• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስርዓቱን ብልግና ለመድነው

June 12, 2015 08:18 am by Editor Leave a Comment

አሁን አሁንማ ዜና የሚሆን ነገር ጠፍቷል፡፡ መታሰር ተለምዷል፡፡ መደብደብ ተለምዷል፡፡ የሀሰት ምስክርነት ተለምዷል፡፡ ከአሁን ቀደም ‹‹ጉድ ነው!›› ያሰኙ የነበሩ ህገ-ወጥነቶች አሁን የቀን ተቀን ተግባር ሆነው ወደ ጎን እያየን እየተውናቸው ነው፡፡ በአጠቃለይ የስርዓት ነውር፣ ብልግና፣ ስርዓት አልበኝነትን ለዜናም የሚበቁ አልሆኑም፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹እንትና ጠያቂ ተከለከለች፣ እንትና ምግብ እንዳይገባለት ተደረገ›› ተብሎ ዜና ይሰራ ነበር፡፡ እንደ ትልቅ የስርዓቱ ብልግና እና ነውርም ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ እንዲያውም ይህ አይነት በደል የሚፈፀምባቸው በፀረ ሽብር ህጉ ተከሰው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን በሰልፍና በሌሎች ሰበቦች የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ በደል እየተደጋገመ ወደ ተራ አሰራርነት (የስርዓቱ ህግና ደንብ) ተቀይሯል፡፡ ነውር ቢሆንም እኛ ግን ለምደነዋል፡፡

ዛሬ በጠዋት ተነስተን ከኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጋር ቃሊቲና ቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞችን ለመጠየቅ አቀናን፡፡ መጀመሪያ ወደ ቃሊቲ ስንሄድ ኢ/ር ይልቃል ቃሊቲ የታሰሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጠያቂዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሙ እንዳለ በማወቅ ነበር፡፡ ህገ መንግስቱ እስረኞች በዘመዶቻቸው፣ በህግ አማካሪዎቻቸው፣ በሀኪሞቻቸው፣ በጓደኞቻቸው የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ቢደነግግም እስረኞቹ ግን ‹‹የሚጠይቃችሁን የጥቂት ሰዎች ስም ዝርዝር አስቀምጡ›› ተብለው ተገደዋል፡፡ ‹‹አይ! መብታችን ነው፡፡ ማንም ሊጠይቀን ይገባል!›› ያሉት ደግሞ ከእነአካቴው እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ እኛ ይህንንም ስለለመድነው እስረኛ ለመጠየቅ ‹‹የጠያቂ ስም ዝርዝር ላይ ተመዝግበሃል?›› መባባል አዲስ አይደለም፡፡ ይህ ማጎሪያ ቤቶቹ ህገ መንግስቱን በአፍ ጢሙ ገልብጠው ያወጡት ‹‹ህገ አራዊት››› ነውር ቢሆንም እኛ ግን ለምደነዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የሚጠየቁት ከ6፡00 – 6፡30 ባለው ጊዜ ነው፡፡ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ30 ደቂቃ ማለት ነው፡፡ ይህም ቢሆን ማረሚያ ቤቱ ያወጣው ሌላኛው ነውር ነው፡፡ ያም ሆኖ በ30 ደቂቃ ውስጥ ለመጠየቅ እንዲያውም እንዳይዘጋብን ተጣድፈን እንሄዳለን፡፡ ለዛምው እድሉን ያገኘ ‹‹ዛሬ እኮ ገባሁ!›› እያለ እንደ እድል ማውራት ሁሉ ተጀምሯል፡፡ ለ30 ደቂቃ ያህል እነ ወይንሸትን ለመጠየቅ እየተጠባበቅን ባለንበት ወቅት አንዱ መዝጋቢ እኛ የተቀመጥንበት አካባቢ ሆኖ መመዝገብ ጀመረ፡፡ ሁለት ታሳሪ ለመጠየቅ የጓጉ የሚመስሉ ወጣቶች ለመመዝገብ ቀርበዋል፡፡

‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?

‹‹አቡበክር አህመድን!››

‹‹ምኑ ነህ?››

‹‹ጓደኛው!›› መዝጋቢው ትንሽ ተጨነቀና ሌላ ነውሩን የሚያስቀጥልበት ጥያቄ ጠየቀ፡፡

‹‹ከአሁን ቀደም ገብተህ ታውቃልህ?››

‹‹አዎ! በቀደም ዕለት ገብቻለሁ!›› የገባበት ቀን ሩቅ ቢሆን ኖሮ ከዛ በኋላ የወጣ ህግ እንዳለ በመግለጽ እንዳይጠይቅ ለመከልከል ይመስላል፡፡ ግን ነውር ተለምዶ የለ?! ‹‹ጓደኛው ነኝ›› ብሎት ወደ ሌላ ጥያቄ አልፎ ያነሳው ጥያቄ ለመከልከል የሚያስችል ባለመሆኑ ወደ ኋላ ተመልሶ ‹‹ጓደኛ መጠየቅ አይችልም፡፡ ለመጠየቅ ዘመድ መሆን አለብህ፡፡ አባት፣ እናት፣ወንድም..››

‹‹እንዴ! በቀደምኮ ጠይቄዋለሁ!››

‹‹አይቻልም! ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው!››

በእርግጥ እናት፣ አባት፣ ወንድም መሆኑን ይህን ነውር አያስቀረውም፡፡ ምክንያቱም ቂሊንጦ ታስረው የሚገኙት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እነ ናትናኤል ያለም ዘውድ ‹‹ማንም ሊጠይቀን ይገባል፡፡ ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡›› በማለታቸው በቤተሰቦቻቸውም ጭምር እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ አቡበክርን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ የሄዱት ወጣቶችም ዘመድ ቢሆኑ የሆነ ምክንያት ተመዞላቸው መመለሳቸው አይቀርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከዛ ቤት ነውር ተለምዷል፡፡ እኛም ለምደንላቸዋል፡፡

በዚህ እየተገረምኩ እያለ አንድ እነ ወይንሸትን ለመጠየቅ እንደመጣን የገባው ወጣት ወደመዝጋቢዋ ጠቆመን፡፡ ኢ/ር ይልቃል መታወቂያውን አሳይቶ ወይንሸት ሞላን እንደሚጠይቅ ለመዝጋቢዋ ነገራት፡፡ ወይንሸት ሞላ ያስመዘገበቻቸው ጠያቂዎች ስም ዝርዝር ተፈለገ፡፡ የኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ወይንሸትን የሚጠይቁ ሰዎች ስም ዝርዝር ይታያል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ስም የመጀመሪያ ተራ ቁጥር ላይ ነው፡፡ ግን በኮምፒውተር የተፃፈው የስም ዝርዝር ላይ የኢ/ር ይልቃል ስም መሃል ለመሃል አንድ ጊዜ በእስክርቢቶ ተሰርዟል፡፡ ምን አልባት የኢ/ር ይልቃልን ስም መጀመሪያ ላይ ያየው የህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬ በንዴት የሰረዘው ይመስለኛል፡፡ መዝጋቢዋ የሆነ ደስ ያላት ትመስላለች፡፡

‹‹ተሰርዟል!›› አለች፡፡ ህግ ጠቅሳ መከራከር የምትችል ያህል በልበ ሙሉነት ነው የምትናገረው፡፡ በኮምፒውተር የተፃፈ ስም ዝርዝር ላይ በእስክርቢቶ ሰርዘው አትገባም ከሚሉ ሌላ የኢ/ር ይልቃል ስም የሌለበት ስም ዝርዝር ቢያስቀምጡ የጠያቂዎች ስም ዝርዝር ላይ የለህም ማለት ይችሉ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያ ነውራቸውን ሊቀንሰው ሆነ፡፡ ነገሩ ለማንስ ተጨንቀው? ምንስ ይመጣባቸዋልና?

በአንድ ወቅት ነገረ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያውን ተማም አባቡልጉን ይህን ለ30 ደቂቃ ብቻ መጠየቅ እና ጠያቂን መከልከልን በሚመለከት ጥያቄ አቅርባለት ነበር፡፡ ተማም እንደሚለው ይህ አሰራር ከህገ መንግስቱም፣ ከሞራልም፣ ከኢትዮጵያዊ ባህልም የሚቃረን ነውር ነው፡፡ እሱስ ብልግናም ነው ይለዋል፡፡ ተማም ‹‹በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን በምታክል ትልቅ አገር እንዲህ አይነት ነገር መከሰቱ በእውነቱ ነውር ነው፡፡….እንዲያውም ለእኔ ይህ ብልግና ይመስለኛል፡፡›› ይላል፡፡

አንድ ሰው የሚታሰረው ከጥፋቱ ይታረም ዘንድ ለማስተማር ነው፡፡ ነገር ግን አሁን የሚፈፀመው በደልና ግፍ ስርዓቱ ሲያስር ከዛም በላይ ዓላማ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ ተማምም ‹‹ሰውን ካሰርከው በኋላ የግል ጉዳይ የለህም፡፡ …. የግል ካልሆነ ደግሞ በግለሰብ የሚፈጸም በቀል አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም የግል ጉዳይ አይደለም! …የግል የሚሆነው ሰዎች ህግን ለተወሰነ ሰው አድርገው ስለሚወስዱት ነው፡፡›› ይላል፡፡

እውነት ነው! መጀመሪያ ነገር እነ እስክንድር፣ አንዱዓለም፣ ወይንሸት፣ አበበ ቀስቶ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ የሽዋስ አሰፋ ….. የታሰሩት አጥፍተው መታረም ስለሚያስፈልጋቸው አይደለም፡፡ መታረም ላቃተው ስርዓት የራስ ምታት ስለሆኑበት እንጅ፡፡ እንደ በደል ከተቆጠረ የእነዚህ ሰዎች በደል በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ስራ የሚሰራውን ስርዓት በመቃወማቸው ነው፡፡ ህግ ደግሞ የስርዓቱ ቁንጮ ሰዎች የግል ንብረትና ማጥቂያ መሳሪያ ሆኗል፡፡ ለህዝብና ለሀገር ዋስትና ከሚሆን ህገ መንግስት ይልቅ የራሳቸው፣ የግላቸው ‹‹ህገ አራዊት›› ነግሷል፡፡ ይህ ህገ አራዊት ደግሞ ለበቃል እንጅ ለፍትህ ቦታ የለውም፡፡ መብቱን የጠየቀ መልሱ በቀል ነው፡፡ ስርዓቱን በህጋዊ መንገድ የጠየቀ መልሱ በቀል ነው፡፡ ምግብ እንዳይገባለት መከልከል፣ ጠያቂ እንዳይገባለት ማድረግ፣ ማሰቀየት፣ መስለብ፣ …..ስቀይ፣ ነውር….፡፡ እኛም ቢበዛ፣ ቢደጋገም…ይህንን ነውር፣ የስርዓት አልበኛውን ስርዓት ብልግና ለመድነው፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule