተጠቀሙ ለምንስ እንዲያ እንዳደረጉ ባላውቅም የቤተክርስቲያንንና የሀገራችንን ጥቅሞች የሚጎዱ በርካታ ክፉ ክፉ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ በእርግጥ ሃይማኖታቸውን ቀይረው ካቶሊክ መሆናቸው ምክንያት ሆኗቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖታቸው እንጅ ደማቸው አልተቀየረ ሊቀይሩትም አይችሉም ያንን ያህል ጤነኝነታቸውን እጅግ በሚያጠራጥር ደረጃ በገዛ ሀገራቸው ላይ እራሳቸውን ለጠላት ቀጥረው በጠላትነት መሰለፋቸው ለምን?
ቸር ይግጠመን
ቅጽ 4 ቁጥር 72 ሐምሌ 2004 ዓ.ም.
Qaalluu says
ወንድማችን የገለጽክልን ድርሰት ጥሩ ነበር። ግን ገለባበጥከው እንጂ። ፊደሎቹን መጀመሪያ የፈጠሩት ኣጊኣዚያን(የግዕዝ ተናገሪዎች) አይደሉም። ወይም ሴሜትኮች (ሐበሾች እና ፋላሾች) አይደሉም። የኩሽ ነገድ የሆኑ የኬሜት ጎሣዎች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ደግሞ የነበሩት በአባይ ሸለቆ ውስጥ ከኑቢያ /ሜሮዌ እስከ ሜዲትራኒያን ባህር ድረስ ነው። ህብሩዎችም ወደዚህ ኣህል ፍልጋ ሲመጡ ስዎቹ በጠም ብልሆችና አዋቂዎች፥ የጥበብ ሰዎች መሆናቸውን ይረዱ ነበር። አብርሃምም ከከላዲያ አካባቢ ተነስቶ ወደ አሁኑ ግብጽ ከመጣ በሁዋለ ነው እግዜብሔርን የወቀውና። እስማኤልን ከወለደ ብሁዋላ በ103 ዓመቱ የተገረዘው። መጽሀፍ ቅዱስ ተመልከት። ኹሾች ሲገረዙ በማየቱ ነው ያንን የፈጸመው። በመጽሀፍ ቅዱስ የተጠቀሰው “ኢትዮጵያ” ደግሞ “አሁኑ የሓበሻ -ኢትዮጵያ” ሳይሆን የኩሽ ኢትዮጵያ ነው። ይህ የጠቀስከው ብንወስድ፥
“ለምሳሌ የሐ.ሥ.፰፣፳፮-፵ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደኢየሩሳሌም ሔዶ በነበረበት ወቅት መጽሐፈ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡”
ንግሥት ሕንዳኬ የኣጊኣዚያን ሳትሆን የኩሾች ንግስት ቤተ መንግስትዋም ኑቢያ ውስጥ ቴቤስ አካባቢ ነው።
ፍደሎቹ ከኣጊኣዚያንና ከፋላሾች/ሰቃሊያን ጋር አልመጠም። ከኩሾችና አክሱምን ከቆረቆሩት ጋር ነው።
ከኬሜት ወደ ፌንቃዊያን፥ ጊሪኮችና ላቲኖች ተስፋፈ። የኛ የሚቱሉትም ቁጥሮች የግሪክ ናቸው። የግዕዝ ፊዳልም ከዚሁ ነው የተገኛው።
የኢትዮጵያ የእውቀትና የመድሃኒት አገር የተባለው የኩሾች ምድር እንጂ የአሁኑ ሐበሻ-ኢትዮጵያ አይደለም። የሬሣ ማድረቂያ ሜምህ ሁሉ የሰሩት እነሱ ናቸው። ስለዚ ውሸት ብቀርባችሁ ይሻላል። በአሁኑ ወቅጥ ራዲዮ-ካርቦን ተፋጥሮዋልና ያጋልጣችዋል። ወደፊት ደግሞ የበለጣ ይፈጠራል።
ፀዳለ says
Qaalluu አንተያልከው አውነት እንደሆነ ጽፈሃል፡፡ ሌላውን እውሸታም በማለት ከመሳደብ በስተቀር፤ ያንተ እውነት ለመሆኑ እኮ ምንም ዓይነት ማስራጃ አላቀረብክም፡፡ሁለተኛ ኢትዮጵያ አንድ ኢትዮጵያ ናት፡፡ የምን “የሓበሻ የኩሽ ኢትዮጵያ” ነው ደግም የምታወራው? የዘመኑ የዘር ፖለቲካ አራማጅ ነህ ለበል?
Gudu Kasa says
Qaallu…. ዘር ዘር ትሸታለህ
abebe says
ደነዝ ሰው የማይገባህ፣ የሀገር ሸክም ፡፡ ድሮስ አንተ መች ኢትዮጵያዊ ነህ ፤ ስደተኛ ወፍ ዘራሽ ታሪክ ከማበላሸት ታሪክን ፈልገህ አግኝ፤ አንተ መሀይም፡፡
abebe says
ከብት ታሪክ ሳይኖርህ ታሪክ ታወራለህ፡፡ ማንነትክን በምትናገረው