• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቅዱስ ጦርነት

January 15, 2014 03:19 am by Editor 4 Comments

ሰሞኑን ከያኔ (አርቲስት) ቴዎድሮስ ካሳሁን ለዕንቁ መጽሔት የሰጠውን ቃለ ምልልስ ተንተርሶ በተለይ በማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛ ልክና ገደብ ያለፈ መራኮት ተፈጥሮ ነበር ፡፡ አጋጣሚው የሀገር ጠላቶች ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ለማድረግ ያላቸውን ዝግጅትና አቅም ያሳየ ሆኗል ፡፡ ክርስቶስ አደቡን ማስተዋሉን ይስጥልን ከማለት ውጪ ዓላማ ብለው ለያዙት የጥፋት ልጆች ለጊዜው ምንም የምለው ነገር የለኝም ፡፡ በእነዚህ የጥፋት መልእክተኞች እየተወናበዱ ላሉ የዋሀን ዜጎች ግን በአጭሩ የምለው ነገር አለኝ ፡፡ እባካቹህን አስተውሉ ይሄንን የተሳሳተ አስተሳሰብ የፈጠረው መርዘኛው የወያኔ የዘር ፖለቲካ እንደሆነ ልብ በሉ ፡፡ በእርግጥ እውነት ነው ዐፄ ምኒልክ 2ኛ ከዐፄ ቴዎድሮስ የተረከቡትን አደራ ኢትዮጵያን እንደገና የመሰብሰብና አንድ የማድረግ ተልእኮ ለመፈጸም ሲሉ እዚህም እዛም የገደሏቸው የፈጇቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ አሉም፡፡

በእርግጠኝነት ልንናገር የምንችለው ነገር ቢኖር ዐፄ ምኒልክ የኦሮሞም ይሁን የሌላ ተወላጆችን የዚያ ብሔረሰብ አባል ስለሆኑ ብቻ አላጠፉም አልፈጁም አልገደሉም ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያን ክፍለ አካላት ለመሰብሰብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት  መንገዳቸው ላይ የቆሙ ወይም እንቅፋት የሆኑ የኢትዮጵያን መሰባሰብ አንድ መሆንና እንደገና ተጠናክሮ መውጣት የማይፈልጉ የባዕዳንና የጠላት ቅጥረኞች የሆኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ግን ፈጽሞ ለመመከርና ለመማር ፈቃደኞች ሆነው ባለመገኘታቸው ጨርሰዋል ፈጅተዋል ፡፡ ይሄንን ከማድረግ ውጭም ሌላ አማራጭ አልነበረምና ትክክል ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህልውና በሽታ የሆነባቸው ደናቁርት ጠባቦችና የኢትዮጵያ ጠላቶች (ወያኔ) ለጥፋት ተልእኳቸው ይመቻቸው ዘንድ የፈጠራ ታሪኮችን በመፈብረክና አንድና ሁለት ብሔረሰቦችን ነጥለው በመጥቀስ እነዚሁ ብሔረሰቦች ብቻ በዚህ ዘመቻ እንደተጨፈጨፉ አድርገው በማናፈስ የሕዝቡንና የሀገሪቱን አንድነት ለማፈራረስ ከፍተኛ ጥረት ላይ ናቸው ፡፡ ብዙ የዋሀንንም ማጥመድና ማታለል ችለዋል ፡፡ ይሄንን የወያኔን መርዘኛ ስብከት አምነው ለተቀበሉት ወገኖች ላነሣው የምፈልገው ጥያቄ ዐፄ ምኒልክ በዚህ ዘመቻቸው የፈጇቸው እንቢተኛ የኦሮሞና የወላይታ ተወላጆችን ብቻ ነው ወይ ? በዚሁ ዓላማ ምክንያት (ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ወይም አሐዳዊ መንግሥት ሥርዓት የመመሥረት) በየ መሳፍንቱ የተደለሉና የተከፋፈሉ እንቢተኛ የአማራ ተወላጆችስ አላለቁምን ? ዐፄ ምኒልክ ጎጃም ንጉሥ ተክለሃይማኖትን ድል ለመምታትና ጎጃምን የዚሁ አሐዳዊ መንግሥት ወይም የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ በላኩት ጦር የአማራ ተወላጆች አላለቁምን ? የኋላ ኋላ ግን ዐፄ ምኒልክ የማረኳቸውን ንጉሥ ተክለሃይማኖትም ሆነ ንጉሥ ጦናን በዚህ ዓላማ ማመናቸውን ዓላማውን መቀበላቸው ሲያረጋግጡ  ግዛቶቻቸውን መልሰውላቸው እስከ ህልፈታቸው ድረስ በጋራ ለአንዲት ሀገር በየፊናቸው ይሠሩ እንደነበር ይታወቃል ፡፡ አስቀድሞም ዐፄ ቴዎድሮስ ይሄንን ዓላማ ለማስፈጸም በመሳፍንት ተከፋፍላ የነበረችውንና ህልውናዋ አደጋ ላይ ወድቆ የነበረችውን ሀገር አንድ ለማድረግ ባደረጉት ዘመቻ ከማንም በላይ ያለቀው የተፈጀው በየመሳፍንቱ ተይዞ የየመሳፍንቱን ጥቅም ለማስከበር ተገዶ እርስ በእርሱ ይዋጋ የነበረው የአማራ ሕዝብ አይደለምን?

እናም መሆኑን ባንወደውም አማራጭ ያልነበረው እርምጃ በመሆኑ ድርጊቱን ፈጽሞ ልንኮንን ልናወግዝ አንችልም አይገባምም የተለየ ዓላማ ካልያዝን በስተቀር ፡፡ አይ የሚል ወገን ቢኖር ኢትዮጵያን አንድ የማድረጊያው ሌላኛውንና ነገሥታቱ ያልተጠቀሙበትን አማራጭ ማቅረብ ይኖርበታል ቢያንስ ለወደፊቱ ይጠቅመናልና፡፡ እነሱ እንደሚመኙት ይህች ሀገር የተበጣጠሰችና ያልተሰበሰበች እንደሆነች ወደ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጥታ ቢሆን ኖሮ ምን ዓይነት የከፋ ውጥንቅጥ ውስጥ ልንገባ እንደምንችል እንኳን መገመት የሚችሉ አይደሉም፡፡ ተሰባስበን በአንድ ቆመን ያለቻልነውን ሁለንተናዊ ፈተና እንዴት ተበጣጥሰን እንችለዋለን የተሻለም ነው ብለው እንደሚያስቡ አይገባኝም፡፡ የትኛውም የኢትዮጵያ አካል አሁን ያለችው ኢትዮጵያ አካል ሳይሆን የቀረ ቢሆን ኖሮ ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ ሀገር ሆኖ እንደሀገር የመቀጠል የመኖር አቅምና ዕድል ማግኘት የሚችል የለምና፡፡ ተለነገሩ እነዚህ ሰዎች ይሄንን ያህል ርቀው ማሰብ የሚችሉ ስላልሆኑ ያለው አደጋ ጨርሶ አይታያቸውም በመሆኑም ነው ፈጽሞ ኃላፊነት የጎደለውን ተግባር በድፍረት እየፈጸሙ የምናያቸው፡፡ እናም የነበረውንና ሳንጠቀምበት የቀረነውን አማራጭ ሳናቀርብ እንዲሁ በደፈናው መወንጀል መኮነን ማውገዝ ከሆነ ይህ ከባድ ድንቁርናና ከውስጥ ከተደበቀ የሀገር ጠላትነት ከአባቶቻቸው በደም የወረሱት የባንዳነት ስሜት የሚመነጭ ነውና አድማጭ ሆይ ልብ በል መስማት ማዳመጥ ያለብህን ለይተህ ስማ ፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ይሄንን እያራገቡ ያሉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንነት ብታጤነው በእርግጠኝነት ለዚህች ሀገርና ለሕዝቧ ጠላቶች የሆኑ ሆነው ታገኛቸዋለህ ፡፡ ወደፊትም ቢሆን በተመሳሳይ አቋምና እርምጃ መንቀሳቀስ እስካልቻልን ጊዜ ድረስ የዚህችን ሀገርና ሕዝብ አንድነትና ህልውና ማስጠበቅ ፈጽሞ አይቻለንም ፡፡ እዚህ ላይ ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር የአሥተዳደር በደልንና ኢትዮጵያዊነትን ለይታቹህ እንድታዩ ነው ፡፡ ችግሩ እየተፈጠረ ያለው እነኝህን ነገሮች እየቀላቀሉ ከመመልከት ነው ፡፡ የሰው ፍጹም ይኖራል ተብሎ ባይገመትም ያለ ሀገራዊ ወይም ብሔራዊ ምክንያት ማለትም ለሀገርና ለሕዝቧ ሲባል ከሚወሰድ ምክንያታዊ እርምጃ ውጪ ለግል ጥቅሙ ብቻ ሲሉ ግፍና በደል የፈጸሙ ግለሸቦች ካሉ ሊጠሉ ሊወገዙ ይገባል ፡፡ ነገር ግን ሊጠሉ ሊወገዙ የሚገባቸው የአሥተዳደር በደሉን ያደረሱት ግለሰቦች እንጅ ሀገርና የወጡበት ብሔረሰብ አይደለም ሊሆንም አይችልም፡፡ ነው ካልን ግን ከዚህ ድንቁርናችን የተነሣ ገና ካሳለፍነውም የሚከባብዱ ፈተናዎችን እየጋበዝን ነውና በእጅጉ ልንጠነቀቅ ይገባናል ፡፡

ይህ አቋምም ማንንና እንዴትም ሊጠቅም እንደሚችል ለሕሊናችን እንመልስ ፡፡ እናም በእነዚህ እኩያንና አጋንንት እነሱ ብቻ ወደሚያውቁት እኛ ወደማናውቀው መታረጃ ከመነዳታችን በፊት ይህ ድንቁርና ለሀገር፣ ለሕዝብ፣ ለራስም ለማንም እንደማይጠቅም ተገንዝበን የሰው ደም ጥማት ያንቃቃቸውን አጋንንት እንቢ በማለትና በማሳፈር ህልውናችንን የማረጋገጥና አስተማማኝ የማድረግ ግዴታ በሁሉም ዜጋ ጫንቃ ላይ ነው ፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Comments

  1. anonymos says

    January 18, 2014 08:23 am at 8:23 am

    ante erash atrebam sebawi futrin Gedlo tikikil new tilaleh…..

    Reply
  2. anonymos says

    January 18, 2014 11:15 pm at 11:15 pm

    Mechayeme ke ande intellectual endee aletebqeme. Ante erase narrow minded eyhoneke sewe neh. Ye ande group yeblayenete yemtamene enjee sele Ethiopia menme yemtasebe endlahone kenegegere ena ke stufe terdechalewe. Ante yemetewflegew Ethiopia erase yasebkewe ena yeflekewe Ethiopia newe kalhone lela endamteflege. Manme sewe yetelaye asab meyaze mebetme sayhone teqameeme newe. Gene hasabu leke adeleme teblo yane sewe mechefchefe ena chefecfawene tekekele malete ante erase menem yalteshashaleke ambagenene mehonene asqemetale. Ethiopia menore metechelewe yehulu berhasebe mebete seekeber, yehulu haymnote seekbere, andu belalalwe laye yeblaye mehone seeqome, ye Ethiopia hizb yeflegewene mree memerte seechele, ye sebahwi mebete teste seeqome, manme sewe yeflegewen astesasebe meyz mechale endalebete hulum seweme mesemamate seechel…wezete. America le Ethiopia teru mesale methone ager nate, yehenesuene constitution beeqeda teru newe elalalewe. Bemechersha shame on you elehalewe endete endzee bele tenagerele, megedelachewe tekekekele nachewe. Leke aydelhum wenjela nachewe.

    Reply
  3. tizibt says

    January 22, 2014 02:09 am at 2:09 am

    Surprising to see this stupid racist script which is entirely the mind set of minilik’s time than a man in this modern era. Please wake up my friend you are still as ignorant as your forefathers. How could you intensify that Minilik’s mass killing was the best option at the time? You are the most ignorant who simply love to shout. It might have led to the formation of better nation than the ruined today’s Ethiopia if minilik wouldn’t have conquered most parts of Oromia and others. Its shame on you to appreciate the formation of this disadvantaged country of the world because of your fore parents. You better go school and take some history courses before you bluff and mix up the reality with your lie. You are as rude as illiterate teddy who delightedly calls a war ‘holly’ . You animals believe me better change yourself and behalf as humans. Asedabi yemayim mecheresha!

    Reply
  4. kuaraw teshale says

    April 4, 2014 05:05 pm at 5:05 pm

    nasula:
    Any comment on a political discourse of a period preceding 120 years has to be viewed in time context. Ethiopia of that time was so divided, backward, war torned (of zemene mesafint). It was internally weakened and exposed to the dangers of colonialism. Europians were coming to africa to divide it up among themselves like a bread in a basket. Had it been not for the visionary Menelik who could see the fate of his country, there was none optional other than bringing together territories of his fore fathers including others around. His approach in reforming/ reviving the nation was by means of diplomacy and war. If you think rational he was an enlightened person, astute, diplomatic and a determined patriot. He was highlly respected not by his fellow men but also enemies for his deeds, kindness and generosity. He was more human, respectful and kind towards his enemies than any of the leaders after him including the pseudo democrat,EPRDF. Almost all who hate menelik and condemn him for his deed before 120 years, in a time when no word of democracy, human rights and for a man who believed in and accepted by people that no one was above him other than god are confined in a bottle neck of narrowness and ethnocentrism, irrational and judge history against its background. Menelik was a man who was gathering his people in a time concomitant to the unification of Italy and Germany. Unification in Italy and Germany was completed in a similar fashion i.e through diplomacy and war. We are admired of being the only independent nation in africa, we are proud of our culture, language which in fact served as a framework of the federal structure but still condemn the man who spearheaded this glory. If war was a must to keep the nation unified, death was a natural order. If we loved freedom, unity was the only option. Unity was not to come by beating the drum. The natural desire for power among local kings and tribal leaders was not all to be surrendered. Diplomacy would be followed by arms which deaths were common from both sides. Therefore, it is logical, rational and human to justify that Menelik was the wright man at the wright time with a wright action. People who condemn menelik for killing of their forefathers in the dark age before 120 years in a battle are those who kill people at home and in streets today in the age of democracy. Menelik did not kill people on racial basis but for the sake of freedom, nationhood and civilization. If menelik has to be condemned, it should be for his hard work in keeping his people independent who chant and dance feel proud of their language culture.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule