• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሞት ጉዞን አናቆምም?

June 28, 2016 07:04 pm by Editor 3 Comments

መቼም በዚህ ዘመን ጧት ከእንቅልፉ ሲነሳ መልካም ዜና የሚሰማ ሰው የታደለ ነው። ካለ ማለቴ ነው። አዎ መልካም ዜና ደስ ይላል። በተለይ በማለዳ የሚሰማ ደስ የሚል ወሬ መንፈስን ያነቃል፤ ለእለቱም የደስታ ስንቅ ይሆናል። ግን ያ ለታደለ ነው። ዛሬ ብዙዎቻችን ቀናችንን የምጀምረው በጦርነት ዜና፣ በስደት ወሬ፣ በድርቅና ረሃብ መርዶ ነው። አይ አለመታደል!!

በተለይ እኛ የኢትዮጵያ ልጆችማ መልካም የማለዳ ብስራት መስማት እንደናፈቀን እነሆ 50 አመት ሊሞላን ነው። ክፉውን ዘመን የሚቀይር ለውጥ መጣ ተብሎ፥

ጨለማው ተገፎ ብርሃን መጣላችሁ፤

ለስራ እንታጠቅ እንዴት አደራችሁ፤

ሲዘፈን ለኢትዮጵያና ህዝቧ ጎኽ ቀደደ፤ አዲስ የተስፋ ህይወት ተጀመረ ብለን ዜናውን በቅጡ አጣጥመን ሳንጨርሰው ደስታን ያበሰረን ያው ጣቢያ፥

የፍየል ወጠጤ ትከሻው ያበጠ ልቡ ያበጠበት፣

እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት፤

በሚል ቅረርቶ እህት ወንድሞቻችን መረሸናቸውን በኩራት ያረዳን ጀመር። አዎ ጨለማው ተገፎ ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ተተካ፤ ምናልባትም ከፊተኛው የባሰ ድቅድቅ ጨለማ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ስለዚያች ውብ ሀገር የምንሰማው የለት ዜና ሁሉ መርዶ፣ ኑሯችን ሁሉ እየየ ሆነ። አይ አለመታደል!

ማክሰኞ (ሰኔ 21 ቀን ይመስለኛል) (እንደአጋጣሚ ይህ ቀን ደግሞ ደርግ የተፀነሰበት እለት ነው መሰለኝ) ከእንቅልፌ ስነቃ እንደወትሮዬ የማለዳ ዜና ለመስማት አንዱን ጣቢያ ከፈትኩ፤ ቢቢሲ ነበር። እንደልምዴ መጀመሪያ የምፈልገው ስለሀገሬ ኢትዮጵያ ወሬ ካለ መፈለግ ነው። አዎ፣ ስለ ኢትዮጵያ ምንም ይሁን ምን መስማት አለብኝ። ስለ እርስዋ ክፉም ይሁን ደግ ሳልሰማ መዋል አልችልም። ስለሀገራቸው ምንም መስማት እንደማይፈልጉ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያንን ስሰማ ይገርመኛል። አንዳንድ ጊዜም አዝንላቸዋለሁ። አዎ፣ ያሳዝናሉ። ምክንያቱም ሀገሩን የጠላ ራሱን የጠላ ነው። ሀገርም የለውም። ራሱን የጠላ ደግሞ አደጋ ውስጥ ነው። ባልደከሙበት የስልጣኔ ምቾት ህሊናን ሸፍኖ የማንነት መነሻና ምንጭ የሆነችውን ውብ ሀገር አይንሽን አያሳየኝ የሚል ክፉ በሽታ ከተፀናወተው ምስኪን በላይ ለማን ይታዘናል። ብቻ ይህን ለሌላ ቀን ትቼ ወደያዝኩት ጭብጥ ልመለስ።

እናም በዚህ ማለዳ የዜና ሃሰሳዬ ስለእናት ኢትዮጵያ ወሬ አላጣሁም። ክፋቱ ግን ወሬው መርዶ ነበር። “የ19 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስከሬን ወደሀገራቸው ተላከ” ይላል። መቼም አዘንኩ ቀላል ቃል ነው አነባሁ፤ ግን አልወጣልኝም። ለቅሶ ስለምወዳት ሀገር የሚሰማኝን መሪር ሀዘን አውጥቶልኝ አያውቅም። እንዲያማ ቢሆን እነዚያ ያገሬ ጀግኖች በሊቢያ በረሃ ለማተባቸው ሲታረዱ፣ እንጀራ ፈላጊ እህቶቼ በሳውዲ ሲዋረዱ፣ ተንከራታች ያገሬ ልጆች ለኩርማን እንጀራ በባህር አዘቅጥ ሲወርዱ ስንት ጊዜ አልቅሼ አነበር? ሀዘኔ ግን ከሆዴ ወጥቶ አያውቅም። ወይ ሀገሬ! ስለአንቺ የማነባው እስከመቼ ይሆን?

እነዚህ እንደሌሎች አያሌ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባገራቸው ያልቀናቸው ምስኪን ወገኖቼ ካሰቡት ሳይደርሱ ሞት ቀደማቸው። ህያው ሆነው ሊኖሩባት ባልቻሉባት ሀገራቸው ሊቀበሩባት ተመለሱ። እሷም የመከራ እናት ሆና ከሞት ባታድናቸውም አፈሯን ግን አልነፈገቻቸውም። ግን፣ ግን አንቺ ሀገር፣ ለልጆችሽ መቀበሪያ ብቻ ሳይሆን መኖሪያ የምትሆኝውስ መቼ ነው?

አዎ ይህን ጥያቄ የምጠይቀው ኢትዮጵያን አይደለም። ልጆቿን ነው። ሀገርማ በማር በወተት ከማሳደግና ለራስ ብቻ ሳይሆን ላለም የሚተርፍ ለምለም እርስት ከማውረስ በላይ ምን አድርጊ ብዬ ልጠይቃት? እናም የምጠይቀው ያገሬን ሰው ነው። ጎበዝ፣ የሞትን ጉዞ የምናቆመው መቼ ነው? ህዝባችን ለሞት ይጓዛል፤ እኛም ለሞት እንጓዛለን። መንግስት የያዘው የሞት መንገድ ነው። የተቃዋሚም ጉዞ ቢሆን የህይወት ጎዳና አይመስልም። ሁላችንም የሞት መንገደኞች ሆነናል። የሞት መንገደኞች ደግሞ መጨረሻቸው ያው የቡድን ሞት ነው። እንደ ቡድን መሞት እንደ ሀገር መሞት ነው። እንደ ሀገር መሞት ደግሞ የማንም ግብ ሊሆን አይገባም።

እናም ሰሚ ካለ ይህን እላለሁ። የሀገራችንንና የተንከራታቹን ህዝብ መከራና ሞት ማቆም የምንችለው እኛው ነን። እንችላለንም። አቅሙም እውቀቱም አለን። የጎደለን ፈቃደኝነቱ ብቻ ነው። ፈቃደኝነቱ ደግሞ ቆም ብሎ በማሰብ ይገኛል። እስከዛሬ የሄድንበትን መንገድ ዞረን እንየው። ርቀቱን ብቻ ሳይሆን ውጤቱን እንመዝነው። ትርፍና ኪሳራችንን እናስላው። እንደ ቡድን አስበን እንደ ሀገር መክሰራችንን እናጢን። በጉልበት ሳይሆን በስልጣኔ እናስብ። በየትኛውም አለም እንኑር ባስቸኳይ ካልነቃንና ቀናውን መንገድ ካልያዝን እየጠፋን መሆናችንን እናስተውል። የየግል ሂሳባችንን ትተን ያጣነውን ክብር መልሰን ባለም ኮርተን የምንኖርባትን ሀገር እንደገና በፍቅር ለመገንባት የጀግና ውሳኔ እንወስን። የጠፋብንን መንገድ እናግኘው፤ ያም አንድ ብቻ ነው፤ እሱም ሰላም ነው።

በያለንበት ስለ ሰላም የምናስብበት ልቦና ይስጠን! አሜን!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. tesfai habte says

    June 29, 2016 10:06 am at 10:06 am

    ሁሩይ ደምሴ እሺ ሰላም ይፈለጋል ኣልክ። ሰላምን ከየት ይምጣ? ሰላም በምን ይገኛል?—-ወያኔ እስካለ ሰላም ማግኘት ማለት ፍጹም የማይታሰብ ነው። ወያኔ የሚፈልገው ከሰላም ይልቅ ሽበራ ነው። ሰው መግደል ነው። ከኣመሪካን ዶላር ላማግኘት ሰውን ወደስደት ያደርጋል። ኣፍሪካን በርሃብ፡ ብውግያ፡ በስደት፡ ሰላምን ለማደፍረስ፡ ዋና ተዋናይ ዋያኔ ነው። ለወያኔ ሰላሙ ዶላር ብቻ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ልማት፡ ፍቅር፡ ሰላም፡ አንድነት ማሰብ ከባድ ነው። በሱማል፡ ኤርትራ፡ ደቡብ ሱዳን፡ ኬንያ፡ ሽብር ፈጥሮ ዶላር ማግኘት እንጂ ስለየኢትዮጵያ ሰላም ለወያኔዎች ራስ ምታት ነው። ዛሬ መቀሌ እና ኣዲስ አበበ በቡድን የተደራጁ ማፍያዎች፡ ሰዎች ወደ ሌላ አገር መሸጋገር፡ ዶላር ለማግኘት ወድያና ወዲህ በሊዝሙ እና ላድኩሩዝር መኪናዎች የሚረጡ ከፍተኛ ገዳዮች የተከማቹ ሰፈር ሁነዋል። የነዚህን ነፍሰ-ገዳዮች ምስልና ፎቶ-ግራፍን ኣለን። ከተፈለገ መስጠት ንችላለን። የተሰወረ አይደለም። ስለዚ ሁሩይ እዚህ ሁሉ ካለ ሰላምን ከየጥ ይመጣ ብለህ ታስባለህ?——እኔ ልነግርህ!——በጥይት ለሚገድልህ በእጅ ሰላም ማለት ኣይቻልም!—–በጥይት መመለስ ብቻ ነው ሰላሙ ማግኘት የምቻለው። ኣንዳንዴ ግዜ ሰላም ብዲሞክራሲ ለመምጣት ከተሳነ፡ ብረትን (ውግያን) ሰላምን ያመጣል። ለወያኔ መፍራት ራሱ ለፈሪው ወያኔ ሰላም ይሰጠዋል። ውግያ ሰላምና እና አርበኛ ሰውን ይፈጥራል። ወያኔ ይህ ሁሉ የሚያደርገው ድርጊት ከኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚፈራ ነው። አመሪካኖች እደወያኔ የመሰለ ከህዝቡ እና ኣከባቢው የሚፈራ፡ ንኡሳን ብሄር ለትልቁ ብሄረሰቦች ለመግዛት፡ ብሃገር ሰላም እዳይኖር፡ መተራመስ፡ እያንዳንዱ ሰው መረዳዳት የማይችል፡ በሪሞይ የሚዘውር ቡችላ ነገርን ይወዳሉ፡ ይፈልጋሉ፡ ይተግብራሉ። ወጣቱ ትውልድ ግን ይህ ኣምኖ፡ አውቃ፡ መቃውም ብቻ ሳይሆን፡ ህወትን ለመስዋእትን ቅድመ-ግንባርን በመቆም ሰላም መምጣት ኣለበት።

    Reply
  2. koster says

    July 1, 2016 10:12 am at 10:12 am

    no fascist in world history transferred power freely and willingly. TPLF fascists should be dismantelled by all means possible like the Monarchy and the DERG. 23 years is more than enough (yemirotulet wusha yeferut yimeselewal) the fascists should learn that their arrogance is not right. They are humans (although we sometimes doubt due to their barbarism) and should understand that they should also be defeated like the Monarchy and the DERG.

    Reply
  3. gud says

    July 5, 2016 07:09 pm at 7:09 pm

    Lol lol

    Z writer in Amharic is Tigrigna speaking eretrian

    I saw a lot of words that sound tigrina than Amharik

    Bwigiya 1
    Hunewal 2
    Letter A ( as in Alebet !)

    Shabia your days are numbered ,
    You shall be buried by the mighty woyane soon .

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule