ከዝግጅት ክፍሉ – ይህንን ጽሁፍ የላኩልን ጋዜጠኛ መስፍን አብርሃ በግልጽ እንደጠቆሙት ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መምህር ግርማም ሆኑ የርሳቸው ደጋፊም ይሁን ተቃዋሚ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ በመስጠት በጨዋነት የሚልኩልን አስተያየት የምናስተናግድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን::
በኢትዮጵያ አገራችንና ኢትዮጵያዊ ወይም የአበሻ ዘር ባለበት በዓለማችን ክፍል በአሁኑ ወቅት ስለ መምህር ግርማ ወንድሙ የማያውቅ ቢያንስ ያልሰማ የለም።
መምህር ግርማ በመጀመሪያ መስቀል አደባባይ በሚገኘው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ቀጥሎም በኤረር ሥላሴ ቤተክርስቲያን የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመምህር ግርማ አገልግሎት ላይ በተለይም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሃይማኖት ተከታዮች በሆንን ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት እየተፈጠረ አንዳንድ አካባቢም ከስያሜያቸው በመነሳት አጥማቂ ነው፣ ፈዋሽ ነው፣ ጠንቋይ ነው፣ አስማተኛ ነው እየተባለ መከፋፈልን ፈጥሮ እስከ መደባደብ የተደረሰበት ሁኔታም አለ። የፖለቲካውን
ቃል እንደወረደ በመጠቀምም “Rent seeker” ኪራይ ሰብሳቢ ናቸው ብለው የሚናገሩም አሉ።
መምህር ግርማ እንዲህ ናቸው ብሎ የዚህ ጽሑፍ ጸሓፊ መጠቀሙን አልመረጠም። ምክንያቱም ይህ ጸሐፊ ጸሐፊ እንጂ የሃይማኖት እውቀት ኖሮት እሳቸው እንዲህ ናቸው ብሎ አቋም የመውሰድ ወይም የመፈረጅ ሥልጣን የለውምና።
ነገር ግን ሙያዊ ግዴታም ስላለበት ጸሃፊው ይህንን ጉዳይ በአደባባይ አውጥቶ ሊቃውንትም ይሁኑ እናውቃለን የሚሉ ወገኖች በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩበት እነሆ የክርክር/የውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ ብዕሩን ወደ ታች ወድሮ መቀለሙን ተያይዞታል።
በእርግጥ እንደ ባለሙያ የሁለቱንም ወገኖች የመምህር ግርማ ደጋፊዎችም ይሁኑ ተቃዋሚዎችን መድረክ ፈጥሮ ለማሟገት ወይም ሃሳባቸውን ለመስማት አቅምና የቦታ መራራቅ ቢያዳግተውም ሃሳቡን ወደ ነፃ የውይይት መድረክ ማምጣቱን ጸሐፊው መርጧል።
ምናልባት አንዳንድ የዋህ ሰዎች ጉዳዩ የሃይማኖት ስለሆነ በሃይማኖት መድረኮች ቢታይ ጥሩ ነበር ብለው ያስቡ ይሆናል። ነገር ግን እነሱ እንደሚያስቡት ቀላል አይደለም። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጉ በቅርብ የሚያውቋቸውን ካህናት/መነኮሳት ስለ መምህሩ ቢጠይቋቸው እንዲህ ነው ብለው በድፍረት አይነግሯቸውምና።
የሃይማኖት መካነ ድሮችም ልክ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ልሳኖች በባህሪያቸው የሚደግፉትን አቋም ብቻ የሚያራምዱላቸውን ጸሐፍትና ጽሑፍ ያስተናግዳሉ እንጂ ተቃውሞ ይዘው ወይም በገለልተኝነት የሚመጡ ሃሳቦችን ለማስተናገድ ዝግጁዎች አይደሉም። ድፍረቱም ይጎላቸዋል። ስለዚህ በመላው ዓለም ባሉ ኢትዮጵያውያንና አበሾች ዘንድ በመጎብኘትና በአሳታፊነት ግንባር ቀደም በሆነው ኢትዮ-ሚዲያ ዶት ኮም እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ተደማጭነትንና ተነባቢነትን ባገኘው የጎልጉል ድረ ገፅ ጋዜጣ ይህ ጽሑፍ መውጣቱ የተለያዩ ሃሳቦችን ለማስተናገድና መላውን አበሻ ለመድረስ ተገቢ ድልድዮች ናቸው ብሎ በማመን ጸሐፊው ይህን ጽሑፍ ወደነዚህ ሚዲያዎች ብቻ ልኳል።
መምህር ግርማ ቀደም ብለው አገልግሎታቸውን ከሚሰጡበት የመስቀል አደባባዩ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ወደ ኤረር ሥላሴ ሲሄዱ በቤተክርስቲያኑ አስተዳደርና በጠቅላይ ቤተክህነቱ የተሰጠው ምክንያት የሚከተለው ነው።
“መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን።“
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግን ለቤተክርስቲያን ቅርበት ያላቸው ወገኖችም አይ ዋናው በውስጠ ታዋቂ ያለው ግልፁ ምክንያት የመምህሩ አገልግሎት ሕገ-ቤተክርስቲያንን ያልተከተለና የፈውስ መንገዱ ችግር ስላለበት ነው ይላሉ። በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ለዓመታት በየክፍሉ ተቀርጸው የተሰራጩት ቪሲዲዎች በተለይም በyoutube.com ላይ በተደጋጋሚ የተሰራጩትና በመሰራጨት ላይ ያሉት ‘‘የፈውስ“ አገልግሎቶች ያናደዷቸውና በመምህሩ ተደማጭነት ቅር የተሰኙ የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች ናቸው በተንኮል ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ያስነሷቸው ይላሉ። ከአገልግሎቱ ጋር ተያይዞ መምህሩ ያለችግር ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ገንዘብ በሙስና እንዲሰጧቸው የሚጠይቁ አባቶች እንዳሉም ይነገራል።
እንደዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዓይነት ደግሞ እንዲህ ናቸው ብሎ ለመፈረጅ በቂ ግንዛቤ ያላገኙ የሁለቱንም ወገኖች ሃሳቦች የሚያዳምጡ ግን አቋም ለመውሰድ የተቸገሩ አያሌ ወገኖች እንዳሉ ልብ ማለት ያሻል። አቋም የያዙትንም ሁለቱንም ወገኖች ቀረብ ብለው እንዴት ነው ቢሏቸው ከሥር መሠረቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጣቅሰው ከማስረዳት ይልቅ የቲፎዞነት ጉዳይ ጠፍሯቸው በድፍረት ይሄ ነው ለማለት ሲንገታገቱ ማስተዋል ይቻላል።
ቅዱስ እስጢፋኖስም ይሁን ኤረር ሥላሴ አብያተክርስቲያናት ሁለቱም መምህሩ አገልግሎታቸውን የሚሰጡባቸው/ የሰጡባቸው ማለት ነው- የኢ/ኦ/ተ/ቤ ንብረት ናቸው። እውነት ችግሩ ያለው ከቦታው ነው ወይስ አገልግሎቱ ላይ ነው?
በእርግጥ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ታሪክ ከፍተኛ ልዩነቶች የፈጠሩ የእምነት ነክ ጉዳዮች ተነስተው ጉዳዮቹ በቀጥታ ከሚመለከተው ከፍተኛ የሃይማኖት አካል ይልቅ በየወቅቱ የነበሩና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ነገሥታት ነበሩ መፍትሄ ሲሰጡ የነበሩት።
ከቀድሞዎቹ ነገሥታት መካከል አንዱን ለአብነት ያህል ብንጠቅስ፤ ከ1434-1468 ዓ.ም ድረስ የነገሡት የኢትዮጵያ ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለቤተክርስቲያናችን ከሠሯቸው ተግባራት መካከል ጉባኤ ሰብስበው በቤተ አውስጣቴዎስና በቤተ ተክለሃይማኖት መካከል ያለውን ክፍፍል መፍታት፣ የደቂቀ እስጢፋኖስን ችግር ማስወገድ፣ ባዕድ አምልኮን ማጥፋት፣ ለመንፈሳዊና ለዓለማዊው የስነ ጽሑፍ እድገት መነሻ የሆኑ ጽሑፎችን ማዘጋጀት በዋናነት ይጠቀሳሉ። (አባ ወልደ ትንሳኤ ጫኔ፤ ቀራንዮ መጽሔት ቅጽ ሁለት መጋቢት 2006 ዓ.ም ካስል -ጀርመን)
አሁን በአገሪቱ ያለው የመንግሥት አስተዳደር/አስተዳዳሪ ይህን ለማድረግ አቅሙም ሥልጣኑም የለውም። ይህን ማድረግም አይጠበቅበትም። ስለዚህ የዚህን ጉዳይ ወይም በመምህሩ ላይ የተነሳውን የግራና ቀኝ ሃሳብ በመመርመር ሊቃውንትን በማሰባሰብ ውሳኔ መስጠት ያለበት መምህሩ ተጠሪ የሆኑለት ሀገረ ስብከት ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያናችን የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶሱ ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
መላው ምእመናን የመምህር ግርማ አገልግሎት ላይ ግልጽ መሆን ይፈልጋል። ልክ ነው ልክ አይደለም፤ ልክ ይሁኑ አይሁኑ የምናውቀው ነገር የለም በሚል ተከፋፍሎ ቡድን ለይቶ በዚህ ጉዳይ እስከ መደባደብ የሚደርስበት ሁኔታ ሊቆም ይገባል።
አብዛኞቻችን በቪዲዮ/በአካል እንዳየነው ሕሙማኑ ተፈወስን ነው እያሉ ነው። በሌላ ወገን ያሉት ደግሞ የመምህሩ መንገድ ከአስማት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ሕሙማኑ ተመልሰው ለሕመም እየተዳረጉ ነው የሚሉም አሉ።
የመምህሩን አገልግሎት የሚቃወሙ ወገኖች ለሚያነሷቸው ተቃውሞዎች ራሳቸው መምህሩ አጋንንት ስላለባቸው ነው የሚቃወሙኝ እስከ ማለት ደርሰዋል። ትልቁ ሰይጣንም ያለው ቤተክህነት አካባቢ ነው እስከ ማለትም የደረሱበት ሁኔታ እንዳለ ይሰማል።
ከደገፍክ የአስማቱ ሰለባ ነው ትባላለህ። ከተቃወምክ አጋንንት ስላለበት ነው ትባላለህ። ግራ ገብቶህ ዝም ካልክ ወይም ምንም ካላልክ እንደ opportunist (ወላዋይ) ትታያለህ። ለመሆኑ አገርን/ምእመኑን ለሁለት/ለሦስት ቦታ የከፈለን ጉዳይ ሲኖዶሱ እያየ ዝም ነው እንዴ የሚለው?
በቅርቡ አንድ ደብዳቤ ተሰራጭቶ ተመልክተነው ነበር። መምህሩ በፓትሪያርኩ ዕውቅና ተሰጥቷቸው በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ የፈውስ አገልግሎት እንዲሰጡ ተፈቅዶላቸዋል የሚል ነበር። ደብዳቤውም በኢ/ኦ/ተ/ቤ ጠቅላይ ቤተክህነት የውጭ ግንኙነት መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ በብጹዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ እንደወጣ ይገልጻል። ትንሽ ዘግየት ብሎ ደግሞ ደብዳቤው ሕገ-ወጥ መሆኑ እና ብጹዕነታቸው የማያውቁት የተባለውም ነገር እውነት እንዳልሆነ በመግለጽ ድርጊቱ የማጭበርበር በመሆኑ በፖሊስ ጉዳዩ መያዙን የሚጠቁም ደብዳቤ ተሰራጨ።
ልብ በሉ ሁለተኛው ደብዳቤ ጠቅላይ ቤተክህነት የበፊቱን ደብዳቤ በመቃወም መምህሩ እንዲህ ቢሏችሁ አትስሟቸው አትመኗቸው ነው የሚለው።
ያም ሆነ ይህ መምህር ግርማ አስማተኛ/አጥማቂ? መሆናቸውን አቋም ይዞ ለሕዝቡ አውጆ እርምጃ መውሰድ ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ሕዝብ ሲከፋፈል እያዩ አባቶቻችን አጀንዳቸው አድርገው ካልተወያዩበትና አቋም ካልወሰዱበት ችግሩ ነገ ወደማይፈታበትና ወደማንወጣው ትርምስ ሊወስደን ይችላል። ለቀጣዩም ትውልድ ፈተና ማውረስ ይሆንብናል።
አንድ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ ልክ እንደነ “ኤሊያስ ከሰማይ ወርዷል“ ብለው ስለሚንቀሳቀሱት ወገኖች ጉባኤ ተጠርቶ በቂ ምላሽ እንደተሰጠ ሁሉ በመምህር ግርማ ወንድሙ ዙሪያ በመነጋገር ጉባኤ ከተዘጋጀ በኋላ ጉባኤው መሰረዙን ሰምተናል። ለምንና በማን? እስካሁን ምላሽ የለም።
ብርዐቸው ሲተፋ ቀለሙን የሚያንዥረግገው ታዋቂ የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንትም በመምህሩ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ ወይም ለመናገር ምነው ልሳናቸው ተያዘ? ቀለማቸውስ ምነው እዚህ ጋር ሲደርስ ቁርጥ ቁርጥ አለ?
ነገሩ መቼም ጉድ የሚያሰኝና ግራ የሚያጋባ ነው። በዚህ ልክ አይደሉም መምህሩ ይሉናል። በዚያ ደግሞ አንድ ሊቀጳጳስ በመምህሩ አገልግሎት ተደንቀው መስቀል ሁላ ሸልመዋቸዋል። መምህሩም አገልግሎታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው። ይህንንም አይተናል። ነገሩ እንዴት ነው ጃል? ቋጠሮውስ እንዴት ነው ሚፈታው? ሲኖዶሱ ደብዳቤ መፃፍ ብቻ ነው ወይ ሥልጣኑ?
በዚህ ዙሪያ ላይ ጠቃሚ ሃሳብ ያላችሁ ወገኖች እንደ ጋን ውስጥ መብራት ከምትታፈኑ በዚህ በነፃ መድረክ ብንወያይበት ለመፍትሄውም ይበጃል። ልብ ብላችሁ ካያችሁት አንድነታችንን ከሚፈታተኑት ነገሮች አንዱ ይሄው ጉዳይ ሆኗል። በአንድ ቤት ጣሪያ፤ በአንዲት ኦርቶዶክስ እምነት ሥር ያሉ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ የተለያየ አቋም ያላቸው ተወያይተው የማይተማመኑ ወገኖች በዝተዋል። እባካችሁ አባቶች ይሄን የመሳሰሉ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ወደ ጎን ትታችሁ ስለ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ልማት ከማውራት በመቆጠብ፥ የቄሳርን ለቄሳር በመተው የእግዚአብሔርን ሥሩ! አንድነታችንን የሚፈታተኑ ነገሮችን እግዚአብሔር ይስበርልን! አሜን።
dawit lemma says
Endet new negeru lebe belo layehe Tehadeso new yemetemeselew,sewen kebesheta selefewesu endet asemategna yasegnachewal asemategna menorun kamenek selemen ye Egeziabeheren tamere mayet tesaneh
kindalem gurmu says
I share your idea memehir girma is not asmategna.because I and my friend know everything about asmategna and majician.debtera is a manic works around ethio orthodox church.they study the science of debtera in a secret manner.they use this they call it tibebe liqawunt.we n know there are other manic we call tenquwai .and also qalicha in Muslim .These all majics work with a devil help.Memehir girma says.go church.have a confesuoni.e neseha.take a commonion.ie qidus qurban.pray every day and night…I was never ever heard these prayer suggested by a manic.why?because I tried all teqniques to get money and to get a girl I wanted her for all my life.legenzeb:leset:lesiltan:seleminfelegachew menafsten eneteyiqachewalen.But in levetics chapter 19.versus 1 God said do not do and follow evil.I was quit every thing now I am free from that dirt. I can say 100%mwmehir firms is not a majician.there are majicians around the Ethiopian orthodox church we call them debtera.There are majicians around Muslim community in Ethiopia they ate called qalicha.There are other majicians they are not included in both religions but they are well known by the community I mean they are licenced I can say because they work openly..even though the community going there secretly.But letGod help us.Generally,I definitely know who a majician is!!!!!because I was their member,but to tell the truth because the truth matters;me lake menkirat Firms Wondimu is the best Ethiopian Orthodox fathere
Kalab abiye says
This is not true. Melake Minkerat Memhir Girma Wendimu is a good man. He gives his credit to God. But what you said, kindalem gurmu is wrong. Debtera is not bad. It is a level of promotion higher than the clergy. Debtera is a non ordained priest who will study until he is 85 so that God may give him the eyes of intelligence, the mouth of peace and the ears of heaven. Buda is a evil spirit that comes through you by makeup which allows Buda to make your eye a bridge to our body. Zar is a screaming spirit from hell that will control you in ways you don’t want it to. Zar comes from the lack of prayer and praise, family string or from an enemy. This is the things Debtera study to understand the Word of God. Now you said that Debtera is a wizard which is false. A wizard is someone that repeats the name of Satan to kill and to do wrongdoing. An example is Anstasious. He was the wizard asked to give George the drink of Death. He said the names of Satan over the drink so it is now poisonous. This is what Wizards do. Debtera give prescriptions to the sick, the possessed and the weak. They help not kill. They teach not lie. They thrive and not fall. They learn Prayer, Bible, Zimare Yared, Metsahft and the works of Satan. They learn about Satan so they can give awareness to the people to protect the people. Tibebe liqawent means the wisdom of our leaders. This is the term people use to describe the knowledge of the Debtera. The reason why they work alone is because the Debtera like I said are feared of there knowledge and are not considered welcome in some places. It takes years to accomplish this. At 85 someone may be named Debtera. Melake Minkerat Memhir Girma Wendimu is a great man. He is a Debtera that gives knowledge about the demons he casts out. The title of this question is Wizard or Baptist. The answer is Baptist because he heals not only Christians but also Muslims. This however does not mean Debtera are Wizards. As Memhir himself said “The wizards give bad information and trick you into the wrong path which can make you a bridge to Zar. So this means Debtera will help you away from this wizards and help you.
Talisman ጠልሰም
This is the word that describes the pictures with many faces. This pictures are of Angels and the Power of God. For example in the Bandlet of Righteousness (an ancient script written by Debtera) it talks about how to keep yourself away from Death itself and help you in life. It also comes with Pictures that have words of God written on them. These pictures are drawn only by Debtera because they know the knowledge of this Power.
SELSHIE says
መምህር ግርማን የማውቃቸዉ ቦሌ ሜካኤል በ1996 አካባቢ በማስተማርና በፈዉስ ስራ ነበር ሲያገለግሉ የማዉቃቸዉ ከቤተሰቦቼ አንዱ በመታመሙ ምክንያት በርግጥ ሰዎች ያስ ጮሀሉ ተፈወስኩ ይሉና በንጋታዉ ወይም በሳምንቱ ይመጣሉ እንደገና ተነስቶባቸዉ አጋንንት ከወጣ በሆሀላ ተመልሶ እንዳይመጣ ትጋት እንደሚያስፈልግ አዲስ ኪዳን ይናገራል ሆኖም እስከዛሬ ድረስ ከቤተክርስቲያን አስተዳደሮች ለምን ትክከል የሆነ ያለመሰጠቱ ጉዳይ ከእርሳቸዉ ይልቅ አስተዳደሩን ጥያቄ ዉስጥ የከታል
kirk says
hi all I have some comments based on the VCD released recently to be honest the message of it is not based on the Holy Bible because I do not see Glorifying Jesus Christ instead glorifying Virgin Mary I saw peoples talking that saying we can not call the name of Mary but they can say the name of Jesus it seems funny to me or drama. Jesus said “Go to the world and preach the Gospel cast out demons in my Name” but in Memhir Girma service its opposit
Ethiopian Orthodox Miracles says
መምሕር ግርማን በተመለከት ላነሳሐቸው አንዳንድ ነጥቦች ይህ ብሎግ መልስ አለው:
1. የመምሕር ግርማ ታሪክ
2. ቤተ ክህነት ያለው አመለካከት
3. ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤው የመቋረጡ እውነት – ከ ቀድሞ አስተዳዳሪ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ/ገንዘብ በሙስና /
4. መምህር ግርማ በተለያየ ግዜ ያደረጓቸው መረጃ ሰጪ ቃለምልልሶች
Who is Memher Girma Wondimu?
http://ethiopianorthodoxmiracles.blogspot.be/search/label/Who%20is%20Memihir%20Girma%3F
ygermal says
ጋዜጠኛ መስፍን ኣብርሃ ante erasehi bememihir Girma layi lemetsfi ke sinodosu belayi min aschenekehi ate alamahi filagotehi min edehone tsufihi yinageral.ye memehir Girma setetu minu layi newu memhir girma ke Egziabher yetesetachewun tsega hiziben eyagelegelubet newu.Ewur ayinu selebera, diski ke opreshin seledanu ena tenama hunewu seleseru,keseyitan keganal sewuchi seletefewesu,tekuyochi ketekolachewu sewun kematefat selaskomuachewu,tewuleden wedetfat godana edayihed bemekeru basetemaru, bemilion yemikoter hizib emenetun atebeko ediyiz badergu, yetefuten begochi bemelesu, Egziabher meretachewu kebachewu aganten yemasewetat seletan tesetachewu Ede abone sinoda abune sinoda abune sinudam be Egibt ager aganint ede memehir girma yawetu neber memehr Girman tewachewu yifewusubet tewachewy tewachewu
Hailemichael says
የእግዚያብሄርን ስም ጠርተዉ እስከ ፈዎሱ ድረስ ኣስማተኝነታቸው ኣይታየኝም
nebey bageru ayekeberem new derom bihon
kindalem gurmu says
I like your said
Mekonnen Tafere says
“ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” የማቴዎስ ወንጌል ፥ምዕራፍ 6 :24
መምህር ግርማ ወንድሙ ለገንዘብ ያላችው ፍቅር በጣም በጣም የሚያስፈራና የሚያሳስብ ነው። በአሁኑ ስአት በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ አጥማቂና ፈዋሾች አሉ ፥ ነገር ግን መምህር ግርማን የተለየ የሚያደርጋቸው VCD እና መቁጠሪያ በመሸጥ ብዙ ብር ኣካብተዋል። እንዲሁም በራዲዬ ኣቢሲኒያ አማካኝነት ከዳያስፖራው በጣም ብዙ ብር እየተበዘበዘ ነው።በእስጢፋኖስም ሆነ በየረር ስላሴ ከአስተዳደሩ እና ከቄሶች ጋር በገንዘብ ድርሻ በመደራደር እስካሁን እንደፈለጉት ግቢውን ለንግድ ተከራይተው ከባድ ገንዘብ እየሰሩ ነው።
ይህ አውነቱ ሲሆን ስውየው ግን ጠንቖይ ወይም አስማተኛ ተባልኩ ብለው በየኣጋጣሚው ይጮሃሉ። ግን ከመምህር ግርማ ሌላ ማንም ይህን ሲላቸው ኣልተሰማም።ኣሁንም እደግመዋለሁ መምህር ግርማ ወንድሙ ለገንዘብ ያላችው ፍቅር በጣም በጣም የሚያስፈራና የሚያሳስብ ነው።
fish says
“ስውየው ግን ጠንቖይ ወይም አስማተኛ ተባልኩ ብለው በየኣጋጣሚው ይጮሃሉ። ግን ከመምህር ግርማ ሌላ ማንም ይህን ሲላቸው ኣልተሰማም”. You made a mistake. It seems you do not usually read various “religious” blogs.
senu says
Gazetegna Mesfin? kkkkkkkkkkkkk..
awo Memhir Girman yemetala Aganent yalebet,, ,, weyem ye Debtera Metetegna weyem _
ye Awdenegest degame Qes or debtera new !!!
Mesfin sera feleg ena seta pls
senu says
anzagnaw ye Memger telat Menafiqan nachew !!
aygermenem !!! Menafiqanen Aganint negn eyale sechoh alayechum ???
aygermenem !!!!!Egziyabher yegesetsachu !!
Ewunet says
tadeso ena menafikan yeteleyaye sem lisetachiwu yichilal egnagin besachewu layi anteraterim yeEgziyabhern sem tertewu eskefewesuders wengalen kasetemaru , aynesewur kaberu, shiban ketereteru , beshitegna kedane Egiziyabeher tsegachewun yabezalachewu amen kemenfesawi agelgilotachewu lemaskom yeteleyaye mukera edetemokere enawuki alen ahun degimo bezi bekul metachihu. betewachewu menfesawi tegadiloachewun bigadelubet terunewu.
denna abera says
Mekonen Tafere ) ante menafik don’t think about our father like this ya’re leaving with devil Memhr girmaen egeziabehere amelake new new le ethiopin people barko yestan menem asmataga aydalum yeha yetlat where new degmo sint zemen lenoru ganzb yemytarqmut ante weshatem bado chenqlet menelabet misken hezbe mehrat endyage belak new enj ante yefalakaw bado adarsh wist maten kstan ger selalchnilk new egeziabehere amelake orthodox hymnotcenen tsta tenoralch lazlalm
Memer girma asmtag aydalum
Egzybher yemasgen! !!!
ቲታ አብ says
እውነትን ለማወቅ የሲኖዶስ ወይም የቤ ተክህነት ማረጋገጫ የሚስፈልገን ትውልዶች
አይደለንም መምህር ግርማ ህሙማን ፈወሱ ምኑ ላይ ነው ስህተት ? ድሮም የኢትዮጵያ
ጥበብ ተደብቆ የቀረው በቤተክህነት በተሰገሰጉ ሀሰተኛና ከእወቀት ነፃ በሆኑ መምህራን
ነኝ ባዮች ነው ዛሬም መመህር ግርማ ላይ የደረሰው ይህ ነው ክርስቶስ በፈሪሳውያን
እንደተፈተነው የዘመናችን ፈሪሳውያን ደሞ በክርስቶስ ስም ተሰብስበው ለድውያንና
ለህሙማን የመጣን በፈጣሪ ስም የቆመን መምህር ሲንገላታ ማየት እጅግ አሳዛኝ ነው
ቢሆንም ዛሬ ያለው ትውልድ ባሉት መንገድ የሚረዳ ሳይሆን እውነትን መረዳት የሚችል
በመሆኑ የመምህሩን በረከት ብዙዎች እያገኙ ነው በመጨረሻ ማስተላለፍ የምፈልገው
ጥበብ በሰዎች ዘንድ በእግዚያብሔር ትገለፃለች ለችግሮች ሁሉ መፍትሔን ትሰጣለች
መልካም የሆነ ስራ የሰይጤን ሊባል አይችልም ሰይጣን የሚለው ስያሜ ከመልካምነት ጋር
ምንም አይነት ቁርኝት የሌለው ነገር ነውና በምክኒያት የሚሞግተኝ እንደሚኖር ተስፋ
አደርጋለሁ
didi says
እግዚአብሄር በመምህር ላይ አድሮ ፍጥረቱን ከዲያብሎስ ባርነት ሲያላቅቅ ዲያቢሎስ ይቀናል። በሰዎች ላይ አድሮ ክፉ ያናግራል፣ያሰራል። በመምህር ላይ ከዚህም የባሰ ቢባል አይደንቅም። ምክንያቱም ውጊያው ከዲያብሎስ ጋር በመሆኑ። እኔ ግን ፈጣሪን የማመሰግነው ጠላት ቢያወራ ዲንጋይ ቢፈነቅል አምላክ ተክሎዋቸው፣ እንደኛ ሳይሆን ለፍጥረቱ የሚራራ ጌታ አድሮባቸው የፈውስ አገልግሎታቸውን እየሰጡ አመታት ማስቆጠራቸውን ነው። ሰው ግን የዲያቢሎስ ማህበርተኛ ከሚሆን ወንጌሉ እንዳለው መንፈስን በጾም በፀሎት ተወስኖ ይመርምር። ከእግዚአብሄር ያልሆነ መሰረት ስለማይኖረው ይወድቃል፣ፍሬ አፍርቶም አይታይም፣እድሜም የለውም። እና ወገኖቼ የዲያቢሎስ መሳሪያ በመሆን እድሜያችሁን በከንቱ በተንኮል ኣትጨርሱት። እግዚአብሄር በመምህር ግርማ ላይ አድሮ የማዳን ስራውን አላቆመም እና!!!!
ተዋህዶ ቅድስት says
በመገመሪያ በዚህ በከፋ ዘመን እንዲህ አይነት አባት አስነስቶ የጎበኘን አባት ይመስገን
ጠንቋይ ናቸው
ገንዘብ ይሰበስባሉ
ህገወጥ ናቸው
አጭበርባሪ ናቸው ውዘተ…………..
እኔ የምይገባኝ ነገር በመስቀል‹ በጸበል፣ በመቁጥሪያ የእግዚአብሔርን ስም ፣የእመቤታችን ስም፣የመላክቶችን ስም እየጠራ የሚፈውስ ምን አይነት ጠንቋይ ነው
ምን አይነት አጨበርባሪ ነው እንዲይው ዝም ብለን የማዳኑ ስራ ብንመለከት ይሻላል
በማናቸውም ጥፋት ከተገኘባቸው እግዚአብሔር ይጠይቃቸው
ህገወጥ ናቸው ለተባለው › ህገወጥ መሆናቸው ከተረጋገጠ ልክ እንደአለፈው አመት በስጢፋኖስ እንዳገዷቸው ቤተክህነት ማገድ ይችላል እንጅ በሄዱበት ሁላ ደብዳቤ እየላከ እገወጥነታቸውን የሚከላከል አይመስለኝም
Aster Semaw says
በአባታችን ላይ ክፉ ሰወች እና አጋንንት እየተነሡ ነው.እግዚያብሔር ያሥታግስልን.የሠውን መዳን የማይወደው ርኩስ መንፈስና ተባባሪዎችን እግዚያብሄር ይገስፃቸው.
Nigus Tadesse says
እግዚአብሔርን የሚያውቅ፥ እግዚአብሔርም የሚያውቃቸው ይህን ጉዳይ መሰረቱን ለመረዳት ብዙ መቅበዝበዝ አያሻውም። ምክንያቱም፤ ስለጉዳዩ ወይ ቀድሞ ሽቷል ወይም ጸልዩአል ወይም እየፀለየ ነው ካልሆነም ባየ ግዜ እግዚአብሔርን አመስግኗል። ልባቸው የተጣመመባቸው ቀድመው ነገሩን ሲጠመዝዙ ደግሞ፤ ይህ ሰው ቆም ብሎ ያስተውላል ይመረምራል። የሚደንቀው ደግሞ፧ የእግዚአብሔርን ስራ እያየ ቅዱስ፣ቅዱስ፣ቅዱስ እግዚአብሔር፡ ልዩ ፍቅር ይላል። የሚገርመው ደግሞ፤ የሌላውን ማረጋገጫ አይሻም።
ለዚህም ይመስለኛል፡ በመጨረሻ፤ እግዚአብሔር ብራቆት፡ ብጠማ፡ ብታሰር… ለዚህም ይህን ፅሑፍ ሲያነብ እራሱ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ለዚህም ይኀው ወገኔ፡ ዛሬም ልብህ በእግዚአብሔር ደስ ይበለው።
ያልታደለው ደግሞ፡ ዛሬም ይቃወማል፡ ቤተክርስትያንን እና መስሪያ ቤትን መለየት ልቡ ተስኖት።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር…ማን ይቃወመናል።
mulualem tessema says
memehires Geta Yemeretachew Nachew. Setotaw Kesew Sayihon Keamlak Newe. Mene Yidereg Engdih .Atizerfuachew . Enant Leboch. Metetgnoch Gudachehu Siweta Gize Yihenen Aderegachehu. Mekegnoch Nachehu Byebetkerstiyanu Tewetefachehu Hizbun Cheresachehu.Gudachehu Sigalet Newe. Esachewes Yifetalu Yebelagn Lenante. weregna Bicha, Adame Amenshem Alamenshem Meleakm Menkerat Keamlak Yetesetun Talkena Bichegna Abatachen Nachew.Ayidelem Genzeb Kiyabezu Endezihe Yemiluten Tekawami Nachew. Ezih Hager laye Behak Menor Ayichalem Enawekewalen.
Alem says
wey good wey good… yehen asteyayet seleseten yale hatiatachew yetaserut Abatachinin yetekemal ? weyes bey aketachaw lemiseru researchoch tekami yehon?
I mean keresu bijemir minim deg neger lemantsebarek ayemechem, kesedib silejemer malet nw. Melak Menkerat Memehir Girma Wondimun EGZIABEHER kene ABUN TEKLHAIMANOT tereta yedemirachew legna fana berehanin endasayun yezelalem YE-EGZIABHER fana ena berehan ayeleyachew. Neketew yanekun tilik abat nachew, yelek wegene bastemarut temihirt enetekemibet. Tsegachinin kibrachinin enemarbet, betelatachin enenkabet. Sewn kemeret tenesto mezelef ena mesadeb min yahil Ke-HAYMANOT endewetan EGZIABHEREN weyem EGZIABHER yayegnal kemilew hasab endet enderakin yasayal. yehe demo man eyemeran endal gelets nw simun meterat ayasfelegim….
ተስፋ says
አቶ ግርማ ሲያስተምሩም ሲያጠምቁም በስላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝቼ አይቻለው።
ያስተዋልኩት
1. በግቢው ውስጥ የሚካሄደው ገደብ የሌለው የቅባቅዱስ፣ የመቁጠሪያ፣ በተለይ ደግሞ የvcd ሽያጭ ከሁሉም የቀደመው አስተማሪያችን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ካስተማረን የሚቃረን ሆኖ ሳለ አቶ ግርማ ግን ይሄን ድርጊት ሲቃወሙ አላየሁም
2. አቶ ግርማ እየሰራሁ ነው ለሚሉት መንፈሳዊ ስራ በምንም መልኩ ስጦታም ሆነ ክፍያ ሊቀበሉ አይገባም ሆኖም የስላሴ ቤተክርስትያን ደብር ኃላፊ በግልፅ ህዝቡን ለአቶ ግርማ ስጦታ እንዲሰጡ ሲጠይቁላቸው ከመቃወም ይልቅ እንዳልሰማ ማለፉቸው።
3. ቤተክርስቲያን የሚሄድ ሰው ሀሉ ሃሳቡ አንድ አይደለም ለማመስገን፣ለመፀለይ፣ፈውስን ለማግኘት ወዘተ… ሆኖም ለፈውስ የተዘጋጀ ቦታ እያለ የዋናውን ቤትክርስቲያን ግቢ መንፈስን በሚረብሹ ሁኔታዎች ውስጥ በማስገባት በቅዳሴ ሰዓት እንደሚሆነው ሰላም እንዳይኖረው በማድረግ የእርኩስ መንፈስ መሯሯጫ አድርገውታል።
4.ፍፁም መንፈሳዊ ስራ በምንም መልኩ እንቅፋት አይገጥመውም ሆኖም አቶ ግርማ እያጠመቁ ሳሉ ዉሃ በመቋረጡ አብዛኛው ምእመን ያሰበውን ሳያገኝ በቁጭት ሲመለስ አይቻለው።
ማጠቃለያ
አቶ ግርማ እያደረጉት የሚገኙት፤ ተስፋ አስቆራጭ ችግር ውስጥ የምንገኝ ሰዋችን እርሳቸው የሚያናግሯቸውን እርኩስ መንፈሳትን በመጠቀም በክርስቶስ አዳኝነት በእመቤታችን አማላጅነት ብቻ መዳን የሚገባንን ወደ ሴጣናዊ ተግባር እየወሰዱን እያሳሳቱን ይገኛሉ።
ማሳሰቢያ
እኔ ክርስቲያን ነኝ ለህመሜ መዳን ሙሉ እምነት አለኝ። ለዚህም ከእየሱስ ክርስቶስ ወጭ ማንንም አልፈልግም። እከሌ ያድነኛል ብዬ አገር አቋርጬ ሰው ፍለጋ ሳይሆን አምላኬን አምኜ አጠገቤ የምትገኘው ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ እድናለሁም።
የሚያድነን እምነታችን እንጂ ያረፈብን ፀበል ወይን መቁጠሪያ ወይም የአስተማሪው እጅ አይደለም
ክርስቶስ እንዳለው
“እምነትህ አድኖሃል”
“እምነትሽ አድኖሻል”
Nsr nigusie says
ተነቃቅተናል ሹልክ ብለሽ ውጪ
ገዛ says
የቀናተኞች ሤራ ነው የመናፍቃንሴራ
Nsr nigusie says
ተነቃቅተና በይ ሹልክ ብለሽ ውጪ አይጥ
Gizaw Getye says
Abate Enes erswon lemaggnet fekadegna negne yefetari fekad kehone bereketwo yidresegne
አስቻለው says
እስኪ የመምህር ግርማ ወንድሙ ልጅ ሱቅ መዋለንዋናዘያት ሚሸጥበት ሱቅ አድራሻው ያለው ሰው ተባበሩን ቤተሰብ