
የማሰብ ነፃነት ማጣት ባርያነት ነው፤ ያሰቡትን አለመናገር: ባርያነት ነው፤ ያሰቡትን አለመጻፍ: ባርያነት ነው፤ ፍትህ ማጣት: ባርያነት ነው፤ ከገዛ አገሩ መሰድደ: ባርያነት ነው፤ ተማሪው “መሬት ለአራሹ” ብል በደሙ የዋጀውን የመሬት ባለቤትነት መብት: ከገበሬው ነጥቆ በማፈናቀል: በድንበር ዘለል ከበርቴ መቸብቸብ፤ የባርያነት ቀንበርን መልሶ መጫን ነው፤ ሠራተኛውን በዓለም አቀፍ ዘራፊ ኢንደስትሪዎች፤ በገዛ አገሩ ጉልበቱን ማስበዝበዝ: ባርያነትን ማስፈን ነው፤ ምሁራንን በአገራቸው ጉዳይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው በየምክንያቱ ማግለል: ባርነትን እንዲነግሥ ማድረግ ነው፤ ወጣቱን ለሥራ አጥነትና ለስደት መዳረግ አገርን መግደል ነው፤ ዝምታ ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል ነው፤ አድር ባይነት: ባርያ መሆን ነው፤ ሕዝብን በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች እንዲሆን ማድረግ: የባርነት ሥርአትን ማስፈን ነው፤………….ወዘተ :: (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply