• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ

April 14, 2014 08:37 pm by Editor 1 Comment

የኢህአዴግን የስለላ መዋቅርና አካሄድ አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ተበራክተዋል። ኢህአዴግ ራሱን እንደሚስለው ዓይነት ድርጅት ሳይሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉድለት ያለበት፣ በሚዲያ ነጻነት ኋላ ቀር፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በማሳደድ ግንባር ቀደም፣ አፋኝ ህግ በማውጣትና በማሸማቀቅ ወደር የማይገኝለት፣ ለሚያወጣው ህግና ደንብ የማይገዛ፣ የውስጥ ችግሩ ታይቶ በማይታወቅ መጠን ዜጎችን ለስደት እየዳረገ እንደሆነ እየተመሰከረበት ነው።

ኦባንግ ሜቶ
ኦባንግ ሜቶ

ኢህአዴግን ሸሽተው አገር ለቀው የተሰደዱ በስደት ምድርም ኢህአዴግ እየተፈታተናቸው እንደሆነ መግለጽ ከሰነበቱ ቆይቷል። በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በጀርመን፣ በስዊድንና በእንግሊዝ አገር ስደተኞችን በመሰለል ተግባር ላይ የተሰማሩ “የስደተኛ ሰላዮች” በስፋት ስለመኖራቸው መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። የተለያዩ ድርጅቶች በዚህ ጉዳይ ምን ያህል እንደገፉበት መረጃ ባይወጣም አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስራውን ያገባቸዋል ከሚላቸው ክፍሎች ጋር እየሰራ እንደሆነ በዚሁ መድረክ መገለጹ ይታወሳል። በወቅቱ አቶ ኦባንግ “ስደተኛ ሆኖ ስደተኛን መሰለል በህግ የተከለከለ ወንጀል ነውና በዚህ ጉዳይ ርህራሄ ሊኖር አይችልም” ነበር ያሉት።

ማርች 11 ቀን በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር አስተባባሪነት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የፓርላማ ተወካይ፣ የኖአስና/NOASና ዘረኝነትን የሚቃወመው ድርጅት መሪ ተገኝተው ነበር። በሰላማዊ ሰልፉ ተገኝተው ንግግር ካደረጉት መካከል ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ይጠቀሳሉ። በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ “እነሱ አገር ቤትም አገር አላቸው፤ በስደትም አገር አላቸው” በማለት ነበር ለጎልጉል አስተያየታቸውን መስጠት የጀመሩት።

yeshihareg
የሺሃረግ በቀለ

በሰልፉ ላይ ካቀረቡት ንግግር በተጨማሪ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡት ጸሐፊዋ፣ ስደተኞች ሁሉ አንድ አይደሉም። “ሆን ተብሎ የስደት መረጃና ማስረጃ ማመልከቻው ተመቻችቶላቸው የሚላኩ የወያኔ ቅጥረኛ ሰላዮች አሉ። እነሱ ባለሁለት አገር ናቸው። እኛ አንድም አገር የለንም” ብለዋል። ይህንን ጉዳይ አቅም በፈቀደ ሁሉ ማህበሩ ከአባላቱና ድጋፍ ከሚሰጡት ሁሉ ጋር በመሆን ከዳር እንደሚያደርሰው ገልጸዋል።

“ልብ እንበል” በማለት አስረግጠው የገለጹት ስለ ሁለተኞቹ ስደተኞች ነው። ስርዓቱ ባለው የግፈኛነት፣ የዘረኛነት፣ የከፋፋይነት፣ የዴሞክራሲና የነጻነት እጦት የገፋቸው እውነተኛ ስደተኞች ባግባቡ መልስ ያለማግኘታቸው ጉዳይ ነው። “እነዚህ እውነተኛ ስደተኞች እኔን ጨምሮ አገር የለንም” ሲሉ አገር አልባ የመሆንን ስሜት ይገልጻሉ። ወ/ት የሺሃረግ የኖርዌይ ሚዲያዎችና በስለላ ተግባር የተሰማሩ “ስደተኞች” እንዳሉ በይፋ ቢናገሩም መንግሥት መልስ አለመስጠቱ ቢያሳዝናቸውም ማህበራቸው ትግሉን ይበልጥ እንዲገፋበት እንዳደረገው ነው የሚናገሩት።

የዲሞክራሲ ለውጥ ድጋፍ ሰጪ በኖርዌይ ተወካይ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ያረጋገጡትን በመጥቀስ ወ/ት የሺሃረግ የትግሉን መደጋገፍ አመላክተዋል። ድጋፍ ሰጪው መረጃ የማሰባሰብ ስራውን ማጠናቀቁን ማረጋገጡ፣ የስደት ከለላ ካገኙ በኋላ በስለላ የተሰማሩትን ክፍሎች አደባባይ ለማውጣት የሚደረገውን ትግል እንደሚያፋጥነው ከምስጋና ጋር እምነታቸውን ገልጸዋል።

3ማህበራቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባሉበት ሁሉ ወኪሎችን በመሰየም የግንኙነት መረብ መፍጠሩን ያመለከቱት ጸሐፊዋ፣ የግንኙነት ሰንሰለቱ መረጃዎችን በቅርብ ለመሰብሰብ እንደሚረዳ አስታውቀዋል። ላለፉት ሰባት ዓመታት የስደት ማመልከቻቸው አዎንታዊ መልስ እንዳላስገኘላቸው የጠቆሙት ወ/ት የሺሃረግ፣ “እንደ እኔ አይነቶች ብዙ ነን። ከኔም የሚብሱ አሉ። ከሚደርስብን የማህበራዊ ችግር በተደራቢ ካገራችን እንድንባረር ያደረጉን ሰዎች እዚህም እረፍት ሊነሱን አይገባም። አገር አልባ መሆን ያሳዝናል። እዚህ ኖርዌይ የተወለዳችሁ ወገኖችም ብትሆኑ ስደተኞች ናችሁና በመረጃ ማሰባሰቡ ስራ ተባበሩን” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ቀደም ሲል ለተባበሩትም ምስጋና አቅርበዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሙያዊ ምክርም ሆነ አግባብነት ያለው አስተዋጽዖ ለማበርከት ለሚፈልጉ ሁሉ ማህበራቸው በሩ ክፍት እንደሆነም ተናግረዋል።

በኖርዌይ የኢትዮጵያዊ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ፋሲል አለባቸው በበኩላቸው በተጠቀሰው ቀን ለተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። “ሆን ተብሎ የስደት መረጃና ማስረጃ ተመቻችቶላቸው የሚመጡት ሰላዮች የስደት ሂደቱን በማበላሸት እውነተኛ ስደተኞች የከለላ ምላሽ እንዳይሰጣቸው ያደርጋሉ። በዚህ ዜጎች ተጎድተዋል” ሲሉ ለጎልጉል ገልጸዋል።

“እነዚሁ የተመቻቸላቸው ስደተኞች መልስ ካገኙ በኋላ ሆን ብለው ወደ አገራችን መመለስ እንፈልጋለን በማለት የስደተኛ ጉዳይ ለሚያስተናግዱት ክፍሎች የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የሌሎች ስደተኞችን ጉዳይ በማበላሸት ስራ ይሳተፋሉ” የሚሉት አቶ ፋሲል አንዳንዴም የተሳሳተ መረጃና የተሳሳተ ምክንያት እንዳቀረቡ በመግለጽ እውነተኛ ስደተኞች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ የሚችል ተግባር እንደሚፈጽሙ አመልክተዋል።2

ከዚህ በተለየ መልኩ ገንዘብ በመላክ /በሃዋላ/ ስራ የተሰማሩ ሰዎች እንዳሏቸው የሚገልጹት አቶ ፋሲል፣ “ወያኔዎቹ ገንዘብ በመላክ ስራ ባሰማሯቸው ሰዎች አማካይነት አገር ቤት ያሉትን ቤተሰቦች በመለየት እንደሚያስፈራሩ ይታወቃል” ሲሉ የትግሉን አስፈላጊነትና ከስደተኞች ማህበር ጥሪ ጎን ስለመቆም ይናገራሉ።

ኮሚኒቲው ለወገኖቹ ጉዳይ ዘወትር እንደሚያደርገው ሁሉ አሁን ለሚደረገው ትግል ከድጋፍ መስጠት ባለፈ አብሮ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ ያሳሰቡት አቶ ፋሲል፣ ማንም ቢሆን ለህግ ሊገዛ እንደሚገባ በሚያስገድድ ስራ ላይ መሰማራት እንደሚኖርበት አመላክተዋል። በማያያዝም አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ወደ ማህበረሰቡ፣ ወደ አክቲቪስቶችና አቅም ያላቸውን ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበትና ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ የመትከል ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ ስራው እንደሚሰራ አስረድተዋል።

ወ/ት የሺሃረግ የመረጃ ማሰባሰቡ ስራ ሲጠናቀቅ ጉዳዩን ከኖርዌይ የፍትህ ተሟጋች አካላት ጋር በመሆን አስቀድሞ ለፍትህ ሚኒስትር፣ በመቀጠልም በየደረጃው ለሚመለከታቸው ክፍሎችና ለዓለም አቀፍ ተቋማት የማሳወቁ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለጎልጉል ተናግረዋል።

4በሰላማዊ ሰልፉ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ሃሳቡን የደገፉ ተገኝተዋል። አቶ መለስ ለመጨረሻ ጊዜ ኖርዌይ በመጡ ጊዜ የተፈጠረውን ጉዳይ በማስታወስ የስደተኞች ማህበር ቢዘገይም አሁን የደረሰበት ደረጃ ሊበረታታ እንደሚገባ የጠቆሙ አሉ። ስቴንሻዬር የስደተኞች ካምፕ “ስደተኛ” ተብሎ ተመዝግቦ የነበረ እብድ ወጣት አብረውት ካምፕ የሚኖሩ አገር ቤት ያለውን ስርዓት በመቃወም ለህዝብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ሲሰሩ አብሯቸው ይሳተፍ ነበር። ሲሰለፉና ህወሃትን ሲያወግዙ፣ ኢህአዴግን ሲቃወሙ፣ አብሮ በመሆን እየተቃወመ ቪዲዮ ይቀርጽ ነበር። በመጨረሻ በድንገት ተነስቶ አገር ቤት ተመለሰ።

የልጁ በድንገት መሰወር ያሳባቸው የካምፑ ነዋሪዎች ሲያጣሩ በስም የጠቀሱት ሰው አዲስ አበባ መመለሱ ተረጋገጠ። ከወራት በኋላ አቶ መለስ ኦስሎ ሲመጡ ይኸው ሰው ኦስሎ ተገኘ። በማለት የጠቆሙት ክፍሎች ይህንን ጉዳይ ፖሊስ እንደሚያወቀው፣ ማመልከቻ እንደገባለት አብረውት የነበሩት አሁን ድረስ በስጋት ላይ እንዳሉ ይገልጻሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. zeraer says

    April 16, 2014 03:16 pm at 3:16 pm

    ***ኩክ ማውጫ***
    …የእኛ ሀገረ ገዢ!…
    የየዋህ ህዝብ እንባ ሀዘን እንጉርጉሮ
    የዘወትር ዋይታ ብሶትና እሮሮ
    እራፊ ,ማይሰማ ባላንቴና ጀሮ
    ባይሆንማ ኖሮ ሳትጠልቅ ጀምበር
    ረሃብ እና ችጋር አፈር በልተው ነበር
    …የእኛ ሀገር ገዢዎች…
    የስልጣንን እርካብ ወጥተው የማይወርዱ
    የህዝብ አቤቱታ መስማት የማይወዱ
    …ለምድን ነው ቢባል?
    እኔን እንደገባኝ ሁሉ አፈቀላጤ
    ጀሮ ታምቡራቸው!
    ሳይቋጥር አይቀርም ትንሽ ኩክ ቢጤ
    ወሬ አፈናፋኙ ጀሮ ጠቢው ሁላ
    በጀሮ ታምቡሩ ኩክ ነው የሞላ
    …ይህም ስለሆነ!…
    የፍትህ ያለህ፣የነፃነት ያለህ
    የምግብ ያለህ፣ የውሃ ያለህ
    የመብራት ያለህ፣የመሪ ያለህ
    ያገር ያለህ ብለን ሰልፍ ከምንወጣ
    እኛው ተመካክረን ሌላ መፍትሄ እናምጣ

    …እንደኔ እንደኔ ግን!…
    ኑ! ስሙኝ አንሰማም መጋፈጡን ትተን
    በአንድነት ተባብረን አውጫጭኝ አውጥተን
    በካዝናቸው ላይ የጎደለ ሞልተን
    ለመሪዎቻችን እናድርግ እገዛ
    ጀሮ መቧጠጫ ኩክ ማውጫ እንግዛ፡፡

    ዘቢ
    እስኪ ለግጥሙ እናንተ ከዚህ የተሻለ ርእስ ስጡት?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule