• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም

July 11, 2014 11:55 pm by Editor 1 Comment

“እነሱ ሁለት አገር አላቸው። ኢትዮጵያን ይዘዋታል። በስደትም እንደፈለጋቸው እየኖሩ ነው። እኛ ግን አንድም አገር የለንም። በስደት እንኳን እንዳንኖር እየተደረግን ነው። ሸሽተን በተሰደድንበት ምድር እንኳን ዋስትና የለንም። ከዚህ በላይ ምን ይምጣ?” ይህንን የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ለጎልጉል የተናገሩት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ነበሩ። የወ/ት የሺሃረግን ሃሳብ በመንተራስ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንዳሉት “አገር ውስጥም እስር፣ በስድት ምድርም ስጋትና እስር ካለ፣ የይለይለት መንፈስ መነሳቱ አይቀርም። ሰዎች የመኖር ተስፋቸው ሲመናመን የፈለገው ይምጣ ይላሉ። አሁን ኢህአዴግ ከስጋቱ ብዛት እየፈጸመ ያለው ድርጊት ሰዉን ሁሉ ወደዚሁ የሚያመራ ነው።”

ሰሞኑን ኢህአዴግ የወሰደውን፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ሲከናውን የቆየውን፣ ወደፊትም በቀጣይነት የሚገፋበትን እስርና አፈና አስመልክቶ የተፈጠረው ስሜት ከራር ነው። ኢህአዴግ ቋንቋው ሁሉ እስር መሆኑ እየፈጠረ ያለው ስሜት ኬላና ልጓሙ እንዳይፈርስ የሚሰጉ ጥቂት አይደሉም። የኢህአዴግ የአፈና መረብ ያልገባበት ቤትና መንድር እንዲሁም ክልል የለም። በሃይማኖት ቤትም ያለው እሳትና ችግር ቀን የሚጠብቅ ነው። ኢህአዴግ ግን ሁኔታዎችን ከመመርመር ይልቅ ቋንቋውና መፍትሄው እስርና አፈና ብቻ መሆኑ አስገራሚ እንደሆነ ስምምነት አለ።

የሰሞኑ አጀንዳ

“የጦር አውሮፕላን በመያዝ ኢህአዴግን ያመለጡ ወገኖች የመን አመቺ ብትሆንም እንደማይመርጧት ይናገራሉ። የመን ከቶውንም የማይታመን አገር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ አለ። አቶ አንዳርጋቸው ታዲያ እንዴት ሰንአን ረገጡ? ምን ቀን ጣላቸው? እሳቸው በየመን ትራንዚት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ መረጃው እንዴት ደረሰ? ከሦስት ሳምንት በፊት ስለሚያደርጉት በረራ ማን? እንዴት? መረጃ አስተላለፈ? የሚሉት ጉዳዮች በዋናነት መመርመር ግድ ነው። ቀጣዩ የቤት ስራም ይህ ነው።” ይህ በኢሜል ከደረሰን በፖሊሲያችን መሰረት ከማናትመው ሰፊ ጽሁፍ የተቀነጨበ ነው። ጽሁፉ ሌሎች የበረራ አማራጮች ስለመኖራቸውም ያወሳል። አቶ አንዳርጋቸው በተያዙበት ቅጽበት ወደ አዲስ አበባ መላካቸውና በበነጋታው ሽያጩ በትዕዛዝ ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል የትራንስ ኢትዮጵያ ሸሪክ ድርጅት ስለመሆኑም ይጠቅሳል።

andargachew11ሠሞኑን እጅግ አነጋጋሪ የሆነው ይህንን ዜና ተከትሎ የተለያዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ቢከናወኑም የአንዳርጋቸው ጽጌ የጉዞ መርሃ ግብር አስቀድሞ ሊታወቅ የቻለበት አግባብ ሊመረመር እንደሚገባ የሚጠቁሙ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። የየመን አቋም እየታወቀና ሌሎች አመራሮች ወደዚያ እንዳያመሩ ተከልክለው አቶ አንዳርጋቸው እንዴትና በምን የተለየ ምክንያት የመን ሊገቡ ቻሉ? የመንን ተደጋጋሚ የጉዞ በረራ መስመር አድርገው ለምን መጠቀም መረጡ? ለወደፊቱስ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል? የሚለው አሁን እየተከናወኑ ካሉት ተግባራት ጎን ለጎን ትግሉ ወደሌላ አቅጣጫ በመጓዙ በፊት ሊመረመር እንደሚገባው ጠንካራ ጥቆማዎች አሉ።

በኢህአዴግ እጅ ሆነው “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” ሲሉ የተደመጡት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን “በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ” ሲል ግንቦት 7 ይገልጻቸዋል። አንዳርጋቸው መያዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላም ሆነ አስቀድሞ የሚመሩት ድርጅታቸውን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ የየመንን መንግሥት የሚቃወሙ መግለጫዎች ተበትነዋል። ሁኔታው ያንገበገባቸው ወገኖች ተቃውሞ አሰምተዋል። እያሰሙ የሚገኙ አሉ። ዜግነት የሰጣቸው የእንግሊዝ መንግሥትም በየዓመቱ 300 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደጉመውን ኢህአዴግን ከዚህ ቀደም ሲል የተወሰነው የሞት ፍርድ ተግባራዊ እንዳይሆን እየተማጸነ መሆኑ ተሰምቷል።

ወ/ሮ የምስራች ሃ/ማርያም አስቀድመው ባለቤታቸው አቶ እንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን መስኮት ለመመልከት ቢከብዳቸውም፣ ከተረጋጉ በኋላ ያዳመጡት የባለቤታቸው ንግግር የተለመደ መሆኑንን አመልክተዋል። የሶስት ልጆች እናት የሆኑትና አስራ አንድ ዓመት በትዳር አብረዋቸው የኖሩት ወ/ሮ የምስራች ባለቤታቸው ኢህአዴግ በሰየመው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ወ/ሮ የምስራች ለአሜሪካ ሬዲዮ በሰጡት አጭር መግለጫ አቶ አንዳርጋችው ወዲያው ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን የእንግሊዝ መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን እንዳረጋገጠላቸው አመልክተዋል።yemi

ወንድማቸው አቶ በዛብህ ጽጌ ከአሜሪካ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ ስለወንድማቸው የሚያወቁትን አብራርተዋል። በንግግራቸው ወንድማቸው ከራሳቸው ጋር ስለመታረቃቸው የተናገሩት “የቀረውን ራሳችሁ አድርጉ” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ገልጸዋል። በማያያዝም “ለፕሮፖጋንዳ የሚቀርብ” በማለት የወንድማቸው ንግግር ሁሌም እንደሚደረገው የተቆራረጠና ለተፈለገው ዓላማ እንዲመች የማድረግ ነገር ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ወንድማቸው አቶ አንዳርጋቸው በቅጽበት ወደ ኢትዮጵያ በመተላለፋቸው ሙሉ በሙሉ የእንግሊዝ መንግሥትን ነገሮችን የማጣራት ጊዜ እንኳን እንዲያገኝ አላስቻለውም ሲሉ ተደምጠዋል። የ1966 የተማሪዎች ንቅናቄ አባል የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ለራሳቸው ያልኖሩ ሰው እንደነበሩም አስታውቀዋል።

የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ሲናገሩ “እንደ አንዳርጋቸው ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው አላየሁም … በእውነት በጣም እድለኛነት ነው እንዲህ ከውስጥ ከራስ ጋር መታረቅ” በማለት አስቀድመው የተናገሩትን አቶ አንዳርጋቸው በኢቲቪ ዜና እወጃ ላይ በተመሳሳይ “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” በማለት ተመሳሳይ ቃላትን/ሃሳብን በመጠቀም በኢቲቪ ላይ አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል።

ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ

ኢቲቪ ተለቅ ያሉ ጉዳዮች ሲገጥሙት በተደጋጋሚ ከፊት መስመር የሚሰለፈው ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ነው። አቶ መለስ “በድንገት ቢያልፉም” በፖለቲካ ጉዳይ ታፍኖ የቆየውን ያረጀ ዜና እንደ አዲስ ይዞ የቀረበው ተመስገን ነበር። ተመስገን ጥቁር ልብስ አሰፍቶ፣ ጥቁር ስሜት ውስጥ ሆኖ፣ እምባ እምባ እያለው አቶ መለስ “ተሰዉ” ሲል የሃዘኑን ጥልቀት ከቶውንም ሊሸሸግ temesgen1የማይችል እንደነበር ወቅቱን የሚያስታውሱ የሚሰጡት ትዝብት ነው።

ሰሞኑን አቶ አንዳርጋቸው ተያዙ የሚለውን ዜና ለማቅረብ አሁንም ግንባር የሆነው ተመስገን፣ ዜናውን ሲያውጅ ልቡ በአፉ ሾልካ የምትወጣ እስክትመስል ደስታው ወደር አልነበረውም። ለፍረጃ የሚጠቀሙባቸውን ቃላቶች እየረገጠና እያጎላ፣ በኩራት መንፈስ አንዳርጋቸውን ጽጌ “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” ሲሉ እንድንሰማ “ጋብዞናል”። ለሙያው ቀረብ ያሉ ለጎልጉል እንደገለጹት እንዲህ ያለው ወሬን ተከትሎ የሚፈራረቅ ስሜት ሙያውን የሚያረክስ ነው። ትንሽ ቆየት ቢልም ተመስገን መንገድ ላይ መደብደቡ የሚታወስ ነው።

ኢህአዴግ – የቂምና የበቀል “ገበሬ”

“ኢህአዴግ፣ በተለይም ዋናው የኢህአዴግ አስኳል ህወሃት ቂም በመዝራትና በቀል በመፈልፈል ቀዳሚ ነው” በሚል በተደጋጋሚ አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች በአገሪቱ እየተበራከተ የሄደው እስር፣ አፈና፣ ቶርቸር፣ ያልተመጣጠነ ኢኮኖሚያዊ “ወረራ”፣ የቅኝ ግዢ ይዘት ያለው አገዛዝና ከአገዛዙ ባህሪ በመነሳት እየተተገበሩ ያሉ “የወደፊት ዓላማን” ተገን ያደረጉ ክንዋኔዎች ህዝብን ሆድ ካስባሱ ዓመታት አልፈዋል።

በስደት አገራቸውን ለቀው ለመኖር የተገደዱ፣ በስደት አገር እንኳ ራሳቸውን መከላከል እየተሳናቸው ነው። በኬኒያ ኢህአዴግ ያሻውን እንዳያደርግ ከልካይ የለውም። ኬንያ ተጨማሪ የኢህአዴግ የስለላ መረብና የስለላ ሰራተኞች መፈንጫ ስለመሆኗ በርካቶች በምሬት የሚናገሩት ነው። አገር ጥለውና ሰሽተው ኬንያ የመሸጉ በህወሃት ታጣቂዎች ይያዛሉ፣ ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፣ ስር ስር እየተከታተለ የሚያቀርበው የለም እንጂ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ታፍነው የሚወሰዱት ጥቂት አይደሉም።

ደቡብ ሱዳን ገድጋዳና እንብጭ መንግስት ከመሆኗ ጋር ተዳምሮ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንዳሻው የሚጋልብባትokello መናፈሻው እንደሆነች በርካታ ማስረጃ በመዘርዘር አስተያየት የሚሰጥበት ነው። በደቡብ ሱዳን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ዘልቀው የፈለጉትን ማፈን ህወሃት ለሚመራው የአፈና መዋቅር እጅቅ ቀላል ጉዳይ ነው። የቀድሞውን የጋምቤላን ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎን በተመሳሳይ አፍኗል። በርካታ የጋምቤላ ወጣቶችም አሸባሪ በሚል ታፔላ ተለቅመዋል።

አገር ቤት እስር ላይ የሚማቅቁ ወገኖች ቁጥር ከቀን ወደቀን እያሻቀበ ኢህአዴግ የሚዘራው የጥላቻና የበቀል ስሜት እያጎነው ነው። በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ታሳሪዎች በምህረት ስም ቢለቀቁም በሚታወቁትና ሚስጥር በሆኑት ማጎሪያዎች የታፈኑ ወገኖች ቁጥር የሚቀንስ እንዳልሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የችግሩ ሰለባዎች ቢማጸኑም ሰሚ ጆሮ ባለማግኘታቸው በየቤቱ ቂም እየተወቀጠ ነው። በየዘመድ አዝማዱ ዘንድ ቂም እየተደለዘ ነው። በየቀዬው ቂም እየተላመጠ ነው። በየቦታው ቂም ያፈራው የበቀል ፍሬ ሊቀነጠስ እየተቃረበ ነው። በራሱ በኢህአዴግ ሟቹ መሪ አገላለጽ “ቂም ሊያተራምስ” ተቃርቧል በሚል ስጋታቸውን የሚገልጹ እያየሉ ነው።

እስካሁን የታሰሩትና ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉት ያነሱ ይመስል አሁንም እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቅርቡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ከሚሉት ክፍሎች ውስጥ መልካቸው ቀይረው ብረት ካነሱ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራ ተናግረው ነበር። እንደተባለውም አቶ አንዳርጋቸው በየመን ታግተው ኢትዮጵያ ላይ ላለው አገዛዝ ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢና ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ እንዲሁም የዓረና ስራ አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይፋ ሆኗል። የታሰሩት የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮች እስካሁን ድረስ ክስ አልተመሰረተባቸውም። የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የት እንዳሉ እንኳ እንደማይታወቅ ድርጅታቸው አረናን በመጥቀስ አሜሪካ ራዲዮ ዘግቧል። ሚዲያ የማያውቃቸውን ቤታቸውና ወገናቸው ይቁጠራቸው።4 party officials 1

ምርጫ መጣ – የኢህአዴግ ምርጫም ቀደመ

ምርጫ በመጣ ቁጥር ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት 1997ን እያሰበ ብርክ ብርክ እንደሚለው የሚናገሩ በተለይ በወቅቱ አቶ መለስ ህመማቸው እንደጨመረ ይገልጻሉ። የስልት ችግርና ተራ የወንበር ጥማት አባዜ ድሉን እንደ ጉም አበነነው እንጂ ኢህአዴግ ዛሬ ላይ ሊኖር እንደማይችል የሚገልጹ ክፍሎች፣ ምርጫ ሲደርስ ኢህአዴግን የሚያጥወለውለው “ጠፍቼ ነበር” ከሚለው የሞት ያህል የሚከብድ ፍርሃት በመነሳት ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ እንደ ሸምዳጅ ተማሪ ምርጫን 99.6% በማምጣት እየነቀነቀ ማሸነፍ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።

ለዚህም ውሳኔው አፈጻጸም እራሱ የፈለፈላቸው “ባለሃብቶች” ገንዘብ አሰባስበው ዘመቻ ያካሂዳሉ። ማታ ማታ የሚጠየፉትን የንብ አርማ ለብሰው ይተጋሉ። የተቀናቃኝ ፓርቲ ውስጥ ጎላ ያለ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ይለቀማሉ። ከዚህ ቀደም እንደታየው ሁሉ ህዝብን የሚገዛ ስብዕና ይኖራቸዋል ተብሎ የሚታሰቡትን መልቀም ይጀመራል። በተለመደው የፍርድ ሂደት “አሸባሪ” ተብለው እስር ቤት ይጣላሉ። ከምርጫ ጋር አብሮ የሚመጣው የኢህአዴግ ምርጫ እንዲህ አይነቱ ምርጫ እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል።

በዘንድሮ ዓመት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች የርስ በርስ ንትርክ በንጽጽር የቀነሰበት፣ ውህደት የታየበት፣ ከውጪ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉት አገሮችም ከወዲሁ ምርጫ ላይ ኮስተር የማለት እቅድ እንዳላቸው ምልክት የሰጡበትና ተቀናቃኞችን ወደ አንድ ህብረት እንዲመጡ ያሳሰቡበት በመሆኑ ኢህአዴግ የራሱን ምርጫ “እስር” አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፓርቲዎች ዘንድ ስጋት አለ።

“አገዛዝና” “መንግሥት” አልተለዩም

በአገር ውስጥም ሆነ ውጭ ባሉት ዘንድ ህወሃት/ኢህአዴግን እንደ ሕዝብ እንደሾመው አመራር “መንግሥት” እያሉ የሚጠሩት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አገር ውስጥ ያሉት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች አማራጭ የላቸውም፣ ተገድደው ነው፣ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ላለመክተት ነው፣ … ቢባልም በውጭ የሚገኘው ተቃዋሚ ግን ይህንኑ አጠራር መከተሉ የሚያሳስባቸው ወገኖች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከድርጅቶች በሚወጡ መግለጫዎችና ማሳሰቢያዎች ኢህአዴግን አብጠልጥለው እየወቀሱ “የህወሃት መንግሥት”፣ “የኢህአዴግ መንግሥት”፣ “የወያኔ መንግሥት”፣ የሚሉ ስያሜዎችን በንግግርም ሆነ በጽሁፍ መጠቀም እርስበርሱ የሚቃረን ሃሳብ ነው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ በተለይ “መንግሥት” የሚለውን መሠረታዊ ሃሳብ ገደል የሚከትና ለህወሃት/ኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር ሥልጣን እንዳለው ዕውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ በተለይ በውጭው ዓለም በሚገኙ ድርጅቶች ዘንድ የሚታየው ይህንን እንኳን ያላገናዘበ ተቃውሞ ፈጽሞ ሊስተካከል እንደሚገባው አስተያየታቸውን የሚሰጡ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ “ዱሮ ድልድይ ከማፍረስ ጀምሮ አሁን አገር የሚመራ ሽፍታ፣ ራሱ አሸባሪና ወንበዴ ነው፤ “መንግሥት” ሳይሆን በግድ በሕዝብ ላይ ራሱን የጫነ “አገዛዝ” ነው፤ ይህም አጠራር ሲበዛበት ነው” በማለት ተቃዋሚዎችም ሆኑ ሌላው ለህወሃት “መንግሥት” የሚለውን ቃል ከመጠቀም በመቆጠብ “አገዛዝ” በሚለው መተካት እንዳለባቸው ከአገር ውስጥ ለጎልጉል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. hussein amanu says

    July 15, 2014 10:48 am at 10:48 am

    enem enditafen new ende Yemnagerew

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule