• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሕያው ቤተ መዘክር

June 3, 2016 03:12 am by Editor Leave a Comment

ደራሲ፣ ተዋናይና አዘጋጅ ጌታቸው ደባልቄ በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ደማቅ አሻራቸውን ካኖሩ አንጋፋ አርቲስቶች አንዱ ናቸው፡፡ በብዙዎች ዘንድ ‹‹ሕያው ቤተ መዘክር›› በሚል ስያሜ ይታወቃሉ፡፡ መረጃ በመሰብሰብ፣ ጠንቅቆ በመያዝና ለጠየቃቸው ሁሉ በማካፈል የሚወዳደራቸው የለም ለማለት ይቻላል፡፡ በተለይም በኪነ ጥበቡ ስለተከናወኑ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች ጥልቅ መረጃ ለማግኘት የሳቸውን በር ማንኳኳት የብዙዎች ቀዳሚ ምርጫ ሲሆን ይስተዋላል፡፡ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎችም ግለሰቦች ለሚፈልጓቸው መረጃዎች በማስረጃ የተደረገፈ ማብራሪያ ከጌታቸው ያገኛሉ፡፡

እኚህ አርቲስት በኢትዮጵያ ቴአትርና ሙዚቃ ታሪክ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ተወዳጅነትን ካተረፉ ቴአትሮቻቸውና ብዙዎችን ካስደመመ የትወና ብቃታቸው በተጨማሪ ግሩም የቴአትር አዘጋጅም ናቸው፡፡ እሳቸው ግጥም የጻፉላቸው ዘፈኖች ዘመን ተሻግረው ዛሬም ይደመጣሉ፡፡ አርቲስቱ 80ኛ ዓመታቸው ላይ ቢገኙም፣ ዛሬም ከዓመታት የሙያ ቤታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቅጥር ግቢ አይጠፉም፡፡

በ1928 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አዲስ ዓለም ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የጥበብን ዓለም የተቀላቀሉትም በወጣትነታቸው ነው፡፡ በ1944 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የቴአትርና ሙዚቃ ማስፋፊያ ክፍልን ተቀላቅለው በሙዚቃና ቴአትር ሥልጠና መውሰድ ጀመሩ፡፡ ከ1946 ዓ.ም. በኋላ ደግሞ ቴአትሮች እየጻፉ በቴአትር ቤቱ ያሳዩ ጀመር፡፡

1947 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 25ኛ ዓመት የዘውድ የብር ኢዮቤልዩ በዓልን ለማክበር መሰናዶ የተጀመረበት ዓመት ነበር፡፡ የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት የአሁኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ግንባታ የተጀመረውም በወቅቱ ነበር፡፡ ባለሙያዎች ለቴአትር ቤቱ መክፈቻ የሚሆኑ የቴአትርና የሙዚቃ ሥራዎች በማዘጋጀት ሥራ ተጠመዱ፡፡ ጌታቸውም የመሰናዶው አካል ነበሩ፡፡

getachewመስከረም 3 ቀን 1948 ዓ.ም. ቴአትር ቤቱ ሲመረቅ ከአገር ውስጥና ከውጪ የመጡም ከዋንያን ሥራዎቻቸውን አቀረቡ፡፡ የነጌታቸው ተራ ደርሶ ‹‹ዳዊትና ኦርዮን›› ከተሰኘው ቴአትር ቀንጭበው አቀረቡ፡፡ ከዚያን ወቅት ጀምሮ በጡረታ ምክንያት እስከሚወጡ ድረስ በብሔራዊ ቴአትር ከተሙ፡፡

ከወቅቱ ‹‹ዳዊትና ኦርዮን››ን ጨምሮ ‹‹ቴዎድሮስ››፣ ‹‹ሀኒባል››፣ ‹‹አስቴር›› እና  ‹‹ጎንደሬው ገብረ ማርያም›› ታዋቂ ቴአትሮች ነበሩ፡፡ ጌታቸው በበርካታ ቴአትሮች ከመሳተፋቸው ጎን ለጎን ተወዳጅነት ያተረፉ ሙዚቃዎች ጽፈዋል፡፡ ‹‹የኔ ሐሳብ››፣ ‹‹ምነው ተለየሽኝ››፣ ‹‹እንገናኛለን››፣ ‹‹በል ተነስ ልቤ›› እና ‹‹ዓለም እንዴት ሰነበተች›› ጥቂቱ ናቸው፡፡ አስናቀች ወርቁ፣ ምኒልክ ወስናቸው፣ ግርማ ነጋሽ፣ ተስፋዬ ሳህሉና ጠለላ ከበደ ግጥም ከሰጧቸው ዕውቅ ድምፃውያን መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በ1960ዎቹ መገባደጃ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ለፖለቲካዊ ቅስቀሳና ለፕሮፖጋንዳ መዋል የጀመሩበት ወቅት ነው፡፡ ባለሙያዎች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎችን ለቅስቀሳ በሚገለገሉበት ጊዜ ጌታቸውና የሙያ አጋሮቻቸው እንደ ‹‹ሀሁ በስድስት ወር›› ያሉ ሥራዎችን በአገሪቱ እየተዘዋወሩ ያሳዩ ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ከአጎራባች የአፍሪካ አገሮች ጀምሮ በተለያዩ አገሮች በመዘዋወር በርካታ ቴአትሮች አሳይተዋል፡፡ በቴአትር ቤቱ የቴአትር ክፍል ኃላፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆንና በሌሎችም ኃላፊነቶችም  አገልግለዋል፡፡

በቀጣይ በነበሩት ዓመታት ቅድመ ምርመራ ባለሙያዎችን በእጅጉ ይፈታተን ነበር፡፡ ጌታቸው በወቅቱ ታስረው ነበር፡፡ ከሙዚቃ ግጥሞቻቸው መካከል ‹‹ሎሚ ተራ ተራ›› የሚለው ዘፈን ፖለቲካዊ ትርጓሜ ተሰጥቶት ብዙ ጥያቄዎች አስነስቶባቸውም ነበር፡፡ ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ‹‹ደንቆሮ በር›› የሚል መጽሐፍ ያሳተሙ ሲሆን፣ በታሰሩበት ወቅት ስላለፉበት ሁኔታና ስለተመለከቷቸው ነገሮች ያትታል፡፡ የዝነኛዋን ድምፃዊትና ተዋናይት አስናቀች ወርቁ የሕይወት ታሪክ ጽፏል፡፡ ጌታቸው በ1994 ዓ.ም. የሕይወት ዘመን የቴአትር ዘርፍ ተሸላሚ በመሆን የወርቅ ሜዳልያ አግኝተዋል፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበርም በሙዚቃው ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሸልሟቸዋል፡፡

የእኚህ አርቲስት 80ኛ ዓመት የልደት በዓል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ተከብሯል፡፡ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው የተገኙ ሲሆን፣ ለዓመታት አብረዋቸው የሠሩ የሙያ አጋሮቻቸው ትውስታቸውን አውስተዋል፡፡ ከቅርብ ጓደኞቻቸው አንዱ ከጥቂት ወራት በፊት 80ኛ ዓመታቸውን ያከበሩት አርቲስት መርዓዊ ስጦታ፣ ጌታቸው ለዓመታት ያለመታከት በቴአትር ቤቱ መሥራታቸውን ተናግረዋል፡፡

መርዓዊ ‹‹ጌታቸው፣ ሀብቱና ንብረቱ ከብሔራዊ ቴአትር ጋር የተቆራኘ የጥበብ አባት ነው፤›› በማለት ነበር የገለጹት፡፡ ሌላው አስተያየት ሰጪ አርቲስት ተስፋዬ አበበ በበኩላቸው ጌታቸው ብዙ ወጣቶች ወደ ሙያው እንዲገቡ መነሻ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጌታቸው በሙያው ለሁላችንም ዓርአያ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ኢ/ር ታደለ ብጡል ስለጌታቸው መረጃ አያያዝና በእጃቸው ያሉ ሰነዶች ብዙዎችን መጥቀማቸውን ታናግረዋል፡፡ ውብሸት ወርቃለማሁ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠና ተስፋዬ ገብረሃናና ንግግር ካደረጉ ባለሙያዎች መካከል ይገኙበታል፡፡ ከጌታቸው ጋር በተለያየ ወቅት ያሳለፏቸውን ትውስታዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹መስታወት ማለት አንተ›› የተሰኘ ግጥም የጻፈው ጌትነት እንየው፣ ጌታቸውን የገለጸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡

‹‹. . . ምንም እንኳ ከመሠረቱ

ዕድሜ መስታወት ነው ሁሉንም ያሳያል ቢልም ተረቱ

ለሀገሬ ቴአትር ግና ከዕድሜም የላቀ ማሳያ

አንተ ሰው ነህ መስታወቱ

አዎ አንተ ነህ

ገና ከጮርቃ ዕድሜ አንስተህ

አካል ሆነ በመንፈስህ ከቤተ ተውኔት ሳትነጠቅ

በማያረጅ በማያፈጅ በማያልቅ ፍቅር ተጣብቀህ

ግጥም ለዜማ ቀምረህ

ተውኔት ጽፈሕ ተውነህ መድረክ መርተህ

ውስብስቡን የጥበብ ሕይወት ጭንቅ ሸክም ሁሉ ተሸክመህ

ቤተ ተውኔትን ቤት ቤተ መድረክን መቅደስ አድርገህ

በሦስት የሥርዓት ቅይርይር አንተ ላገር ለኪነት ታምነህ

እየመጣ የሚሄደውን ስንቱን የጥበብ ሹም ሹመት ተቋቁመህ

ስንቱን ቢሮክራሲ ግንባር ለግንባር ተላትመህ

ስንቱን የሳንሱር ስለት ቁስል ሕመሙን ችለህ ታመህ

የስንቱን አድርባይ ጥበብ ከልካይ ቅስም ስብራት መክተህ

የግሌ ኑሮህን ተወት አድርገህ

ሕይወትህን ለጥበብ ሰጥተህ

ቴአትርን ያቆየህ አንተ ራስህ እየሞትክ

የሀሬን የተውኔት ሕይወት ያየሁብህ

ከዕድሜም የጠራህ የነጣህ

የሀገሬ ጥበብ ማስረጃ መስታወት ማለት አንተ ነህ . . .››

(ምንጭ: ዓለማየሁ ላቀው)

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule